የኔታ: እንዴት ነህ? ዊኬንድ እንዴት አለፈ? ለዛሬው ከ"አንቱ" ወደ "አንተ" ተመልሻለሁ...........የኔታ የሚለውን ትርጉም እስከምረዳ ድረስ:: እኔ እንዳልሁህ እኛ ሀገር ዲያቆኖቹን የሚያስተምሩ ሰዎች "የንታ" ይባላሉ እና ምናልባት አዲስ አበባ ደሞ "የኔታ" ከተባሉ ብየ ገምቸ ነበር:: ስሁን ግን ተጠራጠርሁ........እስቲ መልሱን ካንተ እጠብቃለሁ::
የኔታ: የእንግሊዘኛው ነገር አሁንም እንደከበደኝ ነው:: ለምሳሌ receord spped የምትለዋን ያለዛሬም አልሰማኋት:: Concorde Speed ለማለት ይሆን ብየም ተጠራጠርሁ:: የሆነው ሁኖ ናፍቆት ናት እንጂ የጠፋችው እኔ በጣም አለሁ:: ባለፈው ላንተ እና ለጉዱ ካሳ መልስ እየጻፍሁ እያለ ኮምፒዩተሬ ፍሪዝ አደረገ:: በጣም ብዙ ነበር እና የጻፍሁት በጣም ተናድጀ መልሸ ሳልጽፍ ቀረሁ:: እዚህ የምሰራበት ቢሮ የኮፒዩተራችንን ስክሪን ሁለት መሆን አለበት ተብሎ ሁለተኛን ስክሪን ከገጠሙልኝ በኋላ አልፎ አልፎ ፍሪዝ ያደርጋል:: እናም ዋርካ ላንተ እየጻፍሁ ባለበት ሰዓት ልክ ሰብሚት ልለው ስል ፍሪዝ አደረገ:: አሁን እንኳን ከIT ዲፓርትመንት መጠው ነካክተውት ስለሄዱ የተስተካከለ ይመስላል:: ኤኒወይ: እኔ አልጠፋሁም ለማለት ያህል ነው:: ናፍቆት ግን ሁሌም ቶሎ ቶሎ እንደማትመጣ የታወቀ ነው:: እንዲያውም ለረጅም ጊዜ ከቤቷ የጠፋሁት ከርማ ከርማ ስለምትመጣ ነው:: እንግዲህ አንተ የሷ Public Relation ስለሆንህ ቅሬታየን አቅርብልኝ...... :lol: :lol: :lol:
ጎጃም አዘነን በተመለከት ስለተዘፈነው ዘፈን ግጥም ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም:: እኔ ብዙ ጊዜ ዘፈን የምሰማው ከግጥሙ ይልቅ ዜማውን ነው:: ይሄም ዘፈን ግጥሙን በደንብ አልሰማሁት:: አስተያየት ለመስጠት ደጋግሜ መስማት ሳይኖርብኝ አይቀርም:: R Kellyን ይመስላል (R Kelly ኮርጆታል) ብለህ የለጠፍኸውን ሰውየ አየሁት የሆነ ነገሩ ደስ ይላል:: ግን ዘፈኑ አመረኛ ይሁን ኦሮምኝ አልሰማሁትም:: ጮህ አድርጌ እንዳልሰማው ሰው ረብሻለሁ ብየ ሰጋሁ:: በኋላ ቤቴ ስሄድ እሰማዋለሁ:: አንድ ነገር ልነግርህ የምፈልገው ግን R Kelly ያልኸውን ዘፋኝ ድሮ ሰይፉ ፋንታሁ አዲስ ዜማ ላይ ስሙን ሲጠራው ነው እንጅ ትዝ የሚለኝ አላውቀውም:: በእርግጥ ከዛ በኋል ጓደኞቸም ስሙን ሲጠሩት ሰምቻለሁ:: ከዛ ያለፈ ግን አላውቀውም............ከምሬ ነው!!! እኔ እንግሊዘኛ ዘፈን እንደማልወድ ድሮም ተናግሬያለሁ::
ባለፈው ልመልሰልህ ያሰብሁት ስለዚህ ጉዳይ ነበር...
actually a very good friend of mine has this big dream of bringing all these anonymus identities to the light ... an effective social networking can not be established on such exclusively anonymus identities.
እኔ ራሴ ሁሌም የምመኘው እዚህ ዋርካ ውስጥ በኒክ ብቻ የሚተዋወቀው ሁሉ ሰው በአካል እንዲገናኝ ነው:: እንዴት ሊሳካ እንደሚችል አላውቅም:: ናፍቆትን ባገኝሽ ደስ ይለኛል ያልሁት እሷ በጣም ለየት ያለች ስለሆነች ነው እንጅ ሁሉንም የዋርካ ተሳታፊ በአካል ባውቀው ደስ ይለኛል:: እስቲ ጓሰናህን በሀሳብህ ግፋበት በለው:: የሚታገዝ ነገር ካለ እኔም አግዛለሁ:: አንተም አግዝ: ደሞ እስኪ ናፍቆትን ከኔ ጋር በማገናኘት ጀምር....... :lol: :lol: :lol:
ውይ!!! በጣም ዘበዘብሁ............ይቅርታ ይደረግልኝ! ናፍቆት: እባክሽ በባዶ ቤት አታስለፍልፊን:: እስቲ ብቅ በይና ስለውጭው ሀገር ገጠመኝሽ አውጊን:: ምናልባት ካዱ ከተማ ወደሌላው ከተማ ዞር ዞር እያልሽ እየጎበኘሽ ይሆናል አንዴ ብቻ ብቅ ብለሽ እንዲህ የተሰወርሽው:: መልካም የመዝናናት ጊዜ ይሁንልሽ!!! (ለቫኬሽ እንደመጣሽ ገምቸ ነው)::
የኔታ..........አንተም መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልህ!!!
ጉድሻ.........አንተ ደሞ መልካም የቢዝነስ ሳምንት ይሁንልህ: ስጋው በደንብ ቸርችር በኋላ ከሰርሁ ብለህ እንዳትዘጋው::
ሁሉም ዋርካዊ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥመው ምኞቴ ነው!!!!!!!!!