ወራሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Oct 02, 2008 3:27 pm

ግራ ገብቶኝ አዳራሹ መሀል እንደቆምኩ ጨበሬው ዶክተሬ ፈገግታ በፈገግታ ሆኖ መቶ ተቀበለኝና ተያይዘን ወዳዛች የስራ ክፍሉ ገባን ...በተለመዱት ድሎት የበዛባቸው ሶፋዎች ላይ ተቀመጥን ...ዛሬ ቡናም ሆነ ቢራ አላቀረበልኝም አልጋበዘኝም ...እንዲያ በደረቁ ኮስተር ብሎ ስለዛች መከራዬን በቁሜ ስለምታበላኝ የለሊት ህልሜ የቀን ቅዠቴ እንዳጫውተው ጠየቀኝ ...
ይቺ መከረኛ ህልሜ አብራኝ ለዘመናት ስለኖረች ..ክፋቷ ቢበዛብኝም ብታስጨንቀኝም ተላምጃታለሁና በደንብ ታሪኳን አውቃታለሁና ..ለዶክተሬ ከ ሀ እስከ ፐ ድረስ ዝርዝር አድርጌ ነገርኩት
ታሪኬን ስጨርስ በታላቅ ሀዘኔታ ሲያየኝ ቆይቶ ...
"አየህ ጌታው ይቺ ነገር ህልም ብቻ ላትሆን ትችላለች ...እንደምገምተው ከሆነ ይቺ ነገር ከአመታት በፊት በክክል ባንተ በራስህ ላይ የደረሰች እውነታ ትመስለኛለች ...አይምሮህ ጽፎ ይዞታል ...አንተ ግን ማስታወስ አትፈልግም ...ቋጥረህ ይዘኸዋል ...አይምሮህ ግን በአገኘው ቀዳዳ ሁሉ እየገባ በህልም መልክ እየመጣ እነዛን ቋጠሮዎች የተዘጉ በሮች ለመክፈት ይጣጣራል .....
ፈቃድህ ከሆነ እነዚህን የተዘጉ አይምሮህ ውስጥ ያሉ በሮችን መግፈቻ መንገድ አለ ...አለኝና መስማማቴን ይጠብቅ ጀመር
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Oct 02, 2008 10:03 pm

ግራ ገብቶኝ አዳሯሿ መሀል እንደቆምኩ ጨበሬው ዶክተሬ ፈገግታ በፈገግታ ሆኖ መቶ ተቀበለኝና ወደ የስራ ክፍሉ ተያይዘን ሄደን እነዛ ድሎት ባላቸው ሶፋዎች ላይ ተቀመጥን ....
ዛሬ ቡናም ሆነ ቢራ አላቀረበልኝም አልጋበዘንም ..ብቻ እንዲያው በደረቁ ትንሽ ኮስተር ብሎ ...ስለ አበሰኛዋ ህልሜ እንዳጫውተው ጠየቀኝ ...ይቺ መከረኛ ህልሜ በርከት ላሉ አመታት ፍዳዬን እያሳየች አብራኝ የኖረች ታሪኳን ስራዋን ማንነቷን አሳምሬ የማውቃት ስለነበረች ስለሷ ለዶክተሬ ለመንገር ማስታወሻም አላስፈለገኝ ብቻ ስለዚች መከረኛ ህልሜ ከ ሀ እስከ ፐ ድረስ ብትንትን አድርጌ የምጸራኝን ስራ አሳበኩባት ...አወራውባት ...
ታሪኬን ስጨርስ በሀዘኔታ ሲመለከተኝ ቆይቶ ....
አየህ ጌታው ይሄ ህልምህ ህልም አይመስለኝም ...በአንድ ወቅትና አጋጣሚ በአንተ ላይ የደረሰ እውነተኛ ገጠመኝ ነው ...አይምሮህ ሁሉንም ጽፎ ይዞታል አንተ ግን በሆነ ምክንያት ልታስታውሰው ስለማትፈልግ በውስጥህ ተብትበህ አስረህ አፍነህ አስቀምጠኸዋል ...እናም አይምሮህ በአገኘው ቀዳዳ ሁሉ እየገባ በህልም መልኩ ከታሰረበት የብረት አጥር ዘሎ ለመውጣት እየጣጣረ ይመስለኛል ...አለኝ ...
ወዲያው ከዚህ የታሰረበት የብረት ገመድ የምናወጣበት ዘዴ ያለ መሰለኝ ..አለና ፈቃደኝነቴን ይጠባበቅ ጀመር
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 11:14 am

ግራ ገብቶኝ በአዳራሿ መሀል እንደቆምኩ ጨበሬው ዶክተሬ ፈገግታ በፈገግታ ሆኖ እየሳቀ መቶ ተቀበለኝና ተያይዘን ወደ የስራ ክፍሉ ገባንንና በነዛ ምንግዜም ድሎት ከማይለያቸው ሶፋዎች ላይ ተቀመጥን

ዛሬ ቡናም ሆነ ቢራ አላቀረበልኝም አልጋበዘኝም ..ብቻ እንዲያው በደረቁ ስለዛች አበሰኛና መከረኛ ህልሜ እንዳጫውተው ጠየቀኝ ...
ይቺ መከረኛ ህልሜ ለረጅም አመታት አብራኝ የኖረች ስለሆነችም በደንብም ስለተላመድኳት ስለ ህልሜ ለዶክተሩ ለመናገር ምንም ማስታወሻ መያዝ አላስፈለገኝም ነበርና ...ስለዚች አበሰኛ ህልሜ ለዶክተሬ ከ ሀ እስከ ፐ ድረስ ዘርዝሬ አጫወትኩት
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 11:25 am

ታሪኬን ስጨርስ ..በሀዘኔታ ሲመለከተኝ ቆይቶ ...
አየህ ጌታው ...ይሄ ህልምህ ወይም ቅዠትህ ...ህልም ወይም ቅዠት አይመስለኝም ...አንተ ማስታወስ አትፈልግም እንጂ በአንድ ወቅት በአንድ ቦታና አጋጣሚ በእውነት ባንተ ላይ የደረሰ እውነታ ነው ...አይምሮህ ውስጥ ተጽፏል ...ግን በሆነ ምክንያት አይምሮህ አግዶ ይዞታል ወይም አይምሮህ ታግዷል ....እናም ለዛ መሰለኝ አይምሮህ ባገኘው አጋጣሚና ቀዳዳ ሁሉ ከታሰረበት ከታገደብት ሰብሮ ለመውጣት ይቺን ህልምህን ፈጥሮ በተደጋጋሚ ፍታኝ የሚልህ ...
ፈቃድህ ከሆነ እነዚህ የተዘጉ የአይምሮህን በሮችለመክፈት የሚያስችል አንድ መሞከሪያ ዘዴ አለ...አለኝና ፈቃደኝነቴን ይጠብቅ ጀመር ...

"ምንድን ነው ያ መንገድ ?"ስል ባጭሩ ጠየኩት
"ሰመመን"አለኝና ቀጥሎ
አዎ ያለው አማራጭ አንተን በሰመመን ወደዛ ጊዜና ቦታ ወስዶና መልሶ እንድታስታውስ እነዚህን የተዘጉ በሮች እንድትከፍት መሞከር ብቻ ነው "አለኝ
ብዙም ሳላስብና ሳልጨነቅ
"እሺ እንሞክረው "አልኩት..ነነገሩ ከዚች መከረኛ ህልም ከመገላገል በላይ የምፈልገው ምንም ነገር የለኝም ...የማጣውም ምንም ነገር አልነበረም
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 11:38 am

በሰመመኑ ተስማማንና ...በረጅሙ..ድሎት ባለው ሶፋ ላይ በጀርባዬ ጋደም እንድል ነገረኝ ...ቀጥሎም ከሰመመኔ ስባንን ...ሁሉንም ነገር እንደማስታውስ ማለት ሰመመን ውስጥ እያለሁ የለፈለፍኩትን ሁሉ ማለት ነው ..ቢሆንም በድምጽ መቅረጫ መቅረጹ ጉዳት እንደሌለው ..እናም ሌላም ሌላም ነገሮች ከነገረኝ በኋላ ለሰመመኑ ዘመቻ መዘጋጀት ጀመርን

ይገርማል በአንዲት ተራ እርሳስ አዝኔ ላይ እያንከራተተ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አስተኝቶና ሰመመን ውስጥ ከቶ ወደዛች መከረኛ ህልሜ ይዞኝ ሄደ .....
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 12:03 pm

በሰመመን ወደዛ ጊዜ ከወሰደኝ በኋላ

"የት ነው ያለኸው?"...ሲል ጠየቀኝ
"ጎሀጺዮን.............አልኩት
"ጎሀጺዮን የት ቦታ ?
"ጎሀጺዮን አፋፍ ከኪቶ ጋር አንዲት ቋጥኝ ላይ ተቀምጠናል "አልኩት
"ኪቶ ማነው ?"
"ኪቶ ውሻዬ ነው ..."
"ምን እየሰራቹህ ነው?
ከገደሉ አፋፍ ላይ ተቀምጠን አባይን እያየን ነው
"ምን ይታያሀል?
""ቀርሰ ጊሮ የምትባል ወንዝ አገር እየቆረሰች ለአባይ ወንዝ ስታቀብል እያየሁ ነው "አልኩት

ሌላስ ምን ይታይሀል ?

"አባይ በረሀ ..የገበሬዎች ማሳ እዚህ እዛም ሰብሰብ ብለው የቆሙ የገበሬ ጎጆዎች ..የገበሬዎቹ ማሳ መሬቱን አረንጓዴና ግራጫ መጋረጃ ያለበሱት ይመስላል! አልኩት

"ሌላስ ?"
ከኔ ብዙ ሳይርቁ ዝንጀሮዎች ስራስር እየነቃቀሉ ይበላሉ "

"ለላስ ?"
"ያው ከብቶች ፈረሶች አህዮች በጎች ..ሁሉም ሳር ይግጣሉ
"ሌላ ሰው አጠገብህ የለም ?"
"በፍጹም ...ዛሬ ቅዳሜ ስለሆነ ..ሁሉም ገበያ ናቸው "
"አንተ ለምን ገበያ አልወጣህም ?ů
"እኔ የገበያ ጩኸት አልወድም ...ለዛም ነው ወደዚህ የምመጣው ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 12:20 pm

"ሌላ ምንም ነገር አይታይህም አይሰማህም ?ů
""ቆይ አንዲት ጥይት ተተኮሰች ....ወፎቹም ቆቆቹም አሞራዎችም ሁሉም ግር ብለው በረሩ ዝንጀሮዎቹም ወደ ዋሻዎቻቸው ገቡ ...ከብቶችም ቀና ብለው አካባቢያቸውን ከቃኙ በኋላ ደንታ ሳይሰጣቸው ወደ ግቶሻቸው ተመለሱ

"ማነው የተኮሰው ?"
"እኔ እንጃ የሆነ አዳኝ መሰለኝ "....ተኩሱ ተደገመ ...አሁን የጥይት መአት ይንጣጣ ጀመር ...ከየት አቅጣጫ እንኳን እንደሚተኮስ አላውቅም ..."አልኩት

"አንተ ምን እያደረክ ነው ?"

ůከኪቶ ጋር ከቕዋጥኛ ላይ ወርደን ከስሯ ተደብቀናል ..."
"አሁንም ይታኮሳሉ"
"አዎ ተኩሱ ብሷል "
"ሰው ታያለህ ...የሆነ የሚታይህ ነገር አለ ?
"ምንም ነገር አላይም ...ኪቶ ከቋጥኟ ስር ወጥታ መሮጥ ጀመረች ...እኔም ለምን እንደሆነ ባላውቅም ኪቶን ተከትዬ መሮጥ ጀመርኩ "
..."ቀጥል.."

"ኪቶን ተከትዬ ሽቅብ ወደላይ ወደቤታችን ጥይት እየዘነበብኝ ስሮጥ ኪቶ ድንገት አንድ በጥይት ተመቶ ከወደቀ ሰው ጋ ስትደርስ ቆመች ......ኪቶ የቆመችበት ቦታ አንድ አምስት ሜትር ሲቀረኝ በአንድ ጥይት ተመትታ በቁስለኛው ሰውዬ ላይ ወደቀች "

"ከዛስ....?"

እኔ አጠገባቸው ስደርስ ቁስለኛው ሰው በአስቸኳይ መሬት ላይ ወድቄ በደረቴ እንድተኛ አዘዘኝ ...እኔም ወዲያው በደረቴ ተኛሁ ...ቁስለኛው በሶስት ጥይት ግራ እግሩን ቀኝ እጁንና ትከሻውን ተመቶ ደም በደም ሆኗል .....ኪቶም በጥይት እግሯን ስለተመታች ልግዜው ብትወድቅም በህይወት አለች ...ቢያንስ ወዲያው አትሞትም ...

አሁንም ይታኮሳሉ ?
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 12:41 pm

"አዎ አሁንም ይተኩሱብናል ....ወደ ላይ ወደ ቤታችን ለመውጣት መሞከር ፈጽሞ የማይቻል ነው ...ተባራሪው ጥይት ሁለት ሜትር አያስኬድም ...ያለው አማራጭ ተመልሶ ወደ ታች ወደ ገደሉ ወርዶ ዋሻ ውስጥ መግባት ብቻ ነው ...ቁስለኛውም ሰውዬ በፍጥነት ወደታች ወርጄ በዋሻ ውስጥ እንድደበቅ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጠኝ ...ግን አልተቀበልኩትም "

"ለምን ?"

"እኔጃ ..ብቻ ቁስለኛውን ሰውዬና ኪቶን በዛ ጥሎ አንድ ነብሴን ለማትረፍ መሸሹ አልሆንልኝ አለ ..እና እዛው እንደተኛሁ የሰውዬውን ጠብመንጃ ጎትቼ ሳቀባብል ...ቁስለኛው ሊከለክለኝ ቢሞክርም ቁስሉ ሳይፈቅድለት ቀርቶ በአቅመቢስነት ...እባክህ ቢያንስ በእግሮቻቸው ላይ አነጣጥር አለኝ "

"ለምን ?"
)
"እኔም አልገባኝም ...ሊገሉን በሚተኩሱብን ጠላቶች እግራቸውን ብቻ እያነጣጠርኩ እንድመታ እንዳዘዘኝ አልገባኝም ...ብቻ ከልጅነቴ ጀምሮ ተኩስ ስለተማርኩ ...አልሞ መተኮስ እንደምችል አውቃለሁ ....ቢሆንም የመጀመሪያዋ ኢላማዬ ስትገባልኝ ምላጯን ሳብኳት "

"ኢላማህን መታህ ?"

"እኔጃ ..ቁስለኛው ሰው ባዘዘኝ መሰረት በጠላቴ የቀኝ እግር ላይ አነጣጥሬ ነበር የተኮስኩት ...እናም ሳልመታው አልቀረሁም መሰለኝ ...ለጊዜው ተኩሱ ጋብ አለ "

"ከዛስ?"
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 1:03 pm

ተኩሱ ጋብ ሲል ቁስለኛው ሰውዬ ..."የገዳሙን ዋሻ አውቃት እንደሆነ ጠየቀኝ ...እንደማውቃት ስነግረው በፍጥነት ወደ ታሽች ወርጄ በገዳሟ ዋሻ ተደብቄ እንድጠብቅ አዘዘኝ "

"አሁንስ ሰማኸው?"

"አዎ ...ግን ወደ ዋሻዋ ቁልቁል ለመውረድ ስነሳ ..እነዛ የማናውቃቸው ጠላቶቻችን ከምንጊዜውም በላይ የጥይት ዝናብ ያዘንቡብን ጀመር ...የሽሸት መንገዴን ትቼ ሁለት ጊዜ አነጣጥሬና አልሜ ተኮስኩ ...ለሶስተኛ ጊዜ ሳነጣጥር አንድ የማውቀው ሰው አየሁ ...ቁስለኛውም ሰው እኔ ያየሁትን ያየ መሰለኝ ...ወደኔ መለስ ብሎ
"በል አንበሳዬ የቀረችህን ጥይት እየተኮስክ ቁልቁል ውረድ ተነስ አምልጥ በርታ እሩጥ እያለ ለመነኝ ......በመጨረሻም ስለኔም ስለኪቶም አታስብ ...አምልጥ እሩጥ እያለ ጮኸብኝ ...

!ከዛስ ?"

"አሁን ሌላ አማራጭ አልነበረኝም ...የቀሩኝን አምስት ጥይቶች ..አቀባብዬ ከተኛሁበት ተነስቼ እንዳቀረቀርኩ ቁልቁል እየሮጥኩ ቆም እልና ሳላነጣጥርና ሳላልም እየተኮስኩ ወረድኩ ......ገደሉ ጋ ስደርስ ቆም ብዬ ወደ ገዳሙ ዋሻ የምታስወርደውን ገመድ ፈለኩ ....ከመዷን አንድ ምቀኛ ቆርጦ ጥሏታል ......ወደ ዋሻዋ ተንሸራትቼ መውረድ ይቻለኝ ይሆናል ...ግን በትክክል እየተንሸራተትኩ ወርጄ በትክክለኛዋ ቦታ ላይ መቆፕም ካልቻልኩ ...እንዳወራረዴ ወርጄ ጭልጥ ባለው ግደል ግብቼ መፈጥፈጤ ነው ....ይሄ ሊሆን አይገባውምና ሌላ መንገድ ስፈልግ እየተሿሿች የምትወርደዋን ወንዝ አየኋት ...ቆሜ በጥይት ቀጥቅጠው ከሚገሉኝ ...ወደዛች ወንዝ ውስጥ ዘልዬ ገብቼ ነብሴን ለማትረፍ ወስንኩና ዘልዬ ገባሁባት "

"ከዛስ?"

"እንጃ ከዛ በኋላ የሆነውን አላውቀውም "

"በቃ ለዛሬ ይበቃል..አሁን እቀሰቅስሀለሁ ሁሉንም ነገር ታስታውሰዋለህ ."..አለኝና

ከሰመመኑ ስቃዬ ...አንድ...ሁለት ...ሶስት ..."ብሎ ቀሰቀሰኝ ገላገለኝ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 2:20 pm

ወይኔ ሰውዬው ...ለፍቼ ለፍቼ ....በላው ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Oct 04, 2008 2:40 pm

እውነትም ሁሉንም አስታወስኩ ....ለምን አላስታውስም ...ሁሌም በህልሜ የማያት አሰቃቂ ድራማ ነች ...ከህልሜ ጋር ልዩነት ቢኖር ..ቢያንስ የት እንደተወለድኩ እንዳደኩ አውቃለሁ ...ያ አሰቃቂ ድርጊትም የተፈጸመበትን ቦታም አውቄአለሁ ...ቤታችንም በየትኛው አቅጣጫ እንደሆነ መገመት አያዳግተኝ ይሆናል ...የዛን የቁስለኛ ትክክለኛ ስም ባላውቅም መልኩን የምረሳው አይመስለኝም ...ማለት ምንም እንኳን ይሄ ነገር ከተፈጸመ አስራ ምናምን አመት ቢያልፈውም ማለቴ ነው ....

ከሰመመኔ ከተመለስኩ በኋላ ዶክተሬ ሁለት ቢራዎች ከፍቶ አንዷን እያቀበለኝ

"እርግጠኛ ነኝ ሁሉንም ታስታውሰዋለህ?"ሲል እዝን ብሎ ጠየቀኝ
"አዎ .."አልኩት ባጭሩ
"እንግዲያው የተቀረጸውን በድጋሚ ማዳመጥ አያስፈልገንም ማለት ነው "አለኝ
"አዎ .."አልኩ በድጋሚ
ከመቅረጫው መሳሪያ ውስጥ ድምጽ የተቀረጸባትን ትንሽዬ ሲዲ ካወጣና ወደ ኮፈኗ ከመለሰ በኋላ
"ለማንኛውም ያዘው "ብሎ ሰጠኝ ...
እኔም ሲዲዋን ተቀብዬ እስከዛሬ ስለተደረገልኝ ከፍተኛ እርዳታ ከልቤ አመሰገንኩ ...

ዛሬ ያለ ልማዱ ዶክተሩ ኪሱን ደባብሶ አንዲት የተጨማደደች የሲጃራ ፓኮ አውጥቶ ...በግቢው ውስጥ እየተዘዋወርን እንድናጨስ ጋበዘኝ
እኔም ቢራዬን ጨልጬ ግብዣውን ተቀብዬ ተከተልኩት

በግቢው ውስጥ እየተዘዋወርን ሲጃራችንን ስናጨስ ቆይተን
ትንሽ ሲተክዝ ቆይቶ
"አየህ ጌታው አደጋ ላይ እንዳልጥልህ ፈራሁ እንጂ አንድ ልነግርህ የምፈልገው ነገር ነበር "አለኝ አሁንም ማዘኑ እየታየበት

"ይገባኛል ዶክተር የግድ ወደ ሀገሬ ተመልሼ ወደ ቦታው በመሄድ ቀሪውን ሚስጢር ማወቅ መፍታት ይኖርብኛል ....መልአኬም ትናንት ባለፈው ለሊት በህልሜ መቶ ወደ ኢትዮጲያ ብሄድ ለሁሉም ጥያቄዎቼ መልስ እንደማገኝ መክሮኛል ነግሮኛል "ስለው
ያበደ ይመስል ያንን ጨበሬ ጸጉሩን እየፎከት ሲስቅ ቆይቶ ...ሳቁን አቁሞና ትንሽ ከሳለና ጉሮሮውን እንደመጠራረግ ካለ በኋላ
"ይገርማል እኛ በእግዜሩ ስራ ገብተን ስንፈተፍት እናንተ በቀጥታ ከሱ ከዋናው ጌታ ጋር ትነጋገራላቹህ ...አስደናቂ ነገር "አለኝ እና በሀሳብ እርቆ ሄደ
ወዲያው የእጅ ሰአቱን አየት አደረገና
"ጌታው አሮጊቷ መምጫዋ እየተቃረበ ስለሆነ ለዛሬው በዚሁ ላሰናብትህ ግድ ይሆንብኛል ...ደውልልኝ ...አይዞህ በርታ ...."ምናምን ብሎ አሰናበተኝ
ዘበኛውን ተሰናብቼ ከግቢው ስወጣ ይቺ የመጨረሻዋ ቀጠሮዬ መሆኗን አምኜ ጓደኞቼን ፍለጋ ወደ ሰፈሬ ተመለስኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ጆቢራው » Wed Oct 15, 2008 9:52 am

ፓኑ አባ ፈርዳ ...ቢቸግረው በዚችኛዋ ስም ብቅ ለማለት ተገዷል.................
ዋርካ የምጽፋትን እየዋጣት ተቸገርኩ ....
በሉ እስቲ ዋርካን አባብዬ ብቅ እላለሁ
ፓን አባ ፈርዳ
ጆቢራው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Mon Nov 08, 2004 10:42 pm
Location: ethiopia

Postby ትትና » Thu Oct 16, 2008 1:50 am

ፓኑ:- የሚገርም ጽሁፍ ነው!!! በፍጹም እንደዚህ አይነት ጽሁፍ አንብቤ አላውቅም:: በናትህ ሳትጨርሰው እንዳትጠፋ:: ሲያልቅ ሚሊዮን ጥያቄ አለኝ ከፈቀድክልኝ::

አክባሪህ
ትትና
ትትና
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1253
Joined: Wed Feb 23, 2005 11:26 am
Location: united states

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Oct 19, 2008 7:21 pm

ትትና wrote:ፓኑ:- የሚገርም ጽሁፍ ነው!!! በፍጹም እንደዚህ አይነት ጽሁፍ አንብቤ አላውቅም:: በናትህ ሳትጨርሰው እንዳትጠፋ:: ሲያልቅ ሚሊዮን ጥያቄ አለኝ ከፈቀድክልኝ::

አክባሪህ
ትትና

ትትና ......አይዞን ጊዜ እያጣሁ ነው እንጂ ሳልጨርሰውስ አልተወውም ...ጥያቄዎችን ካሁኑም ማቅረብም ይቻላል...ከቻልኩ ለመመለስ እሞክራለሁ ....እስቲ ከሰሞኑ ብቅ እላለሁ ...
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Oct 19, 2008 7:35 pm

ወደ ሰፈሬ በምድር ውስጥ ባቡር ..ሜትሮ...ስጓዝ ብዙ ብዙ ሀሳቦች እየመጡ አይምሮዬን በጥያቄ ወጥረው ያዙት .....ይቺን ህልሜን ስፈታ እና ስገላገላት እፎይ የምል መስሎኝ ነበር
ተሳስቻለሁ ....

ምናልባት ያኔ በመጦ ሰአትና ቦታ ያለ ሀጥያቴ ተገኝቼ ይሆናል ....ቢሆንም ሊገሉን በሚተኩሱብን ጨካኞች ላይ አንድ ሶስቴ አነጣጥሬ ተኩሻለሁ ...እርግጠኛ ባልሆንም ባልገል ክፉኛ ሳላቆስል አልቀረሁም ...
ምንም እንኳን በዛን ጊዜ የ11 ወይም የ 12 አመት ህጻን ብሆንም በሰው ላይ መሳሪያ አንስቼ ተኩሻለሁና ከተጠያቂነት ነጻ አያደርገኝም ...ከሁሉም በላይ ወደዛች ቀበሌ ስመለስ ምናልባትም የበቀል ብትር ይጠብቀኝ ይሆናል ...ወደ ሀገሬ ከተመለስኩ በውል በማላውቀው አደጋ ላይ መውደቄ አይቀርም ....ግን እግዜሩ እራሱ ወደ ሀገርህ ተመለስ ብሎ መልክት ሲልክብኝ መቼም ለአደጋ አሳልፎ እንደማይሰጠኝ እያሰብኩ ....ሳላስበው ሰፈሬ ደረስኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests