መድበለ እቴ...

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ሕምምም

Postby ዋኖስ » Sat Apr 27, 2013 4:10 pm

ሕምምምም


ሞትስ ሞቷል ይሁዳ:ጥርጥር የለኝ አልሰጋ:

ተለይቷል ከዚህ ዓለም በአካል ሥጋ:

መንፈሱ እንጅ ያልሞተዉ የሚኖረዉ ከኛጋ::

መልከ-ብዙ ይሁዳዎች: ገጸ-ብዙ ፈርጅ ያላቸዉ:

ለዓለም መናጥ ሰበብ-አስባብ በየፊናዉ:

መንፈሱ ነው የይሁዳ እኛ ከእርሱ የወረስነው::
ሩሙን ለማሞቅ ያክል እንጅ መቼም ያንቺን ግጥም ችሎታ ለመገዳደር እንዳይደል ይታወቅልኝ:: ቅቅቅ

እቴጌይት wrote:አልሞተም ይሁዳ

የክህደቱ- ግዝፈት መጠን- ብርሀነ ውስጡን -አክስሎ
የበደሉ -ጸጸት ሸክም - ሕሊናውን አቁስሎ
መኖር ታክቶት - በጸለመ -እሱነቱ
መስሎኝ ነበር -አኮ ይሁዳ- የታነቀ- በኅጢአቱ

ግና ዛሬ- የዘመን ጉድ- ጉድ አሳየ
ከአንበብነው- ከመጣፉ- የተለየ

ትውፊት ንግርት- ትንቢቱ ሁሉ- ተለዋውጦ
ሀዲስ ብሉይ- ኦሪት ራዕይ- ተገላብጦ
የከሃዲው- መታነቁ -ሞቱ ቀርቶ
ማቅ መልብሱ -ምልጃው ጠፍቶ
በአደባባይ- እንደጻዲቅ- መድረክ ወጥቶ
ክህደት ግብሩን -ገድሉን ሲያውጅ- አፉን ሞልቶ

እውነት ታስሮ- ለስቅላት- ፍርድ ሲነዳ
ብዙ አሳየን- ገና አልሞተም -የኛ ይሁዳ!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: ሕምምም

Postby እቴጌይት » Sun Apr 28, 2013 3:09 am

ሠላም ዋኖስ
ውበት እንደ ተመልካቹ እይታ, ዜማም እንደ አድማጩ ጆሮ የቅኝት ምርጫ እንደሆነው... ግጥምም እንዲሁ በአንባቢው ስሜት ሚዛን ነውና መገዳደር በቤታችን አይኖርም :D ! ..ቤቱን በግሩም ግጥም ሞቅ ደመቅ ስላደረክው ደግሞ እጅ ነስቻለሁኝ! ይልመድብህ


ዋኖስ wrote:ሕምምምም


ሞትስ ሞቷል ይሁዳ:ጥርጥር የለኝ አልሰጋ:

ተለይቷል ከዚህ ዓለም በአካል ሥጋ:

መንፈሱ እንጅ ያልሞተዉ የሚኖረዉ ከኛጋ::

መልከ-ብዙ ይሁዳዎች: ገጸ-ብዙ ፈርጅ ያላቸዉ:

ለዓለም መናጥ ሰበብ-አስባብ በየፊናዉ:

መንፈሱ ነው የይሁዳ እኛ ከእርሱ የወረስነው::
ሩሙን ለማሞቅ ያክል እንጅ መቼም ያንቺን ግጥም ችሎታ ለመገዳደር እንዳይደል ይታወቅልኝ:: ቅቅቅ

እቴጌይት wrote:አልሞተም ይሁዳ

የክህደቱ- ግዝፈት መጠን- ብርሀነ ውስጡን -አክስሎ
የበደሉ -ጸጸት ሸክም - ሕሊናውን አቁስሎ
መኖር ታክቶት - በጸለመ -እሱነቱ
መስሎኝ ነበር -አኮ ይሁዳ- የታነቀ- በኅጢአቱ

ግና ዛሬ- የዘመን ጉድ- ጉድ አሳየ
ከአንበብነው- ከመጣፉ- የተለየ

ትውፊት ንግርት- ትንቢቱ ሁሉ- ተለዋውጦ
ሀዲስ ብሉይ- ኦሪት ራዕይ- ተገላብጦ
የከሃዲው- መታነቁ -ሞቱ ቀርቶ
ማቅ መልብሱ -ምልጃው ጠፍቶ
በአደባባይ- እንደጻዲቅ- መድረክ ወጥቶ
ክህደት ግብሩን -ገድሉን ሲያውጅ- አፉን ሞልቶ

እውነት ታስሮ- ለስቅላት- ፍርድ ሲነዳ
ብዙ አሳየን- ገና አልሞተም -የኛ ይሁዳ!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዲጎኔ » Sun Apr 28, 2013 6:10 am

ሰላም አሸማ ዲጎዲጎና እንደባህላችን
ለእቴጌይቱ መድብል ታዳሚዎቻችን
እናቀርባለን ካለንበት ከመንደራችን
እቴጌይቱ የዋርካ በሳል እህታችን
ለመሞከር ሳይሆን ለቀና ድጋፋችን
ይህው አቤት ብለናል ለታዛቢያችን
በድንቅ ሰማያዊ ስነቃል የተሞላው
ቀና ልብ ላለው በጎ የሚያስተምረው
የይሁዳን ክህደትና ጥፋት የገለጠው
ጠፍተን እንዳንቀር የሚመክረን ነው
እንደኬፋ ወደወንድሞቹ የተመለስው
ዘንድሮ ግን ነገሩ እንዲህ ያልሆነው
ይሁዳ ብቻ ሲክድ ሲያስክድ የምናየው
ጴጥሮስ መንፈስ ተሞልቶ ያልሰበከው
ጾምና ጸሎቱ በቅን ልብ ያልተደረገው
ለንስሀ ለይቅርታ ገና አለመሸም ጊዜው
እስኪ ለመሀሪ ጌታ ልባችን እንስጠው
አንዳች የለውምና ለእርሱ የሚሳነው

[qote="TAዛBI"]

ዲጎኔ ለምን በግጥም አይሞክራትም ?
[/quote]
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby TAዛBI » Sun Apr 28, 2013 8:12 am

ደመላሽ wrote:ግዴለም እኔ ላንቴ ገጥማሎ::

ኢቱዬ ናይለቲ
ባይቺሊም ላንቺ መቀኘቲ
TAዛBIው ፍቅሪ አለበቲ
የሚያስተነፍሶ ነቅሎ በመሰካቲ :lol:

ጊና ኢቱዬ ?
ባማረው የስንኚ ቁዋጠሮሽ
ካካጃለ ሊተኛ አብሮሽ (ሊጫወቲ አባሮሽ)
በቃሎቺሽ ውበቲ ላንቺ ካታመኘ
በምናቡ ሲሎሽ ባሳቢ ከናኘ
ማሰቢያኖ መሸከሚያ ታዛቢውስ ያገኘ? :lol: :lol:

ደምሎ ስንታዮ ኖ
የገጣሚ አስገጣሚና አጋጣሚ አገናኝ :lol: :lol:

TAዛBI wrote:እኔ ሀሳቤን በግጥም መግለጽ አልችልም


ዳሚሎ ሳቅቼ ሊሞት ነበር :lol: :lol:

ሚስቴ እንደምትሎ ወዛደር ኢና ሉካንዳ ቤት ሳራታኛ ቀልዳቾ አያምሪም ቲላለች ወይ ዪራጋጣሉ ዋይ ዪዋጋሉ ኖ የሚትል እሷ
አንታ ጊን ጫዋታ ታቃላህ ጊጢምም ቲሞክራላህ ጢሩ ኖ በርታ :lol: :lol: ኢኔ ግን ላማታኛት ሚናሚን አልፋላግኩም ቁጭ ቡሎ ላማጫዋት ቢቻ ኖ :lol: :lol: አብራኝ ያሚቲታኛ ሌላ አላቺኝ :lol: ጊጢም ካጋጣማ ጋር ሁሉ ሊታኛ ካልኩ ኢማ ሺጊር ኖ :lol:
.
ዲጎኔ

በግጥም መመለስህ መልካም ነው ግን የእትጌን ሙግት ሳብስታንሱን አላገኘኸውም !
እቴጌ በውብ ግጥሟ የሞገተችው ሰው የአርባ ቀን እድሉ ማንነቱን ከወሰነ በራሱ ዴንሲቲኒ ላይ ድርሻ ከሌለው መልፋት መድከሙ ምን ጥቅም አለው አስቀድሞ ባለፈ ውሳኔስ ፍርድ መቅረቡ ለምን ይሆን ፍርዱስ ምኑን ፍርድ ተባለ ? አይነት ስሜት ነው ያለው she may not be challenging the creator but she wants to understand how this works ለዚህ ነው ሀይማኖተኛ የሆናቹህ ወይ ወደሀይማኖት ቅርበናል የምትሉ ሚስጥሩን ፍቱላት ያልኩት ቢቻል በግጥም ብታስረድዋት መለእክቱ ከውበት ጋር ዘልቆ እንዲገባ

ሰላም ለሁሉም
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby ደመላሽ » Sun Apr 28, 2013 1:45 pm

ዐረግ በ--ተ--ሰ--ቀ--ሎ!
ሚን ጉድ ይዞኖ የመጣ አንተ ዲጎኖ?!

አሁኒ ዲንገቲ ምጻቲ ደርሶ
የሰማዩን ምሶሶ ገናድሶ
ኪስቶስ ኢያከነፈ ቢመጣ
እ! እና :wink:
ቢያዮ ይን የቃላት ሲልቀጣ
ተመሊሶ አልነበሪ ዛፍ ላይ የሚወጣ
የሚሰቀሎ ባንተ ጣጣ :?: :lol: :lol:

አሁን አንቴ ጊጥም ኖ የጋጠመ?
ወይስ ለመግጠሚ ተንደርድሮ ኖ የቆመ? :lol:

ቤት ለመምታት ቲባል
የሰው ነፍስ እንዲህ ይጨነቃል? (ጉድኮኖ ኢናንተ!)

ግድኮ አደለሚ ዲጎኔ - ግጥም ቤት ሊመታ
ቃል ድርደራ - አሰካኪ ኖ - ተሁሉም የሚበረታ::

አሁን ጊን አንቴ - ቤት መታሎ ብሎ
ው ው ሲትል ቁርጥ ቦቢን ኖ ምትመስሎ? :lol:

ዶሞ በተጨማሪ
ቃላት ሲደርደሪ
ቤቱም ሲቀወሪ
በሊክ በሊኩ ተመጢኖ ኖ
ለተቃጠለ አየር ሞጫ
እያበጁ ኖ ያራት ነጥቢ መቁዋጫ :lol:
ዚምብሎ አይደለም ሩጫ::


ደምሎ ወጋዮህ ነኚ
ጊጥምና ግጣም አገናኚ :lol:ዲጎኔ wrote:ሰላም አሸማ ዲጎዲጎና እንደባህላችን
ለእቴጌይቱ መድብል ታዳሚዎቻችን
እናቀርባለን ካለንበት ከመንደራችን
እቴጌይቱ የዋርካ በሳል እህታችን
ለመሞከር ሳይሆን ለቀና ድጋፋችን
ይህው አቤት ብለናል ለታዛቢያችን

በድንቅ ሰማያዊ ስነቃል የተሞላው
ቀና ልብ ላለው በጎ የሚያስተምረው
የይሁዳን ክህደትና ጥፋት የገለጠው
ጠፍተን እንዳንቀር የሚመክረን ነው

እንደኬፋ ወደወንድሞቹ የተመለስው የትኖ ቦታዋ ኢቺ ቲንኝ?

ዘንድሮ ግን ነገሩ እንዲህ ያልሆነው
ይሁዳ ብቻ ሲክድ ሲያስክድ የምናየው
ጴጥሮስ መንፈስ ተሞልቶ ያልሰበከው
ጾምና ጸሎቱ በቅን ልብ ያልተደረገው
(ሚን ሆኖ ኖ? ይን ጨርሶ መጀማሪያ ዚም ብሎ አይሮጢም :roll: )

ለንስሀ ለይቅርታ ገና አለመሸም ጊዜው
እስኪ ለመሀሪ ጌታ ልባችን እንስጠው
አንዳች የለውምና ለእርሱ የሚሳነው

[qote="TAዛBI"]

ዲጎኔ ለምን በግጥም አይሞክራትም ?
[/quote]
History teachs us that we DON'T learn from History
ደመላሽ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Aug 17, 2010 11:21 pm

Postby ሳምራውው33 » Mon Apr 29, 2013 8:02 pm

ሰላምታን ለሁላችሁም በማቅረብ ይቺን ቤት አንድ ደረጃ ከፍ ላድርጋት :!:

ድፎ ዳቦ !

ከላይ ረመጥ እሳት ሲፋፋም ባናቱ
ከስር ነበልባሉ ሲወቃው ደረቱን
እሳት ተደፍቶበት እሳት ተሰዶበት
መውጫ መግቢያ ጠፍቶት እንዲያ ተዘግቶበት
እገል ውስጥ ተኝቶ እንዲያ ተመቻችቶ
በኮባ ቅጠል ላይ ተንሰራፍቶ
ጠበቅ ሳይል ላልቶ ፋፍቶ
መቼም አይመቸው እንዲያ ነዶ ::

ግና ግን ጨርሶ ሲወጣ ፍዳውን
የተጣለበትን ግለት መከራውን
ግርማ ሞገስ ያለው ያማረ ይሆናል
በጠላ በቆሎ በዶሮ ይበላል
የበአል ማከበሪያ ማድመቂያ ይሆናል
የከበረ ስፍራ መሶብ ወረቅ መቆያው ....
ማደሪያው ይሆናል :!:

የስኬት ምሳሌም ትሆናለች :!:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ቦቹ » Mon Apr 29, 2013 11:07 pm

ግጥሙ ምንን በተመለከተ ነው ልሞክር እስቲ

ስድስት ቁጥርን ይዤ ስሄድ ወደ ቄራ
ጢም ብሎ ሞልቶ ሞቆኝ ስንጠራራ
ብረት የያዝኩበት እጄ ተቃጠለ
የፈላ ዘይት ውስጥ የገባ መሰለ
ነገሩ ላጣራ አንዴ ስከልመው
እሙዬን አየዋት በቂጧ ስታሸው
ጠላታችሁ ይደንግጥ ክው ብዬ ድንግጥ
ዙሪያዬን ቀስ ብዬ አደረኩት ገልመጥ
የቂጡን ባለቤት ፊታውራሪን ላየው
አንገቴን መዝዤ አሰግጌ አየው
እንከን የሌለባት ደዘደዝ ሞንዳሌ
ምን አድርግ ብላኝ ነው ምታሸኝ በዳሌ
ወይ አቶ በዛብህ መቼ እሱ አስጨርሶኝ
ዘራፍ ብሎ ወጥቶ ተኮፍሶ ታየኝ
እንዳላጎነብስ ከxላ ሰው አለ
ወደ እሷ እንዳልሄድ ከፊቴ አንዱ አለ
ብረቱን ለቅቄ ወራጅ አለ ብዬ
በዛብህ እንዳይታዬ አንካሳ መስዬ
ጉልበቴን በጄ ይዜ ወጣው እያነከስኩኝ
አቶ በዛብህን እየተራገምኩኝ (እውነተኛ ታሪክ) :) :) ይመቻችሁ::
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby እቴጌይት » Sun May 05, 2013 11:05 pm

ሠላም ወገኖቼ
ቤቱን ሞቅ ደመቅ ላደረጋችሁት ለTAዛ BI, ለዲጎኔ እና ሳምራውው 33 ምስጋንዬ ከፍ ያለ ነው::

ወንድሜ ዲጎኔ በቀናነት ለተሞላው ሀሳብህ አክብሮቴ ከፍ ያለ ነው!! ይልመድብህ!

TAዛ BI የ'ዐርባ ቀን'ን ጥያቄ ዋና ጭብጥ በግሩም ሁኔታ ስለተረዳኽልኝ ሳላመሰግንህ አላልፍም::

ወንድሜ ሳምራውው:- 'ዶፎ ዳቦ' በጣም አስደማሚ የሆነ ጭብጥ ያለው ግጥም ነው:: ለ'ቧልት ወይስ ባልትና' መልስ አስበህ ያቀረብከው ይሁን አይሁን እርግጠኛ መሆን ባልችልም ጥያቄ የሚጭር ነውና ሀሳቤን ይዤ ልመለስበት እሞክራለሁኝ:: አንተም እስከዛው መርቅልን:: ለአሁን እስቲ አንድ መርቄ ልሂድ::

ብዕሬ


ባልፈልግ ወጨፎ - ባልሄድ ጦር ቀረጻ
ባልመዝም ጎራዴ - ባልቀስር ፍላጻ............
አትሮኖስ የ'ሚያሲዝ - ብራና የሚያስነሳ
ብዕር የሚያስጨብጥ - ቀለም የሚያስገሳ
ውስጥ የሚለበልብ - አለብኝ አበሳ:-

ሺህ ዘመን ያስማጠ - ሺህ ዘመን ያስጠቃ
ማርያም ያልማረችው - የነፍሰ ጡር ሲቃ
ገሎ ያልገላገለ - ወይ ወልዳው ያልበቃ
ከእምባዋ የሚጨለፍ - 'ሚቀዳ ከጭንቋ
ተከትቦ ያላለቀ - አለኝ ብዕር ቋንቋ!!


ደህና ቆዩኝ
አክባሪያችሁ
Last edited by እቴጌይት on Mon May 06, 2013 11:08 pm, edited 1 time in total.
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዲጎኔ » Mon May 06, 2013 3:12 pm

ሰላም ለሁላችን በግራና ቀኝ ላላችሁ
ወደ እቴጌ መድበለግጥም ለገባችሁ
እስኪ የልቤን እውነቱን ልካፍላችሁ
ምን ለምን እንደምገጥም ላስረዳችሁ
ዲጎኔ ዋርካ ላይ የምመላለሰው
በዘመን እላቂ ላይ ላለነው
በዚያች ጦቢያ ለተወለድነው
ለወገናችን እንድንተርፍ ነው
ታዛቢያችን ወገኔ ያቀረበው
ነገረመለኮት መች አጣነው
ቅድመ ውሳኔ የሚባለው
ብዙዎችን ከጌታ የለየው
ዲጎኔ ከቶ የማይቀበለው
ክርስቶስ በደሙ ያቀናው
አምላክ በፍቅሩ የሰራው
ጌታን ላመኑት የተሰጠው
ቀና ስነመለከት ምቀበለው
ጌታችን አንዱን ለጥፋት
ሌላውን ለመልካሟ ገነት
አስቀድሞ ወሰነ ትምህርት
ቁንጽልና አሳሳች ትንቢት
ሁሉን በሚቀበል ጌታ ፊት
ሚዛን የማይደፋው መክሊት
በሉ ይብቃኝ ለዛሬ ልሂድበት
እመለሳለሁ ወደወትሮዬ ቤት
ሞደሬቷ ባለብእር እቴጌ ቤት
ለታዛቢው የልቤን ለማመልከት
አበሳችንን ለሻረው ልናገርለት
ምስክሬ ነህ ብሎኛል በእርገት

TAዛBI wrote:["]
TAዛBI wrote:

:lol:
ዲጎኔ
በግጥም መመለስህ መልካም ነው ግን የእትጌን ሙግት ሳብስታንሱን አላገኘኸውም !
እቴጌ በውብ ግጥሟ የሞገተችው ሰው የአርባ ቀን እድሉ ማንነቱን ከወሰነ በራሱ ዴንሲቲኒ ላይ ድርሻ ከሌለው መልፋት መድከሙ ምን ጥቅም አለው አስቀድሞ ባለፈ ውሳኔስ ፍርድ መቅረቡ ለምን ይሆን ፍርዱስ ምኑን ፍርድ ተባለ ? አይነት ስሜት ነው ያለው she may not be challenging the creator but she wants to understand how this works ለዚህ ነው ሀይማኖተኛ የሆናቹህ ወይ ወደሀይማኖት ቅርበናል የምትሉ ሚስጥሩን ፍቱላት ያልኩት ቢቻል በግጥም ብታስረድዋት መለእክቱ ከውበት ጋር ዘልቆ እንዲገባሰላም ለሁሉም[/quote]
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby TAዛBI » Thu May 09, 2013 7:57 am

አመሰግናለው ዲጎኔ

ግጥሞችህ ባብዛኛው በሳድስ ፊደል ቢያልቁም እንደገባኝ ቅድመ ውሳኔ የሚባል ነገር የለም ወይንም አልቀበልም ነው መልእክቱ

ሌሎች እንዴት እንደሚያዩት አላውቅም

ሰላም

ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን በግራና ቀኝ ላላችሁ
ወደ እቴጌ መድበለግጥም ለገባችሁ
እስኪ የልቤን እውነቱን ልካፍላችሁ
ምን ለምን እንደምገጥም ላስረዳችሁ
ዲጎኔ ዋርካ ላይ የምመላለሰው
በዘመን እላቂ ላይ ላለነው
በዚያች ጦቢያ ለተወለድነው
ለወገናችን እንድንተርፍ ነው
ታዛቢያችን ወገኔ ያቀረበው
ነገረመለኮት መች አጣነው
ቅድመ ውሳኔ የሚባለው
ብዙዎችን ከጌታ የለየው
ዲጎኔ ከቶ የማይቀበለው
ክርስቶስ በደሙ ያቀናው
አምላክ በፍቅሩ የሰራው
ጌታን ላመኑት የተሰጠው
ቀና ስነመለከት ምቀበለው
ጌታችን አንዱን ለጥፋት
ሌላውን ለመልካሟ ገነት
አስቀድሞ ወሰነ ትምህርት
ቁንጽልና አሳሳች ትንቢት
ሁሉን በሚቀበል ጌታ ፊት
ሚዛን የማይደፋው መክሊት
በሉ ይብቃኝ ለዛሬ ልሂድበት
እመለሳለሁ ወደወትሮዬ ቤት
ሞደሬቷ ባለብእር እቴጌ ቤት
ለታዛቢው የልቤን ለማመልከት
አበሳችንን ለሻረው ልናገርለት
ምስክሬ ነህ ብሎኛል በእርገት

TAዛBI wrote:["]
TAዛBI wrote:

:lol:
ዲጎኔ
በግጥም መመለስህ መልካም ነው ግን የእትጌን ሙግት ሳብስታንሱን አላገኘኸውም !
እቴጌ በውብ ግጥሟ የሞገተችው ሰው የአርባ ቀን እድሉ ማንነቱን ከወሰነ በራሱ ዴንሲቲኒ ላይ ድርሻ ከሌለው መልፋት መድከሙ ምን ጥቅም አለው አስቀድሞ ባለፈ ውሳኔስ ፍርድ መቅረቡ ለምን ይሆን ፍርዱስ ምኑን ፍርድ ተባለ ? አይነት ስሜት ነው ያለው she may not be challenging the creator but she wants to understand how this works ለዚህ ነው ሀይማኖተኛ የሆናቹህ ወይ ወደሀይማኖት ቅርበናል የምትሉ ሚስጥሩን ፍቱላት ያልኩት ቢቻል በግጥም ብታስረድዋት መለእክቱ ከውበት ጋር ዘልቆ እንዲገባሰላም ለሁሉም
[/quote]
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby እቴጌይት » Wed May 22, 2013 6:01 am

መርገመ ልዩነት

እንደ'ብረ ቀለም ድምቀት - እንደ ቀስተ ደመና
ልዩነት ውበት ሳይሆን -መርገም ሆኖ ፈተና
ለራስ ውድቀት መከራ
ከራስ ውስጠ-ምርመራ
ጣት ከ'ሌላ' ቅሰራ
በስነ ልቦና አስራጊ
'እኛ'ን ከ'እነሱ' አዋጊ
የጥላቻ ዘር መዘሪያ - ባያት እዳ ልጅ መቅጫ
የጥፋት አውድማ አንጂ - አልሆን አለ ማጌጫ!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby TAዛBI » Wed May 22, 2013 12:21 pm

እቴጌይት wrote:መርገመ ልዩነት

እንደ'ብረ ቀለም ድምቀት - እንደ ቀስተ ደመና
ልዩነት ውበት ሳይሆን -መርገም ሆኖ ፈተና
ለራስ ውድቀት መከራ
ከራስ ውስጠ-ምርመራ
ጣት ከ'ሌላ' ቅሰራ
በስነ ልቦና አስራጊ
'እኛ'ን ከ'እነሱ' አዋጊ
የጥላቻ ዘር መዘሪያ - ባያት እዳ ልጅ መቅጫ
የጥፋት አውድማ አንጂ - አልሆን አለ ማጌጫ!


Poetry is when an emotion has found its thought and the thought has found words.

Robert FrostPoetry is language at its most distilled and most powerful.”


ቃላት ሳታባክኚ እንደሁልግዜው እየኖርንበት ያለውን ሀቅ ቁጭ አድርገሽዋል !

"LIKE" የሚለውን ተጭኛለው :)
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby እቴጌይት » Sat Jul 20, 2013 9:20 am

አቃጣዩ

ሰንቆ... ንፋሰ-ዓውሎ
ነደዱ... ..አያል- ግሎ
መንደሩን.. ቀዬ አቃጥሎ
ሀገሩን... እያጋየ
ዓይን እያየ
'እኔ ዕፍ - እኔ ዕፍ' ዘራፍ እንጂ
መች መጣና - ውሀ ቀጂ!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Jul 20, 2013 9:43 am

እቴጌይት

ይህ የቦርዴ ቤት ግጥምሽ የመስፍን ሀብተማርያምን "የቡና ቤት ስዕሎች" ፅሁፍ አስታወሰኝ " :D

የራስሽን ጊዜም ሆነ የዋርካን ቦታ በእንቶ ፈንቶ ከምታጣብቢ ደፈር በይና ስለአባይ ግድብ የጀመርሽውን ርዕስ ቀጥይበት :wink:

እቴጌይት wrote:አቃጣዩ

ሰንቆ... ንፋሰ-ዓውሎ
ነደዱ... ..አያል- ግሎ
መንደሩን.. ቀዬ አቃጥሎ
ሀገሩን... እያጋየ
ዓይን እያየ
'እኔ ዕፍ - እኔ ዕፍ' ዘራፍ እንጂ
መች መጣና - ውሀ ቀጂ!
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Wed Aug 21, 2013 11:59 pm

እባክዎን ይሙቱ

በሀዘን ተውኔት አጀብ
በእምባ መዋጮ ወጀብ
ወደ አይቀሬው ሸኝቶ
ከርሰ-ምድርዎን ከፍቶ
ግንዝ አካልዎን ከቶ
ወገን ሲሰናበትዎ......
ምስጥ ራት ቢሆን ገላዎ
ቢበሰብስም ስጋዎ
.....
አምባገነን መንፈሶ
ድባቡን ጥሎ ነግሶ
አልሞት ስላለ ጨርሶ....
ለነጻነት ብልጭታ
ለነግ ትውልድ እፎይታ
አምባገነን ቅሪቱ
ባክዎን ጠቅልለው ይሙቱ!!!
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests