ፈገግ...ፈገግ....ፈገግታ...ላንድ..አፍታ!!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዳጨው » Tue Aug 07, 2012 9:30 am

መላጣ ቀልዶችህ በጣም ይመቻሉ:: እስቲ እኔም አንድ ሁለት ልበል::

አንዲት ዝንብ ከናቷ ጋር በመላጣ ሰውዬ አናት ላይ እየተንሸራሽሩ ሳለ እናትየው እንዲህ አለቻት::

"አየሽ ይሄ ሜዳ እኔ ልጅ እያለው ቀጭን ለእግረኛ የሚሆን መንገድ እንጂ ጥቅጥቅ ያለ ደን ነበር" :lol:


ሚስት- ያን መቶ አመት የመኖር ጥበብ የሚለውን መፅሀፍ የት አደረስከው::
ባል- እናትሽ እንዳያነቡት ካዝና ውስጥ ቆልፌበታለው::

የልጆች ሞግዚት ለመሆን ለቀረበች ሴት የቀረበ ጥያቄ
"ለመሆኑ ስለ ልጆች በቂ ልምድ አለሽ"
'ከበቂ በላይ እንጂ እኔም እኮ ባንድ ወቅት ልጅ ነበርኩኝ"

መለስ ዜናዊ ለመሞት በትቃረበበት ሰአት ላይ ሊጠይቀው ከመጣ ጓደኛው ጋር ይጨዋወታል::
'እንግዲህ ከአምላክህ ጋር እርቅ ፈፅመህ ሴጣንን ለመዋጋት ተዘጋጅተሀል አይደል?' የሚል ጥያቄ አቀረበለት::

"በእርግጥ ከአምላኬ ጋር ተታርቄያለው, ይሁን እንጂ አሁን ማንም ላይ ጦርነት ለማወጅ አቅም ያለኝ አይመስለኝም::
ዳጨው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 209
Joined: Mon Apr 19, 2004 2:39 pm

Postby መላጣ » Tue Aug 07, 2012 10:58 am

ሁለት የባላገር ጓዶች መንገድ ቆመው እያወሩ ሳለ አንደኛው አንተዬ መሪያችን ኮበለለ አሊያም ሞተ ተብሎ ይወራል አልሰማህም እንዴ? ሲለው አንተዬ ሰምቻለሁ ከሄደም መንገዱን ጨርቅ ያርግለት አቦ! ብሎ ሲመልስለት ወዴትኛው መንገድ? ህይወቱ የኃጢያት ናትና ወደሲኦል ገብቶ ዳቢሎስ በሙቀጫ እንዲወቅጠው ብሎት እርፍ::
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Mon Aug 13, 2012 1:06 pm

አንድ ጀርመናዊ ወጣት በመንገድ ሲያልፍ ጓደኛውን ያገኝና ምነው ያዘንክ ትመስላለህ ብሎ ይጠይቀዋል:: አዎ! አዝኛለሁ የማዬን የሥራ ባልደረባ በስም ማጥፋት ወንጀል ስለተከሰሰ:: ማን ነው ከሳሹ?
እማዬ:
ምን ስላለ?
ፀጉርሽ አረዛዘሙ በጣም ደስ ይላል ደግሞም የቅላቱ ልክ እኔ የምወደው ዓይነት ነው ብሎ ስለተናገረ::
ታዲያ ይህ እንዴት ሊያስከስስ ይችላል ጥሩ አባባል ነው እንጂ ሲለው አልገባህም የማዬ የሥራ ባልደረባ "ድንክዬ" ነው ብሎት አረፈ (ቁመት 48 c.m) ብቻ---:

http://www.diretube.com/melat-g-michael ... 16d73.html
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Tue Aug 21, 2012 7:11 pm

አንድ ባልደርባዬ "እርግዝናና ሞት እይደበቅም" ያለኝ ሁኔታ ትዝ ብሎኝ ስለነበረ በአነጋገሩ እውነትነት ተደነኩ::

ቀጠል አድርጎም ሁለት ሴት መኖክሳት ከተማ ገበያ ይወጡና አትክልት ሱቅ ሲገቡ ትልልቅ የሚያማምሩ ሙዞች ይመለከቱና አንደኛዋ አንድ እንግዛ ስትላት ያችኛዋ አይ! ሁለቱን እንግዛ "እንደኛውን ተካፍለን እንበላለን" ብላ አለቻት አለኝ:: በነገሩ የተደናገርኩት ምን ማለትህ ነው? ብዬ ስጠይቀው ለካ ደንቆሮ ነህ አይገባህም እንዴ? ሲለኝ ጉዳዩ ቀስ ብሎ ስለገባኝ በሳቅ አለኩላችሁ:: ምናልባት ነገሩ እንደኔ ግር ካላችሁ አይዟችሁ ሲገባችሁ በደንብ እንደምትስቁ ተስፋ አረጋለሁ::
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Fri Aug 31, 2012 11:20 am

ሰዎች ጉድ ነው የማይሰማ ነገር የለም "መለስ" መናገር ጀመረ አሉ::

ሬሳን ለረጅም ጊዜ አስቀምጦ ማልቀስና ማስለቀስ ባገራችን የተለመደ ባለመሆኑ ሥፍራው ጠቦት እየተወራጨ ""እትትት--- እትትት ----እትትት ኧረ በረደኝ አዜብን ደርቡልኝ"" ማለት ጀምሯል አሉ::

ከወደላይ የተገኘው ምንጫችን እንደገለፀው አባ ጳውሎስ ከዳቢሎስ ጋር የጀመሩትን ትግል እንደቀጠሉ ነው ምክንያቱም ወንድሜ መለስ ሳይመጣ አንተ ቀድመህ ዙፋን አትወርስም አትገባትም በማለት በጥፊ እየወለወላቸው በቡጢ እየነጠፋቸው እንደብራቅ እየጮኸባቸው በጭንቅ ላይ ጭንቅ ደርቦባቸው የመለስን ቶሎ መድረስ በመናፈቅ ላይ ናቸው ተባለ:: :( :( :(
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

ባልና ሚስት

Postby ክትክታው » Sat Sep 01, 2012 7:23 am

ሰላም ወገኖቼ
ከዚህ ቤት እንኳ ከማንበብ በስተቀር ተሳትፎ የለኝም። ዛሬ ግን ከብዙ አመታት በፊት አንድ ጓደኛየ ያጫወተኝን ቀልድ ላካፍላችሁ። ከአሁን በፊት በሌላ የቤቱ ተሳታፊ ተንግሮም እንደሆን አላውቅም። ብቻ ቀልዱ እንዲህ ነው። ለመዝናናት ነውና ረዝም ማለቱን አትጥሉት።

በገጠር ከተማ በጥሩ ሁኔታ የሚኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ አሉ። ታዲያ ካጠገባቸው አንድ ሱቅ ከፍቶ የሚነግድ አረብ ነበር። ታዲያ ይህ አረብ ይችን ቆንጆ ባለትዳር ሴት ይወዳታል። ታዲያ የሆነ ነገር ለመግዛት ወደዚህ አረብ ሱቅ በሄደች ቁጥር እወድሻለሁ ለአንድ ቀን አብረን እንደር እያል ይጠይቃታል። ታዲያ ሴትዮዋ ባለትዳር ስለሆነች ፊቷን እያጠቆረችና እየገላመጠች ትመልስለታለች። ብቻ አረቡ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ሴትዮዋ ወደሱቁ እቃ ለመግዛት በመጣች ቁጥር ያንኑ “ተይ አንድ ቀን ብቻ” እያለ መጠየቁን አላቆመም። ከብዙ ጊዜ በኋላ ሴትዮዋ ይህን ሁኔታ ማስቆም አለብኝ ትልና ችግሯን ለባሏ ታማክረዋለች። ባልየውም ብልህ ነበርና ጥሩ ነው ጤፍ ግዥና ከወፍጮ አጠገብ አስቀምጭ አረቡን ሄደሽ ና ባሌ ሌላ ቦታ ሄዷልና ማታ መጥተህ ማደረ ትችላለህ “በይው ከዚያ ማታ ላይ እኔ መጥቼ በሩን ሳንኳኳ የደነገጠ መስለሽ ባሌ ነው መሰል ና ተደበቅ ብለሽ የሴት ልብስ አልብሰሽ “ሰራተኛየ ናት እለዋለው” ብለሽ ከወፍጮው ጤፉን እንዲፈጭ አድርጊው ይላታል። ከዚያ በኋላ ሁለተኛ አይጠይቅሽም ብሎ ያማክራትና ዝግጅቱን ጨርሰው ሴትዮዋ ወደ አረቡ ሄዳ አንድ ቀን ባሏ ለስራ ወደሌላ ቦታ በሚወጣበት ጊዜ ከእርሱ ጋር ለመጫወት ፈቃደኛ እንደሆነች ትነግረዋለች። ይህ አረብ ይህን መልስ ሲሰማ በጣም ደስ አለው ጮቤ ረገጠ። ለምን ሴትዮዋ ቆንጆ በመሆኗና ባለትዳርም ስለሆነች እሺ ትለኛለች የሚል ግምት አልነበረውም። ብቻ እንደልምድ አድርጎት ስትመጣ ስትሄድ እንደሚወዳት ይነግራት ነበር።

በባልና ሚስት እቅድ መሰረት አንድ ቀን ወደ አረቡን ትሄድና ባሏ ለስራ ሌላ ቦታ እንደሄደና ሰንብቶ እንደሚመለስ ትነግረዋልች። አረቡ ተቻኩሎ ታዲያ መቼ ልምጣ ሲላት ዛሬ ማታ ና ትለዋለች። ይህ አረብ ጊዜው በጣም ረዝሞበት አመሸና በተባለው ሰዐት ቀስ ብሎ ወደሴትዮዋ ቤት ይሄዳል። ራት በልተው ቁጭ ብለው ሲጫወቱ የቤቱ በር በድንገት ከውጭ ይንኳኳል። በዚህ ጊዜ ይህ አረብ በጣም ይደነግጣል የሚሄድበት ይጠፋዋል ። ታዲያ ሴትዮዋ ባዘጋጀችው ወጥመድ መሰረት ተሎ ብላ ወደ ጓዳ እንዲገባ ታደርግና ዘርፈፍ ያለ የሴት ቀሚስ አስለብሳ ከወፍጮ ላይ እህል እየፈጨ እንዲቆይ ታደርጋለች። በተነጋገሩት መሰረት በራፍ ሄዳ ስትከፍት ከውጭ የመጣው ባሏ ነው። ልክ የደነገጠች መስላ “ምንነው በደናህ ነው” ስትለው አይ ደህና ነኝ አንቺ እንዴት አመሽሽ ይልና ከቤት ገብቶ ወዲያ ወዲህ ሲል የወፍጮ ድምጽ ይሰማል። የምን ድምጽ ነው የምሰማው ሲላት ወፍጮ ነው አዲስ ሰራተኛ ቀጥሬ ጤፍ እየፈጨችልኝ ነው ብላ ወደ ጓዳው ትወስደዋለች። አረቡ ፊቱ እንዳይታይ እንገቱን ዝቅ አድርጎ ይህን ጤፍ እንደጉድ ይፈጨዋል። ከዚያማ አረቡ እንዴት ውጥቶ ይሂድ! ባልየው ከጓዳው ፊት ለፊት ከሚስቱ ጋር ቁጭ ብሎ እሳት እየሞቁ ከማዶ አረቡ ይቆጣጠራሉ። አረቡ ከውስጥ ሆኖ ስለሚያያቸው ውጥቶ የሚሄድበት መንገድ ስለሌለ ከአሁን አሁን ተነስተው ይሄዳሉ በሚል ተስፋ ለደቂቃ እንኳን እረፍት ሳያገኝ የቀረበውን ጤፍ ፈጨ። ባልየውም “አይዞሽ በርቺ የመጀመሪያ ቀንሽ ስለሆነ ነው እያለ ድምጹን እያሰማ አንድ ስልቻ ጤፍ ያስፈጭዋል ከዚያ “በይ ለዛሬ ተኝ ይበቃሻል ሌላው እህል ነገ ትፈጫለሽ” ብሎ ለአዲስቱ ሰራተኛ ( ለአረቡ) ተናግሮ ሊተኛ ከሚስቱ ጋር ይሄዳል። አረቡ በጣም ደክሟል ከዚያ በላይ ባሏ አወቀብኝ አላወቀብኝም እያለ በስጋት ነው ሌሊቱን ከወፍጮ ጋር ሲታገል ያሳለፈው። እጁ ዝሏል። አረቡ ባልና ሚስት መተኛታቸውን ያረጋግጥና ምን አይነት ቀን ገጠመኝ እያለ ቀስ ብሎ ሾልኮ ከቤት ይወጣና ወደሱቁ ገብቶ የቀረውን ሌሊት ያገባድዳል። ከዚያ ቀን በኋላ ሴትዮዋን ወደሱቅ እቃ ልትገዛ ስትመጣ መቅለስለስ የለ ወዲህ ወዲያ ማለት የለ የተጠየቀውን እቃ ያቀርባል ሴትዮዋም ገንዘቧን ከፍላ ትሄዳለች። ሰላም ሆነች። ከዚያ በኋላ ምንም ጥያቄ አቅርቦ አያውቅም። ተስፋ መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ከውርድትም ላይ ደርሶ ነበርና። በዚህ ሁኔታ ረዥም ጊዜ ካሳለፉ በኋላ ሴትየዋ በአረቡ ላይ ያደረገችው በደል ከልቧ ይጸጽታትና አንድ ቀን ወደ አረቡ ሄዳ ዛሬ ባሌ ከቤት አያድርም ማታ ከቤት ና እንጫውት ትለዋለች። ታዲያ አረቡ ምን አለ መሰላችሁ “ሴትዮ ዱቄት አለቀ እንዴ”?
ክትክታው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 122
Joined: Mon Jun 27, 2011 5:45 am

Postby feredewnetu » Sat Sep 15, 2012 9:53 pm

ስሞኑን አዲሳባ ነው ሽማግሌው ለቅሶ ለመድረስ አንድ ስፈር ውስጥ ይሔዱና የለቅሶ ቤቱን ቢዞሩ ቢዞሩ ሊያገኙት አልቻሉም ከዛ ብስጭት ብለው ወደ ቤታቸው ለመመለስ አያስቡ አንድ ጎረምሳ በአጠገባቸው ሲያልፍ ያዩና ልጄ አባክህን አስኪ አርዳኝ ለቅሶ ለመድረስ ብዬ ቤቱን ለማግኘት አልቻልኩም አንዳው የለቅሶ ድንኵን አዚህ አካባቢ ተጥሎ አይተህ አንደሆነ አንድትነግረኝ ነበር ቢሉት " የመንግስት ነው የግል? " ብሎ አደናገራቸው ምን ያርግ?
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

Postby ENGEDA1967 » Sun Oct 07, 2012 12:10 pm

አቤትትትትት ሰው ሁሉ ጥፍፍፍት ብሎም የለ ጉድ እኮነው
ለኛዋ ቆንጂት የት ጠፋሽ በሉልኝ ከመጣች
የእየሩሳሌሙ እንግዳ
ከግሪክ
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests