ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ዋናው » Thu Oct 04, 2007 11:26 pm

ሠላም ናፍቆት
ሠሞናቱን ዓይናፋሩ ልጅ ከደጅሽ አልጠፋ ሲል ባይ ምንኛ ወጎች ቢኖራት ይሆን እያልኩኝ እኔም እንደርሱ ብቅ ሳልል ውዬ አላውቅም (<==ዓይናፋሩ ልጅ ዕይታውን ስለምወድለት ነው ቅቅቅ)
ናፍቆታችን ወግሽን ከማድነቄ ጋር የአየን ራንድን ስም ብታነሺ ነው ብቅ ማለቴ በጣም ማደንቃት ፀሐፊ ናት ዘ-ቨርቺው ኦፍ ሰልፊሽነስ ማለት የርሷ ዕይታ ነው:: እንደርሷ ዓይነት ፀሐፍት እጅግ ይስቡኛል: አባባሏን ልጥቀስና እኔም ወደዝምታዬ እናንተም ወደቢራቹ እኔማ አርቢቱ ምሽት ላይ ነው ከቢራጋ ምጋጠመው ቅቅቅቅ
ማንም ሠው ስለእኔ ብሎ እንዲኖር አልሻም እኔም ስለማንም ብዬ መኖርን ስለማልሻ ብላ ነበር

መልካም የሣምንት መጨረሻ
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ShyBoy » Fri Oct 05, 2007 1:13 am

ዋናው wrote:ሠላም ናፍቆት
ሠሞናቱን ዓይናፋሩ ልጅ ከደጅሽ አልጠፋ ሲል ባይ ምንኛ ወጎች ቢኖራት ይሆን እያልኩኝ እኔም እንደርሱ ብቅ ሳልል ውዬ አላውቅም (<==ዓይናፋሩ ልጅ ዕይታውን ስለምወድለት ነው ቅቅቅ)


ዋናው እንዴት ነህ? ሰላም ነው? ቆይ ግን አንተ መቸ ነው ያንን ድርሰት የምትጨርስልን? መቸም ያለቀ ለት ሙክት ነው የሚለቀቅብህ! ደሞ አሳፍረህ ከዚህ ልታስጠፋኝ ነው አይደል እንዲህ የምትለኝ? እዚህ የሚወራው ሁሉ በአካል ተገናኝተን የሚወራ ቢሆን ኑሮ አንዲት ቃል እንኳን ትንፍሽ አልልም ነበር::lol...........የምር ግን የአይናፋርነት መድሀኒት የምታውቁ እግረ መንገዳችሁን ጠቁሙኝ::

የሆነው ሁኖ: እኔ እዚህ እየመጣሁ ሳፈጥ ጊዜ ነው መሰለኝ እሷም ወጉን ቋጠረችው:.............ኧረ ባክሽ ዥደድ ዥደድ አድርጊው!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Oct 05, 2007 12:25 pm

ShyBoy wrote:...........የምር ግን የአይናፋርነት መድሀኒት የምታውቁ እግረ መንገዳችሁን ጠቁሙኝ::


አንድ ሁለት ሶስቷን በደሌ ኳ አድርግ ....ያኔ አይናፋርነቱ ክግንባርህ ድራሹ ይጠፋል.....ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ShyBoy » Fri Oct 05, 2007 3:37 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:
ShyBoy wrote:...........የምር ግን የአይናፋርነት መድሀኒት የምታውቁ እግረ መንገዳችሁን ጠቁሙኝ::


አንድ ሁለት ሶስቷን በደሌ ኳ አድርግ ....ያኔ አይናፋርነቱ ክግንባርህ ድራሹ ይጠፋል.....ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ፓኑ አባ ፈርዳ


ፓን ዘብሄረ ሶሻሊዝም: አማን ነው? የምስራቅ አውሮፓው የቢራ ጎርፍ እንዴት እያደረገህ ነው? ምን እባክህ እኔማ አይናፋርነት እንደሚያስወግድ ሳላውቅም ልምምድ እያደረግሁ ነበር በደሌ ለመጠጣት:: ግን ምን ዋጋ አለው እንኳን 2 እና 3 ላይ ልደርስ ገና ሁለቴ ፉት ስለው እየመረረኝ ይዘጋኛል:: አሁን ትንሽ ለለማጅ ይሆናል ተብሎ Corona (ቀጭን እና ብዙ የማይመር ቢራ) ከሳምንት አንዴ 3 ሰሀታት እየፈጀብኝ አንድ ጠርሙስ መጨረስ ጀምሬያለሁ:: ወደፊት ወደ በደሌ አድግ ይሆናል:: ያም ሁኖ ግን እቤቴ ወስጀ ነው እንጅ የምጠጣው እንዳንተ ጫጫታ ያለበት ቡና ቤት እንኳን ሂዶ ቁጭ ብሎ መጠጣት ይቅርና ባጠገቡ ባላልፍ ደስ ይለኛል::

እየውልህማ..........እስካሁን እንዳየሁት ቢራው እንኳን ሊያደፋፍረኝ ንፍዝዝ ያደርገኝና እንቅልፍ ይለቅብኛል:: እሱን ከምሽከም የጎጃም ካቲካላ አስመጥቸ ብሞክር መፍትሄ የማገኝ ይመስልሀል?
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ፓን ሪዚኮ » Fri Oct 05, 2007 11:39 pm

ጦረኛው ወንድሜ ...


እኔ አልኮሉ በጡጦ ከአሬራ ጋር ሳይሆን አይቀርም የተሰጠኝ ...ብለው ብለው አልሰማም ...---- ምጣድ ብጤ ነኝ ...
በል በል አሮጊቷ መታ ሳትወርድብኝ ቤቷን ለቅቄ ልውጣ ...ደህና እደር
ፓኑ አባ ፈርዳ
Last edited by ፓን ሪዚኮ on Thu Oct 11, 2007 7:32 pm, edited 1 time in total.
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ወንድም » Sat Oct 06, 2007 1:54 am

አንቺ ልጅ ማነሽ ናፍቆት ጉደኛ ነሽ አነጋገርሽ ግድ የሌላት ስለሰው ቀድጄ ልልበሰው አንዳንዴም little bit dam blonde ትመስያለሽ አንቺ ግን ቆቅ ነገር ለኔ አይነቱ ምስኪን በነብስ የምትጫወቺ አንድ ቀን የወንድ አምላክ ፍርድ ቤት የምትቀርቢ ሳትሆኝ አትቀሪም
ድሮ ፈልፈላ እያለው ታላቅ እህቴ ብዙ ሴቶች ጉዋደኞች ነበርዋት እና የዛኔ እኔን ንቀው ልጅ ነው ብለው ስለ ወንድ ብዙ ሲያወሩ እሰማቸው ነበር እንዴት ወንድ እንደሚያጠምዱ ብቻ ስለተለያየ tactic ሲያወሩ ስሰማቸው አሁን መለስ ብየ ሳስበው እነዚ ሰላቢዎች የዛሬዎቹ ሰላቢዎችምኮ እንደትላንትና ለዛወም ብሰው አስራችንን እንደሚያሳዩን ሳስበው ይገርመኛል
God bless america and the rest of the world.
ወንድም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 275
Joined: Thu Jan 13, 2005 3:05 am
Location: united states

Postby ናፍቆት » Thu Oct 11, 2007 10:54 am

ሒትለር - የጻፍከውን ሳነበው እንዴት እንዳሳቀኝ ... ከምር .... ለማንኛውም 'ይሄ fan' ብዬ ያልኩት የዋርካን ..... ምንድነበርማ የምትሉት ........ እ....... 'ታዳሚያን' ብለህ ልትወስደው ትችላለህ

ዋናው - Yeah! እኔም እንደዛው - የማደንቃት ጸሀፊ ነች ... ሁለት ነው ሶስት መጽሀፎችዋን አንብቤ ውድድ አድርጌያቸዋለሁ .... አንድ ሌላ አባባልዋን ለምን እኔ ደሞ አልጨምርልህም 'To say 'I love you' one must first be able to say the 'I.' ብላለች .... ለነሒትለር እንዴት ልተርጉምላቸው በናትህ ...... እ....... 'መጀመሪያ ራስህን ውደድ/አስቀድም ' ቢባል ያስኬዳል? እዚህ ኮምፕዩተሬ ላይ screen saver ያደረኩት የራሴን ፕሮፋይል ነው .... እና ብዙዎች ... 'አንቺ የራስሽን ፎቶ ታረጊያለሽ? ' እያሉ እንትን ይላሉ .... አንዱ እንደውም narcissistic ነሽ እንዴ? ብሎ አሹፎብኛል .... (በትክክል ካስታወስኩ እዚህ ዋርካ ላይም አንዱ ሳይለኝ አይቀርም አንድ ጊዜ) እኔ ለራሴ ትንሽ ሲደብረኝ ወይም በስራ ላይ ወደ ኮምፕዩተሬ desktop መለስ ስል ፈገግታዋን ሳየው እንዴት ደስ እንደሚለኝ .... ከምር


ShyBoy - 'ጦር' ያልከውን ሳነበው አዝናንቶኛል .... ስለስራዬ ባጭሩ ለማስቀመጥ ያህል .... እ.... አይ ይቅር ባክህ ........ ሀገሩ - ሰው - ከብቱ ላልከው ... ሁሉም አሪፍ ነው - ከምር ..... ይሄ በርበሬ ምናምን የሚሉትን ዝም በላቸው ..... ያንድ አገር እድገት ከዋጋ ንረት ውጭ አይታየኝም ... ካለዛ ባለህበት መሄድ ነው - እዚህ ብታይ ሰሞኑን ከወደናንተ ለመጡ ቤተዘመዶች ቤት/መሬት ሲፈላለግ ተውሎ ማታ ማታ ወሬው እሱ ነው .... እና የሚጠራውን ብር አታምንም ..... እኔ ግን ደስ ይለኛል ... ለምን? ያን ያህል የሚከፍል አለ ማለት ነው ..... ታድያ ይሄ ደስ አይልህም? ከምር ..... አሁን በርበሬ ተወደደ ምናምን ዝባዝንኬ ..... እውነት አሁን ምንም የሌለው ኢትዮጵያዊ እንኳን በቀን አንዴ በርበሬ ሳይበላ የሚያድር ይመስልሀል? አያድርም . እመነኝ::

ስለሌላ ቶፒክ ላይ ስላለመጻፌ እና ደሞ ... ሌላም የማወራህ አለኝ - ለምሳ ሊወስዱኝ መጥተው ውጪ ብለው ደውለውልኛልና አሁን መውጣቴ ነው .... ከሰአት እንደገባሁ እጽፍልሀለሁ ..... promise.

ደረቅ ያለ ጥብስ ነው ያማረኝ .....
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

ሁሉም በተራው.....

Postby ቦርዶ » Thu Oct 11, 2007 12:38 pm

ናፍቆትዬ እንኳን እውነተኛው አለም ላይ በደስታ መጡ!!!ይህን ውሰዱልኝ....ይህን አድርሱልኝ....የሚሉት ቃላቶች በውስጥና በውጭ ያለውን ህዝብ ከበከኑት አንሆ አመታታት አልፈዋል:: ዛሬ አገራችን ያለችበትናን ወደፊትም የሚጠብቃትን ስናይ ደግሞ በቅርቡ ልቋረጥ ሊችል ይሆናል የሚለውን ተስፋ ግን ከህሊናችን ብናወጣው ሳይሻል የሚቀር አይመስለኝም:: ይሁንና እንዳሉት እሽ ወይም እምቢ ማለት ሲቀል ሀተታ ማብዝቱ ባላስፈለገ ነበር::በይሉኝታ የተወጠረው የህዝባችን አይምሮና ለራሱ ሲጠይቅ እንጅ ለሰው ሲያደርግ ሰበብ የማያንሰው ወገናችንም ከዚህ ሀተካራ ይላቀቃል ማለትም ገና የአመታት ጉዞ ያስፈልገዋል:: ለማንኛውም ነገሮችን ሳያከሩት በቀልድ ለማሳለፍ ቢሞክሩት ...........
ቦርዶ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 80
Joined: Wed Jan 19, 2005 7:23 pm
Location: united states

Postby ናፍቆት » Thu Oct 11, 2007 5:27 pm

ShyBoy - .......... እስካሁን ቢሮ ነኝ .... ሥራ .... ሥራ ....... ውይ ሊገሉን ነው.... ....... አይኔ ሁሉ ድፍርስርስ ብሎ ብታየኝ አታውቀኝም ... ከምር ..... መቼም ማንበብና ይሄ ፒሲ አይኔን እንደሚያጠፉት ነው :: That, I know for sure. ከምር .....

ጦር ብትል ..... ይሄ .... ወታደሮች ትዝ የሚሉኝ ቲቪ ላይ ...... ለበአል ወይም ደሞ ለመቀስቀስ በሚደረጉላቸው ዝግጅቶች ላይ ነው የማውቃቸው .... እና ...... እ..... ይሄ ምንድነውማ ...... ይሄ ትርምስምስ የሚሉት ነገርና በምኑም በምኑም የሙዚቃ ቢት ወላይትኛ መጨፈር የሚወዱት ነገር እንዳለ ሆኖ .... እንዲሁ ሳስባቸው እርስ በርሳቸው ፍቅር ያላቸው ይመስለኛል:: ልክ ነኝ?

በሌላ ቶፒክ ላይ ከጻፍኩ ብዙ በጣም ብዙ ጊዜዬ ነው .... ሲጀመር አላነባቸውም .... I don't have the time , like before. ..... ሌላው ደሞ I think ብዙዎቹ 'fans' በተለያየ ስም ይጽፋሉ መሰለኝ ብዙው ነገር ተመሳሳይ ይሆንብኛል ... አንዳንዴ ሳስበው ዋርካን የሚያውቁትና የሚጠቀሙት በጣም እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች (ስሞች አይደለም - ሰዎች) ብቻ ይመስሉኛል:: .... አንዳንዴ ጊዜ ሳገኝ ርእሶችን አየት አየት አረጋለሁ ..... ልክ ነህ ዘፈን ስለማውጣት የተጻፈ አንብቤያለሁ .... ለምን? I think, if I remember correctly, the title was .... like .... ይድረስ ለናሆም ሪከርድስ ... ምናምን ነገር ..... እና ያነበብኩት ....... እ ...... እዚህ አገር በሚዲያ ካሴት ምናምን ሲወጣ ሲያስተዋውቁ ..... ናሆም ሪከርድስ ካሜሪካ እያሉ ልባችንን ዝቅ ያደርጓታል .... እና when I went there, አንድ ቀን ይዘውኝ በግራችን ዞር ዞር ስንል ..... የቤቱን (ቢሮውን? ) ጽሁፍ አየሁና ..... I was like ..... 'ይሄ ነው ናሆም ሪከርድስ ' they said 'yes' ..... then , I was like .... Oh! Ok. የሆነች እንትን ነገር ...... እና ያን ቶፒክ ሳየው 'ምን ተጽፎላቸው ይሆናል? ' በሚል ነበር ያነበብኩት .....

ልበልህማ ..... የከተማው ባለስልጣኖች ባሁኑ ወቅት የተቸገሩበትን ነገር ..... 'የከተማ የድምጽ ብክለት' .... ቤተክርስትያኑ - መስጊዱ - ለማኙ ..... ጩህት አላስተኛ አለን ብለው እነማን ለመንግስት አቤት ቢሉ ጥሩ ነው - እነቱሪስቶችና ... አንዳንድ ሸራተን ወይም ሂልተን ለማረፍ በቂ ገንዘብ ይዘው የመጡ ዲያስፖራ ..... ደስ አይልም? ከሸራተን በታች ያለውን የሀይማኖት ቤት አላውቅም ብትለኝ እገልሀለሁ .... እና ....... እዛ ያረፉት ምን እንዳሉ ...... 'ከ200 ዶላር በላይ ላንድ ቀን እየከፈልን በንትን ጩህት ከለሊቱ በስንት ሰአት ነው ምናምን .... መነሳት አለብን ወይ? ..... አይጥምም..... ትናንት በቲቪ የሚመለከተውን ሁሉ ሰብስበው ... 'ድምጾች የወቅቱ ያገሪቱ ችግሮች' እንደሆኑና የመንግስት ልዩ ትኩረት ያሰፈለጋቸው መሆኑ በውይይት ላይ ቀርቦልሀል ...... ይህንን ምን ትለዋለህ? .... የኔን ልንገርህ? .... እድገት መሰለኝ ..... ከለት እንጀራ ሀሳቦች .... ለየት ያለ ስለሆነ ጥሞኛል .....

'Only One Road' የተሰኘውን የ Celine Dion ሙዚቃ እየሰማሁ ነው ..... ደሞ እስዋንም አልወዳትም በለኝ .... ለስለስ ያሉ ዘፈኖችዋን በፍቅር ነው የምወዳቸው ..... Her musics are ....... kind of .... seducing to me ...... በቃ ውስድ ነው የሚያረጉኝ ..... honestly.

...... only one road, I'm walking ,,,,, only one life time, one hear to guide me ..... በናትህ ባትወደውም ተጋበዝልኝ .... ስሞት .....

ቦርዶ - ያልከው ግማሹ ባይገባኝም - ስምህ በጣም አስቆኛል:: ከምር ..... ለምን እንዳሳቀኝ I have no idea.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby እህምም » Thu Oct 11, 2007 6:57 pm

ናፍቆት wrote:
ልበልህማ ..... የከተማው ባለስልጣኖች ባሁኑ ወቅት የተቸገሩበትን ነገር ..... 'የከተማ የድምጽ ብክለት' .... ቤተክርስትያኑ - መስጊዱ - ለማኙ ..... ጩህት አላስተኛ አለን ብለው እነማን ለመንግስት አቤት ቢሉ ጥሩ ነው - እነቱሪስቶችና ... አንዳንድ ሸራተን ወይም ሂልተን ለማረፍ በቂ ገንዘብ ይዘው የመጡ ዲያስፖራ ..... ደስ አይልም? ከሸራተን በታች ያለውን የሀይማኖት ቤት አላውቅም ብትለኝ እገልሀለሁ .... እና ....... እዛ ያረፉት ምን እንዳሉ ...... 'ከ200 ዶላር በላይ ላንድ ቀን እየከፈልን በንትን ጩህት ከለሊቱ በስንት ሰአት ነው ምናምን .... መነሳት አለብን ወይ? ..... አይጥምም..... ትናንት በቲቪ የሚመለከተውን ሁሉ ሰብስበው ... 'ድምጾች የወቅቱ ያገሪቱ ችግሮች' እንደሆኑና የመንግስት ልዩ ትኩረት ያሰፈለጋቸው መሆኑ በውይይት ላይ ቀርቦልሀል ...... ይህንን ምን ትለዋለህ? .... የኔን ልንገርህ? .... እድገት መሰለኝ ..... ከለት እንጀራ ሀሳቦች .... ለየት ያለ ስለሆነ ጥሞኛል .....ይሄ ነገር በጣም ነው ያሳቀኝ :lol: "የደላው ሙቅ ያኝካል" ነገር, I can't contain myself :lol: ከምር ግን ያመለከቱት ሰዎች ሀበሻ ከሆኑ they must be brain dead. boojie a$ folks!
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Oct 11, 2007 7:39 pm

ናፍቆት wrote:ShyBoy - .......... እስካሁን ቢሮ ነኝ .... ሥራ .... ሥራ ....... ውይ ሊገሉን ነው.... ....... አይኔ ሁሉ ድፍርስርስ ብሎ ብታየኝ አታውቀኝም ... ከምር ..... መቼም ማንበብና ይሄ ፒሲ አይኔን እንደሚያጠፉት ነው :: That, I know for sure. ከምር .....

..

.
የልጁን ባላውቅም እኔ የምር ባይሽ አላውቅሽም ....እኔም የምሬን ነው
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ShyBoy » Fri Oct 12, 2007 1:46 am

ፓን ሪዚኮ wrote:
ናፍቆት wrote:ShyBoy - .......... እስካሁን ቢሮ ነኝ .... ሥራ .... ሥራ ....... ውይ ሊገሉን ነው.... ....... አይኔ ሁሉ ድፍርስርስ ብሎ ብታየኝ አታውቀኝም ... ከምር ..... መቼም ማንበብና ይሄ ፒሲ አይኔን እንደሚያጠፉት ነው :: That, I know for sure. ከምር .....

..

.
የልጁን ባላውቅም እኔ የምር ባይሽ አላውቅሽም ....እኔም የምሬን ነው


ፓኑ አባፈረዳ: እኔ ጨዋታው ጥሞኝ ልዝናና ብቅ ብቅ ስል በሌላ ነገር ጠረጠርኸኝ እንዴ? ካሁን በፊትም ሽማግሌ ልኮብሻል አንድ በይው ስትላት ነበር............ኧረ ተው ይሄንን ቢራ በልኩ አድርገው :lol: ያልተጻፈ እያስነበበህ አስቸገረ'ኮ:: መድሀኒት ፈልግልኝ ብልህ የባሰ ድንዙዝ የሚያደርግ ነገር ጠቁመኸኝ.............ደሞ በዛ ላይ ጭራሽ የማላውቀውን ቦርጭ መስራት ጀመረኝ እኮ::

ናፍቆት: ሰላም ነሽ ወይ? ቅድም ቢሮ ሁኜ አጮልቄ ሳይ የሆነ ነገር ጻፍ ጻፍ አድርገሽ ቆይተሽ ለመመለስ ቃል ገብተሽ ወጠሻል:: ከምሳ ተመልሸ ስገባ ደሞ ቃልሽን ጠብቀሽ አዝናኙን ወግሽን ጠርቀሽልናል (ትንሽ ብዚ ሁኜ ነው እንጂ ወዲያው ምስጋና ላቀርብ ፈልጌ ነበር):: በይ እስቲ ይልመድብሽ:: የድምጽ ብክለቱ ነገር በጣም ነው አንፈራፍሮ የገደለኝ! አል ጎር ቢሰማ የሆነ ዶኩመንተሪ ይሰራለት ነበር:: እኔ እምልሽ: እንዲያው መካሪ የለሽም? ለምንድን ነው አይንሽ እስኪጠፋ የምታነቢው? የሆንሽ የንባብ ቀበኛ መሆንሽ በጣም ያስታውቃል! ምናለ ከኔ ትንሽ ቢያካፍልሽ ኑሮ..........እኔ ወይ ካላዝናናኝ: ወይ የሆነ እርካታ ካልሰጠኝ: ወይ ጥቅም ላይ ካላዋልሁት ላንብብ ብየ ንክች አላደርግም:: Pragmatic Theory ነው የምትሉት? የሱ ነገር ደጋፊ ሳልሆን አልቀርም:: እስቲ አሁን ከዛ ሁሉ ካነበብሽው ህልቆ መሳፍርት የሌለው የመጽሀፍ ብዛት ምን ጥቅም አገኘሽ: ስንቱስ አዝናናሽ (አረካሽ)? እንደኔ እንደኔ ትልቅ ጥቅም ቢያስገኝልሽም እንኳን በጣም ቀንሽው ባይ ነኝ..........እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል ብላለሽ አህይት:: አይንሽ ከጠፋ በኋላ ምን ዋጋ አለው? ደሞ እኮ I know it for sure እያልሽ ውበትሽን ትናገሪያለሽ :lol: "አውቆ አበድ" ይሉታል እንዳንቺ አይነቱን ነው......በስላሴ ተብለሽ ነው? :lol: የኔ አይን ገና ጥሬ ጨው እንደመሰለች ናት: ከፈለግሽ ተበደሪኝ:: ኮምፒውተሩ እንኳን ብዙም አይጎዳሽም:: LCD ቴክኖሎጅ እያለ ላይን ብዙም እንደማያሳስብ የሆነ ሙህር ነኝ ባይ ሲናገር ሰምቸዋለሁ:: ያ ባይሆን ኑሮማ ተያይዘን አልቀን ነበር::

'Only One Road' የተሰኘውን የ Celine Dion ሙዚቃ እየሰማሁ ነው ..... ደሞ እስዋንም አልወዳትም በለኝ .... ለስለስ ያሉ ዘፈኖችዋን በፍቅር ነው የምወዳቸው ..... Her musics are ....... kind of .... seducing to me ...... በቃ ውስድ ነው የሚያረጉኝ ..... honestly.

...... only one road, I'm walking ,,,,, only one life time, one hear to guide me ..... በናትህ ባትወደውም ተጋበዝልኝ .... ስሞት .....


ለዘፈን ግብዣው በጣም አመሰግናለሁ! እንዳልሁሽ ለውጭ ዘፈን እና ለኢትዮጵያ እግርኳስ ምንም ስሜት የለኝም:: ግን ያው ከምትሞች ብየ አዳመጥሁልሽ..........የምትለው ባይገባኝም ወድጀዋለሁ:: አልፎ አልፎ ባጋጣሚ የምሰማቸው የእንግሊዘኛ ዘፈኖች ትርጉሙ ሳይገባኝ ደስ ይሉኛል............ሆን ብየ ግን እንግሊዘኛ ዘፈን ሰምቸ አላውቅም: በጭራሽ! በተለይ የጥቁሮችን ራፕ ነው ምናምን የሚሉት ከሰማሁ አርባ ክንድ ርቄ ነው የምሄደው::

ንሽማ እንግዲህ አንድ ሰማኒያ ሶስት ኪሎ በርበሬና አስራ ስምንት ኪሎ ቂቤ በአህያ ጭነሽ ላኪልኝ............ለዲያስፖራ ያለሽ ሀዘኔታ ለመቸ ነው ታዲያ :lol: :lol: :lol:
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby አንበርብር » Fri Oct 12, 2007 4:43 am

ሻይቦይ:
ይህች ነገር እኔንም ግራ ግብት አድርጋኝ ነበር :: ምናልባት 'fun' ለማለት ይሆናል ብየ ቀይሬ ባነበው የተሻለ ትርጉም ሰጥቶኛል ግን በደንብ አልገጥምልህ አለኝ :: አዳሜ ተሰብስቦ (ድመቶች እንኳን ሳይቀሩ ) የእንግሊዘኛ ፊልም በሚኮመኩሙበት ሰሀት እኔ ከብት ስሰበስብ አድጌ እንግሊዘኛ በጣም ያብጥብኛል ! እንዲያው እንደኛ አገር ቁምጣ እጥር ..................


ምፀት የሌለበትን አነጋገርህን በጣም እወድልሀለሁ........ ማንነትህን አትደብቅም...... አትኮራም ወይም የሌለህን አለኝ ብለህ አትልም..... ግልፅ ትመስለኛለህ........ ምናልባት ይህ ባህሪህን በአካል ከምታኘው ሰው ጋር የምትጋራው ከሆነ.......... ልዩ ተሰጥኦ አለህ!! ይህን የሚያደርጉ ጥቂቶች ናቸውና!!!!! ሻት ቦይ ላንተ ያለኝን ክብር በምትወዳቸው......... በመይሳው ካሳ: ነዋይ እና ዚዳን ስም ይድረስህ.......... አንበርብር ነኝ ከናፍቆት ጀርባ :lol: :lol: :lol:
Image
አንበርብር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Apr 09, 2005 12:01 am
Location: everywhere

Postby ጂኒው » Fri Oct 12, 2007 5:34 am

አንበርብር wrote:ሻይቦይ:
ይህች ነገር እኔንም ግራ ግብት አድርጋኝ ነበር :: ምናልባት 'fun' ለማለት ይሆናል ብየ ቀይሬ ባነበው የተሻለ ትርጉም ሰጥቶኛል ግን በደንብ አልገጥምልህ አለኝ :: አዳሜ ተሰብስቦ (ድመቶች እንኳን ሳይቀሩ ) የእንግሊዘኛ ፊልም በሚኮመኩሙበት ሰሀት እኔ ከብት ስሰበስብ አድጌ እንግሊዘኛ በጣም ያብጥብኛል ! እንዲያው እንደኛ አገር ቁምጣ እጥር ..................ምፀት የሌለበትን አነጋገርህን በጣም እወድልሀለሁ........ ማንነትህን አትደብቅም...... አትኮራም ወይም የሌለህን አለኝ ብለህ አትልም..... ግልፅ ትመስለኛለህ........ ምናልባት ይህ ባህሪህን በአካል ከምታኘው ሰው ጋር የምትጋራው ከሆነ.......... ልዩ ተሰጥኦ አለህ!! ይህን የሚያደርጉ ጥቂቶች ናቸውና!!!!! ሻት ቦይ ላንተ ያለኝን ክብር በምትወዳቸው......... በመይሳው ካሳ: ነዋይ እና ዚዳን ስም ይድረስህ.......... አንበርብር ነኝ ከናፍቆት ጀርባ :lol: :lol: :lol:አይ አንቺ ሰውዬ አንበርብር ከስንቱ ጀርባ ነው የምትኖሪው?
ስትፈልግ ከ ሄነሪ ጀርባ ትላለህ ስትፈልግ ከኢምሬት ጀርባ ትላለህ ቅቅቅቅቅ ባስ ሲልብህ ከቫንፒርስ ጀርባ ቅቅቅቅ ብለህ ብለህ ደሞ ከናፍቆት ጀርባ ብለህ አረፍከው? :lol: :lol: :lol: ምን አንተ ቅማል ነህ እንዴ?
ጂኒው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Oct 09, 2007 2:41 am

Postby ጂኒው » Fri Oct 12, 2007 5:39 am

ናፍቆት ላንቺ ያልሆነ ቮካብለሪ ይበጣጠስ @!
fan= አድናቂ, ደጋፊ, አቸፍቻፊ,
ታዳምያን=audiance

ቀደዳዎችሽን ግን ከጀርባ ሆኜ እንደ አንበርብር እየተከታተልኩ ነው:: ወሬዎችሽ አይደብሩምም አይጥሙምም
ጂኒው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Oct 09, 2007 2:41 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests