ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

that's right joe

Postby አንዲ » Fri Apr 23, 2004 5:17 pm

ናፍቆት,
በአማርኛ የጻፍሽው ደስ የሚል ወግ ነው:: ግን joe ትክክል ነው:: አጻጻፍሽ ደስ የሚል ሆኖ ሳለ ሁልጊዜ እንደምትወቅሻቸው አበሾች ( እዚህ ጋር ያንቺን tone
ለመያዝ ነው እንጂ ሁሌ እንደምልሽ አበሻ በሙሉ እንደህ ነው/እንዲያ ነው ለማለት ይከብደኛል) ጽሁፉ ጭልጥ ያለ ሀሜት ነው:: ጋብዘው ያስተናገዱሽን ሰዎች እንደዚህ መንቆር ሌላ ነገር አይደለም:: ያልተስማማሽ ነገር ካለ ለምን ለሴትየዋ አትነግሪያትም ገና ለገና እስቲ ምን ታረግ ይሆን እያሉ ቤትዋ ተመላልሶ እዚህ መተሽ ከምታሚያት ደግሞ :!:
There are many things in life that will capture your eyes; and a few things that will capture your heart, pursue those.
አንዲ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Fri Sep 19, 2003 11:06 pm
Location: kiribati

Postby አራዲት » Fri Apr 23, 2004 7:42 pm

ናፍቆትዬ you are such a character. I love the way you express your self. Thank you again for putting some smile on my face.
አራዲት
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Tue Nov 18, 2003 7:24 pm

Postby አብራራው » Fri Apr 23, 2004 8:08 pm

ናፍቆት

በጽሁፍሽ ውስጥ የተንጽባረቁት ነገሮች ሁሉ እውነት ናቸው ብዬ ለመቀበል አይምሮዬ እንቢ አለኝ; የግድ በቪዲዮ የተቀረጸ ምስል ካላየሁ በስተቀር በቃላት ቅምር ብቻ አላምንም ማለቱ ነው መሰለኝ;;
ውሸት ነው ብዬም እንዳልደመድምም ይህው አይምሮዬ መልሶ ውሸት ለመሆኑስ ምን ማስረጃ አለህ ? ብሎ አፋጠጠኝ;; በኋላ ከአይምሮዬ ጋር በሚከተሉት ነጥቦች ተስማማን ;;
ጽሁፍሽ ልቦለድም ይሁን እውነተኛ ገጠመኝ የራሱ ጉዳይ ነው;; ግን አገላለጽሽ ስነ-ጽሁፋዊ ውበቱ ደስ የሚል ነው:; ልክ አጠገብ ሆነሽ እንደምታወሪ አይነት ቃላቶቹ ቀበጥበጥ ያለና ቀጠን ያለ የአንስታይ ቅላጼ ያለው ድምጽ እየሰጡ ያዝናናሉ ;;
ከሁሉ ለሁሉ
ከዚህ ካድካሚ ህይወት ከሚባለው ጊዜ ውስጥ አንዳንዴ ለትርኪ ምርኪም ሰአት መመደብ ጥሩ ነው ::

ያልሺው በድርብ ጽሁፍ ተጽፎ ባማሩ ቀለማት ደምቆና አሸብርቆ በባለመስተዋት ፍሬም ግድግዳላይ ሊሰቀል የሚገባው ጥቅስ ነው:;

እንኳን ይሄ የመርካቶ ጮሌ እየገጠመ የሚሸጣቸውም ጥቅስ ተብለው ለግድግዳ ይበቁ የለ?

ለምሳሌ ከጎረቤቱ የተጣላ ሰው ቤት ግድግዳ ላይ

ሀኪም አላወቀው በረታ ስቃዬ
ከጎኔ ሻጥ ብሎ ዋናው በሽታዬ

አግኝቶ ያጣ ሰው ቤት ግድግዳ ላይ ደግሞ

ዛሬ እጅ ሲያጥረኝ እንዲህ ጭር ያለው
ሰው ብቻ ነበረ ደጄ ለወትሮው

ችግርና ድህነት የበዛበት ሰው በት ግድግዳ ላይ

ሞልቶ ላይሞላልኝ እባትታለሁ
ዛሬም እንደትናት በስቃይ አለሁ

በሀሰተኛ ፍርድ የተጎዳ ሰው ቤት ግድግዳ ላይ የሚገኝ

ውልቸም ወልቸም ስል በግሬ ስዋበው
በእጃቸው የሄዴት ጉድ ሰሩኝ ቀደመው

ሌላውን ሌላ ግዜ

ባይ በርቺ
አብራራው
ጠባብነት ለዋያኔም አልበጀ
አብራራው
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Wed Nov 05, 2003 5:06 pm
Location: ethiopia

ስላም ምነው ተጠፋፋን

Postby ሚካኤሎ » Fri Apr 23, 2004 9:48 pm

መን አይንት አገር ንው ድሀ ይበዛበት
ሚካኤሎ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Fri Apr 23, 2004 9:29 pm

Postby ዋቆ » Sat Apr 24, 2004 5:21 am

ናፍቆት ሰላም ላንቺ ይሁን ልቤ ውልቅ እስከሚል ነው የምታስቂኝ:: አድራ አትጥፊቢን:: ይህን በአማርኛ ብቻ ብለሽ አትጨነቂ በማንኛውም ቁዋንቅዋ ይሁን የአዲስ አበባ ጫወታሽን ጀባ በይን::

ከውጪ የሚመጡት በቃ ጅላን ጅሎች ናቸው ቶሎ ያስበላሉ በይኝ:: ባይገርምሽ ከገጠር ለመጀምሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ስመጣ በምድር ላይ ይህ ሁሉ ፎቅ ያለ አይመስለኝም ነበር:: መንገድ ላይ ቁሜ ሙሉ ቀን መኪና ስቆጥርልሽ ዋልኩ የአዲስ አበባ ልጆች ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸው አዲስ መሆኔን ሲያውቁ.... እነዚህ ከውጪ የሚገቡት እራሴን አስታውሰውኝ ነው::

Please keep up the good work

PS
አዲስ አበባ መሆንሽን ለማወቅ የፈለግሁት የውጪ ጉዳችንን ብዙ ስለምታውቂ እዚሁ ውስጥ አዋቂ ትሆኚ ብዬ ነው:: አሁንማ እዚያ ከሆንሽ ብዙ ተዝናንተን ለማውራት እንችላለን ቅቅቅቅቅቅ
ዋቆ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 455
Joined: Sun Nov 16, 2003 2:12 am

ይድረስ ለ joe

Postby ትምህርት » Sat Apr 24, 2004 7:21 pm

joe ናፍቆትን ""አበሻን አጥብቀሽ ትኮንኛለሽ"" : ""ሃሜትም ትወጃለሽ"" ብለህ ወንጅለሃል:: እኔ እንደገባኝ ናፍቆት ከኢዮትዮጵያ ውጭ ያለነው ወደ አገር ቤት ብቅ ስንል የምናደርገውን ድርጊት በተጨባጭ ልታሳየን የሞከረችው:: ይህን ነገር እዚህ ማንሳቷ ግን ጠቅላላ ሃበሻን ለመወንጀል አልመሰለኝም:: ምክንያቱም ሃበሻ ማለት በውጭ ያለው ብቻ ሰላልሆነ:: እኔም ብዙ የሚገርሙና የሚደንቁ መሰል ድርጊቶች ሲፈጸሙ አይቻለሁና::

ስለ ባለ ውሻዋም የነገረችንም ሃሜት ሊባል የሚችል አልመሰለኝም:: ለምን? በናፍቆት ፅሁፍ ውስጥ የውሻዋ ባለቤት ሥምም አልተነሳም:: እንኳን የናፍቆትን ጎረቤት ይቅርና ናፍቆትን አናውቃትም:: በዚህ መድረክ ሁላችንም የብዕር ሥም እንደምንጠቀም አንዘንጋ:: ስለዚህም ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይሏል ይኸ ነው::

ወደ እኔ ፅሁፍም ስንመለስ: የፅሁፌም ዓላማ ለናፍቆት ""በዓል እንዴት አለፈ?"" ጥያቄ የበኩሌን መልስ መስጠት ነበር:: በዚህ ፅሁፍም የማንንም ሥም አልጠቀስኩም:: የኔ ፅሁፍም እንዴት እንደ ሃሜት እንደተቆጠረ አልገባኝም::

የናፍቆትን ፅሁፍ በትምህርት ሰጭነቱ ላደንቀው እወዳለሁ:: የአብራራው ፅሁፍም እንደዚሁ::

joe ሌላ ጊዜ ከእንደዚህ ዓይነት ውንጀላ ተግባርህ እንደምትቆጠብ ተስፋ አደርጋለሁ::

ወቀሳ ካበዛሁብህ ይቅርታ!!

ናፍቆት ስለ እኔ ፅሁፍ ለሰጠሽው አስተያየት የምለው የለኝም::

ደህና ሁኑ::
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ሰላም ቤቶች ጫውታችሁ ይጥማል

Postby ndave » Sun Apr 25, 2004 5:46 am

በተለይ መብረቁ የጻፍከው በትክክል እኔም ደርሶብኛል : እዴት መሰለህ ::

በ2000 ከስራ ባልደረቦቼ ጋ ሀገር ቤት
ሔጄ ነበረ ::
እና እዛ አንድ የጉዋደኛዬ እህት ታገባለች
ሰርጉም ጣይቱ ሆቴል ነበረ (ስሙን) ካልተስሳትኩኝ:
ከዛም ከባልደረቦቼ ጋ እሰርጉ ቦታ ደረስኩኝ
በር ላይ ዘበኛ አለ : ስንገባ ዘበኛውን ልክ ስናልፈው ያው በአማረኛ እደምን ዋሉ ስላቸው አማረኛዋን ሰሙና ከባልደረቦቼ ለይተው አትገባም አሉኝ: ችግር ተፈጥሮ መጨረሻላይ መሽራዋ ተጠርታ ልንገባ ቻልን::

በርግጥ እኔም ባልደረቦቼም አለባበሳችን በቦታው ላይ የተለየ ነበረ ይህም ስል እዛው ኑዋሪ የሆኑት ዘንጠው ነበረ አቀራረባቸው እኛ አለባበሳችን ከኑዋሪዎች(ሰርግ ላይ ከተጠሩት) በታች ነበረ ግን ዘበኛው ለምን አብረውኝ የነበሩትን ነጮች አልከለከሉውቸውም ?ለምን እኔን ብቻ በአማረኛ እደምን ዋሉ ባልላቸው አልፌ ነበረ


ደግሞኮ የተጠራሁት እኔ ነኝ

እንዲህ ነው የገጠመኝ እላችሁዋለሁኝ

ሰላም ሁኑልኝ:;
ndave
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Mon Sep 22, 2003 10:29 am

Postby ናፍቆት » Mon Apr 26, 2004 7:38 am

ማርስ - 'ፋፌ' ያልሽውን ቃል ሳነበው በጣም ነው ያሳቀኝ:: ቃሉን ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማው ነው:: ግን from the context ትርጉሙ ገብቶኛል::
'ፋፌ!' I like that.

ሌሎቻችሁ ተዋጠላችሁም አልተዋጠላችሁም ለውሻ የተጠራው ጥሪ እውነት ነው:: Joe - አንተ እንግዲህ 'ውሻ ሀራም ነው:' የሚባልበት አንዱ እስላም አገር ሄደህ ተሸንቁረህ ከሆነ - እኔ አላውቅልህም::
በዚህ አስተያየት አሁን አሁን የመኪና brand names እንደ አባት ስምነት እያገለገሉ እንደመጡ ብነግራችሁ ...... like .... ቶማስ ብላችሁ ስትጀምሩ ... ቶማስ የቱ? ቶሚ 4Runner, መሰረት .... መሰረት የቷ? መሲ መርሰዲስ .... ኤልሲ Rav4 ጆኒ ላንድክሩዘር ... ምናምን እያሉ ነው the high class guys የሚጠራሩት ... ብዬ ብላችሁ ይህንን ደሞ በቅንፍ ውስጥ 'ውሸት' በይበት ልትሉኝ ነው አይደል? ግን እየተባለ ነው:: ግን Of all the countries, here in Ethiopia ይህን ያህል ያኗኗር gap መኖሩ...... አይገርምም?

አንዳንዶቻችሁ የ 'ሀሜት' definition የጠፋባችሁ የምትመስሉም አላችሁ:: ለነገሩ ቢጠፋባችሁም የሚጎዳ ነገር አይደለም::

ሌላ ሌላውን.... እ....... 'እኔና አንዳንድ ዋርካ ላይ የሚጽፉ ሰዎች ትንሽ የአስተሳሰብ ልዩነት አለን" ብዬ አልፌዋለሁ:: 'ኢትዮጵያ' ከምትባል አንድ አገር ስለተፈጠርን ብቻ የግድ አንድ አይነት አስተሳሰብ ይኑረን የሚል ... ይሄ .... ወዝ የሌለው እምነት የለኝም እኔ:: አመዳም ነገር አያስጠላችሁም? እኔ በበኩሌ አልወድም::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby saturn » Mon Apr 26, 2004 8:38 am

ኦ ቦይ! እንዴት ነው ነገሩ?
saturn
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Wed Mar 10, 2004 6:51 pm
Location: saturn

ተባረኪ

Postby ህይወት » Mon Apr 26, 2004 11:40 am

ናፍቆትዬ አቦ ይሄንን የምትፅፊባቸዉን ወርቅ እጆችችሽን እግዚአብሔር ዳይመንድ ያጥልቅባቸዉ:
እነዚህ አናምንም ምናምን እያሉ የሚንጣጡት እዉነታዉንና ስራቸዉን አሳምረሽ ስለነገርሻቸዉ ነዉ:: ናፍቆትዬ እኛ አድናቂዎችሽ ብዙ ነን እና በናፍቆት ነው የምንጠብቅሽ!

ሰላም ፍቅር እና ጤና የምመኝልሽ ህይወት ሚኒባስ ነኝ ከመገናኛ
ህይወት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 167
Joined: Mon Dec 15, 2003 5:11 pm

Postby አራት:ኪሎ » Mon Apr 26, 2004 1:42 pm

አይ ናፍቆት!!
በነገራችን ላይ ከዚህ ብፊት እኢይሮፕ እንድነበርሽ ነው!
አራት:ኪሎ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Fri Apr 23, 2004 12:05 pm

ለናፍቆት

Postby አካኪ ዘራፍ » Fri Apr 30, 2004 12:42 am

i guess you have a point. እንግዲህ እንዳልሽው ከውጭ የተመለሱ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን አለም እየፈጠሩ ይመስለኛል:: I have no reason to doubt your assesment....ለነገሩ ወደአገራቸው ጠቅልልለው የተመለሱት ይቅርና ለሁለት ሶስት ሳምንትም ሰንብተው ወደስደት አለማቸው ሲመለሱ ተለውጠውና ያልሆኑትን ሆነው የሚመጡብን ስንት አሉ መሰለሽ:: የከፋው ደግሞ አገር ቤት ሄዶ ሲያነጅብና ገንዘቡን ለፍቶ እንዳላጠራቀመው ሲበትን ከርሞ ባዶ እጁን ተመልሶ ጉዋደኞቹ ከጉድ እንዲያወጡት የሚለምን ሁሉ አለ (before anybody said anything, ከአገሬ ከወጣሁ 10 አመት በላይ ሲሆነኝ እስካሁን ተመልሼ አልሄድኩም....ስለዚህ my comments could sound one sided....sorry for that!)

በአጠቃላይ ሳየው ይህ ሁሉ የሚመነጨው እራስን ከመርሳትና በራሳችን ላይ ያሳደርነው ግራ የገባው በራስ አለመተማመን ሁኔታ ይመስለኛል:: ለማንኛውም ንፍቆት በጀመርሽው ቀጥይ...ምን ይታወቃል አንድ ቀን ብሎት እኔና መሰሎቼ ወደአገራችን ስንመለስ አሁን የሚባለው አይነት ልንሆን ስለምንችል ከወዲሁ ምን ልንባል እንደምንችል ማወቁ ጥሩ ትምህርት ይሆነናል

በሉ ውሻዬን ለጉዞ ላዘጋጃት....አገር ቤት ገብታ ፋራ እንዳትሆንብኝ :D :D
አካኪ ዘራፍ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Sat Jan 17, 2004 6:45 am

እኔም ደርሶብኛል!!

Postby ትምህርት » Sat May 01, 2004 8:46 pm

የቤቴ ገጠመኝ::
አንዷ እህቴ ልትጠይቀን/ለዕረፍት ወደ አገር ቤት ትመጣለች:: አንድ ወር ከእህታችን ጋር በጥሩ ሁኔታ አሳለፍን:: ጊዜው ይሮጣል:: የእህታችን መመለሻ ጊዜ ሲደርስ ያልጠበቅነው ዱብዳ ደረሰ:: እህታችን የመቀበያ ድግስ ካልተደረገለኝ ሞቼ እገኛለሁ አለች::

ቤተሰብም በዚህ ባልተጠበቀ ጊዜ በመጣ ሃሳብ ግራ ተጋባ:: :shock: ይህ የእህቴ ፍላጎት ብዙ ጥያቄዎችን አስከተለ:: በመሸኛሽ እንዴት የእንኳን ደህና መጣሽ ድግስ ይደረጋል? የድግሱን ወጭ ማን ይሸፍናል? ተጋባዦቹ እነማን ናቸው? የድግሱ ቦታ: መጠን: ወዘተ

ከጊዜና ውይይት ብዛት አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ አገኙ:: ሌሎቹ እስካሁን በጥያቄነት እንዳሉ ናቸው::

ጉዳዩ ከቲዎሪ ወደ ተግባር ተሸጋገረ::
-ከውጭ የመጡ: ቤተሰብ የማያውቃቸው አባላትን ያሉበት ኮሚቴ ተቋቋመ::
-ለድግሱ ወጭ ብድር ከአንድ ዘመዳችን ልንወስድ:: በውላችን መሰረት: እንደተመለሰች ለአበዳሪው አንድ አዲስ መኪና ልትልክለት:: የመኪናው ሞዴልና የፈረስ ጉልበትም ታውቋል::

እድሜ ለኮሚቴው አባላት: ድግሱ በአጭር ጊዜ ተዘጋጀ:: የወጭው ነገር ያስደነግጣል:: ገንዘቡ ሲያልቅ ከአንዴም ሁለቴ ተጨማሪ ብድር ከአበዳሪው ወስጃለሁ:: አብዳሪም በእርግጥ ይኸ ሁሉ ገንዘብ ለድግስ የሚውል ነው? ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ: መልሴም ""አዎ"" ነበር::

የድግሱም ሰዓት መጣ:: ያለ ቪዲዮ ድግስ የለም::

ድግሱ በቪዲዮ መቀረፅ ስለነበረበት: ዘመናዊ ቢዲዮ ካሜራ ተውሰን አዘጋጅተናል:: ጓደኛዬ ይህንን ካሜራ ለእኔ አውሶኝ አያውቅም:: ለኔና ለመሰል ተዋሾች የሚያውሰን ሌላ አሮጌ ቪዲዮ ካሜራ አለው:: ለምን? ስለው: ይኸ ወደ ሰለጠነው ዓለም እንደሚሄድ አጥተኸው ነው? ብሎኛል::

ካሜራው ሲሞከርም በትክክል ይሠራል:: አንድ ትልቅ ችግር ተፈጠረ:: ችግሩም ካሜራው ቀን በቪዲዮው ላይ ይቀርጻል:: ይህ እንዴት ችግር ነው የምንል አልጠፋንም:: እህቴ ቀኑ መቀረፁን በጣም ነው የጠላችው:: እኛም ሆንን የኮሚቴው አባላት ቀኑን ወደ ኌላ: ማለትም እህታችን አገር ቤት በመጣችበት ቀን አካባቢ: መልሶ ማስተካከል አቃተን:: የካሜራውን ባለቤት ጉዳችንን ብንነግረውም እሱም ሊረዳን አልቻለም:: ለሱም ቀኑን ያስተካከለለት ለካ ሌላ ሰው ነበር:: አይ ዘመናዊ ነገር:: በስንት ድካምና ጭንቀት የቀን መቅረጫው መፍትሄ ተገኘለት:: ቀኑ ጭራሽ እንዳይሰራ ተደረገ:: ከውሸትም ውሸት ይመረጣል::

ታሪኩን ላሳጥረው:: ተጋባዦቹ በሙሉ መጡ:: አንድም ተጋባዥ ባላውቅም ሁሉም ከውጭ እንደመጡ ተነግሮኛል:: ድግሱ የተዋጣለት ነበር:: ቪዲዮውም ይህን ይመሰክራል:: :D :D

እህቴም በሰላም ተመልሳለች::

ከድግስ ተከትሎ የሚመጣው የድግስ ወጭ ነው::

አብዳሪ
ከአንድ ወር በኌላ እህትህ አልደወለችም? እያለ ይጠይቃል::
በሁለተኛውም ወር እህትህ አልደውለችም? እንደዚህ እያለ ሲጠይቅ ስድስተኛው ወር አለፈ:: በዓመቱ ጉዳዩ ለዘመድ ጉባኤ ቀረበ:: አገር ቤት ያለነው እህታችን የተበደረችውን ለመክፈል ተስማምተን ግን ባንዴ መክፈል ስለማንችል በየወሩ የተወሰነ እንድንሰጥ ተወሰነ:: ብድሩ ተከፍሎ የተጠናቀቀው እኔ እዚህ ውጭ አገር ከመጣሁ በኌላ ነው:: እህቴ የተበደረችውን ለምን እንዳልከፈለች ያወቅኩትም አሁን ነው::

እህቴም ይህን ጉዳይ አንስቼ እንዳልጨቀጭቃት በተደጋጋሚ :( :( አስጠንቅቃኛለች::

ታሪኩ ባጭሩ ይህን ይመስላል::

ቸር ይግጠመን::
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ወይ ጉድ

Postby ቆንጂት1 » Sat May 01, 2004 9:15 pm

ትምህርት ይቅርታ አድርግልኝና እህትህ ራስ ወዳድ ናት ብላት ድፍረት አትቁጠርብኝ:: ቤተሰቦቿን ችግር ውስጥ ከታ ጸጥ ማለቷ ሁለተኛ ጥፋት ሰርታለች::
ቆንጂት1
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Fri Feb 27, 2004 12:05 am

ድግሱ በቀርስ?

Postby ትምህርት » Sat May 01, 2004 10:54 pm

ሃይ ቆንጂት 1

በሃሳብሽ እስማማለሁ:: ግን እውጭ ያለነው ብዙዎቻችን ራስ ወዳዶች አይደለንም ትያለሽ :?: ድግሱ ቢቀር እኮ እዚህ ሁሉ ዕዳ ውስጥ አንዘፈቅም ነበር:: ሌሎቹ ያደረጉትን ሁላችንም ለምን ማድረግ አለብን :?: ለቪዲዮ ተብሎ ዕዳ!!

ገንዘብ ያበደረን ዘመዳችንም ጋር ብዙ ንግግር የለንም:: ተኮራርፈናል::

ደህና ሁኑ!!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests