መላጣ wrote:አቶ ባል ሳሎን ቁጭ ብሎ ቢራውን እየከሰከሰ ቲቪ ሲያይ ሚስት ከጓዳ ትመጣና እባክህ የተቃጠለውን የበረንዳውን አምፖል ቀይረው ትለዋለች:: ተናዶ ስታዪኝ የመብራት ኃይል ሰራትኛ እመስልሻለሁ እንዴ እምቢ ይላል:: ቀጠል አርጋም እሺ የመሰላሉን መቆሚያ አስተካክሎው ስትለው ሴትዮ ጤና የለሽም እንዴ ስታዪኝ አናጢ መስልኩሽ እንዴ በማለት ተበሳጭቶ እወጣልሻለሁ እሄዳለሁ ብሎ ባር ይገባና ቢራውን እየጠጣ እያለ ሁኔታው በጣም ይሰማውና እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝም የግዴታ ተመልሼ ልሂድና ልስራው ብሎ ቤት እንደደረሰ መብራቱም ተለውጦ መሰላሉም ተሰርቶ ሲያይ ውይ! ፍቅርዬ ማን ሰራው? ብሎ ሲጠይቃት ልክ አንተ እንደሄድክ አዝኜ በረንዳ ላይ እንደተቀመጥኩ የጎረቤታችን ያ ቆንጆ ልጅ መጥቶ ምነው አዘንሽ? ብሎ ሲጠይቀኝ ባለቤቴ ይህን አድርግ ብለው እምቢ ስላለኝ ተበሳጭቼ ነው ስለው አይ እንግዳው አንቺ ለኔ ሴክስ ስጭኝ ወይም ብስኩት ጋግሪልኝና እኔ ልስራልሽ ሲለኝ በዚህ ተስማማንና አደረገልኝ ስትለው መቼም ኬክ እንደጋገርሽለት ይገባኛል ሲላት "ስታየኝ ዳቦ ጋጋሪ እመስላለሁ እንዴ.. ስምህ ዴምሴ አገርህ ዴሴ ዴን የምታጠብቅ ዴዴብ" ብላው አረፈች:: :lol: :lol: :lol:
አለቃ ገብረሐና እና ወይዘሮ ማዘንጊያ
የወይዘሮ ማዘንጊያና የአለቃ ገብረሐና ጋብቻ ሥርቆሽና ጠብ የተደባለቀበት ነበር :: ከሁሉም በላይ ግን አለቃ ቀልድና ለዛ ያለው ጨዋታ ወዳድ ስለነበሩ ጠባያቸውም ሆነ ኩርፊያቸው ለዛቢስ አልነበረም ::
ታዲያ አንድ ቀን ከባለቤታቸው ጋር ለቅሶ ውለው በጣም ርቧቸው ይመለሳሉ :: ቤት እንደደረሱም "በይ እስቲ ቶሎ ብለሽ የምንበላውን አምጭለን" ብለው የሚበላ ሲጠባበቁ ማዘንጊያ ጓዳ ገብተው ቀለጡ :: አለቃ ነገሩ ገርሟቸው "ማዘንጊያ! ኧረ ማዘንጊያ!" እያሉ ሲጣሩ ማዘንጊያ በትልቁ ጎርሰው ኖሮ "አቤት" ማለት ተስኗቸው "እምም" አሉ :: አለቃም ነገሩ ገብቷቸው "ወላዲት አምላክ ! ከምኔው ድመት ሆንሽ !" አሏቸው ::
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Users browsing this forum: No registered users and 3 guests