ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Hi Guys!

Postby ናፍቆት » Wed Jun 02, 2004 5:19 pm

እሺ ባለውጭ አገሮች - እንዴት ሰነበታችሁ? ደህና? Good. ፈረንጆቹ ደህና ናቸው? አረቦቹስ? ውይ ለምን እንደሆነ እኔንጃ ከአረብ ጋር ኑሮን ገና ሳስበው የሆነ ...... ቅልሽልሽ የሚለኝ ነገር አለ:: ከምር:: አብስሎ መብላቱስ እንዴት እንዴት እያረጋችሁ ነው? እስቲ ሰለስዋ አጫውቱኝ:: የምን ዝም ዝም ነው? Some of you guys really have to cook and invite me some day. ከምር:: ስልክስ እየደወላችሁ ነው 'አገርቤት' ላለው ቤተሰብ? ውይ ይቺ ለሊት ላይ የምትደውሏትን ነገር ስጠላት ብታዩ:: ከምር:: በናታችሁ እኔጋ በለሊት እንዳትደውሉ:: እኔኮ አንዳንዴ ሳስበው ከምትልኩት ነገር ይልቅ በዚህ ሀበሻ በያዘው ኑሮ ላይ ሌላ የምትጨምሩት discomfort ሳይበልጥ አይቀርም:: ከምሬ ነው:: ስትሄዱ ለቪዛ ስትገቡ ጀምሮ ያለው የቤተሰብ መጨነቅ መጠበብ ... ከዛ ደሞ ለመሸኘት ያለው ኮተት.... ከዛ ደሞ ከሄዳችሁ በሁአላ ቅቤ በርበሬ ብሎ ጣጣ.... ውይ በስመአብ እቴ.... የምን ጭንቅንቅ ነው?

እዛስ ሄዳችሁ የሚደላችሁ ስንታችሁ ናችሁ? ባለፈው ባጋጣሚ ያንድዋን የማውቃትን ልጅ ፎቶ (እናንተ ጋ የሄደች) ፎቶዋን እዚህ የሆኑ ልጆች ጋር አየሁት:: እና ትልቅ መፈክር ይዛለች እና የኢትዮጵያን ባንዲራ ወገብዋ ላይ ሸብ አርጋለች:: ልጅትዋ እዚህ እያለች ሰልፍ የምትወጣ አይነት አልነበረችም እና ፎቶውን ሳየው ያበደች መስሎኝ I was like 'What the hell happened to her?' ሳቅ ብለው ልጆቹ ለኬዝዋ (Case) አሉኝ:: Then I said 'Case? What case?' ከዛ ነገሩኛ ጉዳችሁን:: የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ምናምንም ዝባዝንኬ...... በህዝብ ቁጥር ውስጥ ተካታችሁ መኖራችሁን በስታቲስቲክስ ከማየት ሌላ እስከመፈጠራችሁም የማያውቀውን መንግስት ... እንዲህ አረገኝ ... እንዲህ ሰራኝ... ትርኪ ምርኪ.... ሴቶቹም ሬፕ ተደርጌ ተስሜ ምናምን ነው አሉ ወሬያችሁ ..... እንደው ጣጣችሁ ብዛቱ..... እኔ የምለው ግን ይሄ ሁሉ ቅብጥርጥር ግን Does it worth it? እስቲ tell me ከምር:: ከዛ በሁአላ እንደገና ፎቶውን ስጡኝ ብዬ ሳየው ልጅትዋ እንደውም እዚህ እያለች ብዙ ብትሰለፍ ኖሮ አልኩኝ... ከምር አምሮባታል ሰልፉ.....
እኔ የምለው ባለኬዞች - እናንተስ ኬዝ ከምን ደረሰ? እስኪ ተንፍሱ::

ቸኩያለሁ አሁን:: ትንሽ ጉዳይ ቢጤ.... ምናምን ነገር....

C ya!
Last edited by ናፍቆት on Thu Aug 26, 2004 2:44 pm, edited 1 time in total.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

NAFF-COT! INK ONE DENA METASH

Postby ዓለማየሁ » Wed Jun 02, 2004 6:40 pm

በኛ በዉጪዎቹ..phhheeew (ፊዉ) ነዉ ሚባለዉ ናፍቆት! ink-one ink-oneተመለሽ ! ወየዉ ጠፍተሽ ብትቀሪ ኑሮ! የደብዚም እንባ የትምርት ቀጠሮ ሰአት..እንድሪያስማ Kill Bill አይነት ምናምን ነገር!
እኔ የሆውልሽ በተፈጥሮዌ ሰዉ ማሳዘን አልወድም!
ሰዉ ሲስቅ ሲደሰት እደሰታለሁ! ሰዉ ሲያዝን ሲቀየም ደሞ ሆቴን ይብሰዋል! Naffkot I'm so glad you are not upset over my ቀልድ ምናምን ነገር!
እና አይለምደኝም ሺ?No matter how many times የዉጭ አገር የሚኖሮዉን ኑሮና ሂወት ብትተርቢ no matter how much አማርኛ እና ኢንጊሊዝኛ ብትቀላቅይ! I ሎቭ ዪ በቃ ምናምን ነገር
ዓለማየሁ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2358
Joined: Mon Dec 15, 2003 4:06 pm

Re: Hi Guys!

Postby እንድሪያስ » Wed Jun 02, 2004 9:48 pm

ቅቅቅቅቅቅ ናፍቆት" ሰላም አለሽልኝ ወይ ? ሰራ ይበዛል አይደል? እንደምንም እያልሽ ቀጥይው :: እኔ ጥሞኛል::

ወንድምሽ እንድሪያስ
እንድሪያስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1784
Joined: Fri Mar 19, 2004 10:55 pm
Location: *****

Postby Debzi » Wed Jun 02, 2004 11:47 pm

ሰው የማያውቀውን ሰው እንዲህ ይናፍቃል? ውይ በናፍቆትሽ ሙትት ነበር ያልኩት::
የዛሬውን ጽሁፍሽን ደግሞ ጀምሬ እስከምጨርስ ስንተከተክ በሳቅ! እንኳን መጣሽ አቦ::

ይሄ አለማየሁ ሲቀልድብሽ ደሞ ተው እያልኩ ከሱም ጋር ጥል ገባሁልሽ:: ሁለተኛ እንዲህ ብዙ እንዳትቆዪ እሺ? ይቅርታ I meant to say, OK?

ለvacation 'እዚህ' ከመጣሽ ትንሽ ቅቤ አልቆብኝ ነበር ላስቸግርሽ? ቀልድ ምናምን እንዳይመስልሽ ደሞ::


We all love you!

ደብዚ
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

ለ አለማየሁ ይቅርታ ለዓለማየሁ

Postby Debzi » Thu Jun 03, 2004 11:35 am

ዓለማየሁ ከዚህ እንደማትጠፋ ስለማውቅ ይቅርታ ለመጠየቅ ነው አሁን የመጣሁት ዓ እንዴት እንደሚጻፍ ገና ዛሬ ነው ያወኩት እስከዛሬ አለማየሁ እያልኩ ነበር የምጽፈው ይሄው አርሜዋለሁ ዓለማየሁ እንግዴህ ይቅርታዬን ተቀበል please please በማለት እማጸንሀለሁ እንግሊዝኛውንም ያደባለኩት you know whoን ደስ እንዲላት ብዬ ነው :wink:

ደብዚ
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

እባካችሁ.....????

Postby ጨመዳ » Fri Jun 04, 2004 1:37 am

ሰላም !!!!
አለማየሁ እና ደብዚ እባካችሁ ጣልቃ እየገባችሁ ጨዋታ አታቆርፍዱ ምክንያቱም ብሂሉ የላችሁም
ለምሳሌ:dbzi>እንዳትቆዪ እሺ? ይቅርታ i meant to say, ok ?....ምን ማለት ፈልገህ ነው??

አለማየሁ>...im so glad your not up set over my
my ቀልድ ምናምን ነገር?
i ሎ ቭ ዩ በቃ ምናምን ነገር.....የዚህኛው ደግሞ
ከአባ ጫኔ የበለጠ ነው..... ማፈሪያዎች :oops:
ለማንኛውም <ናፍቆት> አንድ ጊዜ እንዳለችው
የጻፍኩትን መልሼ ማንበብ ደስ ይለኛል ብላለች እና
እስቲ እናንተም ሞክሩ?? ዝም ብላችሁ<ሙዝዝዝ>
ከምትሉ እሺ ምናምን ነገር....????

ጤና ይስጥልኝ!!
ዝነኛው ጨመዳ !!
ጨመዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Wed Oct 22, 2003 8:23 pm
Location: waqo Qubeic

ለ ጨmeda

Postby Debzi » Fri Jun 04, 2004 2:21 am

እረ አንድ በሉት ጨመዳ ምን ነካው
በቃላቶች ዱላ የሚፈናከተው

ውዱ ወንድማችን እኛን ማፈሪያ ካልክ
እኔም እልሀለሁ get lost ከዚህ መድረክ


ከሠላምታ ጋር
ደብዚ
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

ወይኔ ሰዉ ማስቸገር!!

Postby ዓለማየሁ » Fri Jun 04, 2004 2:28 am

ናፍቆት ይቀርታ እስቲ ለቅጽበት አንዴ.. :!:

ስማ! አንተ ጨመዳ!ያጨማድህ እና! እኔ ኮ ቢሄሌን ለመቸርቸር አይደለም ያለሁት! ዋርካም መወያያ ቦታ ነዉ እኮ! በሰላም የማዋየዉም ናፍቆትን ነበር! አንተን ማን ጠራህ?!! የራስህን ብቻ መልሰህ መላልሰህ ከማንበብ ይልቅ እስኪ ከዚ በፊት ሌሎች የጻፉትን አንበብ. Then you will understand whats going on instead of making a fool of yourself like you just did.ለስድብ አትቸኩል ምን ያጣድፍሀል? ማክዶናልድ ነዉ መሰለኝ የምትስራዉ.. :twisted:

OK naffkott, ሱስ የሚያስይዘዉን ጨዋታሽን ቀጥይ

C ya!

P.S Debzi its ok about the spelling. No harm done. :D
Last edited by ዓለማየሁ on Sat Jun 05, 2004 2:53 pm, edited 1 time in total.
ዓለማየሁ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2358
Joined: Mon Dec 15, 2003 4:06 pm

Postby wolfi » Sat Jun 05, 2004 2:11 pm

ናፍቆት የምትባይው ግለሰብ እንደው በዚህ ምላስሽና ጣቶችሽ ምነው ሌላ ነገር ብትጽፊበት?ውጭ አገሮቹን(.ከኔም ጭምር) ብለሽ ብለሽ አርመሽ አስተካክለሽ አትችያቸውም.አሁን ያንዲት አበሻ ኬዝ ተሳካ አልተሳካ ምን አሳሰበሽ?ስንት የሚታሰብ እያለ?አንቺ ዱሮ ውጭ በንበርሽበት ጊዜ ያንቺስ ኬዝ ምን ነበር?እርግጠኛ ነኝ የመንጌ ጸሀፊ ነበርኩ ምንምን አላልሽም?ወይም ጴንጡሌ ምናምን ነገር.አሁን ልነግርሽ የምፈልገው ውጭዎችን ለማረም እንደ ጸባይ ማረምያ ቆርጠሽ የተነሳሽ ይመስላልና ተይው ይቅርብሽ ትርፉ ድካም ነው.ጉልበትሽንና እውቀትሽን ለሌላ ነገር አውይውና እናንብብልሽ የምትፈልጊ ከሆነ.በተረፈ ሀይለኝ ተራቢ እንደሆንሽ አጻጻፍሽ ይናገራል.
በይ በተረፈ በሚቀጥለው ጥሩ ወግ ይዘሽ ከቸች በይ
መልካም ጊዜ
wolfi
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Fri Sep 19, 2003 7:21 am

Postby ዋቆ » Sat Jun 05, 2004 11:01 pm

ናፍቆት ሰላም ባለሽበት:ይሁን::ሁሉም አንቺን ናፍቆ ሊሞት ነው:: ቁምነገር ያዘሉ ጽሁፎችሽን አደንቃለሁ:: አዲስ አበባ ከመጠጥና ጭፈራ ሌላ ምን የመዝናኛ activity አላችሁ? እኛጋ ሁሉም በያይነቱ አለ::

በነገራችን ላይ አለማየሁ ትልቅ የcyber ፎንቃ ውስጥ የገባህ ይመስለኛል:: አደገኛ ስለሆነ ተጠንቀቅ ቅቅቅቅቅቅ
ዋቆ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 455
Joined: Sun Nov 16, 2003 2:12 am

ወቸ ጉድ!!

Postby ዓለማየሁ » Sun Jun 06, 2004 11:33 am

Hey naffkot,

How is hager bet? is everthing aman? ደሞ አዲስ ፔጅ እስኪጀመር ድረስ እጠብቃለሁ ብለሽ እንዳትጠፊ! ሽ? k?

ዋቆ ለካስ የጠፋህዉ የሳይበር ፎንቃ ይዞህ ነዉ!! እኔ ግን ሲስተርን I love you የምላት በ እህትነት ነዉ! N-Day!! Naffkott iz ፈኒ በቃ ማናምን ነገር!

ቻዉ
ዓለማየሁ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2358
Joined: Mon Dec 15, 2003 4:06 pm

ፎንቃ??

Postby አባዊርቱ » Fri Jun 11, 2004 4:59 am

በግዜር ፎንቃ ምንድነው??

ዛሬ ገና ቃሉን መስማቴ ነው?? ለነገሩ ቃሉ እራሱ ደስ ይላል:):):)
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

ለ አባዊርቱ....

Postby ደጉ » Fri Jun 11, 2004 12:58 pm

ፎንቃ ማለት ......ፎን ተዋትና (ንቃ) ብቻ ውሰድ (ንቃ ሞኝ አትሁን) ሲሆን (ቃ) ማለት ብለህ ከወሰድክ ደግሞ .....የበሰለ/ች.....እድሜዋ/ው የጫረ የሚል ትርጉሙ ሊሰጥህ ይችላል ...... ፎንቃ ማለት ግን እኔ ራሴ አላውቀውም...የምሬን ነው:-)
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4412
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby Debzi » Fri Jun 11, 2004 1:09 pm

ፎንቃ ማለት እፍ እፍ ያለ ፍቅር infatuation ነገር ይመስለኛል ስገምተው::

እስቲ ቁጭ ብለን የዋቆን መልስ እንጠብቃለና እንግዲህ ሌላ ምን እናደርጋለን

በነገራችሁ ላይ ምነው ናፍቆት ጠፋች ደሞ!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ዮኒ » Fri Jun 11, 2004 3:44 pm

አስቸኩአይ


ናፍቆት የምትባልን ሞልቃቃ/ሞዛዛ ጽሁፍ ማንበብ ነው አሁንስ ያስጠላኝ..................

እባካችሁ የሱአን ብቻ ለይቸ የማጠፋበት ዘደ ካለ ንገሩኝ
ከምስጋና ጋር
ዮኒ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Mon Dec 08, 2003 10:26 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 6 guests