ፈገግ...ፈገግ....ፈገግታ...ላንድ..አፍታ!!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby መልከጻዲቅ » Fri Nov 12, 2010 6:48 pm

አለን አለን.. 8) ሰላም ለሁላችሁም በተለይ ቀልዱ ተዝቆ ለማያልቅበት ለመላጣው ወንድሜ.. መቼም ቀልድ በጸጉርህ ልክ ነው. :D
አንድ ቀልድ ጣል ላድርግ
ሴትየዋ ቤንዚን አልቆባት መንገድ ዳር ቆማ ሁለት ሰዎች ሲያልፉ " እባካችሁ እርዱኝ ..እስከሚቀጥለው ማደያ ድረስ መኪናዬ ግፉልኝ " ትላቸዋለች:: እነሱም መግፋት ጀምረው ቡዙ እንደሄዱ አንደኛው መግፋቱን አቁሞ " ቤንዚን ማደያውን እኮ አለፍነው ለምን አልገባሽም ?' ቢላት እሷም መልሳ " አይ እዚህኛው ማደያ ከሚሰራ ሰው ጋር ባለፈው ቤንዚን ልገዛ ስመጣ ባይኑ እስክወጣ ስለተከለኝ የሚቀጥለው ማደያ ብሄድ ይሻላል ብዬ ነው " አለችው:: ዘመናይዋ ! :D ይሄ ፈገግ ካላደረገ ቪዲዮ ፈላልጌ ከች እል ይሆናል . 8)
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby መላጣ » Wed Nov 17, 2010 11:24 am

ሰለሞን ተካልኝ አገር እንደገባ ከወያኔ ቆንጆ ሚስት ትልቅ ቪላ ትልቅ መኪናና መልካም ሥራ ይቸርለታል:: በዚህም ተደስቶ ስለቅንድብ ማማር በመዝፈኑ ያልተደሰተው መሌ የነበረውን ሁሉ ነጥቆ ያባርረዋል:: በነገሩ በጣም ያዘነው ሰለሞን አንገቱን ደፍቶ ከተማ ለከተማ ሲዟዟር ድንገት አንድ ቀን ባደረገው ድርጊት እየተፀፀተ ሰውና አገር ጉድ ከሚለኝ እራሴን ላጥፋ ብሎ በማሰብ ወደ እንጦጦ ጫካ ሲያመራ ድንገት አቡኑን ለብቻው ያገኘዋል:: ምነው ሰለሞን ያዘንክ ትመስላለህ? ምን ሆነህ ነው? ብሎ ሲጠይቀው አይ መለስ የሰጠኝን ሁሉ ወርሶ አባረረኝ ይኸው ድህነት ከሚጫወትብኝና የሰው መሳቂያ ከምሆን እራሴን ላጠፋ ነው ይለዋል:: አባ ጳውሎስም ይህን ከምታደርግ ፍላጎትህ እንዲሟላልህ እኔ እረዳለሁ ንገረኝ ፍላጎትህን ይለዋል:: ሰለሞንም እሺ ሚስቴም ቤቴ መኪናዬም ሥራዬም እንዲመለሥልኝና አንድ ሚሊዮን ብር በባንክ ሂሳብ ቁጥሬ እንዲገባልኝ ነው ፍላጎቴ ይለዋል:: አይ መልካም ይሄማ ቀላል ነው ሰኞ ሁሉ ነገር ይደረግልሀል ግን ይህ እንዲደረግልህ የምጠይቅህን መፈፀም አለብህ ይለዋል:: ሰሌም በኃሳቡ በመስማማት ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ ሲለው ሱሪህን አውልቅ ሲለው እንዴ መንገድ ዳር ሲለው ግድ የለም አድርግ አድርግ አለበለዚያ ታጣለህ ሲለው ሰሌም እሺ ብሎ ሱሪውን አውልቆ ያፈነድዳል ጳውሎስም ይሰካል:: ከዚያ የደነቀው ጳውሎስ ለመሆኑ ሰለሞን እድሜህ ስንት ነው? ብሎ ሲጠይቀው 47 ይላል ታዲያ እንዴት አንተ ጳውሎስን ታምናለህ ብሎ ጉድ አረገው ይባላል::
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መልከጻዲቅ » Sat Nov 20, 2010 4:36 pm

ሰውየው ሙሉ ሱፍ ልብስ በርካሽ ገዝቶ ትንሽ ከለበሰው በኌላ አሳጥቦ ሲለብሰው ኮቱም ሱሪውም በጣም አጠረው:: የልብሱን ማጠር ለማሳየት ሱፉን ለብሶ ወደገዛበት ሱቅ ሄደና ባለሱቁን በንዴትና በቁጣ እያየ ሊናገር ሲዘጋጅ ...ልብስ ሰፊው ፈጠን አለና
"ቆይ ቆይ ...የኔ ወንድም ባለፈው እዚህ መጥተህ ሙሉ ልብስ የገዛሀው አይደለህም እንዴ?' ሲለው..ሰውየውም " የባሰ እየተናደደ አዎ! እኔ ነኝ" አለው
አጅሬም ልብስ ሰፊ "" ወይ ጉድ ይገርማል..በጣም ረዘምክ " አለው::
:lol:

ሙዚቃ... 8)
http://www.ethiotube.net/video/9098/Com ... eje--Habte
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby feredewnetu » Sun Nov 21, 2010 7:17 pm

ሰላም መልኬ ና ታዳሚዎቹ
ሽማግሌው የስፕርም ካውንታቸውን ለመለካት ህኪሙ ሳምፕል አንዲያመጡ ብልቃጥ ይስጥና ቀጠሮ ስጥቶ ያስንብታቸዋል:: ሽሜውም በቀጠሮ ቀን ህኪሙ ጋ ይቀርባሉ ህኪሙም በብልቃጡ ባዶ መሆን በማዘን ምነው ይላቸዋል:: ሽሜውም አይ ልጄ በግራ አጄ ብል ምንም በቀኜ ብል ምንም ከዛ ለሚስቴ ስጥቼ በግራ በቀኝዋ ብላም በአፍዋ ብትሞክር ምንም አልሆነም ከዛ ቢቸግረን ጎረቤቶቻችንም ጠይቀን አነሱም አንደኛ በግራ በቀኝ አጃቸው ከዛም በአፋቸው ሞክረው ብልቃጡ አልከፈት ስላለ ነው ብለው አርፍ::
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

Postby ወዲ-ፍቃዳ » Tue Nov 23, 2010 9:45 am

አክየ wrote:.....<<<<< አንድ በጣም ያረጀች ሴትዮ ናት በጣም ያረጀች መንገድ ላይ እየዞረች ትለምናለች ከሩቅ አንድ ላይ ተሰብስበው ወሬ የሚያወሩ ወጣቶች ነበሩ አንድ ላይ ሁነው ያወራሉ እነዚህ ወጣቶች ይህችን አሮጊት ሴትዮ ከሩቅ ይመለከቷት እና ........ አይ አንተ እግዚአብሄር እስኪ አሁን የ አሁንን ወጣት ወጣቱን በሞት ከምትቀስፍ እስኪ እንደዚች ያለች ሴትዮ ከምትሰቃይ ለምን አያስርፋትም እያሉ ሲወያዩ ሳሉ ይህች አሮጊት ወጣቶች ካሉበት ቦታ በመድረስ

አሮጊቷ :::-------- ልጆቸ ስለ ድንግል ማ.ር.ያም ብ.....ላ..ች .....ሁ የኔ ልጆች ት.....ጸ...ድ..ቃ....ላች......ሁ ያላችሁን ስጡኝ እያለች (በተንተባተብ አማርኛ) ትለምናቸዋለች


ወጣቶችም አስርም ሀምሳም አንድ ብርም ምናምን አድርገው አጠራቅመው ከሰጧት በሗላ ከ ወጣቶች አንዱ ቀደም ይልና ይጠይቃታል

ወጣቱ .......... እማማ

አሮጊቷ ........... አቤት የኔል ልጅ

ወጣቱ ....... አሁን ይህንን የሰጠንዎትን ገንዘብ ምን ያደርጉታል ???

አሮጊቷ ............ ለእናቴ እሰጣታለሁ :lol: :lol:

ጭራሽ እናታቸውም አለሽ :lol: :lol:

አክየ የእናት ካለ እነ ደሞ የአባቶች ጀባ ልበል
የ 80 ዓመት ሽማግሌ በራቸው ደጃፍ ተደግፈው እጃቸው ግንባራቸው አስደግፈው
ባንደኛው እጃቸው ኢየተናፈጡ ይንደህጻን ያለቅሳሉ, ያያያያያያ.... እያለ.
ሁኔታቸው ያሳዘንዋቸው መገደኛ, ''ምን ሁነው ነው አባባ'' ሲሉ ይጠቅዋቸዋል,
ሽማግሌዉም ''ኣባየ መታኝ እእእእ...'' በማለት ማልቀሱን ቀጠለ.
ብዚህ ግራ የተጋቡት መንገደኛ ነገሩን ለማረጋገጥ ወደ ቤቲ ሲገቡ በርግጥ ሌላ ሽማግለ አገኙ.
ዒሁዒሁኢሁ እያሉ ይስላሉ. ''ኣባባ እኙሁ አባት ምን ሁነው ነው የሚያለቅሱ?'' በማለት ይጠይቃሉ,
''ያል ልጁ ነው ? ወራዳ ያልተቀጣ, አያቱ ዉሀ ሲጠኝ ሲለው አይሰጠው, አይላክ እምቢ አለ ገርፍኩት ቀጣሁት::
ወዲ-ፍቃዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Thu May 13, 2010 10:30 am
Location: Sudan

Postby ወዲ-ፍቃዳ » Wed Nov 24, 2010 7:04 pm

"" ይሀውልህ እንግዲህ ንሴብሆ ወአይረከብነ ውእቱ ዘአቅመነ ይላል:: ይህ ማለት ሰው የማይችለውን ሸክም አይሰጠውም ሲል ነው:: እናም በውነቱ የሆነ እንደሆነ አነተም የምትችለውን ነው የተሰጠህ ገሀነምም ቢሆን አሁን ከዚህ ከምትሰራው የፉርኖ ጋገራ የከፋ አይደለም:: ረቂቀ መለኮት በማይታወቅ ሚስጥራቸው የገሀንምን ኑሮ በዳቦ ጋገራው በምኑ በምኑ እያሉ ጥሩ አላምደውሀል:: አይዞህ የኔ ልጅ ምንም አትሆንም ትችለዋለህ ገሀነምም ከዚህ የከፋ አይደለም:: "" ብለው አባ ሸኙት አሉ::
መልካም ምሽት:: 8)[/quote]

የቄስ ነገር ከተነሳ የሰማሁት ላካፍላቹህ
አንዲት ሴተኛ አዳሪ የነፍሱዋን ነገር አሳስቡዋት ወደ ነፍስ አባታዋ ትሄዳለች.
የነፍስ አብትዋ ለሆዱ ያደረ በጣም ስስታምይ ይሆነ ነገር ነበር.

ሴትየዋ አባት ነብስዋን ግብረሰላም (ለ አባትነብስ የሚደረግ ድግስ) አድርጋ ጋበዘቺው.
ዱሎት, ቀይ ወጥ ከነቕልጥሙ, አልጫ, ጎረድ ጎረድ ጠላ ጠጅ የቀር ነገር የለም.
ይብሉ አባባ እያለች ማጉረስ ነው የቀራት. በዚህ ጊዛ መናዘዝ ጀመርች
''አባቴ እዝጊአብሄር ቡዙ ሀብት ሰጥቶኛል ይመስገነው, ግን ይህን ሀብ ያጠራቀምኩት ቀይን እና ጥቁሩን ጎበዝ እያገላበጥኩ ነው ያገኘሁት ገንዘብ ነው.
ይሄን ነገር ደሞ ለፍሴ ያሳስበኛል'' ብላ ትናዘዛለች, ቄሱ ዝም ብሎ ማግበስበስ ነው መስል የለም.
''አባባአልስሙኙም እንዴ በማለት ትድግምላቸዋለች,
''ሥሚ ልጠይቅሽ ቀዩን እና ጥቁሩን ስታገላብጪ ያልብሻል አይልብስሺም ??''በማለት ይጠይቅዋታል
''ኤንዴ አባባ ላብ በላብ ነው እንጂ'' '"
በቃ መጽሓፍ ቁዱስ በላብህ ብላ ነው የሚለው"" አለቀ ብልዋት እርፍፍፍ
ወዲ-ፍቃዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Thu May 13, 2010 10:30 am
Location: Sudan

Postby መላጣ » Wed Nov 24, 2010 7:09 pm

አንድ አዛውንት የጎረቤታቸውን ሴት ይወዱና ስጭኝ እያሉ ሲያስቸግሩዋት እሷም እምቢ ስትል ሰውየውም ተስፋ ሳይቆርጡ ሲጠይቁ አንዴ ይሳካላቸውና ሰትየዋ እሺ ብላቸው አንጎዳጉደው ከወጡ በኃላ ሰውየው የገጠማቸውን እንዲህ ብለው ይገጥማሉ::

ዓመት ሁለት ዓመት የለፋንብሽ
ገብተን አየንልሽ ቤተ ሰፊነሽ::

ይህን ሰምታ የከነከናት ሴትዮም እንዲህ ብላ ትመልሣለች

እዩልኝ ስሙልኝ ይህን ስመ አጥፊ
ምሶሶ ቢቀጥን አለኝ ቤተ ሰፊ::

ድሮ ጥንት የመጠቃቂያ ዘይቤው ይህን ይመስል ነበር ለማለት ነው:: :)

ወደ ጂማ ተጉዤ ያገኘሁትን አዲስ ሙዚቃ እንድታዳምጡልኝ እጋብዛለሁ:-
http://www.diretube.com/ermiyas-aschale ... c6c79.html
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ዮሲ ዮባ » Fri Nov 26, 2010 6:30 pm

መቼም ባያስቅም አንድ ጀባ ልበላችሁ
ልጅ ሁል ጊዜ ሽንቱ ሲመጣ ሽንቴ መጣ እያለ አባቱን እንግዳ ፊት ቢያሳፍረው ልጄ ሰው ፊት ሽንቴ መጣ አይባለም ፉጨቴ መጣ ነው የሚባለው አለውና በዚህ ተስማምተው ፉጨቱ ሲመጣ አባትም እያስተናገደ ጥቂት ጊዚያት እንደቆዩ አባት ለቤተዘመድ ለቅሶ ከባለቤቱ ጋር ወደገጠር ሲሄዱ ልጁን አጎቱ ጋ አደራ ይሰጠዋል ልጅም አጎቱ ቤት ሲያድር ሌሊት ሽንቱ ሲመጣ
ልጅ አጎቴ ፉጨቴ መጣ
አጎት ዝም በል በለሊት አይፏጭም
ልጅ ኧረ አጎቴ ፉጨቴ መጣ
አጎት ነግሬሀለሁ ሲነጋ ታፏጫለህ
ልጅ አልቻልኩም ላፏጭ ነው
አጎት ቆይ ቆይ ና ወደዚህ ጠጋ በልና ሰው ሳትረብሽ ጆሮዬ ላይ አፏጭ
ልጅ እሰይ አመሰግናለሁ አጎቴ
ወይ ጊዜ
ዮሲ ዮባ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Wed Sep 23, 2009 8:18 pm

Postby መላጣ » Mon Dec 06, 2010 11:51 am

አንድ በጣም አስቀያሚ ወጣት ቆንጅዬና በጣም የሚወዳት ገርል አለችው:: ሁሌ በተገናኙ ቁጥር የኔ ፍቅር እወድሀለሁ አፈቅርሀለሁ የማምነውና የምመካበት ፈጣሪ አድሎኝ ብርሃኔን ቢመልሰው ያለምንም ጥርጥር አንተን ነው የማገባው ትለዋለች:: ለካስ ልጅቷ ዓይነ ስውር ነበረች: ይህን የሰማም ወጣት ለፈጣሪው ልመና አቅርቦ እሱም ሊያገባት እያቀደ እንዳለ ኃኪም ቤት ዶክተሯ ይደውልላትና ዓይን ስለተገኘ ባስቸኳይ እንድትመጪና ተለውጦልሽ ማየት እንድትችይ ትባላለች:: እሷም ወዲያው ሄዳ የተባለው ዓይን ተለውጦላት ማየት ትችላለች:: ከዚያም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅረኛዋን ስትመለከተው አስጠያፊነቱና አስቀያሚነቱ በጣም ስለቀነቀናት ለካ እንዲህ ዓይነት ነህ እንዴ? አንተንስ ብሞት አላገባም ትለዋለች:: በሁኔታው በጣም ያዘነው ወጣት እኔ ግን በጣም ነው የምወድሽ ሆኖም ውሳኔው ያንቺው ነውና አላስገድድሽም ግን የምነግርሽ "ዓይኖቼን ተንከባክበሽ በጥንቃቄ ያዢያቸው" አላት ምስኪኑ ወጣት ባጎረሰ እጁን ተነከሰ ማለት እንዲህ ነው: :(
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ሰባተኛው » Fri Dec 10, 2010 1:24 pm

ሰላም ለናንተ ይሁን ቀልደኞች እኔ እንኩዋን ቀልደኛ አደለሁም ግን አንዳንድ ቀልዶች አስታውሳለው እናም ጀባ ልበላቹ::

አንዲት ሴት ለ ሀላፊዋ በንዴት እንዲህ ትለዋለች

ሴት ልጅ: ይሄ አዲስ የተቀጠረው ልጅ ጸጉርሽ ሽታው ደስ ሲል ይበለኝ ?
ሀላፊ : ጥሩ ነው የተናገረሽ ታዲያ ምን አናደደሽ

ሴት ልጅ: እንዴ ድንክ እኮ ነው::

አለችው እላቹሀለው አጅሬ ድንክ ጸጉሯን እንዳያሸት አይደርስበትም አጠገቡ ያለውን አሽትቶ መናገሩ ነው::
ሰባተኛው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 26
Joined: Wed Nov 10, 2010 6:40 am

Postby ሰባተኛው » Fri Dec 10, 2010 1:34 pm

ሰላም ለናንተ ይሁን ቀልደኞች እኔ እንኩዋን ቀልደኛ አደለሁም ግን አንዳንድ ቀልዶች አስታውሳለው እናም ጀባ ልበላቹ::

አንዲት ሴት ለ ሀላፊዋ በንዴት እንዲህ ትለዋለች

ሴት ልጅ: ይሄ አዲስ የተቀጠረው ልጅ ጸጉርሽ ሽታው ደስ ሲል ይበለኝ ?
ሀላፊ : ጥሩ ነው የተናገረሽ ታዲያ ምን አናደደሽ

ሴት ልጅ: እንዴ ድንክ እኮ ነው::

አለችው እላቹሀለው አጅሬ ድንክ ጸጉሯን እንዳያሸት አይደርስበትም አጠገቡ ያለውን አሽትቶ መናገሩ ነው::
ሰባተኛው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 26
Joined: Wed Nov 10, 2010 6:40 am

Postby ሰባተኛው » Fri Dec 10, 2010 3:06 pm

አንድ ሰውዬ ስራ ሆኖ ወደ ቤቱ ስልክ ሲደውል አዲስ የ ሴት ድምጽ ይቀበለዋል

ሰውዬ : ሄሎ ማነሽ ደሞ አንቺ
ሴትዮ : ሰራተኛ
ሰውዬ : ሰራተኛ የለንም እኛ
ሴትዮ : አይ ዛሬ ጠዋት ነው እትዬ የቀጠሩኝ
ሰውዬ : እሺ እንግዲያውስ ባለቤቷ ነኝ :: አለች ለመሆኑ?
ሴትዮ : እ...እ መኝታ ቤት ከአንድ ሰውዬ ጋር ነበሩ:: ግን
ባለ ቤቷ ናቸው ብዬ ነበር

ሰውዬ በንዴት ይበግን እና ለሰራተኛዋ እንዲህ ይላታል

ሰውዬ :5000 ብር እንድሰጥሽ ትፈልጊያለሽ?
ሴትዮ : አዎን ምን ላድርግሎት?
ሰውዬ : ሽጉጤን ከ ቁምሳጥን መሳቢያ አውጥተሽ ያችን
ባለጌና ያንን ወራዳ ግደያቸው

ሴትዬዋ እሺ ብላ ስልኩን አስቀምጣ ሄደች:: ሰውዬው የ ጫማ ኮቴና አከታትሎ የሽጉጥ ተኩስ ይሰማል:: ከዛ ሰትዬዋ ተመልሳ መጥታ

ሴትዮ : ሬሳዎቹን የት ላርጋቸው?
ሰውዬ : መዋኛ ገንዳ ውስጥ ጣያቸው
ሴትዮ : የምን መዋኛ ገንዳ?
ሰውዬ : እ...እንዴ ይሄ ስልክ 112345 አደለም እንዴ?
ሰባተኛው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 26
Joined: Wed Nov 10, 2010 6:40 am

Postby መላጣ » Sun Dec 12, 2010 1:29 pm

ባል ሚስቱን ሁሌ እወድሻለሁ ይላታል በዚህ አዘውትሮ እወድሻለሁ የሚለውን ቃል መስማት የተሰላቸች ሚስት ፍቅርዬ? ለመሆኑ ምን ያህል ነው የምትወደኝ ብላ ስትጠይቀው ልክ እንደብር ነው የምወድሽ ይላታል:: በዚህን ጊዜ በመልሱ የተበሳጨች ሚስት ቀድሞውንም ሰምቻለሁ እናትህ አንተን ሲወልዱ አልወጣም ብለህ በምጥ ሲሰቃዩ አንድ የጎረቤት አዛውንት ቆይ እስቲ ብለው በሰሃን ሳንቲሞች አርገው ሲያንኮሻኩሹ ሰምተህ ፈትለክ ብለህ መውጣትህንና እናትህም ከስቃይ መገላገላቸውን የሰማሁት ገና ስተዋወቅህ ከቅርብ ዘመዶችህ ነው:: አንተ የብር ጠላት ሰው ለምኔ ብላ አረፈችው:: :lol:
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ሰባተኛው » Tue Dec 14, 2010 6:26 am

የዛኔ ሻእቢያ አስመራን የተቆጣጠረበት ግዜ ነበር:: እናም አንድ ታጋይ ሬድዮና ክላሽን ኮቩን ተሸክሞ የአስመራን ውበት እያደነቀ ይጓዛል በአጋጣሚ አንድ ረዘም ያለ ፎቅ ጋር ይደርስና ወደላይ አንጋጦ በመደነቅ ያያል (በርዝመቱ ማለት ነው) አንጋጦም አልቀረ መቁጠር ጀመረ 1,2,3 እያለ ሲቆጥር ያየው አንድ የአስመራ አራዳ ጠጋ ይልና ይቅርታ የኔ ወንድም በነፃ መቁጠር አይፈቀድም እናም ለ አንድ ፎቅ 1 ብር ትከፍላለህ ለመሆኑ ስንት ነው የቆጠርከው ሲለው ታጋዩ 3 ብቻ አለ እናም 3 ብር ከፈለ:: ልጁ ራቅ ብሎ ከሄደለት በኋላ አይ ጅሎ ከአስመራ ልጅ አራድነት የ ሳህል(ድሮ የነበሩበት ቦታ) አራድነት ይበልጣል 5 ቆጥሬ እያለው 3 ብዬ አታለልኩት ብሎ ተደሰተ::
ሰባተኛው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 26
Joined: Wed Nov 10, 2010 6:40 am

Postby feredewnetu » Sat Dec 18, 2010 8:27 pm

ማናጀሩ ወደ ቢሮ ሲገባ አንዱ ስራተኛው የማናጀሩን ጸሀፊ ጉልበቱ ላይ አስቀምጦ ከንፈርዋን ሲመጠምጥ ያገኝውና በንዴት ስማ አኔ አኮ ደመወዝ የምክፍልህ አንዲህ አንድታረግ አልነበረም ቢለው ጌታዬ አይ ይሄን በነጻ ነው የምስራው ለዚህ ደመወዝ አይከፈለኝም ብሎ መለስለት::
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests