ወራሽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Oct 19, 2008 8:33 pm

ሰፈር ስደርስ ...ገብሱ ኦኛ ራሺና ጨብሲ እና ሌሎችም ከሀገር ቤት በርበሬ ሽሮ ምናምን እንዲላክላቸው የሚፈልጉ ብዙ የሀገሬ ልጆች ጨብሲን ለመሸኘት ተሰባስበው አገኘዋቸው
ጨብሲ ነገ ለሊት ወደ ኢትዮጲያ በራሪ ነው ...ፕራግ...ፍራንክፈርት...አዲስ አበባ ...
እኔም እንግዲህ በቅርቡ ወደ ሀገሬ እንደምሄድ እያሰብኩ ወደ መሸኛው ፓርቲ ውስጥ ትልቅ አልኩ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ኦኛ ቱማና ገብሱ ቅልጥ ባለ የፖለቲካ ክርክር ውስጥ ገብተው ሲጨቃጨቁ አገኘዋቸው...ራሺም ከጎን ቆሞ ለገብሱ እያገዘ ያጨበጭባል ...
ዛሬ የቋጠርኳትን ወሬ ..የህልሜን ጉዳይ ልነግራቸው እየተጣደፍኩ ሰፈር ብደርስም ..ለዚህ አይነት ወሬ ዛሬ ቀኑ እንዳልሆነ ተረዳሁና ...የጨብሲን የመሼኛ ድግስ ማጣጣም ጀመርኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Sun Oct 19, 2008 8:49 pm

እንዲህ በነገብሱ የፖለቲካ ክርክር ሳልገባ አልፎ አልፎ ከጨብሲ ጓደኞች ጋር አጠር ያለች ሰላምታ እየተለዋወጥኩ እንደቆምኩ ገብሱ ከሩቅ አየኝ መሰለኝ ..በእሩጫ ቀረሽ እርምጃ መቶ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ
"ፓኑ ...ሚን ላምጣልህ ?"ሲል ጠየቀኝ
"አንድ ፓኬት ኒያላ "አልኩት ባጭሩ
እሺ ጌታው ብሎኝ ወደ ጓደኞቹ ተመለሰ
ከዚህ ቀደም አንድ የኛን ቡድን የሚቀርብ ሀበሻ ወደ ኢትዮጲያ ደርሶ ሲመለስ ..ሌሎች የተላከላቸውን በርበሬ ሽሮ ምናምን ሲቀበሉ ...ልጁ ለኔ አንድ ስቴካ ኒያላ ሲጃራ ከሁለት መጽሄቶች ጋር አንድ በቅርቡ የወጣ ልብ ወለድ መጽሀፍ ሲሰጠን ጨብሲ አይቶ ስለነበር እንዳው ለወጉ ምን ላምጣልህ?አለኝ እንጂ ...ጨብሲ ከሀገሩ ሲመለስ ምን ይዞልኝ እንደሚመጣ አሳምሮ የሚያውቅ መሰለኝ ..
ብቻ በዚህ መልኩ ምሽቱ አለፈና ....እኔ ለሊት በታክሲ ፕራግ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ወስጄ ሸኘሁት ....ገብሱ ስራ ገቢ ስለነበር ሊሸኘው አልቻለም ...እነዛ የበርበሬና የሽሮ ደብዳቤ ላኪዎች የጨብሲ ጓደኞችማ ልክ ደብዳቤያቸው በጨብሲ ቦርሳ ውስጥ መግባቱን እንዳረጋገጡ ነበር ወደማደሪያቸው የተፈተለኩት
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Dec 09, 2008 9:55 am

ይቺ ነገር እስቲ ወጣ ብላ የክረትምት ጸሀይ ትሙቅ ብዬ ነው ወደፊት ያመጣኋት ...
ታሪኩ ይቀጥላል
ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Dec 09, 2008 11:00 am

ጨብሲን ወደ ኢትዮጲያ ሸኝቼ በአውቶብስ ወደ ሰፈሬ ስመለስ ሳይታወቀኝ በትዝታ ባህር ውስጥ ገብቼ ተዘፈኩ ...አዎ ከዛሬ ብዙ አመታት በፊት ነበር ከሀገሬ ለከፍተኛ ትምህርት የወጣሁት ....ምክንያቱን ባላውቀውም በትዝታ ፈረሴ ስጋልብ በቀጥታ ወደዛች ታሪካዊ ቀን ገስግሼ ደረስኩና እራሴን በትዝታ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ "ቦሌ" አገኘሁት ..
አቤት የሸኚው መአት ...የሚሳሳቁ የሚላቀሱ ሰዎች እዚህም እዚያም ይታዩኛል ...እኔ ግን ሸኚም የለኝም ብቻዬን ነኝ ...ያነገትኳትን ሻንጣ ይዤ ዝም ብዬ እንደቆምኩ ...አንዲት ዘመዶቿ የሚላቀሱባት ኮረዳ ልጅ ቀረብ ብላኝ ..ተጓዥ ነህ ? ወዴት ነው የምትበረው ?ምናምን እያለች ብትጠይቀኝም ..ለምን እንደሆነ እንኳን ሳላውቅ ለጥያቄዋ ምንም መልስ ሳልሰጥ ብቻ እንዲያው ዝም ብዬ በዚያ በሚሳሳቀውና በሚላቀሰው ህዝብ ላይ አይኔን ተክዬ ቀረሁ ...ነገረ ስራዬ ያላማራት ጉብል በቆምኩበት ቦታ ጥላኝ ከሄደች በኋላ ነበር "አሁን ምን ነበረበት ያችን ውብ ጉብል የግዚያብሄር ሰላምታ እንኳን ባቀርብላት ኖሮ ብዬ ተጸጽቼ እራሴን የወቀስኩት ...
ብቻ እንዲህ በትዝታ ባህር ውስጥ ተዘፍቄ ስዋልል አውቶቡሱ የመጨረሻው ፌርማታ ላይ ደረሰና ወረድኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Dec 09, 2008 11:17 am

ሰፈር እንደደረስኩ ለገብሱ ስልክ ደውዬ ጨብሲ በሰላም መሄዱን ከነገርኩት በኋላ ከስራ ሲወጣ ላነጋግረው እንደምፈልግ ነግሬው ስልኬን ዘጋሁና በተመሳሳይ ሁኔታ ለኦኛ ቱማና ለራሺድም ደወልኩላቸው ...የቀጠሮ ቦታ ቀድሞ መነጋገር አያስፈልግም ሁሉም ያውቀዋል ...
ጓደኞቼ በስራ ሲዋከቡ እኔ ቤቴን ዝግቼ በዛች መከረኛ ህልሜ ላይ ማሰብ ማሰላሰል ጀመርኩ ...ከሁሉም በፊት በሰው አገር እንደ ጓደኛ አይደለም እንደወንድሞቼ ለምቆጥራቸውና ለምወዳቸው ብቸኛ ቤተሰቦቼ ችግሬን መናገር ወይም መከረኛዋ ህልሜ የፈነጠቀችልኝ ትንሽ ፍንጣቂ እይታ ላካፍላቸው እንደሚገባ እራሴን ካሳመንኩ ቆይቻለሁና ...ይቺኑ የህልሜን ፍንጣቂ እንዴት እንደማስረዳቸው ሳሰላስል ሳወጣ ሳወርድ የቀጠሯችን ሰአት ደረሰና ወደተለመደቺው የቤት ኪራይ የማይከፈልባት ቢሮዬ አቀናሁ ...
ቢራ ቤቷ ስደርስ ከቀጠሮው ሰአት ቀድመው ..ገብሱ ኦኛ እና ራሺድ በፕሮፌሰሩ የክብር ቦታ ዙሪያ ተቀምጠው አገኘዋቸው ....
ምንም እንኳን እኔ ሳልነግራቸው በፊት ያቺ ጨብራራ ዶክተር ስለኔ ቀድማ ለሽማግሌው ፕሮፌሰር ሹክ ማለቷ ቢታወቀኝም ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ሄጄ ለጓደኞቼና ለፕሮፌሰሬ የሚገባቸው ሰላምታ አቅርቤ ቢራዬን አዘዝኩና አብሪያቸው ዙሪያ ገጥሜ ተቀመጥኩ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby password » Tue Dec 09, 2008 11:49 am

ፓን ሪዚኮ wrote:ወይኔ ሰውዬው ...ለፍቼ ለፍቼ ....በላው ...


ይቅርታ እዚህ ዋናው ገጽ ስለገባሁ,

ፓን , እዚሁ የዋርካ ገጽ ላይ ነው እንዴ የምትተይበው?

እንዳሱማ ካረግህ መብላት አይደለም ቢቆረጫጭምህም አታሳዝነኝም....

እንዲህ አይነት ቁምነገር መጀመሪያ ''ዎርድ ፕሮሰሰር'' ላይ ተጽፎ, ''ሴቭ'' ከተደረገ በሁዋላ ነው ወደ ዋርካ .... እንዲህ አይነት ጽሁፍ በአንድ ቅጽበት በነበረህ ስሜት የሚመነጭ ስለሆን አንዴ ከጠፋ መልሰህ መጸፍ አይቻልምና ..........

በተረፈ ወራሽ ላጭር ጊዘ ስቶት የነበርውን መስመር እንደገና በመያዝ የቀድሞ ጣእሙን አምጥቶ ልብ ማንጠልጠሉን የቀጠለ ይመስላል... እየተከታተልኩ ነው.

አድናቂህ
ፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Dec 09, 2008 12:00 pm

password wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:ወይኔ ሰውዬው ...ለፍቼ ለፍቼ ....በላው ...


ይቅርታ እዚህ ዋናው ገጽ ስለገባሁ,

ፓን , እዚሁ የዋርካ ገጽ ላይ ነው እንዴ የምትተይበው?

እንዳሱማ ካረግህ መብላት አይደለም ቢቆረጫጭምህም አታሳዝነኝም....

እንዲህ አይነት ቁምነገር መጀመሪያ ''ዎርድ ፕሮሰሰር'' ላይ ተጽፎ, ''ሴቭ'' ከተደረገ በሁዋላ ነው ወደ ዋርካ .... እንዲህ አይነት ጽሁፍ በአንድ ቅጽበት በነበረህ ስሜት የሚመነጭ ስለሆን አንዴ ከጠፋ መልሰህ መጸፍ አይቻልምና ..........

በተረፈ ወራሽ ላጭር ጊዘ ስቶት የነበርውን መስመር እንደገና በመያዝ የቀድሞ ጣእሙን አምጥቶ ልብ ማንጠልጠሉን የቀጠለ ይመስላል... እየተከታተልኩ ነው.

አድናቂህ
ፓስ
ሰላም ሰላም ፓሱ...ሀሳብህ ይገባኛል ...ይሁንም እንጂ እኔ ጥሎብኝ ...ያው ጊዜና ሙድ ሲኖረኝ ዘመጣልኝን እዚቺው ቁጭ ብዬ ነው የምጫጭረው ...
መጽሀፍ ጽፎ የከበረ የለምና ..ቢያንስ ለቤት ኪራይ... ለቢራ እና ለሲጃራ የምትሆን ቤሳ ለመቃረም መሸቃቀል ግዴታ ነውና ...ከሽቀላ በተረፈች ጊዜ እዚቺው እጫጭራለሁ ...
ፓሱ በዚህ አጋጣሚ በድጋሚ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ከልቤ አቀርብልሀለሁ
ያንተው
ፓን
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue Dec 09, 2008 1:33 pm

እንዲህ ዙሪያ ገጥመን እንደተቀመጥን ....ደፍሮ ወሬ የሚጀምር ሰው ሲጠፋ ..ለምን አልገላግላቸውም አልኩና ሁለም ከትከሻው የማትለየውን የገብሱን ኖት ቡክ ሳብ አደረኩና ያ ጨበሬ ዶክተሬ ለማንኛውም ያዘው ብሎ የሰጠኝን የኔ ህልም የተቀረጸበትን ዲስክ ከኪሴ አወጣሁና በኮንፒውተሯ ውስጥ ከትቼ እንዲያዳምጡት ከፈትኩላቸው ...ሁሉም ስጋትና ሀዘን ፊታቸው ላይ እየተነበበ እኔ በሰመመን ስለ መከረኛዋ ህልሜ የቀባጠርኩትን ያዳምጡ ጀመር ...
ዲስኳ የቋጠረቺውን ወሬ ስትጨርስ ...
ፕሮፌሰሩ እዝን እና ትክዝ ብለው ሲያስተውሉኝ ቆይተው እንባ ያረገዘች የሽማግሌ አይናጨውን በመሀረባቸው ሊያልቧት መነጽራቸውን አወለቁ ...
ራሺና ገብሱ በጭንቀት አይናቸውን ወደ ጣሪያው ላይ ተክለዋል ..ኦኛ ቱማ ብቻ አይን አይኔን እያየ ...አይዞን ወንድሜ አይዞን ...እያለ ትከሻዬን ቸብ ቸብ እያደረገ አጽናናኝ ..
ምንም እንኳን ይቺ ህልም የሩቅ ትዝታ መሆኗንና ምንም እንዳልተፈጠረ ላስረዳቸው ብሞክርም ሳይሳካልኝ ቀረና ቢያንስ ወደ ሌላ ወሬ ብንገባ ብዬ ለሁላችንም ቮድካ አዘዝኩ ..
እንዲሁ ዝም እንደተባባልን የቮድካ መለኪያዎቻችንን አንስተን ለጤናችን "ናዝድራቪ"ተባብለን አጋጨንና ጨለጥናት ቮድካዋን ..
እንዲ ለሁላችንም በከበደ ዝምታ ውስጥ ተቀምጠን እንደተፋጠጥን ለረጅም ጊዜ ያላየነው ጓደኛችን ጨቅሌ መቶ ሲቀላቀለን ያ አስፈሪ ዝምታ ጠረጴዛችንን ለቆ ጠፋና ወሬው ተለውጦ ጨቅሌ እንዲህ ለረጅም ጊዜ የት ተሰውሮ እንደነበረ በተነሳ ወሬ መጫወት ጀመርን ...
ለግዜው ዘኔ ህልም ጉዳይ ለዛሬ ቢታለፍም የሰሞኑ የሁላችንም ዋና መነጋገሪያ ነጥብ እንደሆነ ሆላችንም ልባችን ያውቀዋል ...
እኔም እንግዲህ ካሁን በኋላ ጊዜ ሳላጠፋ ለጉዞዬ መዘጋጀት መጀመር አለብኝ ...ከሀገሬ ከወጣሁ እረጅም ጊዜ ሆኖኛል ...የሚቀበልም ሆነ የሚጠብቀኝ ምንም ዘመድ ወዳጅ የለኝም ..ያለኝ የቋጠርኳት ህልሜ ብቻ ነች
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Mar 13, 2009 11:20 am

ይቀጥላል
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby password » Wed Jul 02, 2014 11:57 am

ፓን ሪዚኮ wrote:ይቀጥላል


ፓን ይኖር ይሆን_???

የት ግቡ ዋርካዊያን...
እነ ዋናው, ትርንጎ... ሾተል... ትሩዝ... ስሊፒለስስ ... እንሰት... ዳሞት,,, ዛዙ.... እኒያ ያዋርካ ልብና ድምስሮች ሁሉ....
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Re: ወራሽ

Postby password » Sun Jan 05, 2020 8:58 pm

ፓኑ...
hny

"ወራሽ"
ምን ላይ ደረሰ?
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests