ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ናፍቆት!

Postby አልቦ » Thu May 06, 2004 11:38 am

.........ጽሁፍሽ ሲመች! ...............ነፍስ ነገር
አልቦ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Wed Apr 28, 2004 3:09 pm

እኔስ ጠፋሽ ብዬ ነበር::

Postby ትምህርት » Thu May 06, 2004 5:14 pm

ናፍቆት ገጠመኞችሽን ስትገልጭ በጣም ደስ ትያለሽ:: ከዚህ በፊት የፃፍሽውን ፅሁፍ አንብቤ ተከፋሁ:: ተናድደሽ የጠፋኝ መስሎኝ ነበር:: ለተሳዳቢዎች መልስ መስጠት የለብሽም:: ፅሁፍሽን የምንናፍቅ ብዙ ነን!!!

አንዳንዱ ከመሬት ተነስቶ ሰውን ይዘልፋል:: ስድብ እዚህ ቦታው አይደለም:: እንዴት ባንድ ፅሁፍ አንዱ ሌላውን ትምክህተኛ: ትእቢተኛ... ማለት ይችላል? GIZO ልክ አይደለህም:: ሌላው ደግሞ በዚህ መድረክ ላይ ለእገሌ ነው የፃፍኩት ይላል:: ደብዳቤ ይመስል:: የግል ጭውውት የሚፈልጉ ለዚህ ተግባር የሚያገለግል የ Chat መድረክ እዚሁ ዋርካ ይገኛል::

ሁላችንም ሥርዓት እንደምንከተል ተሥፋ አለኝ:: ሥርዓት የማስከተሉን ተግባር እንዲከታተል ለ web administrator አቤቱታዬን በሜይል ልኬያለሁ:: ሁላችሁም እንደዚህ ህገወጥ ተግባር ስናስተውሉ ቅሬታችሁን እንድትገልፁ አሳስባለሁ::

መልካም ይግጠመን::
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ናፍቆትየ

Postby ማርስ » Thu May 06, 2004 5:38 pm

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ እሙ ሀሪፍ አባባል ብለሻል::[ለ እንጀራ ብሎ እንጀራ የሌለበት ሀገር መሰደድ] አድንቄልሻለው::

በርቺ ቀጥይበት ጽሁፍሽ ይመቸኛል::


የዘወትር አክባሪሽ ማርስ!!!
I dreamed of some one like you
you see too marvelous for it to be true.
-
-
Image
ማርስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Sat Jan 03, 2004 12:54 am

ትምህርት.... ላንተ ብቻ

Postby Joe » Thu May 06, 2004 7:11 pm

ትምህርት እኛ ማንንም አልተሳደብንም:: የሚሳደቡትንና ሀሜተኞቹን አቁሙ ነው ያልነው:: የጓደኛየን ስም እየጠራሁ ይህንን ሀሳብ በተመለከተ መልዕክት እዚህ ብተውለት ችግር ያለው አይመስለኝም:: ቻት ሩሙ ያልከው የት እንደሆነ አላውቀውም:: ለማንኛውም ለሀላፊዎቹ የጻፍከው ደብዳቤ ይዞ የሚመጣውን ነገር እየጠበቅሁ ነው::

ናፍቆት ይቅርታ አርጊልኝ, አሁንም የምትናገሪውን ነገር ለመዋጥ ብሞክር ከጉሮሮየ አልወርድልህ አለኝ:: ማወራረጃ ፈልግ እንዳትይኝ, ያልሞከርኩት ነገር የለም:: 'ለእንጀራ ብሎ እንጀራ የሌለበት አገር መሰደድ'---- ማርስ ምኑ ነው አሪፍነቱ? ማንም እንጀራ የሌለበት አገር አልተሰደደም:: ግድ የለም ይሁን አማርኛ ስለማይገባኝ ይሆናል:: እስቲ ማርስ ወይም ሌሎቻችሁ ሌላ ነገር ልጠይቃችሁ? እዚያ ሰርግ ቤት በግራ በኩል የተቀመጡት ባላገሮች ከትረካው ጋር ምን ግንኙነት አላቸው? አጨበጨቡ በቃ አለቀ:: ለማጨብጨቡማ ናፍቆትም ራሷ ስታጮኸው ነው የዋለችው:: ነው ወይስ ባላገሮቹ እዚያው ቁጭ ብለው የደስታ መልዕክት ልከዋል ተብሎ ስማቸው እንዲጠራ ነው የፈለገችው?

ናፍቆት በነገራችን ላይ እኔ ካገርቤት ከወጣሁ 3 አመት አልሞላኝም:: አዲስ በነበርኩበት ጊዜ ብዙ ሰርግ ቤት እሄድ ነበር:: እንዲህ አይነት ነገር አይቼ አላውቅም:: ዌል አፌን ሞልቼ አይደረግም አልልሽም:: ለመሆኑ ያንቺ ሰርግ መቼ ነው? ቅቅቅቅ አንቺ አሪፍ ነሽ የዋርካን ዩዘርስ ሊስት ማስነበብ ነው::

አንድ ነገር ብቻ: ውጭ የሚኖር አበሻ ሁሉ ተሸክሞ የሚኖር እንዳይመስልሽ:: ስንት ፕሮፌሽናልስ አሉ መሰለሽ:: ያሉበትን ደረጃ ብታውቂ ኖሮ እንዲህ አትወርጂባቸውም ነበር...

ስለስም የዘላበድሽው ደሞ ምንኛ ነው? ጎጃምወርቅ ወይም ጋሜ ስም ከሆነ ስም ነው:: ሽንትሽን እስክትጨርሽ ያሳቀሽ ምኑ ነው? ምኑን ነው አውቶቡስ ተራ የሰማሽው? ስሙን? ቅቅቅ አሁንስ አሳቅሽኝ:: በይ እኔም አንድ ሁለት ስም ልላክልሽና ሳቂ....... ጎርደን ብራውን, ታንያ ሽሚድት, ጌራርድ ሽሮደር.... የጀርመን ስሞች ናቸው:: በዚህ ሳቂና ነገ ደሞ ከራሽያ አንድ ጥንድ ስም እልክልሻለሁ::
ሰላም እደሩ
Joe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Tue Sep 09, 2003 11:27 am
Location: united states

Postby saturn » Thu May 06, 2004 9:12 pm

ዋው! በጣም ያስቃል-ከምር!
ጥሩ ትዝብት ነው::አቀራረብሽን እወደዋለሁ-ቦምብ ቃላት ፍለጋ ሳይጨናነቁ ሀሳብን በቀላሉ ማፍሰስ! ግን ግን አንዳንዴ ,በተፈጥሮ(መሰለኝ) በmass ስንተረብ ያልከፋን ተረቡ ጠበብ ብሎ ሲመጣ ቅር ይለናል::እናማ ክፍለሀገሮችን (ክፍልሽ ሲባል እናደድ ነበር) በነጠላ አትተርቢብን::አዲስ አበባ እድሜ ልኩን ኖሮ ከወለንጪቲ ወይም አርቦዬ (ቦታዎቹን በስም ነው የማውቃቸው) ሰው ያነሰ ከተሜነት ያለው ሞልቷል::
ባይሆን ኢትዮጵያ ውስጥና ውጪ ያለውን ልዩነት በጸጋ እየሳቅንም እያዘንንም እንቀበለዋለን::
im lovin it ቀጥይ............
saturn
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Wed Mar 10, 2004 6:51 pm
Location: saturn

Postby maki » Fri May 07, 2004 1:35 pm

sorry
Last edited by maki on Tue Mar 29, 2005 1:25 pm, edited 1 time in total.
maki
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Sun May 02, 2004 1:12 am

Postby GIZO » Fri May 07, 2004 2:22 pmይመችህ አባ...........እኔ መናገር የምፈልገውን በሙሉ ተናግረህልኛል..........መድገም አስፈላጊ አይደለም

አመሰግናለሁ
GIZO
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Fri Feb 27, 2004 12:59 pm

Postby Eritrossse » Sat May 08, 2004 1:11 am

---
Last edited by Eritrossse on Thu Jan 14, 2010 4:13 pm, edited 1 time in total.
Eritrossse
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Wed Sep 17, 2003 12:55 am

Postby ናፍቆት » Mon May 10, 2004 12:14 pm

ትምህርት - ተናደሽ የጠፋሽ መስሎኝ ነው ያልከኝ? No No, እንደዚያ አይነት weak personality እንኳን የለኝም:: እዚህ ስጽፍ I always keep in mind that I deal with different ppl with different background. እና ምናልባትም አንድ ቋንቋ ታይፕ ማድረግ ከመቻል በስተቀር the probability is so high that I can come across with ምንም አይነት common ነገር ከሌለን ሰዎች ጋር......

saturn - No No, መተረቤ አልነበረም:: የተሰማኝን በመጣልኝ መንገድ መግለጼ ነበር:: እንደውም ልንገርህ? የክፍለሀገር ሰዎች በጣም ደስ ይሉኛል:: ከቢሮ ድንገት ቤት ስደውል አንድ ዘመድ ከዛ መጣ ካሉኝ ከስራ ወጥቼ ቤቴ እስከምደርስ ድረስ በጣም ነው የምቸኩለው እና I become excited. ከስራ እንደወጣሁ በቀጥታ ወደቤቴ ነው:: Normally, ይሄ ከ 11:30 እስከ 12:30 ሰአት ባለው ጊዜ ቤቴ መግባት አልወድም:: ቀኑ ለማታው ጊዜውን የሚያስረክበበትን ሰአት በተቻለኝ መጠን ከቤቴ ውጭ ብሆን ነው የምመርጠው:: ..... የት ጋ ነበርኩኝ .... yeah.... ስለክፍለሀገር ሰዎች..... አንድ ነገር ልንገርህማ - ባለፈው እኛ ቤት ያለው የልብስ መስቀያ ገመድ ሰላሳ ጊዜ እየተበጠሰ ልጅትዋን ያጠበችውን ልብስ በሙሉ ታጥቦ ጭቃ እያረገው መከራዋን ሲያበላት ከርሞ አንዱ ከዛ መጥቶ እንዴት እንደተበተበው አላውቅለትም - ያው ስንት ቀኑ .. እፎይ ተብሏል.... እና ብዙ ነገራቸው ዘዴኛና ጥብቅ ያለ ነገር ይመስለኛል.... ጥብቅ ያለ.... ታድያ ሰርጉ ላይ ሲያጨበጭቡም እንደዛ ነበር::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby saturn » Mon May 10, 2004 2:36 pm

የመጨረሻ ጥያቄ ስለ ክፍለሀገር ሰዎች:-
* ለአዲስ አበባውያን ናዝሬት; አዋሳ;መቀሌ;ሀረር...(በደንብ አውቃቸዋለሁ) እና አሮሬሳ;ውጫሌ;ቦዲቲ;ደምበጫ...... ያው ናቸው? ክፍለሀገር?
የመጀመሪያዎቹኮ ከስፋት በቀር በብዙ ነገር ከአ.አ አይለዩም::

ps
ርዕሱን divert ያደርገዋል ብለሽ ካሰብሽ ጥያቄዬን ዝለይና keep on with what you begun.
saturn
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Wed Mar 10, 2004 6:51 pm
Location: saturn

Postby pawulos gneo gneo » Tue May 11, 2004 1:42 am

ናፍቆት??? .... ናፍቆት ማለት ..
1. ከመልእክቶችዋ ለመረዳት እንደሚቻለዉ.... ከነበረችበት የዉጭ ሀገር ኑሮ ተባርራ ወደሀገርቤት የተመለሰችና .. የዚህም ሰበብ በዉጭ (እስዋ በነበረችበት) የነበሩ ሀበሾችን አድርጋ የምትወስድ....

2. ትንሽ ከቀማመሰችዉ የዉጭ እዉቀት ጋር ሀገር ቤትም ብትሆን እንኩዋን ከማንም ዉጭ ካለ ሀበሻ እንድማታንስ በተለይ ለራስዋ ለማረጋገጥ የምትጣጣር..

3. ከባለግዜዎችም ጋር ትንሽ ንክኪ ስላላት .. ምንም አይመጣብኝም በሚል የእብሪት ስሜት ያሻትን መናገር የምትችል የሚመስላት..

4. አንድ ሰዉ አስቀድሞ እንዳስቀመጣት .. ንቀት ጥላቻ ጉራና ማን አለብኝነት የሞላት ናት.....

ምክር
... ጥሩ እዉቀትሽን ለጥሩ ነገር አዉይዉ
... በዉጭ ሀገር የሚኖሩ ሀበሾች ማን እና ምን እንደሚያደርጉ በደንብ ብታስተዉይ ብሶት የሚጭረዉ
ወርቅ ያፈሳልና ልብ በይ ""የክፋት መንገድ ወደ ክፋት ይወስዳል""

... ትንሽ በዉጭ ስላሉት ሀበሾች...
ከአረብ ሀገር እስከ አሜሪካ .. በስደት .. በትምህርትና በሌላም ምክንያት ከሀገራቸዉ ወጥተዉ ይኖራሉ.. የዘወትር ሀሳባቸዉና ህልማቸዉ አንድ ቀን ግዜዉ ሲፈቅድ ወደሚውድዋት ሀገራቸዉና ወገኖቻቸዉ መመለስና በቀሰሙት ማናቸዉም አይነት እዉቀትና ልምድ የሀገራቸውንና የወግናቸዉን ኑሮ መቀየር ነዉ.. ባሉበት ህእገር ሁሉ ጥረዉ በመስራትና ለማደግ በመጣጣር የሌሎች ምሳሌዎች ናቸዉ..
""ካገሩ የወጣ ሀገሩ እስኪመለስ..
ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ""
ነዉና.. ምንም ሳይንቁ ሰርተዉ ምንም ገቢ የሌላትና እያላት ተጥዋሪ በሆነችዉ ሀገራቸዉ ነዋሪ የሆነ ወገናቸዉን ይረዳሉ..

ከግርድና እስከ የጠፈር ሳይንቲስት ሙያ ዉስጥ በከፍተኛ ደረጃ በመሳተፍ በሙያ አለም አቀፋዊ ጥቅም ሲሰጡ.. በኢኮኖሚዉ የሀገራቸዉ ብቸኛ የገቢ ምንጭ ሆነዋል...

ይቀጥላል............................................
pawulos gneo gneo
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Mon Apr 12, 2004 3:49 am

Postby ቃልቻው ዝቄ » Tue May 11, 2004 8:54 am

people do u not get irony? satire? commedy?
does every writing has to be የአባባ ተስፋዬ አይነት ተረት ተረት እና ልጆች የተረቱ መልዕክት እያለ ፈትፍቶ የሚያጎርስ ብቻ ነው ማውራት የሚፈቀድለት?

ናፍቆት ቀጥይበት ቀልድ ቢመስልም ብዙ ቁም ነገር ነው የምታነሺ ያለሽው
Cocaine is a hell of a drug!!
ቃልቻው ዝቄ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Sun Feb 15, 2004 5:20 am

Postby ከቤ » Tue May 11, 2004 12:20 pm

ናፍቆት

አዳዲሱን የአዲስ አበባ ወረት በጥሩ ሁኔታ እያሳየሽን ነው:: በርቺ::

ለመሆኑ ሰአዳ ከሳውዲ : ልብ ይበሉ ከሊባን ይባላል ወይስ ያው የፈረንጁ አገር ብቻ ነው የሚጠራው?
ከቤ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 58
Joined: Mon Nov 17, 2003 1:29 pm

ለናፍቆት

Postby ብሪቱ » Tue May 11, 2004 3:05 pm

ናፍቆት ልብ ወለድ ድርሰትህን/ሺ/ አርስቱን እንዲህ ብትለውስ?"" በውጭ ሀገር ያሉ አበሾዎች በአዲስ አበባ"" ድርሰቱ ግን ማጋነን ይበዘዋል ለፈጠራው ግን በርታ/ቺ/
ብሪቱ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Sun Mar 07, 2004 5:37 pm

ናፍቆት if u don't mind sth. about የመብረቅ ገበያ ...

Postby የኔታ » Thu May 13, 2004 12:45 am

hey nafqot!

the accounts of Addis are presentable stuffs! አንቺም ታውቂዋለሽ ለነገሩ ...

እኔ ሰሞኑን የሰማሁት (i may even probably be late) is that there's a hot market for መብረቅ down there ... በጣም lucrative business እንደሆነም ነግረውኛል ...
I'm actually curious about it that some friends of mine are said to be out early in the morning over the እንጦጦ ተራራ hunting for a good marketable መብረቅ ... ለማንኛውም I found it to be coureageous and andventurous
would be interesting to learn few things about this new line of business, particularly the quantification: weight, volume, ... የአያያዝ (hunting) techniques ...

Is it one of those mercury type of things? በውነት በዚህ fortune ያከማቹ ሰዎች አሉ?

the very idea of capturing a መብረቅ for resale has fascinated me እና ናፍቆት እህታችን it's quite some of us over here that we'll be indebted to you if u can elaborate on this ...
------------
I want to tell u that u r a great source of updates on what's going on. we count on you ... keep up the good job
የኔታ
የኔታ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 23
Joined: Sat Nov 15, 2003 2:28 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 5 guests