ፈገግ...ፈገግ....ፈገግታ...ላንድ..አፍታ!!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ፈገግ...ፈገግ....ፈገግታ...ላንድ..አፍታ!!!

Postby መልከጻዲቅ » Tue Apr 15, 2008 2:39 am

ሰላም ውድ ዋርካውያን 8)
ይህች ቤት የሳቅና የፈገግታ ቤት ናት :lol: :lol: :lol: ያነበባችሁትን የሰማችሁትን አስቂኝ ቀልዶች አምጡአቸውና ትንሽም ቢሆን ህይወታችንን እናጣፍጣት... :lol:
ቀልድ የህይወት ማጣፈጫ ቅመም ናት ይባል የለ....!! በሉ ያላችሁን ጣል ጣል አድርጉባት::
ካነብብኩት አንድ ጀባ ልበል.....

ልጃገረድ; ""አንተን ባየሁ ቁጥር አንድ ትልቅ ሰው ይታየኛል""
ተወድጃለሁ ባይ; "" ውይ ታድዬ የኔ ቆንጆ ማነው.. :?: ""
ልጃገረድ; "" ቻርልስ ዳሪውን""
ተወድጃለሁ ባይ; ትንሽ ድምጹ ጎርነን እንደማለት እያለ ""እንዴት ሆኖ ነው እሱ ትዝ የሚልሽ ""
ልጃገረድ; "" ሰው ዝንጀሮ ነው የሚል ሀሳብ ያቀረበው እሱ ነበራ...."" :oops:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Tue Apr 15, 2008 12:38 pm

ሌላ አንድ ካነበብኩት ልጨምር......

ሁለት ጔደኛሞች ምግብ ቤት ይገባሉ:: አስተናጋጁም የሚታዘዙትን ጠይቆ አንድ የበግ ቀይና አንድ አልጫ እንዲመጣላቸው ያዙታል:: ታዲያ የአልጫው ወጥ ስጋ ብጥቅጥቅ ያለበት አንደኛው አስተናጋጁን ጠርቶ
""ስማ እንጂ... :!: ""

አስተናጋጅ "'አቤት ምን ጎደለ :?: ""

""ለመሆኑ በጔ በቢላ ነው የታረደችው ወይስ በፈንጂ ነው የተመታቸው :?: ""
:lol: :lol: :lol:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ማህለይ » Tue Apr 15, 2008 1:30 pm

ቀልድ በቀልድነቱ ለፈገግታ ብቻ ይወሰድልኝ

ኦሮሞ 1 የተባለ ሰው ሻይ ቤት ገብቶ ዳቦ በሻይ እያጠቀሰ ሲበላ ስልኪ የሚባል ወያኔ ጥግ ቁጭ ብሎ ደረቅ ዳቦ እየገመጠ ሲቸገር ኦሮሞ 1 አይቶት አዘነለትና...

ኦሮሞ 1:- "ሲማ አንቴ ሰው ለሚን ኢንዳዚ ኢያጤኬስክ ኢንዳኔ አቲበላም?"

ይለውና አበላሉን በራሱ ሻይ እያጠቀሰ አሳየው አብረው በኦሮሞ 1 ሻይ እያጠቀሱ እንዲበሉ ይጋብዘዋል:: ስልኪም ግብዣውን ተቀብሎ ጠጋ ብሎ በኦሮሞ 1 ብርጭቆ ሻይ እያጠቀሰ ሲበላ በጣም ጣመውና ዳቦውን ሻይ ዉስጥ ነክሮ ብዙ አቆይቶ ኖሮ ግማሽ ሻይውን በዳቦው ይዞበት ይወጣል....ከዛም ኦሮሞ አንድ በሻይው በትልቁ መጉደል ተናዶ

ኦሮሞ 1;- ኢንዴ ኢንዴ...ድሮም እናንቴ ቲኒሽ ሲሰጧቹ ሌላ ቲሰርቃላቹ.....! ኢኔ አጥቂስ አልኩህ ኢንጂ ዘፍዝፍ አልኩህ ኢንዴ..? በል ቶሎ ዳቦውን ጪመቅ...ቶሎ የወሰድከውን ሻዪ ጪመቅ.....አለው ይባላል
ማህለይ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1067
Joined: Wed Sep 26, 2007 8:13 pm

Postby ፉፊ » Tue Apr 15, 2008 4:38 pm

አንድ ሳዋ ሊሰለጥን የሄደ ኤርትራዊ እንግሊሽ ክላስ ላይ ስለተነባቢና አናባቢ እየተማሩ እያለ አንዳንድ ቦታ ላይ በጽሁፍ K ብትኖርም ግን አትነበብም ለምሳሌ knife ሲነበብ ናይፍ ነው የሚባለው ናይት ሲጻፍ knight ነው እያለ ሲያስተምራቸው ቆየና ሰውየው ሰውየው ይህን ከሰማ በሀላ መምህር ጥያቄ አለኝ እሞ ንክፍላይ ሀወይ ፍላይ ክንብሎ ዲና(እና ለክፍላይ ወንድሜ ፍላይ ልንለው ነው) ብሎ ቁጭ.
ፉፊ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 209
Joined: Tue Jan 11, 2005 12:06 pm
Location: united states

Postby meote » Tue Apr 15, 2008 4:54 pm

ፉፊ wrote:አንድ ሳዋ ሊሰለጥን የሄደ ኤርትራዊ እንግሊሽ ክላስ ላይ ስለተነባቢና አናባቢ እየተማሩ እያለ አንዳንድ ቦታ ላይ በጽሁፍ K ብትኖርም ግን አትነበብም ለምሳሌ knife ሲነበብ ናይፍ ነው የሚባለው ናይት ሲጻፍ knight ነው እያለ ሲያስተምራቸው ቆየና ሰውየው ሰውየው ይህን ከሰማ በሀላ መምህር ጥያቄ አለኝ እሞ ንክፍላይ ሀወይ ፍላይ ክንብሎ ዲና(እና ለክፍላይ ወንድሜ ፍላይ ልንለው ነው) ብሎ
ቁጭ.


ስላም ስላም አስንቺ አይጥ አለሽ? ስምሽን ሳየው ግዜ ነው ጥልቅ ያልኩት አትጥፊ እስቲ ..........
LIFE IS A WOUNDERFUL THING.....
meote
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 443
Joined: Sat Apr 22, 2006 8:08 pm
Location: warka

Postby ሊስትሮው » Tue Apr 15, 2008 5:14 pm

meote wrote:
ፉፊ wrote:አንድ ሳዋ ሊሰለጥን የሄደ ኤርትራዊ እንግሊሽ ክላስ ላይ ስለተነባቢና አናባቢ እየተማሩ እያለ አንዳንድ ቦታ ላይ በጽሁፍ K ብትኖርም ግን አትነበብም ለምሳሌ knife ሲነበብ ናይፍ ነው የሚባለው ናይት ሲጻፍ knight ነው እያለ ሲያስተምራቸው ቆየና ሰውየው ሰውየው ይህን ከሰማ በሀላ መምህር ጥያቄ አለኝ እሞ ንክፍላይ ሀወይ ፍላይ ክንብሎ ዲና(እና ለክፍላይ ወንድሜ ፍላይ ልንለው ነው) ብሎ
ቁጭ.


ስላም ስላም አስንቺ አይጥ አለሽ? ስምሽን ሳየው ግዜ ነው ጥልቅ ያልኩት አትጥፊ እስቲ ..........ህምምምምም ..........
......... አይጧ የትኛዋ ትሆን ... ጥልቅ ባይዋ ወይንስ .... :wink:
ሊስትሮው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 233
Joined: Tue Feb 03, 2004 11:30 pm

Postby ፉፊ » Tue Apr 15, 2008 5:17 pm

የኔ ቆንጆ አለሁልሽ ምነው እንዲህ ጠፋሽብኝ ውድድድድድድድ

በይ ባለቤቱ እንዳይቆጡ በጋሮ ብቅ በይ እናወጋለን
ፉፊ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 209
Joined: Tue Jan 11, 2005 12:06 pm
Location: united states

Postby ocean12 » Wed Apr 16, 2008 1:18 am

ዋርካ ባሁኑ ሰዓት የሚያስፈልገው ክፍል....
እዚህ የማቀርበው ቀልድ ባላውቅም አንድ ዋርካ ስመጣ የምገባበት ክፍል አገኘሁ......ከጦርነቶቹ ሽሽት.....
መልከጻዲቅ ምስጋና ይግባህ..... :D :D
Visit EthioForum
ኢትዮፎረም, News, Music, Love, Politics
http://ethioforum.ethiopiaforums.com
http://AddisNews.net
ocean12
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 495
Joined: Thu Jul 08, 2004 6:56 pm

Postby መልከጻዲቅ » Wed Apr 16, 2008 3:41 am

ለውድ የዚህ ቤት ተሳታፊዎች በሙሉ ሰላምታየ ይድረስ: 8)

ማህልይ ለተሳትፎህ አመሰግናለሁ:: በባህላችን ጉርሻም ጥፊም ይደገማልና ሌላ አንድ ጀባ በለን:: አትጥፋ:: 8)

ለፋፊ ቀልዷ አስቃኛለች ጽቡቅዩ:: :lol: እስኪ ጨመር ጨመር አድርጊልን ትርጉሟንም አትርሺ 8)

Meote & ሊስትሮ 8) እዚህ ቤት የገባ ሁሉ አንድ ቀልድ ጣል አድርጎ ይሄዳልና በሚቀጥለው ቀን ባዶ እጃችሁን እንዳትመጡ :lol: :lol: አለበለዛ Door price እናስከፍላለን:: :lol:

ኦሽናችን ጥሩ ብለሀል:: :lol: የዚህ ቤት "Motto" ቀልድ የህይወት ማጣፈጫ ቅመም ናት የሚል እንዲሆን ነው የኔም ምኞት:: ምንም ይሁን ምን ትንሽ ፈገግ የሚያደርግ ነገር ከለጠፍን ለሌላው የደስታ ምንጭ ልንሆን እንችላለን ብዬ አስባለሁ:: እናም በሚቀጥለው ከዌብ ሳይትህም ላይ (www.freewebs.com/ethiopians) ላይ ፈልገህ ይዘህ ና :lol: አመሰግናለሁ:: 8)

አንድ ካነበብኩት ጀባ ልበላችሁ::

ገንዘብ ማውጣት የማይወድ ቌጣሪ ንፉግ ቆንቌና እጁ የማይፈታ ኪሱ የማይፈታ ግንባሩ የማይፈታ ባጠቃላይ ሁለንተናው የማይፈታ አንድ ሰው ነበር:: :lol: ታዲያ አንዴ ጉንፋን ያመውና ከሱ በትንሽ ሜትር ራቅ ብሎ የሚኖር ጎረቤቱ ሀኪም ነበርና ወደ ስራው ሲወጣ ጠብቆ ሰላምታ ከተለዋወጡ በሆላ
"እንደው አንድ ጥያቄ ነበረችኝ...ይላል..."ቆንቌናው በሽተኛ::

"ጠይቀኝ ምን ችግር አለ :?: " ሀኪም ጎረቤት ይመልሳል::

"ጉንፋን ሲይዝዎት ምን ያደርጋሉ ጌታው :?: "

"ህምም ጉንፋን ሲይዘኝማ....."አለና ቀጠለ ሀኪሙ " አስላለሁ" :: :lol: :lol:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መልከጻዲቅ » Sun Apr 20, 2008 2:10 am

እጄ የገባውን አንድ ቀልድ ላካፍላችሁ.. :lol:
እናት ወደ ኢመርንጀሲ ክፍል ስልክ ትደውላለች::
ዶክተር "" ሀሎ..""

እናት "" ልጄ እስክርብቶ ዋጠብኝ""

ዶክተር "" እርዳታ የሚሰጥ አምቡላንስ እንልክላችኌለን""

እናት "" አምቡላሱ እስኪመጣ ምን ላድርግ ታዲያ ""

ዶክተር "" እስከዚያው በርሳስ ጻፊ "" :lol: :lol:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby አክየ » Sun Apr 20, 2008 8:06 am

መልከጻዲቅ ደስ የሚሉ ቀልዶች ናቸው ቀጥልበት አንች ፉፊ አለሽ እንዴ በአገር ምነው ጠፋሽ ......... ናፈቅሽኝ ከምር

እስኪ ባዶ እጅ የማይወጣ ከሆነ ባያስቅም አንድ ልበል

ሰውየው መጠጥ ቤት ቁጭ ብሎ እየጠጣ ነው መሀል ላይ ይህ ሰውየ ሞቅ ሲለው ሽንቱ ይመጣበት እና ሽንት ቤት ለመሄድ ፈልጎ መጠጡን ይጠጡብኛል ብሎ በመስጋት ወረቀ ላይ ተፍቸበታለሁ ብሎ በወረቀት ጽፎ ያስቀምጥ እና ለመሽናት እንደሄደ አንዱ መጥቶ ያነበው እና መጠጡ ላይ ተፍቶ እኔም ተፍቸበታለሁ ብሎ ጽፎበት ይሄዳል ይህ ሰውየ ሲመለስ መጠጡ ላይ የደፈቀ ሳሙና የሚመስል ምራቅ ተከምሮ ያገኘዋል

ለሞራልም ቢሆን ፈገግ በሉ
"Say what you have to say in the fewest possible words"
አክየ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2615
Joined: Thu Jul 28, 2005 7:43 am

Postby መልከጻዲቅ » Mon Apr 21, 2008 2:36 am

ሰላም አክዬ 8) ስላቀረብከው ቀልድ አመሰግናለሁ: :lol: ሌላም ሲኖርህ እንግዲህ እቺን ቤት አትርሳት :lol: ስለመጠጥ ስታነሳ አንድ ቀልድ ትዝ አለኝ::
ስውየው ከልክ በላይ ጠጅ ልፎ ልፎ ሲወላገድ ከፊት ለፊቱ ካጋጠመው አንድ ዛፍ ጋ ይላተምና ይወድቃል:: ከወደቀበት ሲነሳ አንድ የነበረው ዛፍ ሁለት ሆኖ ይታየዋል:: በሁለቱ መካከል ለማለፍ ሲሞክር አሁንም ይጋጭና ይወድቃል:: ተመልሶ ሲነሳ ያው አንዱ ዛፍ አራት ሆኖ ይታየዋል:: አሁንም ለማለፍ ሲሞክር ተጋጭቶ ይወድቃል::እየወደቀ እየተነሳ ከቆየ በኌላ ""ወይኔ ሰውየው ምን አይነት ጫካ ውስጥ ነው የገባሁት :!: "" አለ አሉ:: :lol: :lol: ሰላም :lol:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby ዱዲ » Tue Apr 22, 2008 4:57 am

ስውየው ጣጤ ነቅሎ ወደ ቤቱ ሲሄድ አንድ ጠና ያለችና አንድ ወጣት ስትሪት ገርሎች ራቁታቸውን መንገድ ላይ ቆመው ይመለከታል ;-

ሰካራም :- ምነው የኔ ልጅ ዕርቃነ ስጋሽን ?
ወጣትዋ - አባባ ስስ ስለሆነ ነው እንጅ ለብሰናል እኮ...
ሰካራም ጠና ወዳለችው ይዞርና

ሰካራም :- አንችስ ምናለ ልብስ ብትለብሺ ?
ጠና ያለችው- ሰውዬ ምን ትጨቀጭቀናለህ ... ስስ ስለሆነ
ነው እንጂ ለብሰናል አልንህ እኮ ...

ሰካራም :- ታዲያ ምናለ እንደግዋደኛሽ ተኩሰሽ ብትለብሺ

መልካም ሳቅ
ዱዲ ነኝ
ዱዲ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 316
Joined: Fri Mar 05, 2004 8:41 am
Location: united states

Postby ኦሮሞ 1 » Tue Apr 22, 2008 3:37 pm

መልኬ......እንደምነህ ወንድማለም?

ቤትህን ልመርቅ ብየ ነው በዚህ ሳልፍ ብቅ ያልኩት :)

መልካም ጭውውት :)
ኦሮሞ 1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 110
Joined: Sat Aug 11, 2007 4:35 pm

Postby ቡናማ » Tue Apr 22, 2008 10:01 pm

ሰላም ወዳጆች
በጤናማ አያያዝ እስከተፈጠረና እስከተነገረ ድረስ ቀልድ ቁም ነገርም ነው-አስተማሪ አዝናኝና አስደሳች::
ይሔም ከጠቀመ እንግዲህ እንካችሁ!

የእውነቱን የሰከረ ሰውዬ ነው-ቤቱ ደርሶ ቁልፉን በመከራ አግኝቶ ከፍቶ ሊገባ ሲታገል ፖሊሶች በድንገት ይደርሱና ሁኔታውን ከተረዱ በኋላ እንደምንም ረድተውት ደጋግፈውት ወደውስጥ እንዲዘልቅ ያግዙታል::
እርሱ ግን መልካም ያደረጉለትን ፖሊሶች እንዲሁ ከበር ሊመልሳቸው ስላልፈለገ ቤቱን እያዙዋዛረ ያስገበኛቸው ይጀምራል::
"ይህ የምታዩት...ስራ ክፍሌ ...ይህ ደግሞ መታጠቢያ ቤታችን..." እያለ እየቀጠለና እየቀጠለ ሁሎች ክፍሎቹን ካስጎበኛቸው በኋላ መኝታ ቤቱንም ሊያሳያቸው ወዶ ይዟቸው ይገባል...
""እ እ ይሄ መኝታ ቤቴ ነው...ያቺ አልጋው ላይ የተኛችው ባለቤቴ..ናት-ከጎኑዋ---ተኝቶ..ያለው-ም....እኔ ነኝ!..."ብሎት አረፈው::
የባልን እግር መውጣት እየጠበቁ የጎን አታኚ የሚያሻቸው አንዳንድ ሚስቶች እንዲህን መሳይ ገርና ተላላ ባል ይስጠኝ ብለው ቢፀልዩ ሳያዋጣቸው ይቀራል?

በወዳጅነት እንቀጥል
ቡናማ
ቡናማ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Nov 29, 2004 1:53 pm
Location: germany

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests