ወራሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby password » Wed Jun 25, 2008 10:19 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:በቅድሚያ በህይወት ጣጣ ስለጠፋሁ እጅጉን በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ
...ወራሽ...ይቀጥላል
ፓኑ አባ ፈርዳ


እንኩዋን ደህና ማጣህ, ፓን ሪዚኮ,

ያቺ ቁራጭ ወርቅ ከተቆረጠችበት ወርቅ ጋር የምትገናኝበትን እለት እየጠበቅኩ ነው..... :D
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 6:41 pm

ካለፈው የቀጠለ

"ነገሩ እንኳን ያው ተራ ወሬ ነው "አለ ኦኛ
"ተው እንጂ ...ለኔ የነገረችኝ የፓኑሻ የዱሮ ፍቅረኛው ነች "አለ ገብሱ
እንደመሳቅ እየቃጣኝ "ምን አለችህ ደሞ?"ስል በተራዬ በገብሱ ላይ አፈጠጥኩ

"አይ ...ያው ...እብድች ሀኪም ቤት ካንዴም ሁለቴም ..ሲሄድ አይቼዋለሁ ብላ ነው ደውላ የነገረችኝ ...ፓኑሻ ልጂቷ እኮ አሁንም ትጨነቅልሀለች "አለኝ ...እንዳልጮህበት የፈራ ይመስል

ወይ ጉድ አልኩ በሆዴ
ቀጥዬም
"ወንድሞቼ ...ሀኪም ቤት ማለት የእብዶች ሀኪም ቤት መመላለሴ ትክክል ነው ...ማበዴን ግን እኔም በትክክል ስለማላውቀው ...ማበዴን በትክክል ስረዳና ሳውቅ ግን በጊዜ አሳውቃችኋለሁ "ስላቸው ሁለቱም በሳቅ ፈረሱ
ሁላችንም የሳቅነውን ያህል ስቀን በሳቅ የፈረሰውን ሆዳችንን ቢራ ቸልሰንበት እንባችንን ጠራርገን ትንሽ እንደተረጋጋን
"ችግር አለ ፓኑሻ ?"ሲል ከምርና ፍጹም ከልብ በመነጨ ደግነት ገብሱ ጠየቀኝ

ምን ልበለው ?በዚች ምድር ላይ ካሉኝ በጣም ጥቂት እውነተኛ ጓደኞቼ በጣም ከሚቀርቡኝ አንዱ ነው ...አሁን ልዋሸው አልችልም ...እና ቢያንስ እንዳይጨነቅየራሱ ሀዘን አንሶ በኔ ችግር ሲያስብና ሲጨነቅ እንዳይውል ...
"ይሄን ያህል እንኳን ከባድ ችግር አይደለም ....አንዲት መከረኛ ህልም ለሊት ለሊት እየመጣች አበሳዬን እያበላችኝ አስቸግራኛለችና እሷን ልከስ ነው የምመላለሰው "ስላቸው ህልም ከሳሽ መሆኔ ትንሽ አሳቃቸው ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 6:54 pm

የኔ ህልም ከሳሽነት ግራ ያጋባው ኦኛ ..."አልገባኝም ትንሽ ብታብራራልኝ ሲ ለጠየቀኝ ጥያቄ

አያቹህ ....ሁሌም በተደጋጋሚ አንዲት አስፈሪ ህልም እየመጣች አስፎክራና አስጩሀ ከአልጋዬ ላይ አውርዳ በላብ ጠምቃ ከወለሉ ላይ ትዘረጋኛለች ....ይቺ መከረኛ ህልሜ ብዙ ቆነጃጅቶችን በጥቂት ለሊት ከቤቴ ብታባርረኝም እስከዚህ በጣም አልጠላዋትም ነበር ....አንዳንዴ ክፉም ነገር ቢሆን እየተላመድከው ስትመጣ ባትወደውም ትችለዋለህ ...ዱሮ አልፎ አልፎ ሰላም ትሰጠኝ ነበር ...አሁን ግን ከምን ጊዜውም በላይ ዱላዋን አበረታችብኝ ...እና ይሄው ቢቸግረኝ እዛ ጨብራራ የስነ ልቦና ሀኪም ጋ እየተመላለስኩ ቢያንስ የዚችን አበሰኛ ህልሜ ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቆ ቢነግረኝ ብዬ ይሄው እየከሰስኩ ነው አልኳቸው
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 7:16 pm

እንዲህ በኔ ህልም ከሰሳ ሳል ስናወጋ የመናዊው ራሺድ መቶ ስለተቀላቀለን የጫወታችን መስመር ፍጹም ተለውጦ የጫወታ ቋንቋችንም ሙሉ በሙለ በሀገሬው ቋንቋ ሆነ ...እዚህ ላይ ኦኛ ቱማ አማሪኛ ባይችልም አንዳንድ ጊዜ በአማርኛ እርስ በርስ ስናወራ እምብዛም ግድ የለውም ....ራሺ ግን የምናማት ስለሚመስላት ሁሌም ትበሳጫለች ....ለነገሩ የራሺድ አያት ኢትዮጲያ ወስጥ ሻይ ቤት የነበራቸውና የራሺድ አባትም ከኢትዮጲያዊት እናት የተወለደ ስለሆነ በራሺም ደም የኢትዮጲያውያን ደም ስለሚፈስ አንዳንድ ጊዜ አማርኛ ባለመቻሉ ወይም እኛ አረብኛ ለመማር እንኳን ፈቃደኛ ያለመሆናችን ያናድደዋል ...ቢሆንም ጥሩ የሀበሻ ወዳጅ ነው ....
ለራሺም ቢራ ቀረበለትና ያቺን ያት አጠቋቁሮ የሸረፋትን ጥርሱን ብልጭ እያደረገ
"ናዝድራቪ "ብሎ ብርጭቆውን ሲያነሳ እናም "ናዝድራቪ ብለን አንስተን አጋጨንና ቢራችንን ተጎነጨን

በየመኖች ቤት የመጋበዝ እድል የገጠመው ሰው ምስክር ሊሆን ይችላል የመኖችን ከኛ የሚለያቸው ነገር ቢኖር ያው የመኖች እና አረቦች መሆናቸው ብቻ እንጂ ሌላው አበላላቸው ባህላቸው ሁሉም ተመሳሳይ ነው ...እዚህ ላይ እነሱ ከንጀራ ይልቅ ሩዝ ከኮስታራዋ የሀበሻ ወጥ ይልቅ ለስለስ ያለቺውን አልጫ ቅቅል ያበዛሉ ...ቢሆንም ሁሌም ደስ እንያለኝ ትንሿ ሆዴ የቻለችውን ያህል እጠስቃለሁ ...
ራሺድ አሁን ያለነው የሶስታችንም የትምህርት ቤት ጓደኛ ነው ...ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ አንዲት ሱቅ ብጤ ከፍቶ ብዙ ጊዜ ጊዜ ተርፎት ከኛ ጋር በአስባብ አስባቡ ወደ ቢራ ቤት ማዘውተር ከተው ሰነባብቷል
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 7:45 pm

ቢሆንም ዛሬ የራሺን መምጣት የጠላው የለም ...ሁላችንም የዱሮ የት/ቤት ጓደኛማሟቾች በደስታ በፍቅር ተቀበልነው
እንዲህ አራት የጥንት የት/ቤት ጓደኛሞች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠን ስንጫወት ...ፕሮፌሰሩ ከወንድማቸው ጋር ወደ ቢራ ቤቷ ጎራ አሉ ...ምንም እንኳን በዚህ ሀገር ባህልና ወግ የተለመደ ባይሆንም እንደ ኢትዮጲያውያን ባህልና ወግ ፕሮፌሰሩ ከነወንድማቸው ከተከበረው ቦታቸው ደርሰው እስኪቀመጡ ድረስ ቆመን ሰላምታችንን እያቀረብን ጠበቅናቸው

እንዲህ አይነቱን ታላላቆችን የእድሜ ባለጸጋዎችን ማለቴ ነው የማክበር የኢትዮጲያውያንን ባህል የሚወዱት በጣም የሚያከብሩት ፕሮፌሰር ለዛሬው ጠረጴዛቸው ወርዶ ከኔ ጠረጴዛ ጋር እንዲገጠም አስተናጋጁን ጠርተው አዘው ታላቁ ፕሮፌሰር ክንት ተማሪዎቻቸው ጋር ወርደው ተርታውን ተቀመጡ
ገና ቢራ ቤቶ እንደገቡ ያስተዋወቁን በብዙ እድሜ ልዩነት የሚበልጡትን ታናሽ ወንድማቸው...ጥቂት ቢራዎች ከሳበ በኋላ ..በለንደን ከተማ ስለሚኖሩ ኢትዮጲያውያን ...ስለ ምግብ ቤቶቻቸው ስለ ምግቦቻቸው ..ስለ ክትፎ ስለ ቀይ ወጥ ስለ ዶሮ ወጥ ...ስለ ቆንጆዎቹ ሴቶቻቸው ሲያወሩን አብዛኞቻችን ምራቃችንን አስሬ ዋጥን ...እዚህ ፕራግ አንድ አራት አምስት ሴቶች ቢኖሩም ወይ የሽማግሌ ፈረንጅ አግብተዋል አሊያም ያው ትርፉ ድካም ነው አዝነት ነገር ሆኖ ሁሉም ሲበርደው ከጎኑ የሚወሽቀው የሀገሬዋን ሴት ነው
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 7:54 pm

የፕሮፌሰሩ ወንድም ...በለንደን ከትዮጲያውያን ምግቦች ጥፍጥና እና ከሴቶቻቸው ቁንጅና አለፍ ብለው በለንደን ያሉትን ኢትዮጵያውያንን እዚህ ፕራግ ካለነው ጋር ጥቂት ሲወዳድሩ ቆይተው ...ለንደን በርካታ እንግሊዘኛ በወጉ እንኳን የማይችሉ ኢትዮጵያውያን የሞሉባት ብትሆንም አሉ የሚባሉ ሳይንቲስቶች ሳይቀሩ በየዩንቨርሲቲው የታጨቁባት ከተማ እንደሆነች ገልጠው በፕራግ ቢያንስ 99%ለትምህርት መቶ እዚሁ በሴትና በቢራ እየተታለለ ተለማምዶ የቀዘቀዘ አሁንም ለማደግ የሚጠር በኢኮኖሚ ግን ደሀ የሆነ እንደሆነ ገላልጠው ኮርኩመውን ዝም ይላሉ ስንል አሁን ቮድካቸውን ጨልጠው ወደ ኢትዮጲያ የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታና ይዘት ወስጥ ገቡ ...እዝች ላይ እኔና ገብሱ ተለያየን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 8:07 pm

እኔ በወቅቱ የኢትዮጲያ ፖለቲካ የማንም ደጋፊ አይደለሁም ....በተቃራኒው ገብሱ የቅንጅት ዋና አቀንቃኝ ነው ....ቅንጅት የጀርባ አጥንታቸው ከደርግ ጋር በተቀባባ ሽማግሌውች ከሚመራ እንደ ገብሱ ባሉ ቅንና ጠንካራ የሶስተኛ ትውልድ ወጣቶች ቢመራ ኖሮ የቱን ያህል የተነሳበት አላም ከግቡ ሊደርስ ይችል እንደነበረ መጠየቁ አስፈላጊ አይደለም
ከገብሱ ጋር እሱ የቅንጅት አቀንቃኝ ብቻ ሳይሆን የዚህ አገሩ የቅንጅት አባሎች መሪና ተወካይ በመሆኑ አንድም ቀን ከፍቶኝ አያውቅም ...
እንዳውም ስለ ቅንጅት ደካማ ጎኖች ተነስቶ ስንጫወትና አስተያየቴን ሲጠይቀኝ ...በተለይ ስለ ሽማግሌዎቹ ግንባር ቀደምትነት አንስቼ ...ይሄ በትክክል አስፈላጊ ያለመሆኑንና ..ይልቅ ሽማግሌዎቹ ከመጋረጃው ጀርባ ተቀምጠው መካሪዎች አስታራቂዎች የልዩነቶች አቀራራቢዎች ብቻ መሆን እንዳለባቸው ስነግረው ...ሀሳቤን ሰምቶ ...
እኔ ለአስተማሪዬ ለሽማግሌው ፕሮፌሰሬ የምሰጠውን ክብር ያህል እንኳ ለቅንጅት ታላላቅ መሪዎች እንድሰጥ በጠየቀኝ ..እንዳውም ባስጠነቀቀኝ ጊዜ ...ያልኩትን በትክክል አስታውሳለሁ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 8:22 pm

አዎ እንዲህ ነበር ያልኩት
"የኔ ፕሮፌሰር የጡረታ ጊዜያቸውን ...ቀሪ ህይወታቸውን በህዝብ ትራንስፖርት ከተራው ህዝብ ጋር ተቀላቅለው እየተጓዙ ...ልክ እንደዛሬው በተራ ቢራ ቤት ከተራ ሰዎች ጋር እየተጋፉ ተራ ቢራ እየጠጡ ...በዚህ ተራ ህዝብ መሀል ተስፋ የቆረጠ የተቸገረ ተራ ሰው ሲገጥማቸው ..በሀሳብ እረድተው ካለቻቸው የጡረታ የቀን ወጪያቸው ላይ ያቅማቸውን እረዳድተውን አይዞህ ነገ ያልፋል ብለው ተስፋ እየሰጡ እራሳቸውንም ህዝባቸውንም ሳይረሱ ነው ....
የኛን ሽማግሌዎች ያየህ እንደሆነ ...ከዱሮም ጀምረው ከተራው ህዝብ እርቀው አንዲት ቀን እንኳን ወደገጠር ወተው በተራው ህዝብ ጠጅ ብት እንኳን ጎራ ብለው ጠጅ ለመጠጣት እየተጠየፉና እየኮሩ ....ዱሮም ተራው የሀገሬ ህዝብ ሳይጠይቃቸው ሳይለምናቸው ችግሮጭን እኛ ብቻ ነን የምናውቅልህ ሲሉት ኖሩ ....ዛሬ እንኳን በዚች የስተርጅና እድሜያቸው ከሚስኪኑ ህዝብ ጋር ተቀላቅለው ችግርህ ችግራችን ነው አይዞህ እያሉ ቤተስኪያን እየሳሙ መስኪድ እየሰገዱ ...እንዳይመክሩት ተስፋ እንዳይሰጡት .......ይሄው ዛሬም አንተ ዝም በል ምንም አታውቅም የሚበጅህን የምናውቅልህ እኛ ብቻ ነንና እኛን ብቻ ተከተል ይሉታል ....
ግራ የገባው የቸገረው ከዚህ ከጨካኙ ሳይሻሉ አይቀርም እያለ በማያውቀው መንገድ እነሱን ተከትሎ ተነዳላቸው ...
ሲያሸንፉ እሰይ ብሎ ሆ አለላቸው ሲታሰሩ ስንቅ ቋጥሮ ጠየቃቸው በየቤተክርስቲያኑና መስኪዱ ተደፍቶ ጸለየላቸው ....በሚስኪኑ የኢትዮጲያ ህዝብ ጽሎትና ልመና ሲፈቱ .....የኢትዮጲያ አምላክ አሜሪካ የተሰደደ ይመስል አይኑን እንኳን ሳያዩት ተያይዘው ወደ አሜሪካ ፈርጥጠው እንደ ተራ ለማኝ የስደተኛ ፍርፋሪ ይለምናሉ ...አሁን ማ ይሙት የስደተኛ ፍርፋሪ የኢትዮጲያን ህዝብ ችግር ይቀርፍለታ ....ነበር ያልኩት
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 8:58 pm

የፕሮፌሰሩ ወንድም የአለም አቀፍ ፖለቲከኛ ናቸው መሰል...በጥያቄያቸው ገፍተው በወቅቱ ባለው የኢትዮጲያ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ያለንን አቋም እንድንገልጥላቸው አፋጠጡን
እንደመጀመሪያ ሰው ገብሱ ለኢትዮጲያ አንድነት ሉአላዊነት ከምርና ከልብ የተነሳ የፖለቲካ ፓርቲ ቢኖር ቅንጂት ብቻ እንደሆነ ከብዙ እውነተኛ ማስረጃዎች ጋር አትቶ አስረዳ ....እዚህ ላይ የመናዊው ራሺ ሳይቀር የቅንጅት ደጋፊ መሆኑ ነው ...እስቲ አሁን እሱ በኛ ችግር ምን አግብቶት ነው
የኔ ተራ ሲደርስ አጠር አድርጌ እኔ ይየትኛውም የወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊ አለመሆኔን አስረግጬ ከተናገርኩ በኋላ በህቡው የሚንቀሳቀሰው የኢትዮጲያ ሶሻል ዲሞክራቶች ደጋፊ መሆኔን ተናገርኩ ...

የፕሮፌሰሩ ወንድም ወደኔ እያዩ
"አንተ የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ መሪ ብትሆን ምን ታደርግ ነበር ?"ሲሉ ደረቅ ጥያቄ ጠየቁኝ ...
ለሰውዬን ጥያቄ መልስ ሳሰላስል ...
ግብሱ ቀድሞ ኧል ስውዬን ካሁኑ መሪ ሳትሆን አትቀርም ....ለነገሩ ያለው ፓርቲ ካለ ..መስራቹም መሪውም አባሉም ደጋፊውም እሱ ብቻ ነው "ብሎ አሳቀብኝ ....
ሁሉም መሳቃቸውን ሲያቆሙ ወደሰውዬው በቀጥታ እያየሁ ...
"ጥያቄዎን በትክክል ለመመለስ ያስቸግር ይሆናል ...ግን እንዳሉት እኔ የሶሻል ዲሞክራቶች መሪ ሆኜ በነጻ ምርጫ በህዝብ ተመርጬ አገሪቷን የመምራት እድል ቢገጥመኝ እንደመጀመሪያ አላስፈላጊና ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመች ሆኖና ተከልሎ የተመሰረተውን አጉል የብልጣብልጦች ፌዴሬሽን ለማሰረዝ እሞክር ነበር "አልኳቸው
ራሺድና ገብሱ በኔ የድፍረት ንግግር የንዴት ...ጉረኛ አይነት ነገር ሳቅ ሳቁ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 9:22 pm

ከዚች የሁለቱ ሳቅ በኋላ ኦኛ መናገር ይችል እንደሆነ ጠይቆ ..ሁሉም መናገር ሀሳቡን መግለጥ መብቱ እንደሆነ በአንድነት ሲገልጡ እኔንም ጨምሮ ማለት ነው
"ሁለቱ ኢትዮጲያውያን ወንድሞቼ ሀገራቸውን ከማንምና ከምንም በላይ አስበልጠው ይወዳሉ ...ሁለቱም ለዛች ሚስኪን ሀገር ችግር መፍቻ ዘዴ የማይቆፍሩት ገደል እንደሌለ አሳምሬ አውቃለሁ ..እመኑኝ የምናገረውን አውቃለሁ ...ብቻ ሁለቱም ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን በማሳደጉ መንገድ ይለያያሉ ...
ገብሱ ኢትዮጲያን እና ህዝቦቿን ማሳደግ የሚቻለው የወቅቱን ገዢ መደብ በአፋጣኝ በትጥቅ ትግልም ቢሆን ፈንቅሎ መጣል ሲቻል ብቻ ነው ብሎ ..አደገኛውንና አጭሩ መንገድ ይሄዳል

ፓኑ ...ኢትዮጲያንና ህዝቦቿን ማሳደግ የሚቻለው ያለፉት የኢትዮጲያ የገዢ መደቦች ያሁኖቹንም ጨምሮ ብተደጋጋሚና በግድ ያሳደሩበትን እና እያሳደሩበት ያለውን አንድ አንዱን የመናቅ አንዱን በአንዱ ላይ የማስነሳትና የማስጨራረስ ....እንዳይታረቅና እንዳይፋቀር እዚህም እዚያም የሚጭሩት የከፋፍለህ ግዛው የተንኮል እሳቶቻቸው ሲጠፉና ...እንደ እትዮጲያውያን የጥን ባህል ሁሉ ...ታቦት ወቶ ፓትሪያርኩም ሼኩም ጎን ለጎን ቆመው የኢትዮጲያ ባንዲራ ተነጥፎ በበባንዲራው ስም ይቅር ለእግዚያብሄር ተባብሎ እውነተኛው ህዝባዊ እርቅ ሲመጣ ብቻ ነው ...ይህ የሆነ ለት የራሱን ሶሻል ደሞክራቶች ይዞ አገሩ ለመግባት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን አውቃለሁ.."አለና የመጨረሻዋ አረፍተነገሩ እራሱን ስላሳቃቸው ሁላችንም ሳቅን ...
ብቻ ልጨርሰውና ብሎ
"ፓኑ መሰረታዊ እርቅ ይቅደም ባይ ነው .... በዚህ መልኩ አስተማማኙንና እረጅሙን መንገድ ይመርጣል ......
ሆነ ቀረ ሁለቱም በጣም የምወዳቸውና የምኮራባቸው ወንድሞቼ ናቸው ...አንዱ አደገኛውንና አጭሩን መንገድ መርጧል ሁለተኛው ረጅሙንና አስተማማኙን መንገድ ቢመርጥም ..ሁለቱም እኩል ወንድሞቼ ናቸው .....ግን አንተ በየትኛው መንገድ መሄድ ትመርጣለህ ብላቹህ ብትጠይቁኝና መምረጥ ግድ ቢሆንብኝ ...እረጅሙንና አስተማማኝUን መንገድ እመርጣለሁ ..."ብሎ ንግግሩን ሲጨርስ
ለኦኛ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ፕሮፌሰሩ ሲያጨበጭቡ እኛም እሳቸውን ተከትለን አጨበጨብንለት
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 9:36 pm

በዚህ መልኩ ስንጫወት አመሻሽተን ...የፕሮፌሰሩ ወንድም በዚህ መልኩ ጨዋታችን እንደምንቀጥል ተስፋ እንዳለው ተናግሮ ከታላቅ ወንድሙ ጋር ተሰናብተውን ሄዱ ...
ጥቂት ቆይቶን ራሺ እደር ቢባል ...በጥዋት ሱቅ ከፋች ነኝ ..እዚህ አድሬ ጋዜጣዎቼን እንዳልሸጥ ልታደርጉኝ ነውይ ብሎ እሱም ወደ ማደሪያው ተሰናብቶን ሄደ

እኔና ቱማ መቼም ያበሻ ወግ ነውን አብረነው ልናድር ወደ ግብሱ ቤት አብረነው ሄድን ግብሱም የገባው መሰለኝ.....
በገብሱ ሳሎን ተቀምጠን ያቺን የሀበሻ አረቄ አንዳንድ መለኪያ ቀዳልንና የፎቶ ከረጢቱን ሰፈታትሽ ቆይቶ የወንድሙን ፎቶ አውጥቶ አሳየን ...ደካክሞን ነበርና ብዙም በጫወታ ሳንገፋ መኝታ ሲከጃጅለን ኦኛ ተነስቶ ወደ እንግዳ ክፍል ደህና እደሩ ብሎን ሄደ ...ቀጥሎ ገብሱ ..የወንድሙን ፎቶ ግራፍ ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ ...የአበባ ማስቀመጫውን አስደግፎ ኮሞዲኖው ላይ አስቀምጦ ..ደህና እደር የኛ እርጅም መንገድ ተጓዡ ...ብሎኝ ሄደ
በገብሱ የደህና እደር ለከፋ ስስቅ ቆይቼ ...እዛች ሶፋ ላይ ዘና ብዬ ጋደም አልኩ...መለስ አልኩና ፈጣሪዬ ያችን መከረኛ ህልም ዛሬ እንዳትመጣብኝ ወጥሮ ይዞ እንዲያስቀራት ልለምነው አሰብኩና ...መልሼ ከንቱ ድካም ምስሎ ስለታየኝ ትቼው ብሻት ጊዜ ትምጣ ብዬ ጋደም አልኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Mon Sep 29, 2008 9:50 pm

ዛሬ በገብሱ ሶፋ ላይ ጋደም ስል ጀምሮ ያቺ መከረኛ ህልሜ መጥታ እንደምትቀሰቅሰኝ እርግጠኛ ብሆንም ....ዥው ያለ እንቅልፍ ወስዶኝ እሷም ብቅ ሳትል ያው ፈጣሪዬ አልፎ አልፎ መልክት አሲዞ የሚልክብኝ መላክተኛ የኔ መልአክ መቶ ቀሰቀሰኝ ...መቀስቀሴን ብጠላውም በዛች አስፈሪ ህልም ተቀስቅሶ በላብ ተደፍቆ ወለሉ ላይ ተዘርሮ እራስን ከማግኘት የከፋ ምንም ነገር የለም ብዬ መላኬ ሲቀሰቅሰኝ ሳላንገራግር ተነሳሁ ....ምንም እንኳን መልአኬን የምጠይቀው ብዙ ጥያቄዎች ቢኖረኝም እሱ የብዙ እንደኔ አይነት እድለቢሶች መልአክ ነው መሰለኝ ጊዜ የሌለው ባተለ ንገር የተባለውን ብቻ ተንፍሶልኝ ቻዎ እንኳን ሳይለኝ ልማዱ መሆኑን ስለማውቅ መጠየቁ ፋይዳ ይሌለው ነገር መሆኑን አውቄ የሚነግረኝን ተኝቅቄ ለመስማት ጆሮዬን አጠራርቼ አቤት አልኩት ...
መልአኬም እንደሁልጊዜው ሁሉ ባጭሩ ...
"ይሄ እብዶች ሀኪም ቤት መመላለሱ ዋጋ የለውም ...ይልቅ ወደ ኢትዮጲያ ተመለስ ..ለሁሉም ጥያቄዎችህ መልሱን የምታገኘው እዚያው ነው "
ብሎኝ እንደ ሁልጊዜው ልማዱ ደህና እደር እንኳን ሳይለኝ ተሰወረ ...ለምጄዋለሁና ስለ ኢትዮጲያ እያሰላሰልኩ ተመልሼ በገብሱ ሶፋ ላይ ተጋደምክ ....
ይቀጥላል ጊዜ ሲገኝ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Oct 02, 2008 11:02 am

ራሺ ሰሞኑን ሱቁን ዘግቶ ውሎው ከኛጋር ሆኗል ...እናም እኔ ኦኛ ራሺናና ገብሱ ....ቀኑን በቢራ ቤት እያሳለፍን ለሊቱን ደሞ በገብሱ ቤት እያሳለፍን ሰኞ ደረሰና ...ከኔ በስተቀር ሁሉም ወደየስራቸው ሄዱ
እኔም እነሱን ወደ ስራ ሸኝቼ ወደ ቤቴ ተመለስኩና ጨብራራው ዶክተሬ ዛሬ ሊቀበለኝ እንደሚችል ስጠይቀው ..በደስታ እንደሚቀበለኝ ሲነግረኝ ...በአስቸኳይ ዝግጅቴን አጠናቅቄ ከአምላኬ ትእዛዝና ምክር ውጪ ወደ እብዶች ሀኪም ዘንድ ተፈተለኩ....
ምንም እንኳን መልአኬ እብዶች ሀኪም ቤት መመላለሱ ዋጋ የሌለውና ከንቱ ድካም እንደሆነና ወደ ሀገሬ መመለሱ እንደሚበጀኝ ቢነግረኝም ...የተጀመረ ነገር ለመጨረስ ቢያንስ የዛችን መከረኛ ህልሜን ፍንጭ ለማግኘት ስለጓጓሁ ወደ ጨበሬው ሀኪሜ ሄድኩ ....
አሁን ዘበኛስው ስለተላመደኝ ይሁን ...ጌታው የሆነ ነገር ነግሮት እንደሆነ ...ብቻ አላውቅም ጥንት እንደሚያውቀኝ ጓደኛው አይነት ነገር ሞቅ ያለ ሰላምታ አቅርቦልኝ ወደ ውስጥ እንድገባ በሩን ከፍቶ አሳለፈኝ .....
ዛሬ በንግዳ መቀበያዋ አዳራሽ ውስጥም ሆነ በዛች ግማሽ ክብ ጠረጴዛ ዙሪያ ያቺ ውብ ቂጤ ረጅም ቆንጆም ሆነች ሽብረተኛዋ የጨበሬው ሚስት የሉም ....
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby harar_beer » Thu Oct 02, 2008 1:43 pm

selam all bro ጉዳይ ከልሰ
hi eve one bro and sisr
harar_beer
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Thu Oct 02, 2008 1:10 pm

Re: ግ

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Oct 02, 2008 3:15 pm

harar_beer wrote: selam all bro ጉዳይ ከልሰ
ሀረር ቢራ ...ልትነግረኝ የፈለከው ነገር አልገባኝም .....ይብራራ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests