ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ናፍቆት » Thu Nov 08, 2007 7:58 am

ሰሞኑን የሆነ የቤተሰብ 'get together' አይነት ነገር ላይ ተከስቼ ነበር .... እና ሰዎች ሰብሰብ ያሉበት ቦታ መገኘትና ሰዎችን ዝም ብሎ መታዘብ ደስ ከሚለኝ ነገር አንዱ ነው ..... ..... የኢቲቪ ደሞ ቢዮንሴ ዝግጅትዋን አቅርባ የሄደች ሰሞን የስዋኑ ነገር እያቀረበ እንዲሁ ህዝቡን ናላውን ሲያዞረው ነበር የከረመው .... እና ቲቪው ድምጹ ጠፍቶ ምስሉ ብቻ ይታያል ..... ትልልቅ ሰዎች ... ልጆች ... ወጣቶች .... ሀብታም ..... ድሀ .. ምናምኑም ...... ሰብሰብ ብሎ የተገኘበት አይነት scene ነው ..... እና ያው ስለቢዮንሴ ... ምናምን ተነስቶ አንድዋ ዘመዳችን - ትልቅ ሴት ናት ..... የቤተክርስትያን አዘውታሪ ምናምን ነገር .....

'ይቺ ያገር መዋረጃ ..... እስዋማ ምን ታድርግ ... የኛዎቹ ናቸው እንጂ ........ ጳጳሱን አነጋገረች ሲባል? ..... እንዴ? .... እስቲ ምን ስለሆነች? ...... ጉድ እኮ ነው ..... ' እያለች ተብከነከነች ..... 'እንዴ እስቲ አሁን ጳጳስ በጁ ይጨብጣል? መስቀል ያሳልማል እንጂ? ' ...... ጉድ ....... አንድ ወደ ግራቸው የተቀመጡ ትልቅ ሰውዬ
'አይ ... ምን ለነገሩ ሰውየው እዚያ ውጭ ሲሄድ እኮ በቁምጣ ነው አሉ የሚቀመጠው ' ......
'እረ .... እረ .... እሱን እኔ አልሰማሁም .... አንተ ደሞ እንደው ትንሽ መንገድ ከከፈቱልህ' .....
' ሙች ስልሽ .... '
ሆ ሆ ይ .....

(አይጥሙም? )
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby sleepless girl » Fri Nov 09, 2007 2:48 am

ናፍቆት wrote:ሰሞኑን የሆነ የቤተሰብ 'get together' አይነት ነገር ላይ ተከስቼ ነበር .... እና ሰዎች ሰብሰብ ያሉበት ቦታ መገኘትና ሰዎችን ዝም ብሎ መታዘብ ደስ ከሚለኝ ነገር አንዱ ነው ..... ..... የኢቲቪ ደሞ ቢዮንሴ ዝግጅትዋን አቅርባ የሄደች ሰሞን የስዋኑ ነገር እያቀረበ እንዲሁ ህዝቡን ናላውን ሲያዞረው ነበር የከረመው .... እና ቲቪው ድምጹ ጠፍቶ ምስሉ ብቻ ይታያል ..... ትልልቅ ሰዎች ... ልጆች ... ወጣቶች .... ሀብታም ..... ድሀ .. ምናምኑም ...... ሰብሰብ ብሎ የተገኘበት አይነት scene ነው ..... እና ያው ስለቢዮንሴ ... ምናምን ተነስቶ አንድዋ ዘመዳችን - ትልቅ ሴት ናት ..... የቤተክርስትያን አዘውታሪ ምናምን ነገር .....

'ይቺ ያገር መዋረጃ ..... እስዋማ ምን ታድርግ ... የኛዎቹ ናቸው እንጂ ........ ጳጳሱን አነጋገረች ሲባል? ..... እንዴ? .... እስቲ ምን ስለሆነች? ...... ጉድ እኮ ነው ..... ' እያለች ተብከነከነች ..... 'እንዴ እስቲ አሁን ጳጳስ በጁ ይጨብጣል? መስቀል ያሳልማል እንጂ? ' ...... ጉድ ....... አንድ ወደ ግራቸው የተቀመጡ ትልቅ ሰውዬ
'አይ ... ምን ለነገሩ ሰውየው እዚያ ውጭ ሲሄድ እኮ በቁምጣ ነው አሉ የሚቀመጠው ' ......
'እረ .... እረ .... እሱን እኔ አልሰማሁም .... አንተ ደሞ እንደው ትንሽ መንገድ ከከፈቱልህ' .....
' ሙች ስልሽ .... '
ሆ ሆ ይ .....

(አይጥሙም? )


ቕቕቕቕቕቕቕቕቕቕቕቕቕቕ
ቕቕቕቕቕቕቕቕቕቕቕ ተመቹኝ!!! ነው የምልሽ ናፍቆት.................ቕቕቕቕቕቕቕቕቕ
Nothing is impossible!!
sleepless girl
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1510
Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
Location: near u!

Postby ክሪስታል » Wed Nov 14, 2007 5:51 pm

አንዱ ጋዜጣ ላይ ያሏችሁን ልንገራችሁ - ካፒታል የሚባል የሀገር ውስጥ ጋዜጣ ሰዎችን ኢንተርቪው አድርጎ የሰጡትን መልስ ነው ያቀረበው ....

ጥያቄው: Do you think Ethiopians abroad
promote their nation’s interests well?

መልሶቹ......
I don’t think the so-called diaspora Ethiopians are representing Ethiopia as well as they can, given the huge resources at their command. Even Eritreans abroad, who number much less than Ethiopians (abroad) do more to support their country. In my opinion, the majority of Ethiopians abroad are concerned more with their personal lives and only occasionally, whenever they feel homesick, remember their nation.

Beza, Actress

Lets clarify what is meant by the ‘nation’s interests; I think you are referring to standing up for your nation. Well, I have two view points on this. If promoting your country’s interests is to organize/ participate in anti- EPRDF rallies in foreign capitals, then I don’t think that the best way of helping your nation. On the other hand, if they consciously and consistently try to portray a positive image of their country, regardless of politics, then they are representing us well.

Mikias, Program officer

I believe that Ethiopians residing abroad, especially in the USA, are doing a great job in promoting our national interests. They write letters and sign petitions to congressmen and senators so that they can influence decisions by the US government in regard to Ethiopia. The passing of HR 2003 is proof that the diaspora is active and influential.

Lema, Lecturer

The only good that foreign based Ethiopians contribute to their homeland is in the form of the few dollars they send their dependent parents and often lazy brothers and sisters.

Asfaw, Teller
"We can do no great things--only small things with great love." -- Mother Teresa
ክሪስታል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 256
Joined: Sat Sep 03, 2005 3:35 pm
Location: Crawkozia

Postby ናፍቆት » Mon Nov 19, 2007 7:42 am

*** deleted ***
Last edited by ናፍቆት on Tue Nov 20, 2007 9:53 am, edited 1 time in total.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Mon Nov 19, 2007 11:05 am

አንድ የሆነ ነገር ጀምሬ በቃ .... ብጭርቅ ነገር ብያለሁ .... ጊዜም የለኝ ... እንደዛም ሆኖ ግን ያሁኑ ቅዳሜ ጠዋት ሳምንታዊ እቃ ግዢ እኔ ማድረግ ነበረብኝ .... ብዙ ጊዜ ባልሄድም ገበያ ያለውን ትእይንት ማየት ደሞ ስለሚያዝናናኝ ደስ እያለኝ ነበር የሄድኩት ....

እዚህ እቃ የምንገዛቸው ሰዎች አሉ .... ገበያ ነገር .... ቆየት ያልን ደንበኞች ነን (ከነቤተሰብ) ..... የባለቤትዋ ሴት ልጅ እዚያው እያየናት ያደገች አለች .... ቀይ ቆንጅዬ ነገር .... አሁን እቃ መመዘን ጀምራለች ... ከሱቃቸው ፊት ለፊት ተኮልኩለው ጸሃይ ሲጠጡ የሚውሉ ገጠሬ ልጆች አሉ ... ተሸካሚዎች ...እቃውን ገዛዝቼ ጨረስኩ.... መልስ የሰጠችኝ ብር ድፍን ነበር ...
'በናትሽ ዘርዝሪልኝ' አልኳት ....
'ለቆምጬዎች ለምትሰጪው ነው? ' አለችኝ ....
'እረ ለፓርኪንጉም ለምኑም ዝርዝር ያስፈልጋል' .... ዘረዘረችልኝ ... ግብይቱ አለቀ ....
'ቆምጬ! ' አለችና ተጣራች .... ከተኮለኮሉት ልጆች ሶስቱ ብድግ ብለው እየተጋፉ መጡ ... ጥቁር ሉጫ ጸጉሩ ግንባሩ ላይ ድፍት ያለውን .. በግምት 14 / 15 አመት የሚሆነውን ጥቁር ግን ደሞ ጥርት ያለ ፊት ያለውን ልጅ መረጥኩ .... ለወትሮው ጸጉረ ሉጫ ወንድ አልወድም ... ልጁ አፍንጫው ስልክክ ብሎ ቅንድቡ እንደመግጠም ያለ ... ደስ ይላል ... እቃውን ለመሰብሰብና ለመሸከም ጎንበስ ብሎ መሰብሰብ ጀመረ ....
'ቆምጬ በደንብ ሰብስበህ እሰር' አለች እናትየው ደሞ ... ይሄኔ ተደጋገመብኝ መሰለኝ ...
'ለምንድነው ግን ቆምጬ የምትልዋቸው? ... ለምን በስማቸው አትጠሩዋቸውም? .. እዚሁ ነው የሚውሉት ... ስማቸውን አትጠይቁአቸውም? ' አልኩኝ ... ከምሬ ነበር .... ልጅትዋ እንደመቀለድ አለች
'ባክሽ ስማቸው አይያዝም ... እንትን ምናምን ... ጫላ ምናምን'
'እ? ቆምጬ ብሎ ጫላ? በይ እነጫላ እንዳይሰሙሽ' አልኩአት ... ይሄኔ ልጁ ካጎነበሰበት ቀና አለና ፈገግ አለ ... የጥርሱ ተስተካክሎ ግጥም ማለት እና ንጣት ከዛ ከጥቁረቱ ጋር ... አቤ...ት ...
'አሁን እስቲ አንተ ስምህ ማነው? ' አለችው ...
ቀና አለና 'አትንኩት' አለ:: ልጁ የራሱን ስም ሲጠራ ፊቱ ብርት ነገር አለ .... ደስ አለኝ ...

አትንኩት እቃውን ተሸክሞ አብረን ሄድን ... መኪናው ላይ እቃውን ጫነና ራቅ ብሎ አቀርቅሮ ቆመ ... አንጀት የሚበላ ነገር አለው ... በስሙ ስጠራው እንደመደንገጥ ብሎ ጠጋ አለኝና እንደማፈር ብሎ እጅ እጄን አየኝ ... ለከተማው አዲስ ይመስላል ... ጉዳያችንን ጨረስን። አትንኩት ራመድ ራመድ እያለ ወደገበያው ተመለሰ ... ሌላኛዋ የኔ ብጤ እንዳታመልጠው ... መኪናዬን ወዲያው አላስነሳሁም ... ዝም ብዬ ቆሜ አትንኩትን ባይኔ ሸኘሁት ... ከሁአላ አንገቱ ላይ ደሞ ድፍት ያለውን ያ ጥቁር ሉጫ ጸጉሩን ... ለእድሜውም ሆነ ለቁመቱ ካቅሙ በላይ የሚመስለውን አንገቱ ላይ ተሸብሽቦም እንደገናም ወረድ ያለውን አረንጓዴ ሻርፑን ... ውሃ ከነካው የሰነበተውን ጥቁር ሰማያዊ አጭር ቁምጣውን ... አመዳም ጥቁር እግሩን .... አካሄዱን ብዙም ምቹ ያላደረገለትን በረባርሶ ጫማውን ... ... አየሁለት .... ካይኔ ጠፋ ... አሁንም ትንሽ ቆም አልኩኝ ...

አትንኩትን አላዋራሁትም ... ታሪኩን ብሰማ ባይኔ ካየሁት የባሰ አሳዛኝ ነገር ልሰማ እችላለሁ ብዬ ፈራሁ መሰለኝ .... ለገጠሬ ልጆች ያለኝ ስሜት ለየት ያለ ነው .... ከቆማጣው ከቆራጣው... ካይነስውሩ ከሽማግሌው ካሮጊቱ ... ይሄ ድህነት አጠናግሮ ያለመልኩ መልክ ከሰጠው ምናምንቴ ሁሉ .... ከገጠር መጥተው እዚህ ከተማ የሚንከራተቱት ልጆች .... የሆነ በቃ ... ውስጤ ርብሽ ነገር ....

አሁን አሁን እዚህ አዲሳባ የገጠር ልጆች በብዛት በየመንገኩ ይታያሉ ... ሲለምኑ ... ሲሸከሙ ... ሲንከራተቱ ... ምን እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። ከገጠር ወዳዲሳባ የህዝቡ ፍልሰት በጣም የጨመረ ይመስለኛል .. ያስፈራል::

ትናንት እሁድ ደሞ በኢቲቪ ስለ ምግብ ዋስትና በቀረበ ፕሮግራም ላይ .... ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሁኑ ሰአት ብዙ ... በጣም ብዙ ወጣቶች ስራ ያጡ እና የማይማሩም እንዳሉ ... እርሻም ማረስ ያልቻሉ ... መሬት የሌላቸው .... ያገሪቱ ያሁኑ ፖሊሲም አንዱ ችግር ፈጣሪ እንደሆነ (ባሁኑ ወቅት መሬት አይሸነሸንም? ምናምን ነገር? ) ... ተባለ። ብዙ የአትንኩት ዘመዶችና ጓደኞች ታዩኝ እንደገና .... አዲሳባ በየመንገዱ ላይ ..... እንደገና ሲፈሱ አልታየህም?

ለማንኛውም ቅዳሜ ጠዋት ብዙም የሚመች ስሜት አልነበረኝም ...

ትዝታ - አንድ ጊዜ ወደ ላንጋኖ እንሄዳለን .... መሃል መንገድ ላይ ድንገት መንገድ ላይ ተበላሽታ የማታውቅ መኪና ተፍ ተፍ ብላ ቀጥ አለች ... ቆምንና ኮፈኑን ከፍተን ቼክ ማድረግ ጀመርን .... ከየት መጣ ሳንል አንድ ትንሽዬ ልጅ (7 / 8 አመት) ብቅ አለ ... የከብት መጠበቂያ ጅራፍ ነገር ይዞ .. ትዝ ይለኛል .. አንዱ አይኑ ላይ ወደ ሶስት ሌላኛው ላይ ሁለት ዝንቦች ይጫወታሉ ..... መኪናውን ስናይ የሆነ ቺንጋ ይሁን ምናምን ... ብቻ ጫፉ ተቆርጦ መቀጠል ነበረበት ... የሚገርመው ስንት ኮተት የተጫነበት መኪና ምላጭ ወይም መቀስ የለውም .... ኡ...ይ ምላጭ ነገር ያስፈልገናል ተባለ .... አታምነኝም ... ትንሹ ልጅ እኔ አለኝ ... ብሎ ተቀዶ ከተሰፋ ኪሱ ውስጥ ምላጭ ሰጠን ... አላመንኩም ....

(ይህንን ስጽፍ መጀመሪያ ታይፕ ስጠፈጥፍ ውዬ .... ዋርካ 'time out' ብሎ ሲያጠፋብኝ እንዴት ቅጥል እንዳደረገኝ ... ከዛ ምን ትዝ አለኝ አንድ ጊዜ አንድ ሰው እዚሁ ላይ የሆነ ሳይት ጠቁሞኝ ነበር .... በዛ ተጠቅመሽ ታይፕ አድርገሽ ከዛ ኮፒ አድርጊ ብሎኝ .... ከዛ እዚሁ ፎረም ላይ ወደሁአላ ዞሬ ዞሬ አግኝቼው በሱ ነው የጻፍኩት ... ሳይቱን የሰጠኝ ትምህርት የሚባል ጸሃፊ ነበር .... thanks ብያለሁ )

....
Last edited by ናፍቆት on Tue Nov 20, 2007 9:49 am, edited 2 times in total.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Mon Nov 19, 2007 11:38 am

***
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Mon Nov 19, 2007 12:54 pm

***
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ShyBoy » Mon Nov 19, 2007 5:05 pm

ናፍቆትዬ! እግዚአብሄርን ዛሬ መጦብሻል! እንዴት ነች ለመሆኑ? ጠፍተሽ ጠፍተሽ በጣም ደስ የሚል ጽሁፍ ይዘሽ ብቅ አልሽልን! አትንኩት እና ሌላኛው ትንሽ ልጅ (ወደ ላንጋኖ ስቴዱ ያገኛችሁት) በቃ መጠው ፊቴ ላይ የቆሙ እስኪመስለኝ ነው ባይምሮየ የተሳሉት!!! ድሮ ልጅ እያለሁ የነበሩት ጓደኞቸ (እኔን ጨምሮ) ነው ትዝ ያለኝ:: አትንኩት የለበሰው (አንቺ ሻርፕ ያልሽው) ፎጣ እኛ አካባቢ "ጎጃም አዘነ" ይባላል:: ባይገርምሽ ገና ሀይ ስኩል እያለሁ ከ10 አመት በፊት የገዛሁት ጎጃም አዘነ አሁንም ድረስ አለኝ:: አዲስ አበባ ስገባም ይዤው ነበር አመሪካ ስመጣም አምጥቸዋለሁ:: ጭራሽ ፍንክች ይል መሰለሽ? ዛሬም አዲስ ነው! በጣም እወደዋለሁ:: ድሮ በዛ ዝናብ ከብት ለመሰብሰብ ስወጣ ለብሼው የምወጣው ትዝ ይለኛል:: አትንኩትን አይተሽ እንግዲህ ድሮ እኔ ምን እመስል እንደነበር አስቢው: ቁርጥ እሱን (ላልጠቁር እና ጥርሴ እንደሱ ላያምር ይችላል...........የጸጉራችን ሉጫነት: አመዳምነታችን እና ቁምጣችን ግን አንድ ነው):: እኔ እምለው: ለምንድን ነው ግን ብዙ የገጠር ሰዎች (በተለይ እኛ አካባቢ) ጸጉራችን ሉጫ የሚሆነው? ናፍቆት: ሉጫ ጸጉር ካልወደድሽ እንግዲህ ከወደ ናይጀሪያ ጥበሺ ቅቅቅቅቅቅ

ከታሪኩ ልመለስ እና ነገሩ እጅግ ያሳዝናል!!! እኔ ተወልጀ ባደግሁበት እንኳን ስንቶቹ መሰሉሽ ተቸግረው የሚኖሩት:: ትምህርት ለመማር አቅሙ የላቸውም:: ያም ሁኖ እየተራቡ እንኳን ከ20KM የሚበልጥ በእግራቸው እየተጓዙ የሚማሩ አሉ:: የኔም ብዙ የቅርብ ዘመዶች አሉኝ:: በተለይ አሁን አሁን ምንም ችግሩ እየከፋ ቢሄድም እኛ የምንበላው ይቅር እያሉ ወላጆች ከየት እና የት ገጠር ራሱ ልጃቸውን ያስተምራሉ:: ግን አሁንም ቢሆን ከህዝቡ ብዛት አንጻር የሚማሩት ቁጥር ኢምንት ነው:: ናፍቆት ወደድሽም ጠላሽም ለችግሩ መንስኤ የመንግስት እጅ አለበት!!! ብዙ ብዙ መስራት ይጠበቅበታል!!!!!!! እኔ እውነት እልሻለሁ ለራሴ ሀብታም ለመሆን አስቤ አላውቅም:: ግን ሀብታም ሁኜ ቢያንስ የተወሰኑትን ብረዳ የሁልጊዜም ምኞቴ ነው!!!!!!!! እግዚአብሄር እንዲያሳካልኝ ጸሎቴ ነው! በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ድህነት ምን ያህል እንደተስፋፋ ለመንገር ይከብደኛል! and yet ያ የገጠር ሂወቴ ይናፍቀኛል!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ናፍቆት » Fri Nov 30, 2007 11:59 am

'ጎጃም አዘነ' ደስ ይላል:: ለምን ልብሱን ከሀዘን ጋር እንዳጣበቃችሁት መገመት ባልችልም::

ግን shyboy ከምርህ ነው? Really እንደዛ ያደክ ልጅ ነህ? ነው ወይስ ዝም ብለህ you're just trying to impress ....

ናይጄሪያ ላልከው .... አንድ ጊዜ የገጠመኝን ባወራልህ በሳቅ ፍርስ ነበር የምትለው ... ግን ጉዳዩ ትንሽ 'up close and personal' አይነት ስለሆነ ... እዚህ ላይ ብለቀልቀው ትንሽ የወጣ ነገር ይሆንብኛል ....

ሀብታም ሆነህ እውነት ጎጃምና ጎጃም አዘነው ትዝ ብለውህ ከረዳህ ጥሩ ነው :: ከምር::

ልብልህማ ..... ትዝ ያለኝን .... ወደናንተ ባለፈው ስመጣ ፍላይት ውስጥ ያገኘሁት ያንተን አገር ሰው ነበር ... መጀመሪያ ተማሪ ልጅ አጠገቤ ነበረች .... እና እሱ ሌላ ሲት ላይ ነበር ... ግን እየመጣ እንዴት ነው ምናምን ... ተጫወቱ ምናምን ይል ነበር ... ትልቅ ነው ልጆቹም እዚያው ፍላይት ውስጥ ነበሩ ... ለክረምት እዚህ ከርመው እየተመለሱ ምናምን ነገር ..... then ..... after a while, he came and sat next to me .... ልጅትዋን 'እስኪ ከልጆቹ ጋር ትንሽ ተጫወቺ እዛ' ብሎ ወደሱ ቦታ ልኳት ምናምን ..... I was reading a book .... taking a break in between ... so he started some talk about the book .... ... ከዛ ቀጠለ ..... ሰውየው ..... He happens to be a 'would-be' investor in Ethiopia.... .... So he told me that የሆነ ትልቅ በጣም ትልቅ ሪዞርት አገርህ ላይ እንደሚሰራ .. መሬት እንደተመራ .... He lived in the US for about 35 years .... and he seems to be in a good financial status .... kind of ....

He talked nonstop .... I couldn't get back to my book. Or my nap either. After some time, he started being irritating to me. I couldn't preserve my privacy. እንዴት ሀብታም እንደሚኮን ... ምናምን ... ልጆቹን እንዴት እንደሚያሳድጋቸው ... ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ስራ መሰራት እንዳለበት (አንተ እንዳልከው) ..... ከብዙ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጋር እንደተነጋገረ እና ... ብዙ ነገር facilitate እንደሚደረግለት ቃል እንደተገባለት ምናምን ነገር...... መሀል ላይ ልጅትዋ ብትመጣም እሱ የጦፈ ወሬ ላይ ስለነበር .... he didn't want to go .... ምናምን ነገር ....

ለማንኛውም ሰሞኑን በቲቪ አየሁት ሰውየውን:: ያለው እውነቱን ነበር ..... በጣም አሪፍ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል ... የሚለው ልክ እንዳንተ ነው ... አገሩ ውስጥ ኢንቨስት አርጎ ድሀውንም ለመጥቀም ... ምናምን ነገር .... ልቤን በወሬው ቢያወልቀውም እውነቱን ስለሆነ ደስ ብሎኛል ሳየው:: ላንተም ያንን እመኛለሁ::

እዚህ ዋርካ ላይ የምጽፈው ዘና ነገር ስል ነው:: እና ሙዚቃ አለ ሁሌ .... Celine Dion በቅርብ የለቀቀችውን 'taking chances' የተሰኘውን አዲስ አልበሟን እየሰማሁላት ነው .... በዚህ ስራዋ ብዙዎች በደንብ ድምጽዋ አልወጣም .. ምናልባትም እየደከመች እንደሆነ የታየበት ስራው ነው ብለው ቢያጣጥሏትም ..... 'Eyes on Me' የሚለውን ሙዚቃዋን እየሰማሁት ነው ... እና በጣም ወድጄዋለሁ ..... በዚህ ሙዚቃ ላይ የተወሰነ ቦታ ላይ ድምጽዋ የሻኪራን ይመስላል ልበል? ጋብዤሀለሁ:: I really adore her. ከምር::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Fri Nov 30, 2007 12:00 pm

'ጎጃም አዘነ' ደስ ይላል:: ለምን ልብሱን ከሀዘን ጋር እንዳጣበቃችሁት መገመት ባልችልም::

ግን shyboy ከምርህ ነው? Really እንደዛ ያደክ ልጅ ነህ? ነው ወይስ ዝም ብለህ you're just trying to impress ....

ናይጄሪያ ላልከው .... አንድ ጊዜ የገጠመኝን ባወራልህ በሳቅ ፍርስ ነበር የምትለው ... ግን ጉዳዩ ትንሽ 'up close and personal' አይነት ስለሆነ ... እዚህ ላይ ብለቀልቀው ትንሽ የወጣ ነገር ይሆንብኛል ....

ሀብታም ሆነህ እውነት ጎጃምና ጎጃም አዘነው ትዝ ብለውህ ከረዳህ ጥሩ ነው :: ከምር::

ልብልህማ ..... ትዝ ያለኝን .... ወደናንተ ባለፈው ስመጣ ፍላይት ውስጥ ያገኘሁት ያንተን አገር ሰው ነበር ... መጀመሪያ ተማሪ ልጅ አጠገቤ ነበረች .... እና እሱ ሌላ ሲት ላይ ነበር ... ግን እየመጣ እንዴት ነው ምናምን ... ተጫወቱ ምናምን ይል ነበር ... ትልቅ ነው ልጆቹም እዚያው ፍላይት ውስጥ ነበሩ ... ለክረምት እዚህ ከርመው እየተመለሱ ምናምን ነገር ..... then ..... after a while, he came and sat next to me .... ልጅትዋን 'እስኪ ከልጆቹ ጋር ትንሽ ተጫወቺ እዛ' ብሎ ወደሱ ቦታ ልኳት ምናምን ..... I was reading a book .... taking a break in between ... so he started some talk about the book .... ... ከዛ ቀጠለ ..... ሰውየው ..... He happens to be a 'would-be' investor in Ethiopia.... .... So he told me that የሆነ ትልቅ በጣም ትልቅ ሪዞርት አገርህ ላይ እንደሚሰራ .. መሬት እንደተመራ .... He lived in the US for about 35 years .... and he seems to be in a good financial status .... kind of ....

He talked nonstop .... I couldn't get back to my book. Or my nap either. After some time, he started being irritating to me. I couldn't preserve my privacy. እንዴት ሀብታም እንደሚኮን ... ምናምን ... ልጆቹን እንዴት እንደሚያሳድጋቸው ... ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ስራ መሰራት እንዳለበት (አንተ እንዳልከው) ..... ከብዙ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጋር እንደተነጋገረ እና ... ብዙ ነገር facilitate እንደሚደረግለት ቃል እንደተገባለት ምናምን ነገር...... መሀል ላይ ልጅትዋ ብትመጣም እሱ የጦፈ ወሬ ላይ ስለነበር .... he didn't want to go .... ምናምን ነገር ....

ለማንኛውም ሰሞኑን በቲቪ አየሁት ሰውየውን:: ያለው እውነቱን ነበር ..... በጣም አሪፍ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል ... የሚለው ልክ እንዳንተ ነው ... አገሩ ውስጥ ኢንቨስት አርጎ ድሀውንም ለመጥቀም ... ምናምን ነገር .... ልቤን በወሬው ቢያወልቀውም እውነቱን ስለሆነ ደስ ብሎኛል ሳየው:: ላንተም ያንን እመኛለሁ::

እዚህ ዋርካ ላይ የምጽፈው ዘና ነገር ስል ነው:: እና ሙዚቃ አለ ሁሌ .... Celine Dion በቅርብ የለቀቀችውን 'taking chances' የተሰኘውን አዲስ አልበሟን እየሰማሁላት ነው .... በዚህ ስራዋ ብዙዎች በደንብ ድምጽዋ አልወጣም .. ምናልባትም እየደከመች እንደሆነ የታየበት ስራው ነው ብለው ቢያጣጥሏትም ..... 'Eyes on Me' የሚለውን ሙዚቃዋን እየሰማሁት ነው ... እና በጣም ወድጄዋለሁ ..... በዚህ ሙዚቃ ላይ የተወሰነ ቦታ ላይ ድምጽዋ የሻኪራን ይመስላል ልበል? ጋብዤሀለሁ:: I really adore her. ከምር::
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ShyBoy » Fri Nov 30, 2007 6:05 pm

ሀይ ናፍቆት! እንኳን ከጠፋሽበት በሰላም መጣሽ! መቸስ አንች እንደመስቀል ወፍ ኑረስ ኑረሽ ነው ብቅ የምትይው::

የ"ጎጃም አዘነ" ስም አወጣጥ ምንም የማውቀው የለም:: ነገር ግን አንዳንዶች እንደቀልድ እያደረጉ ሲናገሩ የሰማሁት ብርድ ልብስም ተወዶ: ጋቢም ማሰራቱ ከብዶ ሰዉ የሚለብሰው ባጣበት ጊዜ ስለመጣ ነው ይላሉ:: "ጎጃም አዘነ" ሲያስፈልግ ቀን እንደ ጋቢ: ሲያስፈልግ ማታ እንደ ብርድ ልብስ ይለበሳል:: በዚያ ላይ ሲያጥቡት በቀላሉ ይጸዳል: ሲደርቅም አፍታ አይቆይ:: ብቻ ምናለፋሽ እውነትም ጎጃም አዝኖ (ጸልዮ) ያመጣው ነገር ሳይሆን አይቀርም::

ግን shyboy ከምርህ ነው ? Really እንደዛ ያደክ ልጅ ነህ ? ነው ወይስ ዝም ብለህ you're just trying to impress ....


እንግዲህ ሙሉ ለሙሉ አንቺ እንደገለጽሽው ልጅ ላልሆን እችላለሁ:: ነገር ግን.........እንጨት ለቅሜ: ከብት, በግ, ፍየል ሰብስቤ: ቁምጣ እና ጎጃም አዘነ ለብሸ ነው ያደግሁት:: እኔ ያደግሁት በጣም ትንሽ የሆነች የገጠር ከተማ ውስጥ ነው:: እኔ ተወልጀ 2 አመት እስኪሆነኝ ድረስ ወላጆቼ ዋናው ገጠር ውስጥ በግብርና ይተዳደሩ ነበር:: ልክ እኔ 2 አመት ሲሞላኝ ነው አሉ ወደዚያች ትንሽየ የገጠር ከተማ ገብተው ንግድ የጀመሩት:: ከወፍጮ ተነሱና ወደ እህል ንግድ ብሎም ወደ መኪና አድገዋል:: አዲስ አበባም ይመላለሱ ነበር (አሁን እንዲያውም ግማሹ ቤተሰብ አዲስ አበባ ነው):: ነገር ግን ቤተሰቦቸ በጣም ስትሪክት ስለሆኑ አስተዳደጌ እዛው እንደዋናው ገጠር ነው (በርግጥ ሰፈሯ ብዙ ነጋዴ ይኑርባት እንጅ አካባቢው በጠቅላላ/10 ደቂቃም ሳትጓዥ ገጠር ነው):: አሁንም እንቆቅልሽ የሚሆንብኝ ነገር እርሻ ባይኖረንም ከብቶች: በጎች እና ፍየሎች ነበሩን:: ምንም ጥቅም አይሰጡም....እነንና ወንድሞቸን ማልፋት ብቻ!!! ከወፍጮ ቤት ጎን ቤት ተሰርቶላቸው እዛ ያድራሉ:: ጥዋት ጥዋት እየተነሳሁ ከብቶችን ለረኛው አስረክባለሁ: በግና ፍየሎችን ደሞ ዝም ብየ እለቃቸዋለሁ:: ማታ ማታ ደግሞ ከብቶችን ከረኛው እቀበላለሁ: በግና ፍየሎችን ደሞ ከዋሉበት ሁሉ ፈልጌ እሰበስባለሁ:: አንዳንዴ ደሞ የከብቶች እረኛ ሊለቅ ይችላል (የኛን ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰው ነው የሚጠብቀው) እና ያኔ ሰው ሁሉ በየተራ ሲጠብቅ የኛን ተራ እሸፍናለሁ......ጫካ ለጫካ እሾህ እየወጋኝ ስዞርልሽ እውላለሁ ማለት ነው:: ከሁሉም የሚያስመርረኝ ከብቶችም ሆኑ ፍየሎች እና በጎች ሲጠፉ መፈለግ ነው! አንዳንዴ እስከ እኩለ ሌሊትም መፈለግ አለ:: በዛ ላይ ጠፍተው ጅብ በልቷቸው ያገኘናቸውም አሉ:: የእንጨት ለቀማውን ነገርማ ተይው!!! በክረምቱ (ትምህርቱ ሲዘጋ) ሁሌ እንጨት ለቀማ እንሄዳለን (ባል ካልሆነ በስተቀር):: ከዛ ዝናብ ሲያዘራን ውለን አንገታችን እስኪቀላ ተሸክመን እንመጣለን:: ደግነቱ እንጨት ለቀማውን ቶሎ ተውሁት:: ልክ 6ኛ ክፍል ሚኒስትሪን ተፈትኜ 3 ቀን እንደለቀምሁ እንጨቱን ከራሴ ላይ አውርጀ ስገባ አባቴ ከአዲስ አበባ መጦ አገኘሁት:: ከዛ የት ሂደህ ነው ሲለኝ እንጨት ለቀማ አልሁት:: ከዛ እናቴን ተቆጣትና ሁለተኛ እንጨት ለቀማ እንዳትልኪው አላት:: ከዛች ቀን በኋላ እንጨት አለቀምሁም...........ከብት ስብሰባው ግን 12ኛ ክፍልን እስከምጨርስ አልቀረልኝም:: እንጨት ለቀማውን ባርፍም በጣም ደባሪው የወፍጮ ቤት ስራ አልቀረልኝም (እየመዘኑ ሂሳብ መቀበሉ):: እሁድ እና ቅዳሜ ደሞ መጋዝን እህል መግዛት::....................በስማም ምን ሁኜ ነው ግን ይሄን ሁሉ ታሪኬን የምዘረዘው:: Anyway, እና ናፍቆት ኢምፕረስ ለማድረግ ሳይሆን እንደዚህ ነው ያደግሁት ስለሽ ነው:: ቁምጣ 10ኛ ክፍል እስከምደርስ ለብሻለሁ: ጎጃም አዘነው ግን አሁንም አብሮኝ አለ:: እርሻ ባልችልም ከከብት ጋር ነው ያደግሁት:: ግን ያ ሂወቴ በጣም ይናፍቀኛል!!!!!!!!!!!!!!!!!! አሁን እንኳን የኔ ታናናሾች እንጨት አይለቅሙም: ከብት አይሰበስቡም:: በጎችን እንኳን ማታ ማታ ፈልገው ወደማደሪያቸው ያስገባሉ:: በጣም የሚገርሜኝ ግን ምንም ጥቅማቸው አይታየኝም ልጆችን ከማልፋት በስተቀር:: በግ ወይ ፍየል ሲታረድ እንኳን ተገዝቶ ነው እንጅ ከቤት አይታረድም:: ከብቶችም ቢሆኑ ከ ሁለቱ ወይም ሶስቱ በስተቀር ሌሎች ወተት አይሰጡም:: መተዳደሪያም አይደሉም:: በቃ ልማድ ልበለው? ወላጆቸ ገበሬዎች ስለነበሩ የከተማውም የገተሩም ኑሮ እንዳይቀርባቸው ነው::

ሀብታም ሆነህ እውነት ጎጃምና ጎጃም አዘነው ትዝ ብለውህ ከረዳህ ጥሩ ነው :: ከምር ::


ትዝ ብለውህ አልሽኝ? በጣም ነው እንጅ የሚናፍቁኝ!!! ሀብታም አልሆንም እንጅ ሀብታም ብሆንማ ገንዘቡን ለኔ አልፈልገውም:: ከምር! ለራሴ የምፈልገውን አልጣ እንጅ ትርፍ አልፈልግም.................ቁጠባ ትዝ ብሎኝ አያውቅም!!! ሌላው ይቅርና የቅርብ ድሀ ዘመዶቸን መርዳት ብችል በጣም ደስ ይለኛል.........ሁሌም የምመኘው እሱን ነው!!!!!!!

ለማንኛውም ሰሞኑን በቲቪ አየሁት ሰውየውን :: ያለው እውነቱን ነበር ..... በጣም አሪፍ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል ... የሚለው ልክ እንዳንተ ነው ... አገሩ ውስጥ ኢንቨስት አርጎ ድሀውንም ለመጥቀም ... ምናምን ነገር .... ልቤን በወሬው ቢያወልቀውም እውነቱን ስለሆነ ደስ ብሎኛል ሳየው :: ላንተም ያንን እመኛለሁ ::


ናፍቆት: ለምኞትሽ አመሰግናለሁ!!! ሰውየውም እግዜር ይስጠው!!! እኔ እንኳን ትግስት ኑሮኝ 35 አመት ይቅርና ካሁን በኋላ 1 አመትም እዚህ የምቆይ አይመስለኝም:: ሀገሬ በጣም ናፍቆኛል!!! እዚህ ሀገር በመኖሬ ደስተኛ አይደለሁም:: በቶሎ ወደ ሀገሬ መመለስ ነው የምፈልገው!!! እንዲያውም ብትችይ ስራ ብታፈላልጊልኝ ደስ ይለኛል..........ሪዚሜዬን በፕሪቬት እልክልሻለሁ :lol: ስራ የምታገኝልኝ ከሆነ................

..... 'Eyes on Me' የሚለውን ሙዚቃዋን እየሰማሁት ነው ... እና በጣም ወድጄዋለሁ ..... በዚህ ሙዚቃ ላይ የተወሰነ ቦታ ላይ ድምጽዋ የሻኪራን ይመስላል ልበል ? ጋብዤሀለሁ :: I really adore her. ከምር ::


ዛሬም ለግብዣሽ አመሰግናለሁ! ግን የእንግሊዘኛ ዘፈን እንዳመልወድ ታውቂያለሽ አይደል? ጭራሽ አይገባኝም! እንኳን ሲዘፍኑ ሲያወሩም በመከራ ነው የምሰማቸው:: ከከብት ጋር አድጌ የነሱን አክሰንት እድሰማ አጠብቂ.........እንግሊዘኛ ዜሮ ነኝ!!!!

ንሽ እንግዲህ ስራ ፈልጊልኝና ቶሎ ወደ ሀገሬ እንድመለስ እርጂኝ!!!!!!!!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ፀባየ_ወርቅ » Sat Dec 01, 2007 3:49 am

የማናት pedophile ባካቹ!!! :shock: :shock: :shock: :shock:

በታዳጊው ኩሊ--አትንኩኝ የምትሻፍጂ---- :evil: :evil: :evil: :evil:
' በጥቁረቱ በጸጉሩ በጥርሱ ባንገቱ መሀል መርካቶ ላይ
horny ሆንሽበት ቅቅቅቅቅቅቅ :lol: :lol: :lol: :lol:
ማን ያውቃል በሳንቲም አባብለሽው
ተጠቅመሽበትስ ቢሆን?
እዛ ስለዚ ጉዳይ የተጸፈ ህግ ባለመኖሩ you are f.u.c.k.ing lucky!!

እዚ ቢሆን ግን ይሄኔ ዘብጥያ ተከርቸም ነበርሽ!!
hey--- stop this sick practice tho
ፀባየ_ወርቅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 257
Joined: Sun Oct 21, 2007 2:25 am

Postby ናፍቆት » Wed Dec 05, 2007 7:40 am

Hi Shyboy - You have an interesting story. Thank you for sharing it with me. (Honestly)

ልንገርህማ - አንድ ዘመድ አለችን አሁን አንተ ያለህበት ሀገር - ያገባች - እና ባልየው እንዳንተ ገጠር ያደገ ነው ... እና ለረፍት ምናምን እዚህ ሲመጡ ባልዋ በጣም የሚፈልገው ገጠር ሄዶ ሳር ላይ ተኝቶ ጸሀይ ሲከካው መዋልን ነው .... ወይም ከብቶቹን ማየት ... ጎረቤት ምናምን ሰብስቦ ዝም ብሎ ማዋራት ... ስለ ከብቱ ስለ አገሩ ... ምናምን ... ነገር ... እና እዛም ሲሆን በጣም የሚናፍቀው ይሄ እንደሆነ ደጋግሞ ይናገራል - ልክ እንዳንተው - እና እኛ እዚህ ዘመዳችንን በቅጡ ማግኘትና አብሮ መጫወት ወይም መዞር እንደልብ አንችልም - ምክንያቱም ተነስቶ ገጠር ሲሄድ አብራ ተንጠልጥላ መሄድ ስላለባት ... and you know how husbands are.

እና ብዙ ጊዜ ሳስብ የገጠር ልጆች ከከተሜው የበለጠ ካገራቸው ጋር ያላቸው 'attachment' ጠበቅ እና ጠለቅ ያለ ይመስለኛል:: ይሄ ደሞ ቆንጆ 'originality' አይመስልህም? ከተሜው በተለይ አዲሳበባውያንን ያው ታውቃለህ አይደል? ... አዋዋሉ - አለባበሱ - አወራሩ - አበላሉ - ...... ምናምን ...... እና ብዙው ነገር የተደበላለቀ እና .... like .... some sort of originality የሌለው አይነት ነገር ነው .... እና ውጪ ሲሄድም ያን ያህል 'home sickness' እንደገጠሬው የሚጠነክርበት አይመስለኝም ... ካልተሳስትኩ ..... እና ምን ልልህ ነውማ ..... ገጠሬዎች ያንን unique feeling የበለጠ enjoy የሚያደርጉት ይመስለኛል - ናፍቆቱ ቢከብድም .... You are lucky!

I'll check my private mail. ውሸትህን ከሆነ ግን ገደልኩህ .....

የሙዚቃውን ነገር ሁለተኛ አይለምደኝም:: የንግሊዝኛ ሙዚቃ እንዲህ ካማረረህ ይቅር:: My problem is - I don't have amharic songs on my PC.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Wed Dec 05, 2007 7:52 am

ልጽፍልህ አስቤ የረሳሁት ነገር አለ

'Edna Mall' የሚባል አዲስ እንትን ተከፍቷል እዚህ - ቦሌ ቴሌ መድሀኒአለም አካባቢ .... ሰምተህ ይሆናል ... ሶስት ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶች አሉት .... ሌሎችም ብዙ ነገሮች ... ፊልም ቤቱ በጣም በቅርብ የወጡ ፊልሞችን እንደሚያቀርብ ተገልጿል - መግቢያ ዋጋው 40 ብር ነው (እስኪለመድ ለጊዜው በኪሳራ ለመስራት) ....... እና ቅዳሜ ለማየት ብዬ ፊልም ገብቼ ነበር .... ቅዳሜ ማለት 1 Dec. 2007 ነበር አይደል? ከሶስቱ ፊልሞች ያንዱን Release Date ልንገርህ? 30 November 2007. አዲስ ፊልም ቶሎ ልናይ ነው ... አይጥምም?

----


ልበልህማ .... እነዚህ ያፍሪካ መሪዎች አንዳንዴ ድንቅ አይሉህም? ሰሞኑን አንዱ ጋዜጣ ላይ ያነበብኩትንና ሳልወድ ያሳቀኝን ላጫውትህማ - ስልጣንን የሙጥኝ ያሉትን የ ዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤን አንዱ ጋዜጠኛ አንድ ጥያቄ አቅርቦላቸው ነበር:

ጋዜጠኛ - 'When are you going to say your people goodbye? '

ሙጋቤ - 'Where are they going? '

በናትህ ስሞት - Don't you find this amazing? Oh my! Trust me, with such presidents, we're not going any far.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ShyBoy » Wed Dec 05, 2007 8:24 pm

እህታችን ናፍቆት: እንደምን ሰነበትሽ? ሰላም ነሽ ወይ? እኔ ምንም አልልም:: ከነዛውም ደባሪ አገር ብርዱ ተጨምሮበት መከራችንን ያበላናል!

ናፍቆት: ቤትሽን እኮ የኔና አንች ብቻ መጫወቻ አደረግነው:: ቶሎ ቶሎ አለመምጣትሽ ይመስለኛል ሰውን አንብቦ ብቻ ውልቅ እንዲል የሚያደርገው:: ከቻልሽ ቶሎ ቶሎ ብቅ በይማ!

የአፍሪካ መሪዎችን ነገር ተይኝ! ከአባቱ የወረሳቸው ከብቶች መሰሉት እንዴ ሙጋቤ የዝንባቡዌን ህዝብ እስከሂወቱ ፍጻሜ መግዛት የሚፈልገው? So amazing! እኔም ራሴ ወደሀገሬ ለመመለስ በጣም እጓጓና የመሪዎቹን ነገር ሳስታውሰው ዝግንን ያደርገኛል (የምርጫው ጊዜ አዲስ አበባ ስለነበርሁ እስከ ጃኑዋሪ 2006 ያለውን ሁሉ ሂደት አውቀዋለሁ):: ያም ሁኖ ግን ከሌላው ኢትዮጵያዊ እኔ የተለየሁ አይደለሁም እና ወደ ሀገሬ መመለስን ሁሌም እናፍቃለሁ!!! Seriously, ጥሩ ስራ የምታገኝልኝ ከሆነ ለመምጣት አንድ ቀን አላድርም!!! ዋናው ፎሩም ላይ በስንት ቀን አንዴ እየመጣሽ ሳይ የዋርካ ፕራይቬት mailbox ቸክ የምታደርጊ ስላልመሰለኝ ነው እንጅ ረዙሜየንማ እልክልሻለሁ..........check it out ከምር! ብቻ ከዚህ ደባሪ አገር ገላግይኝ!!!

ሌላ ደሞ ስለምን ነበር ልመልስልሽ የነበረው?.........አዎ! ስለ ፊልም:: ለፊልም አፍቃሪዎች በጣም ጥሩ ነው አዳዲስ ፊልሞችን የሚያሳይ ቤት መከፈቱ (ግን 40 ብር አልበዛም?.......ደሞ እኮ እስኪለመድ በኪሳራ ለመስራት አልሽኝ..........ከሰዉ አቅም ጋር ውድ መሰለኝ):: እኔ እንኳን ያው እንደዘፈኑ ፊልሙም ላይ እስከዚህም ነኝ:: ስራየ ብየ ፊልም አላይም:: እንዳጋጣሚ ሰዎች ከፍተው እያዩ ከደረስሁ ወይም አስገድደው ከወሰዱኝ አያለሁ:: እስካሁን ያየኋቸው ፊልሞች በግምት ከ25 አይበልጡም:: እዚህ ከመጣሁ ፊልም ቤት የሄድሁት 3 ቀን ነው::

ይልቅ ከሁለት ቀን በፊት አይቸው በጣም የወደድሁትን ፊልም ልንገርሽ (ግን እንዳትስቂብኝ የድሮ ፊልም ነው):: የአውሮፓ እግር ኳስ ለማየት የሆነ ኬብል ሰርቪስ ሰብስክራይብ አድርጌያለሁ:: እግረመንገዱን ብዙ ቻናሎች አሉት.........እንዲሁም on demand የሚል ፌቸር አለው (በፈለግሽው ጊዜ የፈለግሽውን ፊልም የምታይበት):: እና አብሮኝ ያለው ጓደኛየ ብዙ ጊዜ ያያል........አዳዲስ ፖስት የተደረጉትን ደሞ በየቀኑ ይከታተላል:: ከዛ እሁድ እለት ይሄንን ፊልም ማየት አለብህ ብሎ በግድ እንዳየው ያዘኝ:: አይርሁትና በጣም ተደሰትሁ!!! እስከዛሬ ካየኋቸው ሁሉ ፊልሞች በጣም ወደድሁት!!! የፊልሙ ርዕስ "The gods must be crazy" ይሰኛል:: በጣም ከመውደዴ የተነሳ ስለፊልሙ እና ስለ አክተሩ ኢንተርኔት ላይ ፈልጌ ትንሽ ነገር አነበብሁ:: በጣም ነው የሳበኝ!!! ሌሎች ፓርቶችም እንዳሉት ስላነበብሁ ፈልጌ ማየቴ አይቀርም:: ፊልሙ የተሰራው ልክ በኔ እድሜ (1980/81) ነው ግን ስሙንም ሰምቸው አላውቅም ነበር:: ጓደናዬ ግን ገና ኢለመንታሪ ሲማር እንዳየው ነው የነገረኝ::

እስቲ አንችን ደሞ በጣም ያስደሰተሽን ፊልም ንገሪኝና ጋብዥኝ.................የፊልሙን ግብዣ በደስታ ነው የምቀበለው! ብዙ ፍቅር ባይኖረኝም እንደዘፈኑ ግን አልጠላውም (ለነገሩ ዘፈናቸውም አይስበኝም እንጅ አልጠላውም, ከጥቁሮቹ ቅብጥርጥር በስተቀር-which I hate too much)::

ያው እንግዲህ ሳምንት አሳልፈሽ ነው እና የምትመለሽው መልካም ሳምንት!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 5 guests