ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ናፍቆት » Thu Aug 23, 2007 3:55 pm

Ahmed - 1 : የአምባሻው ነገር .... እየው ..... በሳቅ ቆሰልኩኝ ነው የምልህ ..... ከምር ...... ውይ ... ውይ ...... እሱ ይይልሀ - ሌላ ምን እላለሁ ..... ሰዎቹ ቢያገኙህ ግን በዛ ሞቅ ሞቅ እና ፈጠን ፈጠን በሚለው አነጋገራቸው ይዘው ጉድህን ነበር የሚያፈሉልህ ... ከምር ..... ግን ለምንድነው? እዛ አረብ አገር ያሉ ሴቶቹ በተለይ ንግግራቸው ፍጥን ፍጥን .... የሚናገሩት ነገር ደሞ አንዴ እዛ አንዴ እዚ ..... ያልተረጋጋ ነገር ... ምናምን .... ከሚሉት ነገር ዋና ነጥቡን ለመረዳት ትንሽ ስራ ቢጤ ያስፈልግሀል .... አንድ ዘመድ ነበረችኝ ከዛ የመጣች ... ስትናገር ራሴን የምታሳምመኝ ... ከምር

ለማንኛውም የጠየኩትን ጥያቄ እናንተም ባትመልሱ .... ፕሮግራሙ እሁድ ቀጥሎ እዛው ላይ ሰምቼዋለሁ .... ፕሮግራሙን ሆን ብዬ ነው የተከታተልኩት .... በነገራችን ላይ ባለፈው እንደጻፍኩት members of the Community ብቻ አልነበሩም ስብሰባው ላይ ... ነዋሪዎች ኢትዮጵያውያንም ነበሩ ..... አንድዋ ገጠመኝዋን ስትሰልቅ ምናለች .... እ...... አንዴ ኢትዮፕያ ሄጄ .... ኤርፖርት ውስጥ ... የያዝኩት ኮተት መአት ነው ... ለጎረቤት ለዘመድ ለቤተሰብ ለጓደኛ ..... ምኑም አልቀረኝ አለች ... እና አስተናጋጅዋ .... አንቺ ከአረብ አገር መሆን አለብሽ የመጣሽው ... አለችኝ እና ምንጭቅጭቅ ..... ነገር .... ከዛ ቀጥሎ አንድ ከአሜሪካ የመጣ መንገደኛ ከሁአላዬ ..... አስተናጋጅዋ 'ይህው የሰው ዘር መጣ ..... ሻንጣቸው ቅልብጭ ያለ ... የሰለጠነ ..... አለችና .... በፈገግታ ...... ምናምን ....

ከአሜሪካ የመጣው የኔን ያህል ለቅርቡም ለሩቁም ምናምን አልያዘ ይሆናል ..... ግን እኔ የያዝኩት ነው የምመነጨቀው .... እዬዬ .....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Thu Aug 23, 2007 4:01 pm

ShyBoy - 54ቱንም ፔጅ?? You're kidd'n me. እንዴ?

ደሞ ነዋይ ያልከው ዘፋኙን ከሆነ ትዝ ያለኝን ልበልህማ ..... ባለፈው አንዱ ጸጉር ቤት አንዱ መጽሄት ላይ ትንሽ ያወራውን አየሁትና ..... 'በኢትዮጵያ ውስጥ እስር ቤቶች ባይኖሩ ደስ ይለኛል ' ያለውን Cover Page ላይ አውጥተውት አይቼ .... አንድ አገር ካለ እስር ቤት? Oh come on. Let's be a little realistic here.

ለማንኛውም በህይወት ዘመንህ ለአንድ ጋዜጣ ወይም መጽሄት ምናምን ቃልህን የመስጠት እድሉን ካገኘህ emotional ሆነህ ላለመቀባጠር ሞክር .... seriously
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ShyBoy » Thu Aug 23, 2007 4:51 pm

ታዲያስ ናፍቆት: እንዴት ነሽ? አገሩ; ሰው.........ሁሉ ነገር አማን? እኔማ እንዴት እንደናፈቀኝ!!! (ገና 20 ወር እንኳን ሳይሞላኝ..........7 አመት ምናምን ለቆዩት አዘንሁላቸው)

እንዲ በፍጥነት ብቅ በማለትሽ በጣም ደስ ብሎኛል!!! እኔ ግን ከምሬን ነው: አልዋሽሽም (ኧረ እኔ ውሸት አልችልበትም: ከምሬን ነው):: እንዳጋጣሚ ልየው ብየ ማክሰኞ ከምሳ መልስ ጀመርሁና 48 ሰሀት እንኳን ሳይሞላኝ ትናንት እኩለ ሌሊት አካባቢ ነው የጨረስሁት:: እኔ በዚህ አለም ላይ እንደማንበብ የምጠላው የለኝም: በተለይ አካደሚክ ነገሮች:: (አንች ይሄን መጻፍ ጀምሬ: እዚህ ደርሼ ስትይ ቅንት ነው የምለው) በጓደኞቸም የምታወቀው በዚህ ነው:: ንባብ ላይ በጣም ሰነፍ ነኝ:: ልብ ወለድ ራሱ ያነበብኋቸው መጻህፍት 10 እንኳን አይሞሉም:: ነገር ግን ባጋጣሚ ማንበብ ጀምሬ በጣም አዝናኝ: አስቂኝ: ወይም ልብ ሰቃይ ነገር ከሆነ ሳልጨርሰው ረፍት የለኝም:: ፍቅር እስከ መቃብርን ባጋጣሚ ጀምሬው እንዲሁ በ3 ቀን አካባቢ ነው የጨረስሁት:: የትምህርት ነገር ከሆነ ግን አጠይቂኝ! የሆነ ለሰርቲፊኬሽን ፈተና እወስዳለሁ ብየ አንድ ግንድ መጽሀፍ ጀምሬልሽ አታምኝኝም አንድ ዙር ብቻ ለመጨረስ 3 ወር ነው የፈጀብኝ........ከነሪቪዥኑ 4 ወር:: አሁን ሁለተኛውን ፓርት ለመፈተን አንዱን ምዕራፍ እንደምንም ጨርሼ 19ኙ ቁጭ ብለው ያዩኛል::

መቸም አንቺ ጎሸም ከማድረግ ወደ ኋላ አትይ............ንዋይንም ተናገርሽው ነው የሚባለው:: ይገርምሻል:: እኔ ጥሎብኝ ከንዋይ በላይ ዘፋኝ ላሳር ነው ባይ ነኝ:: ክልጅነቴ ጀምሮ እሱን ስለሰማሁ ነው መሰለኝ በጣም: እጅግ በጣም ነው የምወደው:: አጋጣሚ ሁኖ እዚህ ከመጣሁ በኋላ አግኝቸው በጣም ነው አሁን የምንግባባው:: ሀገር ቤት እያለሁ ስለሱ እና ስለዚዳን የተጻፉ ነገሮች አያመልጡኝም ነበር:: እዚህ ስመጣ ራሱ መጽሀፍ ሳይሆን እነዛን ጋዜጦች እና መጽሄቶች ነው ይዣቸው የመጣሁት:: አሁን አነበብሁት ያልሽውን መጽሄት ራሱ ብትልኪልኝ ደስ ይለን ነበር..... looooooooooooool

ነዋይን ለማግኘት ብዙ አመታ ለፍቻለሁ (ሀገር ቤት እያለሁ አድራሻውን ለማግኘት):: በኋላ ተሳክቶልኛል:: ዚዳንን እንደማደንቀው ለመግለጽ አንድ ሁለቴ ጽፌለት መልስ አላገኘሁም:: ቢሆንም በጣም ነው የምወደው እና የማደንቀው:: አሁን ደሞ ከልቤ ነው የምልሽ አግኝቸ ባናግራቸው ከምላቸው ሰዎች ሶስተናዋ አንች ነሽ!!! በጣም ነው ያደነቅሁሽ..........በምትጽፊያቸው:: I hope እንደ ንዋይ አንድ ቀን አገኝሽ ይሆናል::

መጀመሪያ ማለት ቢኖርብኝም..........እንኳን ለፍልሰታ በአል አደረሰሽ!!! (እንደምትጾሚ ቀደም ሲል ካነበብኋቸው ጽሁፎችሽ ተረድቻለሁ):: እኔ ገና ከቢሮ ስወጣ ነው የምገድፈው:: ጥሎብኝ ቁርስ መብላት አልወድም:: ምሳ ሰሀት ደሞ ከድንች ጥብሳቸው በስተቀር የዚህ አገር ምግብ አይዋጥልኝም:: ድንች ጥብሱም ለsurvival ግድ ሲሆንብኝ ነው:: ከቢሮ ስወጣ ወደ U st. ጎራ እላለሁ::

መላካም የጾም ግድፍት ለጾማችሁ በሙሉ!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby Tጂ » Fri Aug 24, 2007 4:07 am

ሰላም ናፍቆት አነጋገርሽ እያሳቀ እያዝናና ቁም ነገር ያዘለ መልክት የሚያስተላልፍ ነው:: እንደ ሻይ ቦይ ጽናቱን እና ግዜውን አግኝቼ 54 ፔጅ ባላነብም አልፎ አልፎ ያነበብኩዋቸውን በሙሉ ውድድ ነው ያደርኩዋቸው የተቀሩትንም እንደማነብ እርግጠኛ ነኝ::
Tጂ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 301
Joined: Sat Aug 11, 2007 3:59 am

Postby ShyBoy » Tue Aug 28, 2007 9:30 pm

ኧረ ናፍቆት ምነው ጠፋሽ??? Please ሲመችሽ ብቅ በይና ስለ ሰሞኑ ያገር ቤት ሁኔታ በጣፋጩ አጻጻፍሽ ግለጭልን::

መልካሙን ሁሉ እመንልሻለሁ!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ናፍቆት » Mon Sep 03, 2007 4:22 pm

ShyBoy - የነዋይን ያነበብኩበትን መጽሄት ባልክልህም ምን መጽሄት እንደሆነና ቀኑን ልጽፍልህ እችላለሁ:: If you are that much desperate. አድራሻውን ብትጠይቀኝ ኖሮ በቀላሉ እነግርህ ነበር ይመስለኛል ...... ለማንኛውም እንኳንም አገኝተህ ተገላገልክ:: .... ሶስተኛዋ ላልከኝ ግን .... አስቆኛል ከምር ...... ነዋይን ስለዘፈነ ብንል .... ዚዳንን ደሞ ኳስ ስለተጫወተ ብንል .... ናፍቆት ምን ስላረገች ብዬ ሳስብ ...... I'm really laughing here ..... ለማንኛውም እኔ ያለሁት አሰልቺ ድንች ጥብስ የሚበላበት አገር አይደለም ......

አንድ ሌላ ነገር ልበልህማ ... አንድ በ2004 ሚስ ዎርልድ ኢትዮጵያ የነበረች ወጣት .... በ13 አመቴ ተደፍሬ ነበር ብላ የሆነ መጽሄት ላይ ትወጣለች ... እና መጽሄቱ ይህን ለመናገር ድፍረቱን በማግኘትዋ አድናቆቱን ምናምን .... ይልና .... እስዋ ደሞ የተናገረችው ላይ 'ከጓደኛዬ ጋር ሆኜ ... የሆነ ቦታ ... ፋንታ ከፍተው አምጥተው ሰጡኝ.... አስፕሪን ነው ምናምን ብቻ በብዛት ሲወሰድ ፌይንት የሚያስደርግ (ነው እንቅልፍ የሚያስወስድ) ነገር ነበረበት .... ከዛ ጠጣሁ ... ስነቃ በከፍተኛ ህመም ውስጥ ነበርኩ .... ምናምን .... ወንዶቹ አራት ወይም ከዛ በላይ ሊሆኑ ይችላሉ .... ምናምን ' ብላ ቃል ሰጥታልሀለች:: እና አታምነኝም the minute I read that የታየኝ አንዱ የመልስ ምት እንደሚጽፍ ነበር ..... ከጥቂት ቀን በሁአላ አንዱ ጋዜጣ ላይ .... አንዱ አሳመራት ..... እና ..... ብዙ analysis ሰጥቷል እስዋ በሰጠችው ቃል ላይ..... ከሁሉም ደስ ያለኝ የልጁ ጽሁፍ የቱ እንደሆነ ልንገርህ? 'ራሴን አላውቅም ነበር ብላለች ... እንደገና ደሞ አራት ወንዶች ሊሆኑ ይችላሉ ብላለች ..... ካሉ ቁጥሮች በሙሉ አራትን በምን መረጠችው? ...... ደስ አይልም? ከምር .... አዝናናኝ ነው የምልህ ....... እኔም ወደድኩት - አራትን::

'One Man's Dream' የተሰኘውን የያኒን instrumental music እያዳመጥኩ ነው:: ሙዚቃው በቃ ....... ኡ......ፍ ..... የሆነ ልብህ ውስጥ .... በጣም ውስጥ የሚገባ ነገር አለው ልበል? ጋብዤሀለሁ::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ዋናው » Mon Sep 03, 2007 7:49 pm

እንዴት ነሽ ናፍቆትነት?
ፅሑፎችሽን እያነበኩኝ ለአይናፋሩ ልጅ የጋበዝሽዉን ሙዚቃ እኔም ሠረቅ አድርጌ ሠምቼብሻለሁ....
የያኒ አድናቂ ስለሆንኩኝ (ሕንድ ታጅማሀል እና ቻይና ግሬት ዎል ያሳያቸው ትላልቅ ሙዚቃዎች ነፍሴን ነው ሚያንሳፍፉት)
ለእኔም ባይሆን ቴንኪው ለግብዣሽ
እኔም ይሄው ከታጅማህሉ => ላቭ ኢዝ ኦል ሚለዉን ላንቺና ለቤትሽ ታዳሚ ሁሉ ጋብዢያለሁ

==> http://youtube.com/watch?v=Uu67pzugkMQ

ዋናው___________________________________________________::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ShyBoy » Mon Sep 03, 2007 9:34 pm

ናፍቆት..............ሰላም: ሰላም: ሰላም ብለናል! እንኳን ከጠፋሽበት በሰላም ተመለስሽ!!!

መጽሄቱን የጠየቅሁሽ እንዲሁ ነው እንጂ ለመላክ እንደማይመች አውቃለሁ:: ለሀሳብሽ ግን በጣም አመሰግናለሁ!!! አንች ሶስተኛ መሆንሽ ግን ምኑ ነው ያሳቀሽ? ንዋይን በምርጥ የሙዚቃ ጥበቡ: ዚዙን በተካነው ልዩ የኳስ ምትሀት ትይንቱ.............አንቺን ደግሞ እየከሸንሽ በምታቀርቢያቸው ጽሁፎችሽ አደነቅሁ!!! የጻፍሽውን በጣም ባልወደው ኑሮ 54 የዋርካ ገጾችን ከ48 ሰሀት ባነሰ ኮሚትድ ሁኜ የማነበው ይመስልሻል? ብቻ ከልቤ ነው የምልሽ በጣም ነው አጻጻፍሽን ያደነቅሁት!!!!!!!!!!!!!!!!!!

የሞዴሊስቷ ነገር ደሞ የሚገርም ነው ባክሽ! ባለፈው እንዲሁ ስለሷ አንብቤ ነበር:: አካል ጉዳተኞች ሲቃወሟት እንደነበር አንብቤያለሁ::

ለዘፈን ምርጫሽ አመሰግናለሁ!!! ግን እንዲያው አንች ሰው አትንቂም:: እኔ ያኒ የሚባለውን ሰውየ ስሙን እና መልኩን ነው እንጅ የማውቀው (ድሮ ETV ይሁን TV Africa ያሳየው ነበር መሰለኝ) የውጭ ዘፈን አልሰማም:: የሚሉት ስለማይገባኝ ብዙም አልወድም:: ክላሲካልም ሰምቸ ስለማላውቅ ስሜት አይሰጠኝም:: እኔ አያበ በለው በለው: ሆይ መላ ሆይ መላ.............እና የመሳሰሉትን ነው የምወደው:: ባይሆን እረኛው ባለዋሽንት እና ደሞ ፍቅር እስከ መቃብር ልጀመር ሲል የነበረው ክላሲካል በጣም ምስጥ ያደርጉኛል:: ድሮ ገጠር እያለሁም ያገሬው ሰውዎች ስንጥርጥይ (ዋሽንት) ሲነፉ በጣም ነበር የምወደው::

እኔ ደሞ አሁን አሜን የሚለውን የንዋይን ዘፈን (ክላሲካሉን ብቻ) እየሰማሁት ነው:: የምትወጂው ከሆነ እሱን ጋብዤሻለሁ (እኔን ክላሲካሉ ብቻውን በጣም ነው የሚመስጠኝ)::

በይ እስቲ አትጥፊ..................ግን ከምር እግር ጥሎሽ እንደባለፈው ወደዚህ ብቅ ካልሽ ሰላም በይኝ:: እኔም ከመጣሁ በግር በፈረስ አፈላልጌ ላገኝሽ እሞክራለሁ::

መልካም ጊዜ!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ShyBoy » Mon Sep 03, 2007 9:42 pm

ዋናው wrote:እንዴት ነሽ ናፍቆትነት?
ፅሑፎችሽን እያነበኩኝ ለአይናፋሩ ልጅ የጋበዝሽዉን ሙዚቃ እኔም ሠረቅ አድርጌ ሠምቼብሻለሁ....
የያኒ አድናቂ ስለሆንኩኝ (ሕንድ ታጅማሀል እና ቻይና ግሬት ዎል ያሳያቸው ትላልቅ ሙዚቃዎች ነፍሴን ነው ሚያንሳፍፉት)
ለእኔም ባይሆን ቴንኪው ለግብዣሽ
እኔም ይሄው ከታጅማህሉ => ላቭ ኢዝ ኦል ሚለዉን ላንቺና ለቤትሽ ታዳሚ ሁሉ ጋብዢያለሁ

==> http://youtube.com/watch?v=Uu67pzugkMQ

ዋናው___________________________________________________::


ሀይ ዋናው: ሰልማ ነህ?

ልግብዣው በጣም አመሰግናለሁ (እኔንም ስለሚመለከት):: የሰውየው መልክት በጣም ነው ያስደሰተኝ:: ክላሲካሉን ግን አልጨረስሁትም:: ከላይ እንዳልሁት የውጭ ዘፈኖች ብዙም ስሜት አይሰጡኝም:: ብዙዎች እንደሚሉት ግሪን ነገር ነኝ::

ሰላም ሁን!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ላህ » Thu Sep 06, 2007 3:34 am

ብዙዎች እንደሚሉት ግሪን ነገር ነኝ
አሪፍ አባባል ናት ወዳጄ
በራስ መተማመን ራስን መሆን ካሉት አይቀር እንዳንተ ነው ደስ የሚል ባህርይ...ብዙወቻችንን ከተጠናወተን ራስን አለመሆን ብሎም ራስን አለማወቅ በሽታ ተላቀሀልና በጣም አድንቄሀለሁ......
ሰናይ ጊዜ ለዚህ ቤት ታዳሚያን በሙሉ
ላህ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 151
Joined: Fri Oct 29, 2004 2:03 am
Location: ethiopia

Postby አንበርብር » Thu Sep 06, 2007 5:09 am

ሰላም አሊኩም ብለናል........ ለመጀመሪያ ግዜ ከናፍቆት ቤት አንገቴን አስገባሁ.... page 54 ጫን አልኩና ማንበብ ጀመርኩ እንደ አረበኛ ከኌላ ለመጀመር አልነበረም እንዲያው አዲስ ነገር ካለ ብየ እንጅ......... እናም አንድ ነገር አነበብኩ ሻይ ቦይ 54 ገፁን አንብቦ እንደጨረሰ..... እናም ናፍቆትን የእራሱ ሂሮ አድርጎ እንደቆጠረ.. እናም እኔም ምን ነገር አለ ብየ ከገፅ አንድ ጀመርኩ ቀጠልኩ ገፅ 7 ላይ ደረስኩ ሳስበው ለመጨረስ የቆየሁበትን ግዜ በ 8 እጥፍ መቆየት እንዳለበኝ አወኩ.. ፅሁፉን ለመጨረስ ማለቴ ነው እናም አንገሸገሸኝ ብዙ ማንበብ ስለማልወድ... እናም ለመውጣት ወሰንኩ ግን ተመልሸ እንደምመጣ እራሴን አሳመንኩ............. መልካም መልካሙን ለናፍቆት
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ናፍቆት » Fri Sep 07, 2007 4:02 pm

ዋናው - የመረጥክልኝን ሙዚቃ እየሰማሁ ነው የምጽፈው አሁን:: Thank you. አንተም ሙዚቃውን እንኳንም ስርቅ አርገህ ሰማህ:: ..... Yeah! Those were great performances of his. እኔም እንደዛው:: በጣም ነው እነዚያን ሙዚቃዎች የምወዳቸው:: ክላሲካል ሙዚቃዎች የሆነ የሚሰጡህ ነጻነት አለ ብዬ አምናለሁ:: የሙዚቃውን rhythm ተከትለህ ውስጥህ የፈለገውን ሊያዜም ይችላል:: የፈለገውን ፍቅር - የፈለገውን ትዝታ - የፈለገውን ሀዘን - የፈለገውን ደስታ - የፈለገውን ቁጭት - የፈለገውን ናፍቆት ..... ምናምን..... So it gives you the freedom and I like that. ...... የሆነ ቆንጆ የሙዚቃ ቅንብር ላይ አዝማሪው ..... እ...... ለምሳሌ 'ቁመናዋ ቅርጽዋ ..... ' እያለ ቢያዜምበት .... ሀሳብህን ቂጥና ባት ላይ ወስኖብህ ቁጭ ይላል:: በቃ::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Fri Sep 07, 2007 4:25 pm

ShyBoy - የጽፍከውን ሳነበው እንዴት እንዳዝናናኝ አታውቅም:: ለማንኛውም አያ በለው በለው እና ሆይ መላ ሆይ መላህን ሳነበው በሀሳቤ ወዲያውኑ ውል ያለውን ልንገርህ? አንድ ሰማያዊ ሰፋ ያለ አጭር ቁምጣ እና ፍርጥም ያለ ግን ደሞ አመዳም የወንድ እግር .... ነገር ነው ..... አይ - ሰውየው መልኩን እንዳትጠይቀኝ .... ከወገቡ በላይ አልታየኝም .... ከምር .... ስማኝማ (it just clicked my mind) እነዚህ ወደየከተማው የሚፈልሱት የገጠር ሴቶች እነዛን ወንዶች ለምደው ከተሜው የሚጥማቸው ይመስልሀል? ከምር ...... ጉዳቸው ነው መቼም .....

እረኛው ባለዋሽንት በጣም የምወደው ሙዚቃ ነው:: በጣም:: የፍቅር እስከመቃብር.... ያልከውን ሙዚቃ አላወኩትም:: ስንጥርጥይ ማለት ዋሽንት ማለት ነው እያልከኝ ነው? አላውቅም ነበር:: Thanks, በነገርህ ላይ ብዙ ኦሪጂናል የሆኑ የአማርኛ ቃላት ጥጥር እንደሚሉብኝ ነግሬሀለሁ? አዎና .... የኔስ አይቸግርም ... ግን አሁን የሚሰሩ ኢትዮጵያዊ ፊልሞች የሚዘፈኑ ዘፈኖች ላይ በትንሹ እንኳን እንደነዛ አይነት ቃላቶችን ለመጠቀም አይሞክሩም .... So the trend is frightening ..... በቋንቋው እድገት ወይም ተጠቃሚነት ላይ የሚያመጣውን እንትን አለማሰብ ነው ..... አያሳዝንህም?

ፕሮዲዩሰር .... ኤዲተር ... ቅብርጥስ እያሉ እንግሊዝኛውን በአማርኛ ከሚጽፉ ወይ በ እንግሊዝኛ ፊደላት አንደኛውን መጻፍ - ወይም ደሞ የአማርኛ ትክክለኛ ትርጉሙን ከመዝገበ ቃላት ቢጽፉ የበለጠ 'Ethiopian' መሆን ይችሉ እንደነበር አይታሰብህም? ... እኔ ግን ይታሰበኛል::

ለሙዚቃው ግብዣ አመሰግናለሁ:: ፈልጌ እሰማዋለሁ:: Promise. አሁን ክላሲካሉ የለኝም:: ዘፈኑን ግን አውቄዋለሁ::

የሞዴሊስትዋ .... Yeah! ሳይቸግራት የሆነ ነገር ለጋዜጠኛ ቀባጥራ ..... እኔ እኮ የምለው ሰው ለጋዜጠኛ ቃል ሲሰጥ ለምን አስቦ አይሆንም:: Nobody really cares what really happened to you. ዋናው ቁምነገር ላንባቢ አሳማኝ አድርጌ አቅርቤዋለሁ ወይ ነው:: ማሳመኑ ነው ዋናው.... እንጂ ነገሩ በርግጥ ሆኗል ወይስ አልሆነም ያንባቢው headach አይደለም:: ብዙ ጊዜ ግን ሰዎች ሲቀባጥሩ አያለሁ ... በቃ ዝም ብለው ..... በትንሹም ቢሆን በልጅነቱ በንትኑ እቃ እቃ ያልተጫወተ የለም ብዬ አምናለሁ:: ለምሳሌ አንድ ሰው ያንን እንደ 'rape' ላቅርብ ብሎ ቢነሳ .... He should be very careful on how to present the story , I believe.

እንዲህ አይነት የራስ ታሪክ ላይ የሚጠበቅብህ 'ማሳመን' ብቻ ነው:: እውነታ አይደለም::
Last edited by ናፍቆት on Fri Sep 07, 2007 4:37 pm, edited 1 time in total.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Fri Sep 07, 2007 4:30 pm

ረስቼው ..... ስለሙዚቃ ስናወራ ትዝ ያለኝንማ ..... የሙሉቀንን ዘፈኖች በደንብ አላውቃቸውም ነበር ... እና አንድ (ይቅርታ ስሙን አልያዝኩትም) ልጅ አውጥቶት ሰምቼው በጣም ወደድኩት..... እና ስሰማ ሙሉቀን ለምን ሳያስፈቅደኝ ዘፈነ ነው ምናምን ብሉ ልጁን እከሰዋለሁ እያለ እሪ አለ አሉ:: እኔ የምለው ሙሉቀኑ ጴንጤ ሆኛለሁ ነው ቅብርጥስ ሲል አልነበር? ለማንኛው ልጁን አመስግኜዋለሁ .... እዙ ባይዘፍነው ኖሮ ዘፈኖቹን መቼም እንደዚህ አልሰማቸውም ነበር::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Fri Sep 07, 2007 4:31 pm

አንበርብር - I hope you won't get bored.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests