ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ShyBoy » Fri Sep 07, 2007 5:58 pm

ሰላም ናፍቆት ያገር ልጅ: እንዴት ነሽ? የሳምንቱን መጀመሪያና መጨረሻ (ዊኬንድ ሳይቆጠር) እየጠበቅሽ ብቅ ትያለሽ አይደል? ይህን አይፍታው ነው እንጅ ምን እንላለን?

እኔ እውነቴን ነው ያልሁሽ: የውጭ ሀገር ዘፈን አልወድም.........ደሞ እሚሉትም አይገባኝም:: በተለይ ይሄ ራፕ ሂፕ ሆፕ ምንምን እያሉ ጥቁሮች የሚከናብሩት ያቅለሽልሸኛል:: በጣም የሚቀፉኝ ደሞ የዋዎቹ 'ፍንዳታዎች' የጥቁሮቹን ያዘፋፈን: ያለባበስ: ያረማመድ....... ስታይል ሲከተሉ ነው:: ይቅርታ አድርጊልኝ እና በጅንፎ ከዘራ ጀርባቸውን ብላቸው ሁሉ ደስ ይለኛል:: ደሞ 'ጅንፎ ከዘራ' ምንድን ነው እንዳትይኝ? አሁንስ ስልችት ያለኝ ነገር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? አንድ ጓደኛየ አለ እዚህ አብሮኝ የሚኖር:: ድሮም አዲስ አበባ በጣም ጓደኛየ ነበር:: እና እኔ ጥቁሮቹ የሚያወሩት የሚያስቸግረኝን ያህል እሱን ደሞ እኔ የማወራው ያስቸግረዋል:: አሁንማ የተናገርሁትን ሁሉ ማብራሪያ እየጠየቀ እሱን በማስረዳት ሁኗል ጊዜው የሚያልውቀው::

እኔ ደሞ እልም ያለ ገጠር ውስጥ ስለሆነ ተወልጀ ያደግሁት ያዲስ አበባ አነጋገር ሊጋባብኝ አልቻለም እና ያው የጎጃሙን አነጋገር ነው እስካሁንም የምናገረው:: ዘፈንም የምወደው እዛ ስሰማቸው የነበሩት አይነቶችን ነው:: 1997ዓ.ም. ላይ ገና እዛው ኢትዮጵያ ነበርሁ እና ወንድሞቸ ጎጃም ሲያገቡ ይዘፈነው ሰውየ የዛው አካባቢ ታዋቂ ዘፋኝ ነበር (በከተማ አይታወቅም):: እና እዚህ ከመጣሁ በኋላ VCD ማውጣቱን ሰምቸ ከሀገር ቤት አስልKእዋለሁ:: ስሙ ሞላ ሰጣርጌ ይባላ:: አንችን ያኒ ምስጥ እንዳደረገሽ እኔን ደሞ እሱ ምስጥ አድርጎኛል::

እስቲ ለጊዜው ይሄንን ልጋብዝሽ http://www.youtube.com/watch?v=H8rOblDv ... 3%2F117%2F

ፍቅር እስከ መቃብር ያልሁሽ ድሮ ኢትዮጵያ ሬዲዮ ላይ ሲተረክ የሚቀርብ ክላሲካል ነበር (በስንጥርጥይ/ዋሽንት የተሰራ):: በቃ ስርቅ ነበር የሚያደርገኝ! የፍቅር እስከመቃብርን ትረካ ተከታትለሽ ከሆነ ሰምተሽው ይሆናል: ሁሌም ስለማይቀር:: የንዋይ አሜን የሚለው ክላሲካል ካሴቱ ካለሽ 9ኙም ዘፈኖች ካለቁ በኋላ 10ኛው ትራክ ላይ ነው ያለው (ሲዲው ላይ የለም)::

ከዘፈኑ ጋር የሳልሽው ሰውዬ ደሞ በጣም ነው ያሳቀኝ-አገላለጽሽ ማለቴ ነው:: በትክክል አስቀምጠሽዋል:: ገጠር አሁንም አብዛኛው ዘመዶቸ እንደዛ ነው የሚለብሱት:: በጣም ይናፍቁናል:: የሚገርምሽ ወደዚህ ልመጣ 1 ቀን ሲቀረን ሁሉ ገጠር ቤተሰቦቸ ጋር ነበርሁ: በጣም የምወደው እና የሚናፍቀኝ እሱ ስለሆነ:: አሁን አሁን ግን አዲስ አበባም በጣም ይናፍቀኝ ጀምሯል::

በይ እስቲ አልፎ አልፎም ቢሆን እንዳሁንሽ ብቅ በይ:: ደሞ ርዕሱንም አትርሽ: ስለኛም ጻፍ ጻፍ አድርጊ:: ሰሞኑን ደሞ ከሀገርቤት ወደኛ የሚዘገቡ አይጠፉም:: አንዳንዶችን ሪፖርት አድርጊልን::

መልካም የረፍት ቀናት!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby አንበርብር » Mon Sep 10, 2007 7:24 am

ናፍቆት wrote:አንበርብር - I hope you won't get bored.


I dunno what to say ናፍቆት ግን I am at the same place where I were.............. can i say i am bored or any word i can use? መቸም ኮፒ ራይት አይጠበቅም ብየ ነው ይችን ቆራጣ እንግሊዘኛ ተቸግሬ ያስገባኌት :lol: :lol: :lol: በነገራችን ላይ ውሻሽ ደህና ናት... እባክሽ ሀፒ ሚሊኒየም በይልኝ ስሟን አላስተዋወቅሽኝም.......ላንችም የደስታ የፍቅር እና የሰላም ዘመን ይሁንልሽ.... ናፋቂሽ አንበርብር ከዲያስፖራዎች አንዱ :roll: :roll:
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ዋናው » Tue Sep 11, 2007 12:06 am

ናፍቆትቻን ባለሽበት እንኳን አደረሠሽ::

Image
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ላህ » Wed Sep 12, 2007 11:24 pm

አንበርብር እንደጻፈው/ችው
ናፋቂሽ አንበርብር ከዲያስፖራዎች አንዱ

ሆሆይ ሰው መፍጠን ጀመረ ወይስ የናፍቆትን ቤት አለማንበብህን ሳታቀው መናገርህ ይሆን? ዲያስፖራ እንደማትወድ ልጅቱ ከተናገረች ቆየች መሰለኝ እንዳውም ለሷ የሚመቿት ላሜቦራወቹ ናቸው አሉ :lol: :lol: :lol:
መልካም ጊዜ ለዚህ ቤት ታዳሚያን
ላህ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 151
Joined: Fri Oct 29, 2004 2:03 am
Location: ethiopia

Postby ናፍቆት » Mon Sep 24, 2007 3:43 pm

'ዲያስፖራው ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ መኪናዎችን ከቀረጥ ነጻ ለማስገባት እንዲፈቀድላቸው ጠየቁ:: '

ሲመለስላቸው: -
'ጉዳዩ ከኢትዮጵያ ምን እንጠቀም ሳይሆን አገራችንን እንዴት እንጥቀም ወይም ወደ አገራችን ምን ይዘን እንግባ ነው:: '

በአጭሩ የናንተ ዲያስፖራ እስከዚህ ድረስ ነው::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

ሰላም ይብዛልሽ

Postby ጡመዴ » Mon Sep 24, 2007 6:25 pm

ባለፉት ጊዜያት ታቀርቢያቸው ይነበሩ መጣጥፎች የት ጠፉ::አለቁ ወይ ? ካለቁ ይነገረነና ወደዚህ ቤት መመላለሱን ብናቆም::

ሰሞኑን እንዲሁ ደከምን እኮ......... ባየሆን በሌላ ርእስ በንግናኝ::

አድናቂሽ....
ጡመዴ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 87
Joined: Mon Sep 24, 2007 6:06 pm

Postby ናፍቆት » Tue Sep 25, 2007 4:02 pm

ShyBoy - ነዋይህን እኮ አየሁልህ:: የት አትለኝም? ቴዲ አፍሮ USA ከመድረክ ላይ የተቀረጸውን ሲዲ ሰሞኑን በከተማው ይሸጣል እና ቤት አምጥተውት አይቼው ..... ነዋይ ስቴጁ ላይ ወጥቶ ሲያጫፍር ነበር ..... It was good to see him. የሚገርምህ መጀመሪያ ላይ ካሜራው ወደተመልካቾቹ ሲያሳይ እሱም እየታየ ነበር .. ግን አላወኩትም ነበር ..... ስቴጁ ላይ ወጥቶ እንትን እስኪል ድረስ .....

ቴዲን አደንቃለሁ:: In fact, እኔ ተስፋ ያለው ዘፋኝ እንደሆነ የገመትኩት ..... እ ..... በጣም በፊት ይሄ ካሴት ሳያወጣ ... አፍሮ ምናምንም ሳይባል ... በቲቪ ያስቀረጸውና የሚቀርብ በጣም የምወደው ዘፈን ነበር..... ከነልጅነቱና ረጋ ብሎ ድምጹን የምታደንቅበት .... ግጥሙም ትርጉም ያለው ነገር .... (sorry, I couldn't remember the song's name now ... ) .... እና ይሄኛውን ሲዲውን አየሁለት .... አትላንታ ... አትላንታ እያለ እንዲሁ ልቤን ሲያወልቃት .... 'ተቀባይ' ተብለው አብረውት የዘፈኑት ሁለት ጥቋቁር ሴቶቹን አልወደድኩለትም ... ዘፈኑን ሲቀበሉት .... የሆነ .... ብቻ የዘፈኑን 'ኢትዮጵያዊ' ቃና አሳጥተውት .... እነሱ በተቀበሉ ቁጥር ... እኔ ዝግንን ነገር ..... በተረፈ ልጁ he better watch his weight ...... ስማኝማ እነዚህ ስራቸው ከካሜራ ጋር የማይለዩ ሰዎች ለምን ሰውነታቸውን ዝም ብለው እንደማስቲካ ልጣጭ እንደሚጥሉት እኔ አይገባኝም ..... እንደኔ እንደኔ የበፊት መልክና ሰውነቱ ይሻል ነበር ባይ ነኝ ..... አንድ 'Exposed' የሚባል ተከታታይ ፕሮግራም አለ ... ታውቀው ይሆናል ..... (እነአያበለው በለው እዛ ላይ ባይቀርቡልህም) .... It's one of my favorites. So I watch it whenever I have the chance ..... ምናምን .... ባጭሩ ፕሮግራሙ ስለ 'celebrities' ህይወት በካሜራ እንዴት እንደሚተነተን ታያለህ .... ምናምን ነገር .... እና አንድ ደስ የሚለኝ ፉስቶ ነገር ካሜራማን አለ እዛ ላይ .... የጽጉሩ ቀለም አረንጓዴ ይሁን ፒንክ ጠፋብኝ .... ግን የሚሰጠው አስተያየት ደስ ይለኛል .... እና ታዋቂ አርቲስቶቹ 'ፓፓራዚዎች በግል ህይወታችን እይገቡ አስቸገሩን ... ቅብርጥስ ... ' ስሉ ሰውየው ምን እንዳላቸው ልንገርህ? 'You are in the public eye. So act like it. ' ነበር ያላቸው..... ከካሜራ የማያመልጡ ሰዎች ለምን ቡጭ እንደሚሉ አይገባኝም ... እኔም ለኛዎቹ 'ድሎተኞች' ያንኑ ነው የምላቸው ...... ስኳር ድንች ከመምሰላቸው በፊት...

እዚህ ላይ አስተያየት እንድትሰጥ የምፈቅድልህ የዘፈኑን ፊልም ካየህ በሁአላ ብቻ ነው::

( ዛሬ የቢሮዬን ID ረስቼው መጥቼ በር ላይ አንዱ ጥበቃ ተነጫነጨብኝና ትንሽ ተነጋገርን ... እነዚህ ጥበቃ ነገሮች እኔ ብዙም አይመቹኝም .... ሆስፒታል ብትል ... ት/ቤት ብትል ... ወላ ኮሌጅ ..... ችግሩ እነሱ የሌሉበት የለም .... አሁን ስወጣ በዛ ቀያይ አይኑ እንዴት እንደሚገላምጠኝ አታውቅም )
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ShyBoy » Tue Sep 25, 2007 4:45 pm

ሀይ ናፍቆት: nice to see you here again! ስለአም ነሽ ወይ? ሚሊኒየም እንዴት አለፈ? (መቸም ከበዓሉ በኋላ አልተገናኘንም ብየ ነው እንጅ አሁንማ መስቀልም ደርሷል)::

ንዋይን ማየትሽ ደስ ብሎኛል: ግን ሲያጫፍር ያልሽው አልገባኝም:: እሱ አልዘፈነም? የቴዲ አዲስ አልበም እዚህ ገበያ ላይ የዋለ አይመስለኝም እስካሁን አላየሁትም:: ሳየው በደንብ እነግርሻለሁ:: ግን እንዴት ነው የንዋይንስ አዲስ ኮሌክሽን ሰማሽው? ከሰማሽውስ ወደድሽው? እኔ በጣም ወድጀዋለሁ! "ትጠይቅ ዋስ" እና "ያይኔ አበባ ነሽ" የሚሉትን እንድታዳምጫጨው ጋብዤሻለሁ::

በነገርሽ ላይ ዘፈኑን ረሳሁት እንጅ ቴዲ ገና እንዳሁኑ ሳይታወቅ የዘፈነውን እኔም አስታውሰዋለሁ:: ትዝ ይለኛል ገና ከገጠር አዲስ አበባ የገባሁ አመት ነው (1992 ዓ.ም.):: እንዳለ አድምቄ እና ቴዲ ህብረት ትሪት ላይ ይቀርቡ ነበር:: ግን ያኔ ከቴዲ ይልቅ እንዳለ የበለጠ ይታወቅ ነበር::..............................

ይቅርታ ስብሰባ ግባ ስለተባልሁ ነው በኋላ እመለሳለሁ::

እስከዛው ሰላም!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ናፍቆት » Wed Oct 03, 2007 4:08 pm

እዚህ አሁን ከናንተ ጋ የመጡ ብዙ አሉ - አይደል?

እና ከተማ ከተማውን ስትዞር የሚታየው ..... እ..... ሰው some sort of competition ውስጥ ያለ ይመስላል መሰለኝ:: እኔ እንዳየሁት እዚህ ያሉት በዝነጣም ቢሆን በመኪና ደህና ሆነው ተገኝተዋል ይመስለኛል .... እና the people from the Diaspora are trying their best to show off and ተለይተው እንዲታዩ .... ምናምን ነገር..... የታዘብኩት ግን ከ'ዲያስፖራ'ው ልታይ ልታይ የሚለውና የሚታየውም ወንዱ ሲሆን እዚህ ያሉት ደሞ ሴቶቹ ናቸው:: ንገረኝማ .... ሴቶቻችሁን ምን እያረጋችሁ ልካችሁአቸው ነው እንዲህ አልታይ ያሉት? ነው ምንድነው? .... በዚህ በበአሉ ብዙ አዳዲስ ካፌዎች ሬስቶራንት ምናምን እንደጉድ ተከፍተውልሀል .... እና አንዱ ቤት ባለፈው ቁጭ ብለን .... የት ነበርማ .... yeah 'Elephant Walk' ...... አንዱ መጣ ..... ሲጀመር መጤዎቹ ያስታውቃሉ .... ብዙዎቹ ሴታሴትነት ይታይባቸዋል ... ወይም በጣም ..... ምን ልበልህ ...... የሚያስታውቅ አለባበስ .... ምናምን ነገር ..... እነሱም ለመታየት ሲጥሩ ታያለህ ... እና አንዱ ... ከፊታችን ያለው ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ..... ትንሽ ወሰድ መለስ የሚያረገው አይነት ነው .... እና በሱ አንስተን ስናወራ ብዙ እንደሱ አይነቶች ከናንተው እንደመጡ ምናምን ነገር ተወራና .... እኔ ምን እንዳሰብኩ ልንገርህማ ..... እዚህ ዋርካ ላይ ከስንት ቅዥቢ ጋር ቀባጥሬ ይሆን ብዬ በልቤ ሳቅ አልኩኝ ..... ከምር
.... ብዙ ጊዜ ይሄ 'fan' ትዝ ይለኛል .... ከውጭዎች ጋር በተገናኘ ማለቴ ነው ......
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Oct 04, 2007 12:19 am

እማሆይ ናፍቆት ...እንደምነሽ ?
ሳስብሽ የዘመኑ ሰው ሳትሆኚ አትቀሪም ...ግን ምን አገባኝ ....እኔ እንደሆነ ከጥንቱ ከጠዋቱ የሶሻሊስቱ ምድር ...ሆነ ቀረ ...የሚያገባ የሚመስል አለ አይደል ወንድ መሳይ አልጫውን ሚለኒየም የሚመስል አልጫ ወንድ ቀናሽ?ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ከይቅርታ ጋር በቢራ ሀይል የተጻፈ ነው ...ቢሆንም አንጸጸትም
እኔና ቢራው
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ናፍቆት » Thu Oct 04, 2007 4:23 pm

ፓን ሪዚኮ - ውይ ደስ ስትል...... ሞቅታ ያምርብሀል ማለት ነው:: ዛሬ ቢሮ ማምሸት አለብኝ.... ገና ስራው ግን አልመጣም ... we're waiting for some instructions .... ምናምን ነገር ..... እና idle ነገር ስሆን I logged-in here. And here you are , the drinking guy ...

እና ቢራ ስትል ትዝ ያለኝን ልጽፍ ብዬ ..... አንድ ጊዜ .... ይሄ መንዘላዘል ምናምን የምትጀምርበት ጊዜ አለ አይደል? You want to try everything, you want to be here and you want to be there at the same time ..... ምናምን ነገር ..... አንድ ቢራ በጣም የሚወድ ልጅ ጋር ባጋጣሚ ..... እና ሁሌ 'አንቺን በቢራ አስክሬ ማየት እፈልጋለሁ' እያለ ስለቢራ አሪፍነት እንዲሁ ልቤን የሚያወልቀኝ ነበር .... እና እሱ ደሞ ይሄ አንዳንድ ሰዎች አሉ አይደል .... በሆነ አጋጣሚ ትተዋወቅና ከዛ .... ልትወጣም የሆነ የሚቀራቸው ነገር ያለ የሚመስልህ .... ልትዘጋቸውም ደሞ እንዲርቁ የማትፈልጋቸው .... እና ዝም ብለህ አንጠልጥለህ የምታቆያቸው ነገሮች ... የሉህም? You better have one. I think it's common (በተለይ ሴቶች ጋር - መሰለኝ እንግዲህ - ካልሆነም ሴቶቹ ይንጫጩ ) .... እኔ መቼም somebody is always on the line ..... እና እንደሱ ነገር ነበር .... እና መጨረሻ ላይ እስቲ ምን ያመጣል ብዬ ..... በቃ ...... አብረን ቢራ ጠጣን ..... ለመቅመስ ሳይሆን በቢራ ለመስከር የመጀመሪያዬ ነበር ..... እና ተመሸ ... ተዞረ ተዞረ ... ምናምን ..... ከዛ መጨረሻ ላይ እንደሰመመን ...... ማደሪያ አጥተን አንድ ሁለት ቦታ እንደተንከራተትን ትዝ ይለኛል ... ከዛ ግን በቃ .... I think I went blank ...... .... በማግስቱ ስነቃ .... ማን ወስዶ እንዳስገባን አላውቅም .... ራስ ሆቴል .... የሆነ መጋዘን የመሰለ በጣም ሰፊ የሆነ ወና የመሰለ መኝታ ቤት .... Oh God ..... It was horrible. Frankly. ...... እና ቢራ ሲባል እሱ ልጅና ራስ ሆቴል ነው ትዝ የሚሉኝ ...... ከምር

ሶሻሊስት ነው ምናምን ብትል .... 'We the Living' የሚል መጽሀፍ በ Ayn Rand የተጻፈ (she is a famous Russian author - ታውቃት ይሆናል) ሰሞኑን ጨረስኩ .... ስለሶሻሊዝም በደንብ የምትረዳበት በጣም ቆንጆ መጽሀፍ .... ንገረኝማ .... ሰው ግን ሶሻሊዝም ብሎ እንደዚህ በራሱ ላይ ሲኦል ይፈጥራል? What an ideology!

'ሶሻሊስት' ቅብርጥስ እንዲህ በቀላሉ ትዝ የሚልህ አይነት ሰው ከሆንክ .... I think you may be interested in reading the book. Just trust me, you'll enjoy it.

አልጫ ላልከው ...... ከምር ...... አንዳንዶቹ ወንዶቻችሁ የሆነ በቃ ...... እንደሴት ሆነህ ስታስባቸው .... እ? ግን እንዴት ብለህ እንደሴት ማሰብ ትችላለህ እንጂ ..... በቃ ቅልሽልሽ ነገር .... ከምር

ስራውን ገና ሳልጀምረው ሊደክመኝ ነው ... ጉዴ ነው መቼም ..... እስቲ ቸኮሌት ነገር ካለኝ ቦርሳዬን ልፈትሽ ....

ውይ .... I have a new mail .... I think the instruction has just arrived ......
I need a music
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ሒትለር » Thu Oct 04, 2007 7:42 pm

ናፍቆት wrote: እዚህ ዋርካ ላይ ከስንት ቅዥቢ ጋር ቀባጥሬ ይሆን ብዬ በልቤ ሳቅ አልኩኝ ..... ከምር
.... ብዙ ጊዜ ይሄ 'fan' ትዝ ይለኛል .... ከውጭዎች ጋር በተገናኘ ማለቴ ነው ......


እሙዬ እንደው "fan" ስትይ የቱ ፋን ይሆን? የ አርሴናል fan ወይስ የ ሪል ማድሪድ fan? ወይስ ይሄ በሌክትሪክ ተሰክቶ እየተሽከረከረ ንፋስ የሚሰጠው ፋን? ከምር ያንቺ እንግሊዝኛ ደግሞ ረቀቀ
ሒትለር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 28
Joined: Fri Sep 14, 2007 5:55 pm

Postby ShyBoy » Thu Oct 04, 2007 8:24 pm

ሰላም አቴ ናፍቆት: እንደምን አለሽ? ሀገሩ: ሰዉ: ከብቱ: ሰብሉ...........ሁሉም ነገር እንዴት ነው? ዘራችሁ? አጨዳችሁ? ከመራችሁ? ወቃችሁ? እስቲ ሹክ በይንማ...........በተለይ ስለ በርበሬው አዝመራ::

እኔ እምልሽ: እንዲያው ምን ይሁን ብለሽ ነው እንደዚህ ጥፍት የምትይው? እኔ ቢሮ ቁጭ ብየ ቢያንስ በየ 1 ሰሀቱ ዋርካን ሳላያት አልውልም:: ምን ቢዚ ብትሆኝ እባክሽ እንደድሮሽ ጣፋጩን ወግ አውጊን!

ደሞ ቆይ: ቢሯችሁ የጦር ካምፕ ነው እንዴ "መመሪያ እስከሚሰጣችሁ በተጠንቀቅ ጠብቁ" የሚባለው? lol እስቲ ወደ ዘመቻው እንደሄድሽ ቀርተሽ ካልሆነ በቶሎ ምላሽ ስጭን:: ሌላው ደግሞ ሁሌ ግርም የሚለኝ ነገር: ለምንድን ነው ዋርካ ላይ ሌላ ቶፒክ ውስጥ የማትጽፊው? እኔ በበኩሌ አንዴ ወጋ-ወጋ የሚባል ልጀ ዘፈን ስለማውጣት የጻፈው ርዕስ ውስጥ ከጻፍሽው ውጭ ሌላ ቦታ ጽፈሽ አይቸ አላውቅም:: ሌላ ቦታ የተጻፈውን አታነቢም ማለት ነው? ደሞ እንደሁልጊዜው "እንዲህ ብትል ትዝ ያለኝን ልንገርህማ" ብለሽ ጥያቄውን እለፊው አሉ............

ከዘመቻ መልስ በሰላም እንደምንገናኝ ተስፋ አለኝ!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ShyBoy » Thu Oct 04, 2007 8:30 pm

ሒትለር wrote:
ናፍቆት wrote: እዚህ ዋርካ ላይ ከስንት ቅዥቢ ጋር ቀባጥሬ ይሆን ብዬ በልቤ ሳቅ አልኩኝ ..... ከምር
.... ብዙ ጊዜ ይሄ 'fan' ትዝ ይለኛል .... ከውጭዎች ጋር በተገናኘ ማለቴ ነው ......


እሙዬ እንደው "fan" ስትይ የቱ ፋን ይሆን? የ አርሴናል fan ወይስ የ ሪል ማድሪድ fan? ወይስ ይሄ በሌክትሪክ ተሰክቶ እየተሽከረከረ ንፋስ የሚሰጠው ፋን? ከምር ያንቺ እንግሊዝኛ ደግሞ ረቀቀ


ይህች ነገር እኔንም ግራ ግብት አድርጋኝ ነበር:: ምናልባት 'fun' ለማለት ይሆናል ብየ ቀይሬ ባነበው የተሻለ ትርጉም ሰጥቶኛል ግን በደንብ አልገጥምልህ አለኝ:: አዳሜ ተሰብስቦ (ድመቶች እንኳን ሳይቀሩ) የእንግሊዘኛ ፊልም በሚኮመኩሙበት ሰሀት እኔ ከብት ስሰበስብ አድጌ እንግሊዘኛ በጣም ያብጥብኛል! እንዲያው እንደኛ አገር ቁምጣ እጥር..................
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Oct 04, 2007 10:01 pm

ሰላም ናፍቆታችን ....
መቼም መጋዘን የመሰለውን የራስ ሆቴል አልቤርጎ ሁለት አልጋ አያጣውም ቅቅቅቅቅቅ ለካስ እንዴትና ማን እንዳስገባቹህ እንኳን አላውቅም ብለሺኛል ...ሆነ ቀረ ትዝታ ነውና በትዝታው ይቅር....የ Ana Randlovaን መጽሀፍ አላነበብኩም ...በስሟ የራሺያ ፈላሻ ትመስላለች ...ሆነ ቀረ እስቲ አፈላልጌ ባገሬው ቋንቋ አነበዋለሁ ....እንግሊዘኛው እና እኔ ዝምድናችን ተራርቋል...ሶሻሊዝም ውልደቱና ጥፋቱ በምስራቅ አውሮፓ ቢሆንም የምእራብ አውሮፓ ሀገሮች ጥሩ አድርገው ተጠቅመውበታል ...ለዚህ ሲዊድን ቆንጆ ምሳሌ ናት ....ጀርመኖችም ቢሆኑ ሶስተኛውን መንገድ እያራመዱ ናቸው ...
ፖለቲካውን ልተወውና ወደ ቢራው ወሬ ልመለስ
በነገራችን ላይ በደሌን ቢራ ፋብሪካ ከተከሉት የቢራ ጠማቂዎች አገር ነኝ ...እና እዚህ ቢራ የማይጠጣ የለም ሴቱ ወንዱ ሽማግሌው አሮጊቷ ወጣቱ ...ሁሉም ይጠጣል ...ቱሪስቱማ ለጉድ ነው የሚጠግብ አይመስለውም ...አንዳንዱ ቱሪስትማ እርካሽ አገኘሁ ብሎ ወደ ሀገሩ መመለሻውንም ፍራንክ ሳይቀር ጠጥቶበት የፈረደበትን የሀገሩን ኤንባሲ ሲያስቸግር ብዙ ጊዜ አይቻለሁ ....ለነገሩ በማንም መፍረድ አይቻልም ከለስላሳ ወይም ከአንዲት ሲኒ ቡና ዋጋ የግማሽ ሊትሩ ቢራ ዋጋ እጅጉን በጣም ያነሰ ነው ....

በይ ስራሽን ስሪበት ..ለነገሩ አንቺ አንድ ሁለት ሶስቱን ስራ በአንድ ላይ የመስራት ችሎታ ያለሽ ይመስላል ...ቸኮሌት ...ሙዚቃ ...ስራ ...ቅቅቅቅቅ

ዛሬ ለነገሩ ወደ ቢራ ቤት እሄዳለሁ ብዬ ስነሳ ዝናቡ ከቤት አላስወጣ አለኝ ....መቼስ ማል ጎደኒ ብሏል ያገሬ ሰው ...ጦም አይታደር ..የጠርሙሷን ተያይዣታለሁ ....የሚገርመው ቢራው የሚጥመኝ እንደ አገር ቤት ጠጅቤት በሚመስሉት ሆስፖዳዎች ...ሆስፖዳ= ቢራ ቤት ግብቼ ጫጫታውን እየሰማሁ ስጠጣው ነው
በይ ፈረሴ ሰላምታውን እያቀረበ ነው
Image
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests