ሰፈር ስደርስ ...ገብሱ ኦኛ ራሺና ጨብሲ እና ሌሎችም ከሀገር ቤት በርበሬ ሽሮ ምናምን እንዲላክላቸው የሚፈልጉ ብዙ የሀገሬ ልጆች ጨብሲን ለመሸኘት ተሰባስበው አገኘዋቸው
ጨብሲ ነገ ለሊት ወደ ኢትዮጲያ በራሪ ነው ...ፕራግ...ፍራንክፈርት...አዲስ አበባ ...
እኔም እንግዲህ በቅርቡ ወደ ሀገሬ እንደምሄድ እያሰብኩ ወደ መሸኛው ፓርቲ ውስጥ ትልቅ አልኩ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ኦኛ ቱማና ገብሱ ቅልጥ ባለ የፖለቲካ ክርክር ውስጥ ገብተው ሲጨቃጨቁ አገኘዋቸው...ራሺም ከጎን ቆሞ ለገብሱ እያገዘ ያጨበጭባል ...
ዛሬ የቋጠርኳትን ወሬ ..የህልሜን ጉዳይ ልነግራቸው እየተጣደፍኩ ሰፈር ብደርስም ..ለዚህ አይነት ወሬ ዛሬ ቀኑ እንዳልሆነ ተረዳሁና ...የጨብሲን የመሼኛ ድግስ ማጣጣም ጀመርኩ