by ናፍቆት » Tue Dec 07, 2021 10:42 am
አዎ ተከሰትኩ .... ከብዙ ጊዜ በኋላ .... I forgot my password first እና ከስንት ሙከራ በኋላ እንዳገኘሁት
ወይ ስትሬይት - አስቀሀኛል ትንሽ .... ከምር ..... I am actually laughing now. ..... ግን የተሰጠውን ምርጫ በሙሉ ነው የጻፍኩት - እኔ ምንም አላስቀረሁም፡፡ ጥያቄውን ያወጣው ሰው ምናልባት 'ስትሬይት' አያውቅ እንደሆነ ... Oh God, I'm laughing ..... አንድ ገጠመኝ ትዝ አለኝ ..... ግን ይቅር ... May be this is not the right forum to write it here .
ወንድየ?? Really? Frankly, I didn't know I write like that.
ዜጋው በሃገር ጉዳይ ተጠምዶአል ነው የምትለኝ? እውነት ግን ሁሉም በ 'ሃገር' ጉዳይ ይመስልሃል? እኔ አይመስለኝም
ልበልህማ ...... ብዙ ጊዜ ይሄ ሰው ሁሉ በአንድ ወቅት ገብቶበት ሁሉም አንድ አይነት ወሬ የሚያወራበትና የሚያስብበት ነገር ላይ መሃል ገብቶ አብሮ ከመዳከር ይልቅ ትንሽ ራሴን ራቅ አድርጌ ነገሩን from another perspective ለማየት መሞከር እመርጣለሁ.... እና አሁን እዚህ አገር ባለው ግርግር ስለጦርነት አንዳንድ ነገር wonder ማድረግ ጀመርኩና these days በጦርነት ላይ የተባሉ ነገሮችን ለማየት ሞከርኩ ማለት ነው .... ከዚህ በፊት ራሴን ሆነ ብዬ ስለጦርነት ያነበብኩበትን ጊዜ አላስታውስም .. እና I am like 'ሰዎች ለምንድነው ጦርነት የሚወዱት?' ወይም ደግሞ ከፈለክ 'ሰዎች ለምንድነው ጦርነት የሚፈጥሩት?' 'why do people go to war?' 'why do people fight each other and kill each other' የሚባለው ሁሉ እውነት ነው ብለን እንውሰድና why are people so cruel? ምናልባት ሰዎች በተፈጥሮ እንደዛ ናቸው ማለት ነው? Once in a while መገዳደል አለባቸው ማለት ነው? ...... Is it in our nature? ...... ምናምን ...ምናምን ..... እና ያው የተለያዩ ሰዎች የተለያየ ነገር (argument) ብለዋል ..... አንዱ 'The only ones who see the end of war are the dead.' ይላል .... እ..... ሰዎች በህይወት እስካሉ ድረስ ጦርነት ሁሌም አለ .... እንደማለት ..... ካልሞትክ በስተቀር ጦርነትን ላታይ አትችልም ... አይነት ነገር መሰለኝ ....
ሌላኛው ያለውን ልንገርህማ ... it's kind of .... There are two reasons why people go to war : Food and Sex. አይጥምም? ..... እ? ..... አትዋሽ ባክህ ... ይጥማል፡፡ I kind of go with his idea, it seems to be logical. I mean .... ሰዎች በህይወት እስካሉ ድረስ they have to eat and they have to f..k ..... መሰለኝ እንግዲህ .... ለነዚህ ሁለት መሰረታዊ 'resources' ቢታገሉ it makes sense ..... ምናምን ..... እይታው ግን ገርሞኛል
by the way, I like your nickname 'ምክክር' ስምህ (የጊዜው ጋዜጠኛ የተጠናወተውን ቃል ልጠቀምና) 'ወቅታዊ' ስም ነው For all I know, at the end of the day, I think this stupid war is going to end by ምክክር..... አያሳዝንም?
ጋዜጠኛ ብል ..... አሁን እዚህ ሃገር ያለው ጋዜጠኛ ባብዛኛው may be more than 90% የሆነ ነገር ሆኖአል .... journalism እዚህ አፈር ድሜ በልቶልሃል .... Transparency, truthfulness, fairness, informative .... ምናምን የለም .... ወፍ ..... የትኛውም local channel TV ክፈት ብቻ ... የሚታየውን ልንገርህ? በጣም ብዙ ወታደር ሰራዊት... ኢትዮጵያ ሀገሬ - ኢትዮጵያ ሃገሬ ከሚል ዘፈን ጋር ...እና ደሞ ካንድ አይነት ቃላት የታጀሉ አንድ አይነት ወሬዎች ጋር ነው ..... ዜና (አዲስ ነገር) የለም ...ቀረ .... ያንኑ አሁንም አሁንም .... እንዴ አሁንም እዛው ቻነል ላይ ነኝ? አልቀየርኩትም ነበር? ብለህ ቼክ ስታደርግ ... ቻነል ቀይረሃል ግን እዛው ነህ ... አንድ አይነት ነገር .... እኔማ ሰብስበው ስልጠና ነገር ሰጥተዋቸው ይሆን እላለሁ .... እንዴት በተለያየ ቻነል ላይ ያለ ጋዜጠኛ አንድ አይነት ነገር ባንድ አይነት አቀራረብ ያቀርባል? ምናምን ... በትክክል ካስታወስኩ ደርግ ሊወድቅ ሲል ልክ እንደዛ ነበር ቲቪ ላይ የሚታየው... ታሪክ ራሱን ይደግማል የሚሉት እውነት ሳይሆን አይቀርም ... ከምር ... እና እኔ እንደአንድ ዜጋ I am not well informed with what is really going on , though it was my right. ብዬ ነው የሚሰማኝ ....
አሁን እየጻፍኩ ምን ትዝ አለኝ ...... አንድ ጊዜ እዚህ የቦብማርሌይ ልጅ ነው የንጀራ ልጅ መጣ ተብሎ በየቦታው የሬጌ ኮንሰርቶች ነበሩ (by the way, I like reggae beat musics) .... እና ደሞ ብዙ ራስታዎች ከተማው ላይ ምናምን .... - (ለምንድነው ግን እነሱ ሰዎች በብዛት ግር ማለት የሚወዱት?) - እና አንዱ ኮንሰርት ሄጄ ነበር .... ማታ ላይ ... እና በር ላይ ከፍለን ወደውስጥ እየገባን ከኋላችን ወደ አምስት ወይም ስድስት የሚሆኑ ወጣት teenagers ራስታዎች ነበሩ ...probably Jamaicans እነሱም እየገቡ... እና አንዱ ስለኮንሰርቱ አሪፍ ይሆናል አይነት ወሬ ሲያወራለት ሌላኛው ምናለ 'Trust me, it's the same shit , man' ራስታው እኮ ነው ... እኛ እነሱን ለማየት እንገባለን እሱ .... እና የልጁ አባባል ያኔ እንደዋዛ ነበር ጆሮዬ የገባው .... ግን ዛሬ አባባሉን ለምን አልዋሰውም? ... It's the same shit.
የሆነ እብደት ላይ ያለን ይመስለኛል
ስማኝማ አስቴር አወቀ ትዝታን እንዲህ ተጫውታለች? ብዙም የስዋን ዘፈን ሰሚ አይደለሁም ... My PC is on Auto play mode እና የስዋን አመጣው it's playing now. I like it. በስዋ ድምጽ ትዝታን አስቤው አላውቅም ነበር ....
መጻፍ ደከመኝ
ባክህ ማስቲካ ልብላ እስኪ