ወራሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ወራሽ

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Mar 21, 2008 12:29 pm

ማንህ?
አምላክህ ነኝ ..ተነስ
ለምን አሁን ትቀሰቅሰኛለህ ?ደክሞኝ እንደተኛሁ ጠፍቶህ ነው ?
ጠዋት ናና እንጫወታለን
አይ ጠዋትማ አንተን የማናገር አቅሙም እድሉም የለኝም
እንዴት?ማነው የሚከለክልህ?
የእናት አባትህ አምላክ የእናት አባትህ ውቃቢ የአንተ የራሶችህ ሴጣኖች ቀኑን ሙሉ ወጥረው ስለሚይዙህ አኔ ከነሱጋ የምጋፋበት አቅሙ ስለሌለኝ አንተን ማናገር የምችለው እንዲህ አድክመውህ ሲሄዱ ብቻ ነው

ይልቅ ተነስ አንድ የምነግርህ ጥብቅ ሚስጢር አለኝ
መነሳት ቀርቶ መተኛቱም እየከበደኝ እንደሆነ እያየህ እንዴት ተነስ ትለኛለህ
ግድ የለም አንዲት ቃል ለመስማት የምትችልበትን ሀይል አሰባስብና አይምሮህን ብቻ አስነሳው

ይምር ደክሞኛል እግዜሩ ይወቅ ዛሬ ስንት ቢራ እንደጠጣሁ ...ከጠዋት ጀምሬ ስለጋው ነው የዋልኩት ያጨስኩትን ሲጃራ በፓኬት ሳይሆን በየጊዜው እየሞሉ በተደጋጋሚ በተደፉት የሲጃራ መተርኮሻዋች መቁጠሩ ሳይሻል አይቀርም ....ቀኑን ሙሉ ስሞነጫጭርበት የነበረውን ወረቀት እንኳን ይዤ ቤቴ መግባቴን የማውቀው ጠዋት ስነሳ ነው ለጊዜው ያንን ማሰላሰያ ሀይል የለኝም ...እንዲህ ቀኑን ሙሉ ቢራ ቤት እስከምሽቱ ድረስ አብራኝ የሲጃራና የብዙ መጠጦች ሽታ ስትታጠን የዋለቺውን ካኒቴራዬን እንኳን ማውለቁ ደክሞኝ በሷው ተጠቅልዬ ነው የተኛሁት ..እና አሁንም አሁንም የሲጃራ የቢራ የቮድካ ሽታ ይሸተኛል...
ይቺም ኑሮ ሆና ይሄው አላስተኛ የሚል አምላክ አዘዘብኝ ..ተነስ ይለኛል ...ሚስት ያላገባሁት ከዚህ መሰል ጭቅጭቆች ለመገላገል ነበር ...ለነገሩ በየት ወጣህ በየት ገባህ የሚለኝ የቤት አስቤዛ ውለድ የሚለኝ የሚያለቅስ ልጅ የሌለኝ ..የቤቴን ኪራይ ጊዜ ጠብቄ እስከከፈልኩ ድረስ በአሻኝ ሰአት ተነስቼ በአሻኝ ሰአት የምገባ የራሴ ንጉስ ነኝ ....ያው አልፎ አልፎ "ይቺ ሰውዬ ከየት አባቷ እያመጣች ነው ከጠዋት እስከማታ የምትጠጣው ..የሚሉ ባልተኞች ሲያቧልቱ እሰማለሁ ...ብቻ ምቀኛ አታሳጣኝ ነው የሚባለው መሰለኝ ...አያገባው ገብተው ቢቀባጥሩ እኔ ምን ተዳዬ ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Mar 21, 2008 4:28 pm

እውነቱን ለመናገር እኔንም ይገርመኛል ...ሰው ወር ከወር ሰርቶ ሁሌም ሲያማርር ነው የምሰማው ...እኔ ያልሰራሁት የስራ አይነት የለም ከመንገድ ጠረጋ እስከ አንድ ትልቅ የጣልያን የጨርቃጨርቅ ድርጅት ሀላፊነት ደረጃ ሰርቻለሁ ...ግን ይቺን ምድረ ደሀ የሚቀናባትን ህይወት የጀመርኩት ከጥቂት አመታት ወዲህ ነው ...ሰው ገንዘቡን ከየት እንደማመጣው የመሰለውን እየፈጠረ ያወራል እውነቷን የምናውቃት እኔና ፈጣሪ ብቻ ነን ምናልባት አሁን ፈጣሪ የላከብኝ አምላኬም እውነቷን ያውቅ ይሆናል ...አንዳንድ ወዳጆቼ ጥጋ ብለው ለምን ስራ እንደማልሰራ ይጠይቁኛል ....ወዳጆች ናቸውና ማስቀየም ስለሌለብኝ ጥያቄውን አድበስብሼ እንደነገሩ እመልስላቸዋለሁ
ለነገሩ እርጅናም መጣሁ እያለ ነው መሰል አልፎ አልፎ ወገቤን ያመኛል ...ከልጅነቴ ጀምሮ ሀኪም ቤት የሚባል ነገር ስለማልወድ ወገቤን አመመኝ ብዬ ሀኪም ቤትም አልሄድኩም ...እስከዛሬም ታምሜ ስለማላውቅ ሀኪም ቤት ሄጄ አላውቅም ..አንድ በእድሜ ጠና ያለ የኛ ሰው ወገቤን አመመኝ ብሎ ሄዶ የወገብ ሀኪሞች በኮረንቲ ጅራፍ ገራርፈውት አንድ ሰሞን ልክ እንደ ጎረምሳ ሲዘል አይቼው ነበር ...ታዲያ የኮረኒ ጅራፍ ይምትረዳው ለተወሰነ ጊዜ ነው መሰል ይሄው ያገር ሰው በየ 3ቱ ወር እየሄደ በኮረንቲ ጅራፍ ይገረፋል አይጣል ነው
ታዲያ ያው እንደልማዴ እራሴን በቢራ አድክሜ ጋደም ከማለቴ እግዜሩ የላከብኝ አምላኬ ይመጣና ይቀሰቅሰኛል ...እነሆ ዛሬም ጋደም ከማለቴ መቶ ቀሰቀሰኝ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ቤቲ_13 » Fri Mar 21, 2008 5:31 pm

እኔኮ.....በጣም የማደንቅህ በጣም ጥልቅ የሆነና በጣም እጅግ በጣም ዉብ ስራዎችህ
ክብርብር እንዳደርግህ ይገፋፋኛል
አክባሪህ
Image
ቤቲ_13
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 795
Joined: Mon Sep 18, 2006 7:27 pm
Location: ethiopia

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Mar 22, 2008 3:31 pm

ዛሬ የምር ቀኔ አልነበረም በዋልኩበት ሆስፖዳ/ቢራ ቤት/ቀኑን ሙሉ ከደንቆሮዎች ጋር ስጨቃጨቅ ነው የዋልኩት ...ከተጨቃጨኩና ድምጼን ከፍ አድርጌ መከራከር ከጀመርኩ ቶሎ እስክራለሁ .. ብሰክርም ውጡ ሳይባል ወቼ ወደ ቤቴ የሄድኩበት ጊዜ የለም ....
የሆስፖዳዋ እሽታምጋስት ከሆንኩ ጥቂት አመታት ተቆጥረዋል .......ቢራ ቀጂዎችም እኔ ከሌለሁ ቅር የሚላቸው ይመስለኛል ....እሽታም ጋስት እንደመሆኔ ቁጥር የራሴ የሆነ ባል ግማሽ ሊትር ብርጭቆ አለኝ ...ብርጭቆ ሲሏቹህ ደሞ እንዳው ተራ ብርጭቆ እንዳይመስላቹህ ....የሆስፖዳዋ ባለቤት ከቢራ ፋብሪካው በቀጥታ አዞ ለኔ ለሀበሻው ልጅ አሰራልኝ ...ቄንጠኛ ብርጭቆ ነች ....ወገቧ ላይ "NGUS" የሚል ውብ ቃል ተጽፎባታል....እኔ ንጉስ ሆኔ ሳይሆን የሀበሻው ንጉስ በ1960ዎቹ ፕራግን ሲጎበኝ ያዩ የዛሬ አዛውንቶች ሁሌም ደስ እያላቸው ስለታላቁ የኢትዮጲያ ንጉስ ያወራሉ ....በፕራጉ ከተማ አንዱ መንገድ በኢትዮጲያ ሲጠራ ሁለተኛው የሀበሻ መንገድ ይባላል እናም ለዛ መሰለኝ የኔን አስቸጋሪ ስም ከመጻፍ እኔም የሀበሻ ልጅ ነኝና በንጉሴ ስም "ንጉስ"ብለው ጽፈው ብርጭቆ ሸለሙኝ ...ለንጉስ የሚገባው የክብር ቦታ እና ለንጉስ የሚሆን መቀመጫ ዙፋ ሰጡኝ ...
እናም በዚች ትንሽ ዙፋኔ ላይ ተቀምቼ ከእርጎ የማይተናነሰውን ቢራ ስለጋ እውላለሁ ...በዚቺው ዙፋኔ ዙሪያ ብዙ የሀገሬው ሰዎች ስለ ቀረጥ አከፋፈል ምክር ጥየቃም ይመጣሉ ...ያው የተለመደቺውን አጠር ያለች ምክሬንና ያመጧትን ወረቀት በጥንቃቄ ሞልቼ እሸኛቸዋለሁ ....አብዛኛዎቹ ለዚች ቆራጣ ስራዬ በጥሬ ገንዘብ ይከፍሉኛል ...የቀሩት የቀኗን ሂሳብ ዘግተው አመስግነው ይሄዳሉ ......
ሆነ ቀረ ገንዘብ መስራቴ ብቻ ሳይሆን እኔ የሀበሻው ልጅ ፈረንጅን የቀረጥ አከፋፈል አማካሪ ለዚያውም በሆስፖዳ ውስጥ ብቻ እንዲሁ ደስ ይለኛል
የኔ አንዷ እና ትንሿ የገቢ ምንጭ ይቺ ነች ...ይቺን የገቢ ምንጬን ያጤነ አንድ የሀገሬ ልጅ ዙፋኔን የጎሪጥ እያየ "ኪራይ የማይከፍልባት የ ፓን ቢሮ"ብሎ አሽሟጦኝ አልፏል...እውነቱን ነው ልክ እንደመንግስት ሰራተኛ ጠዋት ገብቼ የራሴ የግል ጠረጴዛ እና ወንበር ተሰቶኝ የጠጣሁበትን ብቻ ከፍዬ ስራዬን ስሰራ ውዬ እገባለሁ ..ያው እኔ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ስለምበላ ወደ ቢሮዬ ከመሄዴ በፊት ቤት ያፈራውን አሟሽቼ ነው ይምወጣው ስለዚህ በቀን ውሎዬ የማጠፋው ነገር ቢኖር የጠጣሁትንንና ያጨስኩትን ብቻ ነው ....ቢራ ቤቷ ከመኖሪያዬ ብዙም ስለማትርቅ ለትራንስፖርት ምናምን ቤሳ አላወጣም ...በግሬ ቀጥ ብዬ ሄጄ እየተወላገድኩ እገባለሁ እንግዲህ ከዚች የእለት ከእለት ኑሮዬ የምትለየኝ ቀን ብትኖር ያው እሁድ ነች ...ቤተክርስቲያን ባልሄድም ያው ጠዋት ተነስቼ ታጥቤ በንጹህ ጨርቅ ሸፍኜ የማስቀምጣትን መጽሀፍ ቅዱሴን አነሳና በአጋጣሚ የከፈትኩትን ገጽ አነባለሁ ......ባለፈው እሁድ እንዲሁ ተነስቼ በድል የከፈትኩት ገጽ "የሄኖክ ታሪክ"ይላል ይገርማል ሄኖክ በዛን ጊዜ መሬት እንደምትሽከረከር ያውቅ ነበር ...ሄኖክ ሰማይ ላይ ሆኖ ቁልቁል ወደመሬት ሲያ መሬት መሽከርከሯን ብቻ ሳይሆን ሰባት ትልልቅ ተራራዎችም አየሁ ይላል ....ሰባቱ ተራሮች ሰባቱ አህጉራት መሆናቸው ይሆን ??
ብቻ እግዜሩ ከዚህ የድሀ ልጅ የኑሮ ድካሜ እንዳላርፍ አምላክ መርጦ ልኮብኛልና ይሄው ቀሰቀሰኝ
"ጥብቅ ሚስጢር ሊነግረኝ"
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Mar 22, 2008 3:53 pm

"ጥብቅ ሚስጢር"ልነግርህ ነውና የመጣሁ እያለ አምላኬ ክፉኛ አማረረ
"ጥብቅ ሚስጢር" ይቺን ይወዳል አልኩና እንደምንም ያለ የሌለ ሀይሌን አሰባስቤ የአይምሮዬን ሞተር አስነሳሁት....0አምላኬም መነሳቴን አይቶ በደንብ እንድሰማው የሚነግረኝን ነገር ምንግዜም እንዳልረሳው ደጋግሞ አስጠነቀቀኝ እኔም እሽታዬን ከድንጋይ በላይ የሚከብደኝን እራሴን እያወዛወዝኩ በአወንታ የሚነግረኝን ምን ጊዜም እንደማልረሳው አረጋገጥኩለት
አምላኬ ይሄን ሲያይ
"ወራሽ"ነህ ብሎኝ ሊሄድ ሲል እንደምንም ተነስቼ ከፊቱ ቆምኩና የማን? የምንስ?ወራሽ መሆኔን እንዲነግረኝ ከፊቱ ተደንቅሬ እንደቆምኩ ጠየኩት ...አምላኬ ጥቂት ዝም ብሎ ቆየና
"ወራሽነትህን ለወንድሞጭም ንገራቸው"አለኝ
ኧረ አምላኬ እኔ ወንድሞች የሉኝም "አልኩት
አሁን ትንሽ ቆጣ ብሎ ...ወንድሞችህ እንዳንተው በአለም ላይ ተበትነዋል ፈልገህ ንገራቸው "አለኝና እዛው ተገትሬ የቆምኩበት ቦታ ላይ በየት በኩል እንዳለፈ እንኳን ሳላስተውል ጥሎኝ ተሰወረ
በዚች በተረገመች ለሊት አምላኬ ተመልሶ መቶ የማን ?የምን?ወራሽ መሆኔንና ወንድሞቼንስ እንዴት ፈልጌ እንደማገኝ እንዲነግረኝ ተማጸንኩት
አልሰማኝም ዳግም ላይመለስ አንዲት ፍሬ ቃል አንዲት ጥብቅ ሚስጢር ተንፍሶልኝ ብቻዬን ጥሎኝ እስከወዲያኛው ሄደብኝ ወራሽ?ወራሽ?ወራሽ?እያልኩ አይነጋ የለ ነጋና ተነሳሁ ....ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ለረጂም ሰአት በሞቀ ውሀ እንፋሎቱ ግርግዳዎቹን እስኪያረጥባቸው ድረስ ታጠብኩ
ልብሴን ለባብሼ አፌን እንኳን ሳላሟሽ ወራሽነቴን ለመመርመር እኔነቴን ልፈልግ ወንድሞቼን ላፈላልግ ወደ ቢሮዬ ሄድኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Mar 25, 2008 10:02 am

ወደ ቢሮ ስገባ የቢራ ቤቷ አስተናጋጅ ከላይ እስከታች አገላብጦ አየኝና
"ጌታው ...ሁሉ ነገር ሰላም ነው?" አለኝ
ግራ ተጋብቼ ቢራ ቤቱን ግራ ቀኝ ሳይ ማንም የለም ...ሰአት ማሰር ከተውኩ ቆይቻለሁና ሞባይሌን ከኪሴ አውጥቼ ሳይ ..ቢራ ቤቷ ከመክፈቻ ሰአቷ 20ደቂቃ ቀድሜ መምጣቴን ስገነዘብ ልቀም,እጥ የነበርኩት ሰው ፊቴን አዙሬ ልወጣ ስል ....
"ግዴለም ጌታው ...ተቀመጥ "አለኝ አሁንም እንደጉድ እያየኝ
የምር ግራ ተጋባሁ ..ለአመታት የማውቀው ሰው እንዲህ አገላብጦ በግርምት ሲያየኝ ፍጹም ግራ ተጋባሁና ጉዴን ላይ ወደ መጸዳጃ ክፍል ዘው ብዬ ስገባ እኔው እራሴ ደነገጥኩ ...በትልቁ መስታወት ውስጥ የማየው ሰው መልሶ አስደነገጠኝ .....ወዲያው ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝና ፍርፍር ብዬ ሳቄን ለቀኩት ...
ለካስ እኔነቴን ልመረምር ወራሽነቴን ልመራመርበት ወንድሞቼን ልፈልግበት ብዬ ከቤት ስወጣ ላየ ወትሮዬ ጺሜን ተላጭቼ ጸጉሬን አበጥሬ ሱፌን ግጥም አድርጌ ለብሼ ከረባቴን አስሬ ሽክ ብዬ ከቤቴ መውጣቴን እንኳ ልብ አላልኩትም ነበር ...ምናልባት አምላኬ ከቢሮዬ ከች ቢል በክብር ልቀበለው የክብር ልብስ መልበሴ ነበር ...ይሄንን ያደረገው የውስጡ እኔነቴ እንጂ እኔ የቢራቤቱ ፓን እንዳልሆንኩ ያልተረዳው የቢራ ቤቱ አስተናጋጅ እንዲያ በግርምት እኔን ማየቱ እኔንም መልሶ አሳቀኝ ...ብቻ ለጥቂት ደቂቃዎች እራሴን ተዟዙሬ አየሁና እራሴን "ለካ ሸበላ ነህ"እያልኩ አሞጋገስኩና ወደቦታዬ ተመልሼ ተቀመጥኩ ...
እንደተለመደው መጀመሪያ ..የቱርክ ብና የሚባለው ቡና ከውሀ ጋር ቀረበልኝና ብናዬን ፉት እያልኩ ሲጃራዬን ለኮስኩና የእጅ ቦርሳዬን ከፍቼ ሶስት ንጹህ ወረቀቶች አውጥቼ
በመጀመሪያው ወረቀት ላይ "ፓን"ብዬ ጻፍኩበት
ሁለተኛው ወረቀት ላይ "ወራሽ"ብዬ ከጻፍኩ በኋላ የመጨረሻውና ሶስተኛው ወረቀት ላይ "የፓን ወንድሞች"ብዬ ጻፍኩበት ...
ሶስቱም ወረቀቶች ፈጠው እያዩኝ እኔም እያየዋቸው ምንም ተጨማሪ ነገሮች ሳልጽፍ ቢራ ቤቷ ቀስ በቀስ ሞላ ማለት ጀመረች ...እኔም ሁለተኛውን ቢራዬን አጋምሻለሁ ...የሲጃራ መተርኮሻዋም ሞላሁ ሞላሁ እያለች ነው ...እኔ ግን ምንም ሀሳብ ሳይመጣልኝ ከየት እንኳን መጀመር እንዳለብኝ ግራ ተጋብቼ እንደተቀመጥቁ ..ጡረተኛው የዱሮ የዩንቨርሲቲ አስተማሪዬ እኔን ሲያይ በሳቅ ሊወድቅ እይተንገዳገደ መቶ እሱም በኔ በስተቀኝ በኩል ካለው የክብር ቦታው ሄዶ ከመቀመጡ በፊት ቆም ብሎ
"ንጉሽ"የተፈጠረ ነገር አለ??"ብሎኝ ሳቅ እያለ ሄዶ ተቀመጠ
እኔም ሳቅ አልኩና
"አዎ ጌታዬ...እስቲ አረፍ ይበሉና የማዋዮት ጉዳይ ይኖረኛል "አልኳቸው
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Mar 25, 2008 10:30 am

"ግዴለ ና አንበሳዬ ...ምን ችግር ገጠመህ?"ሲሉ ፕሮፌሰሩ ጠጋ ዬ እንዳዋያቸው ጋበዙኝ
እኔም ወንበሬን ወደ እሳቸው ጠረጴዛ እየሳብኩ ..አስተናጋጁን ምልክት ሰጠሁትና ካጠገባቸው ተቀመጥኩ
አስተናጋጁም እሳቸው የሚወዷትን "ቤከሮፍካ" እና እኔ የምጠጣትን የፊንላንድ ቮድካ ካቀረበልን በኋላ ለጠናችን አጋጭተን በአንድ ትንፋሽ ከጨለጥን በኋላ ሰሞኑን የሚያስጨንቀኝን የአምላኬን የለሊት ጉብኝትና የመጨረሻዋን አምላኬ ፈጽሞ እንዳትረሳው እያለ ያስጠነቀቀኝን ጥብቅ ሚስጢር አጫወትኳቸው
ፕሮፌሰሩ በኔ ትረካ ሳይገቡ የኔን የህልም ታሪክ በጥሞና በታላቅ ትግስት ሲያዳምጡኝ ቆይተው እሳቸውም በተራቸው አስተናጋጁን ወደ እሳቸው እስኪያይ ጠብቀው በምልክት አዘዙት
አስተናጋጁ እንደተለመደው ለሳቸው ቤከሮፍካ ለኔ ቮድካ አመጣልን ...የሀገሬው ልማድ ነውና አሁንም ለጤናችን አጋጭተን በአንድ ትንፋሽ ጨልጠን ቢራችንን ተጎንጭተን እኔም እሳቸውም ሲጃራዎቻችንን ለኩሰን ለጥቂት ጊዜ በዝምታ ተዋጥን ...
እኔ ፕሮፌሰሩ በኔ ህልም ይስቃሉ እያልኩ ስሰጋ እሳቸው አሁንም ዝም አሉ ..አልሳቁም አላዘኑም ...አንዲት ቃል ሳይተነፍሱ ወደፊታቸው ብቻ ፍዝዝ ብለው እያዩ ሲጃራቸውን ደጋግመው ይስባሉ ....አልቻልኩም ተነስቼ ወደ መጽዳጃ ክፍል ሄድኩና ሽንቴን ሸንቼ እጄን ስታጠብ እራሴን በመስታወት ውስጥ ፍጥጥ ብዬ አየሁት ምስሌም ፍጥጥ ብሎ አየኝ እንጂ ምንም ፍንጭ አልሰጠኝ ...ብቻ እጄን በፎጣ አደራድቄ ወደ ፕሮፌሰሩ ተመለስኩ
ገና ከመቀመጤ
"አንበሳዬ እስቲ ስለ ልጅነት ዘመንህ አጫውተኝ" አሉኝ
የኔ የልጅነት ዘመን ከዚህ ህልሜና አምላኬ ከነገረኝ ጥብቅ ሚስጢር ጋር የሚያገናኘው ነገር ባይገባኝም ስለ ልጅነተ ላቻውታቸው ከየት መጀመር እንዳለብኝ ማሰላሰል ስጀምር
"ግዴለም አንበሳዬ ...አያስቸኩልም ቀስ ብለህ አስበህ አውጥተህ ትነግረኛለህ ...ለዛሬው ይበቃል ...እስቲ ስለ ሌላ ጉዳዮች እንጫወት ብለው "የጫወታውን መስመር ለወጡት
ምንም እንኳን በሚያነሷቸው ሀሳቦች ላይ አልፎ አልፎ አንዳንድ ሀሳቦችን መሰንዘሬ ባይቀርም በግማሽ ግን ወደ ልጅነቴ ተመልሼ ነበር
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Mar 25, 2008 5:05 pm

በዛች ቢራ ቤት ደንበኞቿ ተሰባስበው እኔም የግል ጉዳዬን የልጅነቴን ታሪክ ጉዳይ ማለቴ ነው ለጊዜው እረስቼ ብዙ ብዙ ስለአለም የፖለቲካና ማህበረሰባዊ ችግች አንስተን ስንቀበጣጥር አንዳንዶቻችን ፈጽሞ እርቅ በሌለው ጉዳይ ላይ ተኮራርፈን ተጣልተን ተለያየን ...ጠቡ ያው የሀሳብ መለያየት ጠብ ነው እንጂ የሌላ አይደለምና ነገ ስንገናኝ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ነገር ሁሉ ሰላም ተባብለን ብርጭቋችንን አጋጭተን ለጤናችን ተጎንጭተን እንደገና ሞቅ ሲለን ትናንት ከተውንበት ቦታ አልያም አዲስ ሀሳብ አንስተን እንደገና ስንጨቃጨቅ ስንጣላ እናመሻለን ...
ዛሬን በዚህ መልኩ አሳልፌ ...ጠዋት ስወጣ ልብ ያላልኳትን ኮቴን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጌ እየተጀነንኩ ገብቼ አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ ....

ለወትሮው ቢሆን እንዲህ ቢራ ጠግቤ ስገባ ከየት መጣህ ሳይሉት አቶ እንቅልፍ ጫማዬን እንኳን ማውለቂያ ጊዜ ሳይሰጥ ይዞኝ ጭልጥ ይል ነበር .....ዛሬ እሱም እንደ አምላኬ ብለምነው ብማጸነው የራስህ ጉዳይ ብሎኝ ጠፋ ...በቃ ብቻዬን ነኝ ...ሁሌም ማንንም ተለማምጬ አላውቅምና አቶ እንቅልፍንም ብትፈልግ ገደል ግባ አልኩና ፍሪጄን ከፍቼ ያገር ተወላጅ አረቄ አወጣሁና መክደኛዋን ከፍቼ ጠርሚሷን ባፌ ደቅኔ ደቅደቅ አደረኳት ...አረቄዋ ደረቴን ሰንጥቃው ስትወርድ የሆነ ደስ የሚል ነገር ተሰማኝ ...ብቻ ጥቂት ቁጭ አልኩና ቡና አፍልቼ ሲጃራዬን ለኮስኩና ትንሿን ቤቴን ዙራ ገባዋን አየኋት ...ያቺው የማውቃት ቤቴ ነች ...እሷም በኔ ላይ እያፈጠጠች ...አምላክህንም እንቅልፍህንም እኔ አልቀማሁህምና በኔ ላይ አታፍጥ የምትለኝ መስሎኝ ትቂት እንደማፈር ብዬ በዛቺው ትንሿ ሶፋዬ ላይ ጋደም አልኩ ....ምን ያህል ጊዜ እንኳን በዛች አሮጌ ትንሽ ሶፋ ላይ ተኝቼ እንደነበር አላውቅም ግን በጣም አስፈሪ ህልም ከሶፋዬ ላይ ወርውሮ ጥሎኝ እራሴን ልክ ገላውን እንደታጠበ ሰው በላብ ተነክሬ አገኘሁት ..................ወይ እዳ አልኩኝ .....ይቺ አስፈሪ ህልም ለኔ አዲስ አደለችም ....ምንም እንኳን ከጥቂት አመታት በፊት ሰላም ብትሰጠኝም ለረጅም አመታት በተደጋጋሚ እየመጣች አበሳዬን መከራዬን ስታበላኝ የኖረች ህልም ቅዠት ነችና አሳምሬ አውቃታለሁ ....ቢሆንም ዛሬ አልጠበኳትምና ትንሽ በስጨት አልኩ ...
አንድ ሁለት ሲጃራ ካጨስኩና አረቄዋን ጉንጨት ብዬ ወደ ማቀዝቀዣዋ ከመለስኩ በኋላ እግዜርን ተማጽኔ ወደ አልጋዬ ሄድኩ ...ሊነጋጋ ሲል ጤነኛ እንቅልፍ ወሰደኝ ....ተመስጌን አምላኬ አልኩ ...አለበለዚያ አንድ ቀን ማበዴ የማይቀር ጉዳይ ነው
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sat Mar 29, 2008 10:36 am

የቀን መቁጠሪያ አርብ መሆኑን አሳየኝ ....አርብ ከሌላው የተለየች ቀን የሚያደርጋት ያው ወደ ቢሮዬ ያለመሄዴ ጉዳይ ብቻ ነው .....እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ቡናዬን አፈላሁና ሲጃራዬን ለኩሼ ስለ ቀሪው ቀን ማሰላሰል ጀመርኩ ...እንደሁልጊዜው ሁሉ ዛሬ እግር ኳስ እንጫወታለን ...ከኳስ በኋላ እንታጠብና ተያይዘን ወደ ቢራ ቤት እንሄዳለን ...የዛሬው የቢራ ቤት ውሎዬ ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ቢራዬን የምጠጣው ከሀገሬ ልጆች ጋር ነው ....
እንግዲህ ሀበሾች ተሰብስበው ቢራ ሲጠጡ ጭቅጭቅ አይጠፋምና ያው ልጨቃጨቅ ነው የምሄደው ...እኔ የምንም ፓርቲ ደጋፊ አይደለሁም ...የዛሬው የቢራ ቡድን ግን እንደመልኩ ሁሉም የተለያየ አስተሳሰብና የፖለቲካ አቋም ያለው ነው ...ቅንጂቱ ወያኔው ኦሮሞው በሽ ነው ...ብቻ እንዲህ እያሰብኩ ትጥቄን አዘገጃጅቼ እና በቦርሳ ከትቼ አንጠለጠልኩና ቤቴን ቆልፌ ወደ ኳስ ሜዳ ሄድኩ ...ይህ ሁሉ ሲሆን እስካሁን የኔ የልጅነት ታሪክ ከአይምሮዬ አልጠፋም ...አስባለሁ ...ስሄድም ስበላም ስጠጣም ስተነፍስም አስባለሁ ....ይሁንም እንጂ ይሄ ነው የምለው ጭብጥ ነገር አልያዝኩም ...ማሰብ ማሰብ ማሰብ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ይከአሎ » Sat Mar 29, 2008 7:37 pm

ሰላም ያገር ሰው ፓን: ዋርካ ላይ ላለ መፃፍ እራሴን ገዝቼው ነበር ግን የ ወራሽ ጅምር ታሪክህን ሳነበው ቀልቤን ገዛው እናም አድናቆቴን ልሽርህ ጣቶቼን ቀስሬ ፃፍኩልህ :: እስቲ ቀጣዩን ቶሎ ቶሎ ከትብልን....

ወዳጅህ
Long live to tsion !!!!
ይከአሎ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 53
Joined: Wed May 18, 2005 8:16 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Mar 30, 2008 2:11 pm

ዛሬም እንደተለመደው ማልጄ ተነሳሁና ሰውነቴን ተለቃልቄ ቡናዬን አፈላሁና ሲጃራዬን ለኩሼ እንዲሁ ዝም ብዬ ትንሿን ቤቴን መቃኘት ጀመርኩ ...በአይኔ ዳሰስኳት እሷ ግን ዝም አለቺኝ ....
አድራጎቴ እኔኑ እየገረመኝ ...ጠዋት ከፍቻት የነበረቺውን የትንሿን ቤቴን መስኮት ልዘጋ ስሄድ ከመጻፊያ ጠረጴዛዬ ላይ አንዲት ፎቶግራፍ ተደንቅራ አየሁና ...መስኮቱን መዝጋቴን ትቼ ወደጠረጴዛውዋ ሄድኩና ያቺን ጭስና አቧራ የጠገበች ፎቶግራፍ አነሳኋት....
ይገርማል ይቺን ፎቶግራፍ ከጥንቶቹ ጓደኞቼ ጋር መቼ እንደተነሳናት በወል ባላውቀውም ...ጥቂት አመታት እንደተቆጠሩ ፎቶግራፏ ታሳብቃለች ....
አዎ እኔና 4ጓደኞቼ በአንድ አጋጣሚ ፕራግ አሮጌው ከተማ የተነሳናት ናት ...ከአለባበሳችን ወቅቱ በጋ እንደነበረ ይጠቁማል ...ብቻ ፎቶግራፏን አነሳሁና አቧራዋን በሹራቤ ተራረኩና ትኩር ብዬ አየኋት ...እኔ መሀል ላይ ቆሜአለሁ ከበስተቀኜ ዑጁሉና ገብሱ ሲቆሙ ከበስተግራዬ ጎይቶምና ካቻ ቆመዋል ...
አቤት ግዜው እንዴት ይሮጣል ...ከነዚህ ጓደኞቼ ከተለያየሁ ብዙ ጊዜ ሆነኝ ...ዑጁሉ ገብሱና ካቻ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ወደ እንግሊዝ ጀርመንና አሜሪካ ተሰደዋል ...ጎይቶም ወደ አገርቤት ተመልሶ ስራና ትዳር ይዟል .....እኔ ያው እንደተቆረፈደ አህያ አንድ ቦታ እንደቆምኩ እዚቺው አገር አለሁ ....
እንዲህ ፎቶግራፏን እያየሁ ስቆዝም በትዝታ ጭልጥ ብዬ ሄድኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Mar 30, 2008 2:38 pm

ደርግ ከወደቀ ከጥቂት አመታት በኋላ መሰለኝ በቼክ ሪፐብሊክ እንኖር የነበርን ኢትዮጵያውያን ሚና ለይተን መናቆር ጀመርን ...አልፎ አልፎም መደባደብ ሁሉ ነበር ...ጊዜው ክፉ ነበርና ይቺኑ የተቀደሰች ቢራ እንኳን ለመጠጣት አንዱ"እንዴት ሆኖ ከዚህ ወያኔ ጋር እጠጣለሁ"ሲል ...ሌላው ኧረ ምን በወጣኝ ከዚህ ኢትዮጲያዊነቱን ከሚክድ ኦሮሞ ጋር በአንድ ጠረፔዛ ዙሪያ እቀመጣለሁ እያለ ብቻ በፕራግ ብቻ ከ 6በላይ ቡድኖች ተፈጠሩ ከአራት በላይ የተማሪዎች ማህበርና የመረዳጃ ማህበሮች ሁሉ ተቋቋሙ ...ያኔ ነበር እኛ አምስት ጓደኛሞች የተገናኘነው ...ለነገሩ መጀመሪያው ግድም ላይ 13 ነበርን ...ቀስ እያለ ከጊዜ ብዛት ከኛ ቡድን ጥቂቶች ወደ ሌላ ቡድን ሲገለበጡ የቀሩት ደሞ አገር ለቀው ስደት ገቡና በመጨረሻ አምስታችን ብቻ ቀረን ...

እውነቱን ለመነጋገር አብረን ያደግን የአንድ እናት ልጆች ያህል እንከባበር እንዋደድ ነበር ...እንዲህ ፍቅራችን ጠንክሮ የቤተሰቦቻችንን ገበና ሳይቀር እያነሳን እንጫወት ነበር ...ከኔ በስተቀር ሁሉም ስለ ልጅነታቸው ዘመን ስለ አስተዳደጋቸው አንዲትም ነገር ሳያስቀሩ እያወሩ በሳቅ የሰከርንበት ጊዜ ትንሽ አልነበረም ....
አዎ ገብሱ መሰለኝ አንድ ቀን "ፓኑ...እስቲ ስለ ልጅነት ዘመንህ አስተዳደግህ ቤተሰቦችህ ብቻ ስለሁሉም አውራን ያለኝ ....ነገሩ ስጠብቀው የነበረ ስለነበር ....አጠር አድርጌ ነገርኳቸው ...አዎ ባጭሩ
"በልጅነቴ ቤተሰቦቼ በመኪና አደጋ ስለሞቱብኝ ያሳደገችኝ ሴት አያቴ ነች ...አንደኛ ደረጃም ሁለተኛ ደረጃም መድሀኒያለም ት/ቤት መማሬንና በኋላም 6ኪሎ እንደተማርኩ ከዛም ይቺን የውጭ አገር የትምህርት እድል አግኝቼ እንደመጣሁ ሳልደብቅ ነገርኳቸው ...በእርግጥ አልዋሸዋቸሁም .....በአያቴ ቤት መኖር ስጀምር ምናልባት 10 ወይም 11 አመት ቢሆነኝ ነው ...እናም የማላውቀው ነገር ጥብቁ ሚስጢር አዲስ አበባ ወደ አያቴ ቤት ከመምጣቴ በፊት ያለው ህይወቴ ነው ...ስለዛ ነገር ምንም ነገር አላውቅም ....ሁሌም አያቴን እጠይቃታለሁ እያልኩ ሳስብ ከዛሬ ነገ አደርገዋለሁ ስል አያቴ ድንገት ታመው ወደማይቀርበት አለም ብቻዬን ባዶ ቤት ጥለውኝ ሄዱ ...አያቴ ይቺን ምድር ጥለው ከመሄዳቸው በፊት "ሲያመጡህ ይቺን አንገትህ ላይ አንጠልጥለህ ነበር"ብለው አንድ የወርቅ ሀብል ሰጡኝ ....አሁን ድረስ ይቺ የወርቅ ቁራጭ አብራኝ አለች....ይቺ ቁራጭ ወርቅ አንድ ቀን እኔነቴን ፍለጋ ፈረሴን ጭኔ ስነሳ መንገድ እንደምትመራኝ ተስፋ አደርጋለሁ .........
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Mar 30, 2008 3:24 pm

ቁራጫን ወርቅ ካስቀመትኩበት የመጻፍያ ጠረጴዛዬ መሳቢያ ውስጥ አወጣሁና አገላብጬ አየኋት ...ለግዜው የማትናገር የማትጋገር ቁራጭ ወርቅ ነች ...ወቋን እያሻሸሁ ሳይ የአያቴ የመጨረሻ አረፍተ ነገር ድንገት መቶ አንባረቀብኝ
"ያኔ ሲያመጡህ ይቺን አንገትህ ላይ አንጠልጥለህ ነበር "ብለው ነው ቁራጯን ወርቅ መዳፌ ላይ ያደረጉልኝ ...
"ያኔ ሲያመጡህ?"...እነማን ይሆኑ ያመጡኝ ??አያቴስ አያቴ ነበሩ?ለምንስ ነው ወደ አሮጊቷ ቤት ያመጡኝ ?ከማንስ ነው የሚደብቁኝ ?የዚችስ ቁራጭ ወርቅ ሚስጢር ምን ይሆን?....እንዳው ጥያቄውን አነሳሁት እንጂ ይቺ መዳፌ ውስጥ ያለች ቁራጭ ወርቅ አትመልስልኝ ...
ብዙ ጊዜ እኔ ማንም የሌለኝ የሙት ልጅ ነኝና ሁሉን እረስቼና የሙት ልጅነቴን አምኜ የራሴን ኑሮ መኖር እንዳለብኝ እራሴን ለማሳመን ሞክሬአለሁ ....ሙሉ በሙሉ ባይሳካልኝም ...ያቺን አስፈሪ ህልም ከራሴ ማራቅ ተችሎኝ ወጥቼ እገባ ነበር ...በመጠኑም ቢሆን ደስተኛ ነበርኩ ...ምን ያደርጋል እግዜሩ አምላክ መርጦ ላከብኝና ያቺኑ መጠነኛ ሰላሜን አጣሁ ...ሰላም የሰጠቺኝ ያቺ አስፈሪ ህልምም ተቀሰቀሰችብኝ ...እንግዲህ እንዲሁ ብቻዬን ተቀምጬ ማብሰልሰሉ ምንም ፋይዳ እንደማይሰጠኝና ይቺኑ እውነቴን ለጡረተኛው ፕሮፌሰር የዱሮ አስተማሪዬ የአሁኑ የቢራ ቤት ጓደኛዬ ማዋየቱ ሳይበጀኝ እንደማይቀር ተገንዝቤ ያቺን ቁራጭ ወርቅ በጄ ይዤ ልጅነቴን እያሰብኩ ወደ ቢራ ቤቷ ወደ ቢሮዬ ተፈተለኩ ....ቢያንስ እዛች ቢሮዬ ያቺ አስፈሪ ህልም ብቅ ብላ አታውቅም ....
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Mar 30, 2008 5:00 pm

ቁራጯን ወርቅ እያሻሸሁ ሁሉንም ነገር ከፕሮፌሰሩ ጋር ልነጋገረበት ወደ ታላቋ ቢራ ጎራ ብልም እንደተመኘሁት ፕሮፌሰሩ በቢራ ቤቷ አልነበሩም ....ተንቀሳቃሽ ስልኬን ከኪሴ አወጣሁና ሰአቷን ብቻ አይቼ መልሼ ወደ ኪሴ ከትቼ ወደ ክብር ቦታዬ አመራሁ ....
ከመቀመጤ አስተናጋጁ ቢራ ይዞልኝ መጣና
"ጌታው አንድ አፍሪካዊ ሲፈልግህ ነበር "አለኝ ....
ይሄ አስተናጋጅ ቢያንስ በኔ ፊት ጥቁር ማለት ለምን እንደሚፈራ ባላውቅም አመስግኜው ወደ ቢራ ቤቷ አዳራሽ ገባ ብዬ የሚፈልገኝን ጥቁር አፍሪካዊ በአይኔ ፍለጋ ገባሁ ....
ብዙም ሳላማትር ከርቀት አንድ ረዘም ያለ ደንዳና ሰው ወደኔ እየሳቀ ሲመጣ አየሁት ...
አዎ የዱሮ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ የጊኒው ተወላጅ ጂያሎ ነው ....
ጂያሎ ትምህርቱን ቢጨርስም በንግድ አለም ተሰማርቶ ፕራግ ፓሪስ እየተመላለሰ የሚነግድ ጎበዝና ጠንካራ ሰው ነው
ጂያሎ በቀላሉ ተንቀሳቃሽ ስልኬ ላይ ደውሎ ከኔ የሚፈልገውን ነገር ሊገልጥልኝ ሲችል እኔን ፍለጋ ብዙ መንገድ አቋርጦ መምጣቱ ቢገርመኝም የመጣበትን ጉዳይ እሱው እራሱ እስኪነግረኝ ድረስ በትግስት እየጠበኩ ይዤው ወደ የክብር ቦታዬ ወሰድኩትና ለሱ የቡርቱካን ጭማቂ አዝዠ ተቀመጥን ....ጂያሎ ሙስሊም ነው ቢራ አይጠጣም ...
ያው የተለመደቺውን የሰላምታ ልውውጥ ካደረግን በኋላ የመጣበትን ጉዳይ አጠር አድርጎ ነገረኝ ...እንዳልኩት ጂያሎ በንግድ ጉዳይ ከሀገር ሀገር የሚዞርና ብዙም ጊዜ የሌለው ከመሆኑም በላይ የሁለት ልጆች አባት በመሆኑ ያቺኑ ያለች የምትተርፍ ጊዜውን ለቤተሰቡ እንደሚያውል አውቃለሁ ....እናም ዛሬ የመጣበትን ጉዳይ ሲነግረኝ ብዙም ሳላቅማማ ተቀበልኩት ...ነገሩ ቀላል ባይሆንም ልረዳው እንደምሞክር ቃል ገብቼለት ጥቂት ተጫውተን ተለያየን
ይገርማል ...እኔ እኔነቴን ፍለጋ መከራዬን ሳይ ጂያሎ ወንድሙን እንዲማርለት ነገ ሰው ሆኖ በሱ ጫንቃ ላይ ብቻ የወደቀውን የቤተሰቦቻቸውን ችግር እንዲጋራው ወደዚህ አመጣውና ...
ቤት ፈልጌ እንድከራይለትና ያለኝን የቁልፍ ሰዎች እውቂያ ተጠቅሜ ት-ቤት እንዳስገባው በጓደኝነታችን ውለታ ለመነኝ ...እኔ እሺ እሞክራለሁ አልኩት ...
ጂያሎን እስከ ቢራ ቤቷ በራፍ ድረስ ሸኝቼ ወደ ቦታዬ ከመመለሴ ፕሮፌሰሩ ፒፓቸውን እየሳቡ በትንባሆ የጭስ ጉም ተሸፍነው ሲገቡ አየዋቸው ...እሳቸውን ሳይ የቀኝ እጄን ወደ ሱሪዬ ኪስ ከትቼ ያቺን ቁራጭ ወርቅ አወጣሁና አየኋት ....ዛሬ ቁርጥ ነው ፍርጥርጥ አድርጌ አወራቸዋለሁ ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Apr 03, 2008 10:26 am

አቤት የኔ ነገር በራሴ ችግር ተወጥሬ ዛሬ የጥንቱ አስተማሪዬ የዛሬው የቢራ ቤት ጓደኛዬ የጡረተኛው ሽማግሌ ፕሮፌሰር የልደት ቀን መሆኑን እንኳን ዘነጋሁት
ይቺ ቀን የፕሮፌሰሩ የልደት ቀን መሆኑን የተረዳሁት ፕሮፌሰሩ ገና ወደ ቢራ ቤቷ ከመግባታቸው አንዲት ትንሽ ቆንጅዬ ሴት ልጅ እቅፍ አበባ ስታበረክትላቸው ነበር ...ከዛማ ምኑ ይጠየቃል ...ሁላችንምም እየተነሳን መልካም ጤንነትና የማታሱላን እድሜ እንዲሰጣቸው ከተመኘንላቸው በኋላ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሁላችንም የቢራ ቤቷ ሽታምጋስቶች በተሰበሰበ በተዋጣ ገንዘብ የተገዛላቸውን የጋራ የቢራ ቤቷ ስጦታ ተበረከተላቸው ...
ብዙም ሳንቆይ ለዛሬው የልደታቸው ቀን ማክበሪያ ወደተዘጋጀ ልዩ እልፍኝ ገባን ...አቀማመጣችን ቀደም ብሎ ተወስኖ ስለነበር ሁላችንም ስማችንን እየፈለግን ቦታ ቦታችንን ይዘን ተቀመጥን ....እኔም ከፕሮፌሰሩ በስተግራ በኩል ሁለት ወንበር እርቄ ተቀመጥኩ ...አልፎ አልፎ በእንግሊዘኛ ቢያወሩኝም ዛሬ ስለራሴ ጉዳይ ህልሜን አምላኬን ወራሽነቴን ላዋያቸው የነበረኝን ቁርጠኝነት ለሌላ ቀን አሸጋገርኩትና... የሽማግሌውን ደስታ በሙሉ ልቤ መካፈል ጀመርኩ ...
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests