ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

keep it going!

Postby maki » Thu May 13, 2004 11:55 pm

sorry!
Last edited by maki on Tue Mar 29, 2005 1:26 pm, edited 1 time in total.
maki
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Sun May 02, 2004 1:12 am

Postby ናፍቆት » Fri May 14, 2004 7:38 am

saturn - ባክህ ለጨዋታው ያህል ነው እንጂ ኑሮን በደንብ ለሚኖርዋት የአለም ክፍል ሰዎች we are all dumped in the same basket. ለነሱ..... እ.... የት ነው ያልከኝ? ....... ደንበጫ (by the way I found this to be a funny name - ግን ስትቀልድ አይደለም አይደል? እንደዛ የሚባል ቦታ አለ I hope) እ.. ኪጋሊም ይሁን ፕሪቶሪያ , as long as it's in Africa, we're seen with the same eye. ሰሞኑን የሰማሁትን አንዱ economist አንድ ትልቅ conference ላይ አቀረበ የተባለውን proposal ልንገርህማ -- አፍሪካ ብትረዳ ብትረዳ አላደገችም አለ:: እና his proposal was አፍሪካን ልክ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ይዛ እንድትቆይ ብቻ አድርጎ የሀብታም (ያደጉ በለው ከፈለክ) አገሮች ዜጎች እየሄዱ እንዲጎበኝዋት (like zoo ምናምን ነገር) እና በቃ የአለም antique ነገር ሆና እንድትቀመጥ ምናምን .... እና በዛ ገቢ ራስዋን manage እንድታደርግ ... ምናምን ነገር..... And when I heard this, I was like 'Wow! what a proposal!' ..... ሰውየውን ሳስበው ግን he has a point. A good point, in fact. (ስንት አመታት ነው ስንረዳ) ግን for the Africans, it might sound insulting or something. አይደል? ግን የሰውየውን radical የሆነ approach አድንቄለታለሁ:: እና........ where was I now? .......... For those who manupilates our economy (life) , we're all the same. እንደዛ መሰለኝ እኔ... ጋሞም ይሁን ጋና....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Fri May 14, 2004 7:43 am

የኔታ - ስለመብረቅ እኔም እንዳንተ በወሬ ደረጃ ነው የማውቀው:: ግን I think it's for real. እና በዚህ ብዙ ሀብታሞችም ይሸወዳሉ ምናምን ይባላል:: In fact, አንድ ዘመድ አውቃለሁ እናመጣልሀለን ምናምን ብለው ቦታው ድረስ ወስደውት ምናምን ከዛ I don't know what exactly happened. But it didn't work out. ዘመድየው ግን ብዙ ሺ ብር አጥቷል በዚህ:: ከሰማሁ ግን እነግርሀለሁ:: ግን እኔ የምለው ፈረንጅ አገር መብረቅ አይጥልም? እንጦጦ ብቻ ነው እንዴ?
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

ቅቅቅቅቅቅ.....ናፍቆት

Postby ደጉ » Fri May 14, 2004 8:03 am

...መብረቅ እንጦጦ ብቻ አይደለም የሚጥለው እዚህ እንደውም ይበዛል ...ያውም ሳይዘንብ ሁሉ አጉረምሮ ብቻ መበርቅ ይጥላል....ቅቅቅቅቅ ግን እዚህ ህብታም ስለሆኑ ፍለጋ አይሄዱም.....ቢፈለግም አይገኝም ....ሄይ! ስላፍሪካ ያቀረብሽውን አድኔቀዋለሁ ትክክልም ተገቢም ነው ...እንደዙ ታይተንም ገንዘብ ባገኘን......እና .......ቅቅቅቅቅቅ
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4448
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ናፍቆት » Fri May 14, 2004 11:11 am

እሺ የኔ ባለ ውጭ ሀገሮች....... - How u doin? Good? That's great! እዚህ ወርቅ ተወዷል:: እናንተጋስ? ነው ወይስ መወደድ የሚባል ነገር የለም እዛ?

U know what? ስለ ባለውጭ አገሮች bother ከሚያረጉኝ ነገሮች አንዷን ማውራት ፈለኩ ዛሬ.... ስራ ድብር ብሎኛል... አርብ አይደል? .... እኔ የምለው .... ይሄ የምትልኩት ገንዘብ (እቃም ሊሆን ይችላል) ስትልኩ በናታችሁ ለምን እንደሚውል እያሳወቃችሁ (እያወቃችሁ) ላኩ:: especially ወጣቶቹን ከዚያ የሚመጣው 'fund' በጣም spoiled እያረጋቸው እንደሆነ observe አደርጋለሁ:: እና በተለይ ለወጣቶች ገንዘብ የምትልኩ ሰዎች በተቻላችሁ መጠን በቀጥታ ለነሱ ባትልኩ.... እ... ለወላጆች ምናምን ወይም responsibility ለሚሰማው ሰው ልካችሁ ለደህና ነገር እንደዋለ ማረጋገጥ እንድትችሉ አርጋችሁ ምናምን.....
ገንዘብ (ወይም እቃ) ስለላካችሁ ብቻ ጥሩ ነገር አረግን ብላችሁ ደህና እንቅልፍ ከወሰዳችሁ በጣም ተሳስታችሁአል:: (እንደኔ እንደኔ ማለት ነው) You are not helping. I'm telling you. You are NOT helping at all. እንደውም ልጆቹን የያዙትን ነገር በቅጡ እንዳይዙ (mostly ትምህርታቸውን), እ.... በሌለ ነገር እንዲኮፈሱ ማድረግ .... ቤተሰብ ለፍቶ የሚያመጣውን ነገር ንቀው በናንተ ብር ላይ dependent እንዲሆኑ.... በጎረቤት ላይ አላስፈላጊ ትእቢት እንዲያሳዩ .. ማንነታቸውን እንዲረሱና የሆነ fantasy ውስጥ እንዲገቡ .. እዛ እናንተጋ ሁሉ ነገር አልጋ ባልጋ እንዲመስላቸውና (ገንዘቡ እንዴት ተፈግቶ እንደሚመጣ የናንተ confirmation አያስፈልገውም) እናንተ ጋ በመሄድ ፍላጎት ልባቸው እንዲንጠለጠል ማድረግ (አይሂዱ አልልም እኔ - ብዙ ትላልቅ ፎቆችን በፊልም ወይም በህልም ሳይሆን በአይናቸው ያዩ ... እ... ብዙ ኪሎሜትር መንገድ በሜትሮ ከፈረንጅ ጋር አብረው የሄዱ ብዙ ሀበሾች ቢኖሩን ምንም ክፋት የለውም - I think) ... You guys are promoting such acts...... At least basic የሆኑ ነገሮችን መማር ባለባቸው ሰአት የሆነ አላስፈላጊ intrusion እየፈጠራችሁ ያላችሁ አላችሁ::

ለምሳሌ እዚህ አገር ጫት is becoming a very big social problem. እና ብዙዎቹ ቃሚዎች ከውጭ በሚመጣ ገንዘብ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ... እ.... አንድ ጎረምሳ አንድ ስኒከር ከተላከለት ሰፈሩ ያለ አንድ ስልክ እንጨት ተደግፎ ድንጋይ ላይ እግሩን ጣል አርጎ እዛው ሙሉ ቀን ቆሞ ሲያሳይ የሚውል (የሰፈሩን ልጃገረዶች አላሳልፍ እያለ) ... እ .... ወንድሜ የሚልክልኝ ገንዘብ next week ይመጣልኛል እና አንድ ቺክ ጠብሻለሁ እራት የምጋብዝበት ገንዘብ አበድሪኝ ... ምናምን...... ውይ ረስቼው ... ሴቶቹ ደሞ በተለይ ለናቶቻቹ ልብስ ስትልኩ በናታችሁ መቼና የት እንደሚለበስ እየነገራችሁ ላኩላቸው - እናቶቹን አታደናግሩአቸው በናታችሁ:: ከምሬ ነው::

አንድ ባለስልጣን (ማን እንደሆነ አላስታውስም) - ባለፈው ገበሬው በእርዳታ በጣም dependent ሆኖ ማረስ almost አቁሟል ማለት ይቻላል አለ:: እንደውም ልጃቸውን ሊድሩ የሰርግ ቀን ይወስናሉ ድግሱ የሚታሰበው ግን ገና በሚመጣ (ገና አልመጣም እኮ) እርዳታ ነው... ምናምን አለ...... What's the difference b/n this fact and ከናንተ ገንዘብ ጠብቀው በሚበደሩት...... I see none.

Anyways, just be attentive on this issue. Ok? I think this has a long-term damage on the youth. ብዙ ያልጠቀስኩአቸው ግን ማንሳት የምችላቸው ነገሮች ነበሩ በዚህ ላይ.... ግን አንደኛ ታይፕ ማድረግ ደከመኝ... ሁለተኛ ደሞ ርቦኛል ምሳዬን ልበላ ነው:: ቦዘና ሽሮ አምሮኛል .... ከምር.... ባገኘሁ....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

ናፍቆት አሁን ጓደኞች ነን ቅቅቅቅቅቅቅ

Postby Joe » Fri May 14, 2004 11:36 am

እየውልሽ የኔ ናፍቆት ደምበጫን አገሬን ወደ ሩዋንዳ ስትወረውሪብኝ ትንሽ ቅር ብሎኝ ነበር:: ግን ያሁኑ ምክርሽ አንጀቴን አራሰው:: እንዲያው ለማወቅ ከፈለግሽ ደምበጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚገኘው:: እመኝኝ እኔ እዚያው ነው ጭቃ አቡክቼ ብይ ተጫውቼ ያደግሁት...(የአካባቢው አስተዳደግ እንዲህ ነው):: ከአዲስ አበባ 360ኪሜ ወደሰሜን ስትሄጂ ታገኝዋለሽ::

እንዲህ አይነት እምቅ ቁም ነገር እያለሽ ነው ባልሆነ አሉባልታ ጊዜያችንን ስታጠፊው የከረምሽው? በይ ያለፈው አልፏል:: የውሾን ስም የጠራ ውሾ ይሁን ብላለች መንዚ (ከቻት ሩም):: እናም እንዲህ አይነት አንጀት አርስ የሆነው ምክርሽ እባክሽ አይለየን::

አዲሱ አድናቂሽ ጆ (ከደምበጫ)
Joe
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 12
Joined: Tue Sep 09, 2003 11:27 am
Location: united states

Postby አካኪ ዘራፍ » Fri May 14, 2004 3:41 pm

hi ናፍቆት

ላለፉት ጥቂት ቀናት በዚህ ርእስ ስር የሚጻፈው አልጥም ቢለኝ (more on personal insults ያመዘነ ቢሆንብኝ )ሀሳብ ከመስጠት ተቆጥቤ ሰነበትኩ:: i really do appreciate the way you handle the criticism. i am also glad you managed to guide back the discussion forum back to its intended objectives.

anyways, በውጭ የምንኖረው ወገኖች አንቺ የምታነሻቸውን ነገሮች ለምን እንደሚያደርጉ ወይም ምን እንደሚያስገድዳቸው ከዚህ ወገን ሆኜ ለማቅረብ የማደርገውን ጥረት ለመቀጠል እሞክራለሁ...acting like the unofficial defender :-)

you have raised a very pertinent point about us sending money or staffs እንዳባባልሽ ለጥሩ ነገር ያልዋሉ:: እንግዲህ ከላይ እንዳልሽው አብዛኛዎቻችን የምንልከው ገንዘብ ይሁን ልብስ ወዘተ ለማግኘት ልባችን እስክትወጣ ሰርተን መሆኑ ይታወቃል:: አንዳንዴማ ለራሳችን ደፍረን የማንገባበትና የማንለብሰው ዲዛይነር ልብሶች አገር ቤት ያሉ ወንድም እህቶች ካላካችሁ ሞቼ እገኛለሁ ስላሉ ብቻ ተማሙተን እንገዛዋለን...እንግዲህ የህ የሚያሳይሽ there is some sort of pressure በኛ ላይ እንዳለ ነው:: it might be easy to say no, but we simply can't dare to come up with such courage to say it....after all ካገር ስንወጣ ያች ይሉኝታ የሚልዋት መናጢ ነገር ያለቪዛ ተከትላሽ ትመጣ የለ

ሌላው ከቤተሰብ በስልክ: በደብዳቤ አሁንማ እድሜ ለቴክኖሎጂ በኢሜል ጠዋት ማታ ብር መላክ እንዳለብን የችግሩ ብዛት የእነአቶ እከሌ ልጅ ለቤተሰቦቹ ስለሚያደርገው ስትጨቀጨቂ በቃ ያበጠ ይፈንዳ ብለሽ ለምን እንደሚውል ግድ የሌለሽን ገንዘብ ከሚጨቀጭቁኝ ልገላገል ብለሽ ትልኪና አንቺ የዘረዘርሻቸው አይነት ችግሮች እንፈጥራለን

እስኪ ለዛሬ ይብቃኝ...ከሰሞኑ ደግሞ ሌላ እላለሁ
አካኪ ዘራፍ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 4
Joined: Sat Jan 17, 2004 6:45 am

Postby ዋቆ » Sat May 15, 2004 3:16 am

ሰላም ናፍቆት ባለሽበት:: ብዙ በቀልድ የተላበሱ ቁምነገሮችሽ አደንቃለሁ:: አመሰግናለሁ:: የዋርካ በአዲስ አበባ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሹመት እንድታገኚ ቅስቀሳ አካሄዳለሁ::ሹመት ትወጂያለሽ?:: እነ ቶኒ: መሲ የጊዜውን የቤኒዚን ንዝረት እንዴት እየተወጡት ነው?? አሁንማ መኪናው በዝቶ በእግር መጉዋጉዋዝ ይፈጥናል ማለትን ሰምቼ!!
ዋቆ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 455
Joined: Sun Nov 16, 2003 2:12 am

ማስታወሻዋ

Postby ትምህርት » Sun May 16, 2004 9:43 am

ክፍል 1
ወቅቱ ክረምት ነበር:: ጓደኛዬ የቀጠረውን ሰው ባር ውስጥ ቁጭ ብለን እንጠብቃለን:: የሚጠበቀው ሰው ሳይመጣ ግማሽ ሰዓት አለፈ:: በግለሰቡ መዘግየት ጓደኛዬ መናደዱ በግልፅ ከፊቱ ላይ ይነበብ ነበር:: ሦስት ሰዓት እንደጠበቅን: ማስታወሻውን አውጥቶ ""የቀጠሯችን ሰዓት ይኸው"" ብሎ አሳየኝ:: ያለ ቀጠሮ ሰውን ይጠብቃል ብዬ የጠረጠርኩት መስሎታል:: እንዳለው ቀኑ: ሰዓቱና የሰውዬው ሥም በማስታወሻው በትክክል ሰፍረዋል:: ""ታዲያ ሰውዬውን ምን ነካው?"" የሚለውን ጥያቄ ሳልጨርስ: ጓደኛዬ እያነበነበ ጠርጴዛውን በቡጢ መታው:: የሰው ጠርጴዛ እንዳይሰበር ሰጋሁ:: (ለእጁ ያላሰብኩት ጓደዬ ስፖርተኝ ስለነበር::)

አገር ቤት እያለሁ ከውጭ ከሚመጡ ኢትዮጵያውያን ወንዶች እጅ የማትለይ የቀጠሮ ሰዓት መመዝገቢያ ማስታወሻን በጣም እወዳት ነበር:: ማስታወሻው ባለ የቆዳ ሽፋን ሲሆን ወረቀቶቹ በቀለበት የተያዙ ናቸው:: በእዕራቡም ሆነ በምሥራቁ ዓለም ለነበሩ ዘመዶቼና ጓደኞቼ አንድ ማስታወሻ እንዲልኩልኝ ሳላሰልስ ብጠይቅም ጥያቄዬ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል:: ማስታወሻዋን ለመታያነት እንዳልጠቀምባት አሻጥር መፈፀሙን ልቤ ጠርጥሯል:: የዘመድ ምቀኛ አያድርስ ነው:: ከዚህም በላይ አገር ቤት ያለን ሰዎች በቀጠሮ መገናኘት አልሳካልን ብሏል:: በማስታወሻ እጥረት::

ወደውጭ መውጣት አይቀርም ያለማስታወሻ ከአገሬ ወጣሁ:: ከአውሮፕላን እንደወረድኩ ያነሳሁት ጥያቄ ማስታወሻ ካልተገዛልኝ የሚል ነበር:: እሱን ቀስ ብለህ ትገዛልህ ብባል ማን ሰምቶ:: አገር ቤት እያለሁ አልተላከልኝም:: እኔን ከሰው ለማሳነስ ነው? ያለማስታወሻ ሰው ምን ይለኛል? አልኩኝ:: በስንት መከራ ሃሳቤ ተቀባይነትን አገኘ:: ችግሩ የእገሌን የመሰለ ማስታወሻ በአገሩ ሊገኝ አልቻለም:: ሳስበው አሁን ያለሁት ውጭ አገር ነው:: እዚህ እንደመታያ ዕቃ ሊያገለግለኝ እንደማይችል ስለተገነዘብኩ: የተገኘውን ገዝተን ወደ ቤት ገባን::

በአዲሷ ማስታወሻ ብዙም ነገር ሳይመዘግብባት ዓመቱ ተገባደደ:: ሁለተኛው ማስታወሻ ተገዛ:: ሁለተኛውም እንደዚሁ ብዙ ቀጠሮ ሳይመዘገብበት ተቀየረ:: ሦስተኛውም:: አራተኛውም:: አዲስ ጃንጥላ ተገዝቶ ዝናብ ሲጠፋ ያናድዳል:: የአውሮጳ ዓመት ቶሎ ይሮጣል ልበል::

ስንተኛዋ ማስታወሻዬ እንደሆነ ባላስታውስም: ያሁኗ ሥራ በዝቶባታል:: ገዳም ማስታወሻ!! እገሌን በዚህ ቀን: ከእገሌ ጋር በዚህ ሰዓት: እገሌን ደግሞ በዚህ ቦታ ብሎ በጥንቃቄ ተመዝግቦባታል::

የመጀመሪያው ቀጠሮ ደረሰ:: ከተባለው ሰዓት ቀድሜ በቦታው ተገኘሁ:: ከአንድ ሰዓት አለፈ:: ምንም ነገር የለም:: ሰዓቴን ተጠራጠርኩ:: ከጎኔ ተቀምጠው ከነበሩት አንዱን ሰዓት ጠየቅኩት:: አይ ሰዓቴ ይሰራል:: ሰውዬው የከረመውን ከርሞ ብቅ እንዳለ ምክንያቱን ደረደረው:: ቀጠሮ ሳይሳካልኝ አገር ቤት እንሰጣቸው የነበሩ ምክንያቶች ሳይቀየሩ በማግኘቴ ገረመኝ:: የአገር ቤት ትራንስፖርት መሳሪያዎች ከምዕራብ አገር ሲወዳደሩ::

ከሌላ ሰው ለላ ቀጠሮ:: ዘሬ የቀጠርኩት ሰው የተማረና ውጭ ብዙ የቆየ ስለሆነ ቀድሜ በቦታው ተገኝሁ:: ሰውዬው ብቅ ሳይል አንድ ሰዓት እንዳለፈ ስልኬ ተደወለ:: እንግዳ እቤት ስለመጣብኝ ነው:: ከአንድ ግማች ሰዓት በኌላ እንደሚመጣ ቃል ገባልኝ:: እንደገና አንድ ሰዓት ከአለፈ በኌላ መጣ:: ""ለምን ይህን ያህል አስጠበቅከኝ?"" ብየ ስጠይቀው: ""ምክንያቱን በስልክ ነግሬህ የለም"" ነበር ያገኘሁት መልስ::

ሌላ ሦስተኛ ቀጠሮ:: ሌላ መከፋት:: ቡና ቤት ሰውን መቅጠር አቆምኩኝ:: ቀጠሮ የነበረን እኔ ቤት ነበር:: ከቀትር በኌላ 9 ሰዓት:: ግለሰቡ የመጣው ከምሽቱ ሁለት ሰዓት:: ""ምነው እንደዚህ ታደርገኛለህ?"" በዬ ጠየቅኩት:: ""ያለኸው እቤትህ አይደለም"" የሚል መልስ ሰጠኝ::

የሁሉንም ቀጠሮዎች ዝርዝር እዚህ በማቅረብ ላሰለቻሁ አልፈልግም:: ብቻ ብዙ ብዙ ""ያልተሳኩ"" ቀጠሮዎች አለፉ:: ብዙ ማስታወሻዎችም ተቀየሩ::

ይቀጥላል::
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ትምህርት

Postby ትምህርት » Sun May 16, 2004 11:59 am

ክፍል 2
እኔና ጓደኛዬ የብዙ ዓመታት ማስታወሻዎቻችንን ደጋግመን ስንመለከት አንድ ነገር ውጤት አገኘን:: ችግርን መላን ይፈጥራል ተብሎ የለ:: የተገኘውን ውጤት ከዚህ በታች በአጭሩ አቀርባለሁ::

መነሻ ፅንሰ ሃሳብ
ከዚህ በታች የሠፈሩት አባባሎች በኛ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም::
- ኢትዮጵያዊን ከ 15 ደቂቃ በላይ መጠበቅ ውድ ጊዜን ማባከን ነው:
- ኢትዮጵያዊው በእጁ የሚያደርገውን ውድ ዋጋ ያለውን ሰዓት ለጌጥና ሃብትን ለማሳየት (status sybmol) ብቻ ይገለገልበታል::
- ውጭ ያለ ኢትዮጵያዊ ወደ አገር ቤት የሚላክ ደብዳቤ ለመጻፍ ጊዜ የለውም::

የጥናቱ ውጤት
አጠቃላይ
-ከኢትዮጵያዊ ጋር በክረምት ውጭ ለመገናኘት አትቀጣጠር:
-ቀጠሮ ካላከበረ ግለሰብ ይቅርታ አትጠብቅ
-ቀጠሮህ ባር ውስጥ ከሆነ በርከት ያለ ገንዘብ ያዝ:
-ስትናደድ ወደ መጠጥ የምትሮጥ ከሆነ ቀጠሮህን በሻይ ቤት አድርግ:
-በአንድ ቀን ከአንድ ቀጠሮ በላይ አይኑርህ::
-የቀጠሮህ ቦታ እቤትህ ከሆነ በትንሹ 24 ሰዓት ለቀጠሮህ መድብ::

ዝርዝር ቀመር/Formula
የተሳካ ቀጠሮህ እንዲኖር የቀጠርከውን ሰው ምን ያህል ጊዜ ውጭ እንድቆየ ማወቅ ይገባሃል::
ቀጠሮ የቀጠርከው ግለሰብ ውጭ አገር የቆየበት ጊዜ
ሀ. ከአምስት ዓመታት በታች ከሆነ 31 ደቂቃ
ለ. ከ 5-10 ዓመታት ከሆነ 1 ሰዓት ከ08 ደቂቃ
ሐ. ከ 11-20 ዓመታት ከሆነ 1 ሰዓት ከ 43 ደቂቃ
ለመጠበቅ ቅድመ ዝግጅት አድርገህ ሂድ::
መ. ከ 20 ዓመታት በላይ ከሆነ ግለሰቡ በቀጥሮው
ሰዓት ስለማይገኝ ባትቀጣጠር ይሻላል::

ተግባራዊ ምሣሌ
-ግለሰቡ በእኩለ ሌሊት ወደ አንድ ቤት ሂዶ ደውል ቢደውል ሳይከፈትለት ይቀራል:: በዚህ በገጠመው ያልጠበቀው ሰይጣናዊ ድርጊት ተናዶ ወደ ቤቱ ይመለሳል::
-በማግሥቱ ለኔ ስልክ ደውሎ (ልጂቱን ስለምቀርባት) "ያቺ ጓደኛህ አጉል ፈርንጂ ሆናለች" አለኝ:: ንዴቱ አሁንም እንዳልበረደለት ጠርጥሬያለሁ:: "ለምን ቀደመህ አልደወልክላትም?" ብዬ ጠየቅኩት:: "ለምን እራሳችንን እንረሳለን?" አለና ስልኩን ጥርቅም አርጎ ጆሮዬ ላይ ዘጋው::
-ብዙ ሳይቆይ ስልኬ እንደገና ጮኸ:: የወንድ ድምፅ ጠብቄ ነበር:: የገጠመኝ ግን ለቅሦ የተቀላቀለበት የሴት ድምፅ ነበር:: "እቤት በውድቅት ሌሊት እቤቴ መጥቶ እንድዚያ ደወል የሚያጮኸው ሴት በመሆኔ አይደል?" ቀጥላም "ህፃን ልጅ ያለበት ቤት በዚህ ሰዓት እንዴት እንዲዚህ ሰው ደወል ያጮሃል?" ለሁለቱም ጥያቄዎች ምንም መልስ የለኝም:: ለነገሩ ጥያቄው ለኔ አልመሰለኝም::

ማሳሰቢያ
እላይ ኢትዮጵያዊ(ያን) የሚለው ቃል ኢትዮጵያዊ ወንድ በሚሉት ቃላት ተተክቶ እንዲነበብ:: ኢትዮጵያዊያን እህቶቻችን በሙሉ ቀጥሮን እንደሚያከብሩ ጥናታችን አረጋግጧል::
የጥናቱ መሰረት ያደረገው በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያን ብቻ እንደሆነ ማስገንዘብ እንፈልጋለን:

ደስ የሚለው ነገር ግን: ይህ በወንዱ ላይ የሚታየው የቀጠሮ አለማክበር ዝንባሌ በሶማሊያዊያን ወንዶች ላይ እንደሚታይ ሌሎች ጥናቶች ይጠቁማሉ::

ፅሁፌን በጥያቄ ልደምድም::

ናፍቆት: ለመሆኑ ለሁላችንም ቀኑ እኩል 24 ሰዓት ነው:: ሰዓት አንፃራዊ አይደለም? ከውጭ የሚመጡት ኢትዮጵያዊያን እኛ እንደምንገምታቸው ሰዓት ያከብራሉ?

የጥላሁን ገሰሰን "ቀጠሮ" ዘፈን ለሁላችሁም ጋብዣለሁ::
-አርቆ ማሰቢያ እያለን አይምሮ:
እንደምን ተሳነን ለማክበር ቀጠሮ::

ቸር ይግጠመን::[/quote]
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

መልካም ዜና

Postby ትምህርት » Sun May 16, 2004 11:42 pm

ይህን መልካም ተግባር በሥራ ላይ እንዲውል ለደከሙት በሙሉ ከፍተኛ ምስጋናዬን በዚህ መድረክ ሥም አቀርባለሁ::

ዜናውን እራሳችሁ አንብቡት::

http://www.washingtonpost.com/wp-dyn/articles/A55892-2004Apr6.html

መልካም ዜና በጠፋበት ይኼ ትልቅ የምሥራች ነው!!
ትምህርት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1056
Joined: Sun Mar 21, 2004 7:31 pm
Location: somalia

ትምህርት - ጥሩ ነው ቀጥልበት;

Postby ረች » Mon May 17, 2004 9:07 pm

ስለ ቀጠሮ የተጻፈው ጽሁፍ ደስ ይላል::

እንግሊዝኛ መናገር የማይችሉትን (አማርኛ ተናጋሪዎችን ጨምሮ) ለማገዝ በD.C. ቓንቖዎቹን የሚችሉ ለመቅጠር መታቀዱ ለተወሰኑ ኢትዮጵያውያን ተጨማሪ የስራ እድል ስለሚፈጥርም ያስደስታል::
'perpetual optimism is a force multiplier' - C. Powel
ረች
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Fri Mar 12, 2004 12:08 pm

Postby አራዲት » Mon May 17, 2004 9:33 pm

ሰላም ናፍቆት It's amazing how you just pointed out the problems I personally saw in my family. YOu are absolutely right, most of us spoiled our sisters and brothers back home, which lead them to so many bad behaviors.
አራዲት
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Tue Nov 18, 2003 7:24 pm

Postby ናፍቆት » Tue May 18, 2004 8:00 am

አካኪ ዘራፍ - sorry to say but ሀሳብ ከመስጠት የተቆጠብክበትን justification ብዙም አልተቀበልኩትም:: እዚህ ብዙ ሰዎች ነን የምንዘባርቀው:: እና እያንዳንዱ ዘባራቂ influence የሚያደርገው የራሱ የሆነ ብዙ ኮተት አለው:: እና ማንም ምንም አለ አንድ ሰው ማለት የፈለገውን ሁሌም ማለት አለበት ብዬ ነው የማምነው እኔ:: ደሞም መርሳት የሌለብህ ነገር ማንም 'ዘባርቄያለሁ' ብሎ አያስብም:: 'ሀሳብ ሰጠሁ' ብሎ እንጂ.... ስለዚህ ምንም ማለት አይደለም ማለቴ ነው::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Tue May 18, 2004 8:05 am

ዋቆ - ሹመት ያልከውን እዛው አንተው ጋ አስቀምጥልኝ:: ብዙ ጊዜ ሰዎች ወደላይ ሲወጡ የሚያጡት ነገር ያለ ይመስለኛል:: Some even become more stupid, I don't know why.

የቤንዚኑን ነገር እንዴት handle እንዳረጉት አላውቅልህም:: ግን በእግር ይፈጥናል ያሉት ጥሩ አባባል ነው:: ዛሬ ዛሬ መኪና ይዘህ ስትሄድ እግረኛው መንገድ ለመልቀቅ ብዙም ፈቃደኛ አይደለም:: ተለጥጦ ነው የሚሞተው:: አንዳንዴ በመስኮት በኩል ወጣ ብለህ 'እረ ባካችሁ' ብለህ ለመለመን ትንሽ ነው የሚቀርህ::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest