ከኢትዮጵያ ውጪ ላላችሁ ሰዎች....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby recho » Tue Jan 01, 2008 1:13 pm

አክየ wrote:አንች ሪጮ ምንድን ነው ቦታ የምታዝረከርኪው አንዱን አጥፍተሽ ሶስቱን ተይው
ቅቅቅ አክይዬ ሆዴ እስቲ አንተ አጥፋልኝ .. ምን ይሳንሀል .. ! :lol: :lol: ሪጮ ስትወድህ እኮ የኔ 1/0 :lol: :lol:
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ናፍቆት » Wed Jan 02, 2008 7:36 am

ዴቭ - Thanks,

ግን አልደብቅህና - አንዳንዴ ብዙ ርቄ አስብ አስብ አስብና የህይወት ትርጉሙ ጥፍት ብሎብኝ ቁጭ:: ከምሬ ነው የምልህ እኮ:: ውስጤ የሚፈልገውን ምን ያህል ነው የምኖረው ወይም የማደርገው ብዬማ ራሴን ከጠየኩ ..... በቃ ..... I feel like I'm going crazy .... አይነት ነገር ..... እና በንደዛ አይነት ሙድ ሆኜ ጠዋት ስገባ አለቃዬ ወይም አንዱ የስራ ባልደ.... 'እንደምን አደርሽ? ' ሲለኝ በጥፊ አጩይው አጩይው ነው የሚለኝ .... ከዚህ በፊት ስንቴ ያንን ጥያቄ በየጠዋቱ እንዳለኝ እና ደሞ እንደገና ወደፊት ስንቴ ሊለኝ እንደሚለኝ ሳስበውማ ..... በቃ ዘልዬ ባንቀው ወይ በጥፍሮቼ ብቦጫጭረው ደስታዬ ነው:: ከምር:: I just get really bored.

ግን ደሞ ልክ ነህ:: እንደገና ደሞ አንዳንዴም ልክ አይደለህም:: ለምሳሌ Unfaithful ን ውሰድ .... ሴትዮዋ ልጅዋን ወይም ባልዋን ጠልታ ይመስልሀል ያንን ያረገችው? Nope. ግን ያንን የመጨረሻ ጥግ የሚደርሰውን ከፍቅረኛዋ ጋር ያሳለፈችውን ጊዜ ብታስብ ..... ደስታዋን በምን ልትገምት ትችላለህ? በምንም:: ለዛ የፈለገ sacrifice ቢከፈል የሚቆጭ ይመስልሀል? .... I wonder. I am not saying that being unfaithful is a good thing. But was the lady acting like that to be 'unfaithful' ? And to hurt those who love her? Nope. She was just following her heart. እንዲህ አይነት ነገሮች በፍቅር ላይ ብቻ አይደለም የሚሆኑት ..... በሌላም ነገር ልትወስደው ትችላለህ .... The point is how often do we just listen to our 'self' (or heart, if you wish), and do what we really want to maximize our happiness?

ቀባጠርኩብህ? Ok, Ok. I'll stop here.


****
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Wed Jan 02, 2008 9:30 am

ሲታ !!! - Thank you for sharing the lyrics with me. It seems to be nice, don't you think? The lyrics, I mean.

Opra Show ብትል - ሰሞኑን እሱ ላይ ያየሁት Julia Roberts እና Tom Hanks ቀርበው ነበር አይደል? .... እና በጣም አሪፍ 'Kisser' ማነው ስትባል 'Tom Hanks' ነው ነበር ያለችው ... እና እሱም በጣም ደስ ብሎት እዛው በሁለት እጆቹ ፊትዋን ይዞ ሳብ አድርጎ He gave her a quick kiss. .... እና ምን እንዳሰብኩ ... ሀበሾች ቢሆኑ አልኩኝና ..... አንዱ የኛ አገር ወንድ ሚስቱ በሚዲያ እንዲህ አሪፍ አርጎ የሳመኝ ይሄ ነው ብትልና ተስባ ብትሳምለት ምን ሊል እንደሚችል ሳስበው ..... አሳቀኝ - ከሚያስቁኝ ነገሮች አንዱ የሀበሻ 'ወንድነት' ነው:: ከምር:: አንተ ብትሆንስ? ባልየው ማለቴ ነው:: አይ - ተወው - አትመስልስልኝ::

***
Last edited by ናፍቆት on Wed Jan 02, 2008 10:12 am, edited 1 time in total.
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Wed Jan 02, 2008 9:55 am

ትናንት ማታ ቆንጆ ምሽት አሳለፍኩ:: በሀገር ፍቅር ትንሽዋ አዳራሽ 'የጸጋዬ ገ/መድህን መዘከሪያ ምሽት' የመጨረሻው ክፍል ነበር:: ያለፉትን ሶስት ሳምንቶች የመግቢያ ትኬት ለማግኘት ባለመቻል ችግር ማየት አልቻልኩም ነበር:: በብር አይደለም የሚገባው - በ ግብዣ ብቻ ነው:: ከሱ በፊት የመንግስቱ ለማ መዘከሪያ ለ4 ሳምንት ተላልፎ አምልጦኛል - ያኔ እንኳን ስለፕሮግራሙም መኖር አልሰማሁም ነበር:: ዋና አዘጋጅና አቅራቢዎቹ አበበ ባልቻ - ፍቃዱ ተ/ማርያም - ነቢዩ መኮንን ነበሩ - አንድ በሀይሉ የሚባልም ኮሚክ ነገር በየመሀሉ ሲያስፈግገን አመሸ::

በምሽቱ የጸጋዬ ምርጥ ስራዎች ቀርበዋል ... ስለሱ ግጥም አጻጻፍም አስተያየት በነቢዩ ቆንጆ ተደርጎ ተተንትኗል - ደስ ያለኝ ደሞ ከዚህ በፊት የትም ሚዲያ ላይ ያልቀረበ ፊልም ቀርቦ ነበር ... ጸጋዬ አሜሪካን አገር ሆኖ የተቀረጸው ..... probably in his last days ...

እና እዛ ላይ በየነጫጭባ አገር ህይወታቸው ካለፈው ብርቅ ኢትዮጵያውያን መካከል ለ እስኩንድር በጎሲያና ለገ/ክርስቶስ ደስታ የገጠማቸውን ግጥሞች እንዲሁም እንዴት መጀመሪያ የትና እንዴት እንደተዋወቃቸው ያወራል:: .... ምናምን .....

በጣም አሪፍ ነበር:: ሁለቱም በነጭ አገር 'ወድቀው ተገኙ' ነው የሚባለው ..... ብሎ ነበር ..... ሰዎቹ በህይወት እያሉ ምን አይነት ሰዎች እንደነበሩም ይናገራል::

ደስ የሚልም የሚያሳዝንም ምሽት ነበር:: እኔማ በጭራቃ ነገር አይደለሁ ..... አንዳንዴ ለማልቀስ ሁሉ እፈልግ ነበር:: ግን ደሞ የሆነ ውስጥህ .... በቃ የሆነ satisfaction ሲያገኝ ደሞ ይሰማሀል:: እነዛን መሰል ሰዎች 'ከዚህ' መሆናቸው በራሱ የሚሰጥህ እንትን ነገር አለ .....

ከብዙ በጥቂቱ
ጸጋዬ ካላቸው ...
እስኩንድርን መጀመሪያ ሳገኘው 'እስክንድር ነው እንጂ ለምን እስኩንድር ተባልክ አልኩት' ..... እሱም 'እስክንድር ልሁል አለ ብለዋል .... ደስ አላላቸውም ብለዋል .... ሲባል ሰማሁና እኔም Je m'en fou! I don't give a shit! አልኩና ስሜን እስኩንድር ብዬ ቀየርኩት " አለኝ ....... እስኩንድር ብዙ ጊዜ I don't give a shit! ብሎ ንግግር መጨረስ ይወድ ነበር ..... እኔም ታድያ ያው 'ሀጠራው' እለው ነበር ......


****
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ናፍቆት » Wed Jan 02, 2008 10:00 am

......

ዝግጅቱ ላይ ..... አበበ ባልቻ ከኦቴሎ .... ፍቃዱ ት/ማርያም ደሞ ከቴዎድሮስ ትያትር ቀንጭበው አቅርበው ነበር ..... ፍቃዱ የቴዎድሮስን የመጨረሻ ንግግር ሲል ለራሴ እስኪገርመኝ ድረስ አፌ አብሮት ያነበንብ ነበር .... እንዲህ እንደተቀረጸብኝ አላውቅም ነበር ..... መጨረሻ ላይ መነባንቡን ሲጨርስ ሰዉ ብድግ ብሎ ጭብጨባውን ማቆም አልተቻለም ነበር:: ያኔስ እንባዬንም ለማቆም አልታገልኩም::

It was really a memorable night.

******
ናፍቆት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 234
Joined: Tue Sep 16, 2003 7:03 am

Postby ShyBoy » Wed Jan 02, 2008 10:24 pm

እንዴ! ናፍቆት በሳምንቷ መጣች? እንኳን በደህና መጣሽ ናፍቆት!!! እኔስ ተስፋ ቆርጨ በሚቀጥለው ሳምንት ነበር የጠበቅሁሽ:: እስቲ ደሞ ወደ 3 ቀን አውርጅልን መምጫሽን!!! ካልሆነ ፔቲሽን እናስገባ እንዴ?

ናፍቆት: ዛሬ ከነገርሽን ነገሮች የፍቃዱ ተ/ማሪያም መነባንብ በጣም ልቤን ነክቶታል!!! (ማለቴ ያንች ሁኔታ ታየኝና በጣም ልቤን ነካኝ):: እኔን ታውቂናለሽ አይደል? ያው ከስር ፊርማዬን እንደምታይው የመይሳው ቴዲ በጣም አድናቂ ነኝ!!! ከሞቱት ሁሉ ሰዎች ማን ይነሳ ተብየ ብጠየቅ ያለምንም ጥርጥር አጼ ቴዎድሮስ ነው የምለው!!!!! ያለመታደል ሁኖ "ቴዎድሮስ" የሚለውን ቲያትር አላየሁትም:: ባልሳሳት እሱ ሲወጣ እኔ ለአዲስ አበባ ገና ፍሬሽ ነበርሁ (በቲቪ ሲተዋወቅ ትዝ እንደሚለኝ አመተ ምህረቱ 1993ዓ.ም. ሳይሆን አይቀርም....እርግጠኛ ግን አይደለሁም):: እስቲ በማርያም ከቻልሽ መነባንቡን እዚሁ ጻፊልን!!! አደራ!!!!

ሪቾ ያገር ልጅ! እንዴት ነሽ? ኑሮ እንዴት ይዞሻል? እኔን ብርዱ ሊገለኝ ነው ከዚህ አገር ካልገላገልሽኝ!!! ሰመር ላይ ደሞ ሙቀቱ መጦ ቀቅሎኝ ይሄዳል!!! "አሁን ይሄ ኑሮ ነው?" አለ አለባቸው ተካ (ነፍሱን ይማረው እና ከእንግዳዘር ጋር ጭውውት ሲሰራ.......ኧረ እሷንም ነፍሷን ይማረው!):: እና እየውልሽ የኛ ኑሮ ከእጅ ወዳፍ እንኳ አልሆን ብሏል!!!

ሪቾ ደሞ አንዳንዴ ሰው መስማት አለብሽ! አክየም ቢሆን! :lol: ምን ይሁን ብለሽ ነው 4 ጊዜ እኔን quote እያደረግሽ የለጠፍሽው??? ለሰሌዳው እና ለማርከሩም እየታሰበ!!! :lol: (ማርከር ያልሁሽ ቾክ ድሮ ቀረ ሲባል ሰምቸ ነው.....እኛ ድሮ አስተናግር የሚባል ቅጠል ካላመጣችሁ እየተባልን በቅጠሉ ጥቁር ሰሌዳውን እንቀባው ነበር......ከዛማ በቃ ሰሌዳው ጻፉብኝ ጻፉብኝ ይላል አፍ አውጥቶ: ክንድ የሚያህል ቾክ ይዞ ወጦ መጻፍ ያምርሻል..............አዲስ አበባማ አስተናግር ቅጠል ከየት ይገኛል ዋይት ቦርድ እና ማርከራችሁን ተጠቀሙ እንጅ):: አስተናግር ቅጠል ብል አስጠሊታ ሽታው መጣብኝ.....የሆነው ሁኖ ግን ሁሌም አርብ አርብ በአስተናግር ቅጠል ሰሌዳ መቀባት ግዴታችን ነበር::

ሪች: ለኮምፕሊመንቱ አመሰግናለሁ! ግን ስለየትናው ለዛ እንዳወራሽ አልገባኝም:: በስህተት "እጅግ በጣም ለዛቸው ሙጥጥ ያሉ ሰዎች" ከሚለው ሊስትሽ ጋር ተምታቶብሽ እንዳይሆን?

ዛሬ ደሞ ባሪፉ የተዘጋጀ እንግርግብ ቆሎ በጠላ/ቅራሪ አምሮኛል!!! ወይኔ ጎጃም በሆንሁ ኑሮ? ሪቾ ተባበሪኝማ ቤተሰብ ጋ መልክት አድርሽልኝና አዘጋጅተው ሲሰጡሽ ባስቸኳይ በDHL ላኪልኝ:: አንችም ደሞ ያማረሽን ንገሪኝና ከዚህ ይላክልሻል (ከOld Navy ሹራብ ግን እንዳያልፍ :lol:)::

በሉ ደህና አምሹ (ሀገር ቤት ያላችሁት ሪቾና ናፍቆት ደህና እደሩ.......ምናልባትም ይህኔ እናንተ ህልም እያያችሁ ይሆናል)!!!
ShyBoy
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1118
Joined: Tue Apr 04, 2006 10:36 pm
Location: Gojjam

Postby ሲታ!!! » Sun Jan 06, 2008 6:45 am

ናፍቆት:

የ ጁሊያ እና ቶም ሀንክስ ን ነገር ስታወሪ : Uሊ ቢሪ የ ግራሚ አዋርድ የወሰደች ጊዚ የሆነውን አስታወሰኝ :: ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረኩ ልክ እንደወጣች : ሽልማቱን ያቀርብ ከነበረው ሰው ጋር ተቃቅፈው ሞቅ ባለ ሁኒታ ሲሳሙ ላየ : በጣም የሚዋደዱ ፍቅረኛሞች ነበር የሚመስሉት::

ስለ ሀበሻ ወንድ ላልሽው ግን : በሴት እህቶቻችንም እንደዛው ይመስለኛል:: ያ ደግሞ ,የባህላችን: ያስተዳደጋችን...........ውጤት ይመስለኛል:: በለፈው ህንድ ውስጥ:Richard Gere ከ እንዲት የ Bollywood star ጋር in public በመሳሳማቸው ትልቅ ኤሹ ሆኖ ነበር:: እንደውም የ ህንድን ህዝብ ወተው ይቅርታ ይጠይቁ ሁሉ ተብሎ ነበር::

ታዲያ ይህን ስል እነሱ Oprah ላይ ወይም ሀሌ ቤሪ ያደረገችውን መደገፊ እንዳይመስልብኝ:: ገደብ ሊኖረው የሚገባ ይመስለኛል:: ያለዚያ ከ ገርል ፍሪኔዴ ወይም ከሚስቴ ጋር የማደርገው እንዴት ሊለይ ነው:: Pretty Woman የሚለውን የ Julia Roberts and Richard Gere ሙቪ የምታስታውሺው ይመስለኛል: እና እዛ ላይ Julia (the caracter played by julia) እንድ ቀን ከ Richard ጋር ካደረች በሓላ: ጉደኞችዋ ጋር ትደውል እና ከ Richard ጋር እንደተሳሳሙ ስትነግራቸው በጣም ይገረሙና "" ወደሽዋል "" ማለት ነው እይነት ነገር ይሏታል :: ነጥቡ ምንድነው ለገንዘብ ብላ ከተለያዩ ወንዶች ጋር ለምትወጣ በ ሙቪው ላይ እንዳለችው ካራክተር እንኩን : ሌሎችን ነገሮች ብታደርግ እንኳን french kiss ከምትውጂው ሰው ጋር የሚደርግ እይነት ነገር ነው::

በተረፍ በሀገር ፍቅር ሀሪፍ ጊዜ እንዳሳለፍሽ ለመረዳት ችያለሁ:: በወቅቱ የነበርሽን emotiontion በደምብ ሊታይ በ ሚችል መልኩ የገለጽሽ ይመስለኛል:: ለነገሩ Post የምታድርጊያችው ነገሮች ለየት የሚሉት ለዚህ ነው :: ቀላል የሚመስሎ የለት ከለት ገጠመኛች በቀላል እማሪኛ: ያንቺ ስሜት እና እስተያየት ታክሎበት........................

መልካም ገና ለሁሉም የ እምዱ ተከታታይ እመኛለሁ:::

ሲታ!!
ሲታ!!!
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Sat Dec 29, 2007 7:32 am

Postby ሲታ!!! » Sun Jan 06, 2008 6:46 am

ናፍቆት:

የ ጁሊያ እና ቶም ሀንክስ ን ነገር ስታወሪ : Uሊ ቢሪ የ ግራሚ አዋርድ የወሰደች ጊዚ የሆነውን አስታወሰኝ :: ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረኩ ልክ እንደወጣች : ሽልማቱን ያቀርብ ከነበረው ሰው ጋር ተቃቅፈው ሞቅ ባለ ሁኒታ ሲሳሙ ላየ : በጣም የሚዋደዱ ፍቅረኛሞች ነበር የሚመስሉት::

ስለ ሀበሻ ወንድ ላልሽው ግን : በሴት እህቶቻችንም እንደዛው ይመስለኛል:: ያ ደግሞ ,የባህላችን: ያስተዳደጋችን...........ውጤት ይመስለኛል:: በለፈው ህንድ ውስጥ:Richard Gere ከ እንዲት የ Bollywood star ጋር in public በመሳሳማቸው ትልቅ ኤሹ ሆኖ ነበር:: እንደውም የ ህንድን ህዝብ ወተው ይቅርታ ይጠይቁ ሁሉ ተብሎ ነበር::

ታዲያ ይህን ስል እነሱ Oprah ላይ ወይም ሀሌ ቤሪ ያደረገችውን መደገፊ እንዳይመስልብኝ:: ገደብ ሊኖረው የሚገባ ይመስለኛል:: ያለዚያ ከ ገርል ፍሪኔዴ ወይም ከሚስቴ ጋር የማደርገው እንዴት ሊለይ ነው:: Pretty Woman የሚለውን የ Julia Roberts and Richard Gere ሙቪ የምታስታውሺው ይመስለኛል: እና እዛ ላይ Julia (the caracter played by julia) እንድ ቀን ከ Richard ጋር ካደረች በሓላ: ጉደኞችዋ ጋር ትደውል እና ከ Richard ጋር እንደተሳሳሙ ስትነግራቸው በጣም ይገረሙና "" ወደሽዋል "" ማለት ነው እይነት ነገር ይሏታል :: ነጥቡ ምንድነው ለገንዘብ ብላ ከተለያዩ ወንዶች ጋር ለምትወጣ በ ሙቪው ላይ እንዳለችው ካራክተር እንኩን : ሌሎችን ነገሮች ብታደርግ እንኳን french kiss ከምትውጂው ሰው ጋር የሚደርግ እይነት ነገር ነው::

በተረፍ በሀገር ፍቅር ሀሪፍ ጊዜ እንዳሳለፍሽ ለመረዳት ችያለሁ:: በወቅቱ የነበርሽን emotiontion በደምብ ሊታይ በ ሚችል መልኩ የገለጽሽ ይመስለኛል:: ለነገሩ Post የምታድርጊያችው ነገሮች ለየት የሚሉት ለዚህ ነው :: ቀላል የሚመስሎ የለት ከለት ገጠመኛች በቀላል እማሪኛ: ያንቺ ስሜት እና እስተያየት ታክሎበት........................

መልካም ገና ለሁሉም የ እምዱ ተከታታይ እመኛለሁ:::

ሲታ!!
ሲታ!!!
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Sat Dec 29, 2007 7:32 am

Postby እህምም » Sun Jan 06, 2008 11:55 am

ሲታ!!! wrote:ናፍቆት:

ስለ ሀበሻ ወንድ ላልሽው ግን : በሴት እህቶቻችንም እንደዛው ይመስለኛል:: ያ ደግሞ ,የባህላችን: ያስተዳደጋችን...........ውጤት ይመስለኛል:: በለፈው ህንድ ውስጥ:Richard Gere ከ እንዲት የ Bollywood star ጋር in public በመሳሳማቸው ትልቅ ኤሹ ሆኖ ነበር:: እንደውም የ ህንድን ህዝብ ወተው ይቅርታ ይጠይቁ ሁሉ ተብሎ ነበር::

ሲታ!!

ኢሹ የሆነው መሳሳማቸው ነው ወይስ እሱ ህንዳዊ አለመሆኑ:: መሳሳማቸው ከሆነ ለማመን ትንሽ ያስቸግራኛል cuz i've watched quite a few bollywood movies (ahhmm... I have too many indian friends, don't judge :D ) with very graphic scenes that i couldn't believe they were made in india. but then again, ppl are hypocrats so you could be right.
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby ሲታ!!! » Mon Jan 07, 2008 6:40 am

እህምም

ያንተን/ችን ፓስት ካየሁ በኍላ: ተጨማሪ ወሪ ለማግኘት Richard Gereን ጉግል አድርጌ ነበር :: በዚህ የ BBC ዜና መሰረት Gere ተይዞ ፍርድቤት እንዲቀርብ የህንድ ፍርድቤት መያዣ ወረቀት አውጥቶበት ነበር:: እዚህ ላይ እንደምታየው/ዊ: እሟሟ!! ያደረጋት ጉንጯ ላይ ነው:: በለው!! ከንፈሩዋ ላይ ቢሆን ምን ሊሆኑ ነበር????

እነሆ ሊንኩ:

http://news.bbc.co.uk/2/hi/entertainment/6596163.stm

ሲታ
ሲታ!!!
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Sat Dec 29, 2007 7:32 am

Postby እህምም » Mon Jan 07, 2008 4:32 pm

ዋው! በጣም ነው የገረመኝ! thanx for posting the link.
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby የሚሚ:ባል » Mon Jan 07, 2008 5:01 pm

ሲታ!!! wrote:እህምም

ያንተን/ችን ፓስት ካየሁ በኍላ: ተጨማሪ ወሪ ለማግኘት Richard Gereን ጉግል አድርጌ ነበር :: በዚህ የ BBC ዜና መሰረት Gere ተይዞ ፍርድቤት እንዲቀርብ የህንድ ፍርድቤት መያዣ ወረቀት አውጥቶበት ነበር:: እዚህ ላይ እንደምታየው/ዊ: እሟሟ!! ያደረጋት ጉንጯ ላይ ነው:: በለው!! ከንፈሩዋ ላይ ቢሆን ምን ሊሆኑ ነበር????

እነሆ ሊንኩ:

http://news.bbc.co.uk/2/hi/entertainment/6596163.stm

ሲታ


ከዛ ደሞ እህምም ...

ዋው ! በጣም ነው የገረመኝ ! thanx for posting the link.


ያኔ ህንዶቹ አካበዱ!
ስንት የህንድ ፖርንእስታር አለ አይደል እንዴ?
Image
የሚሚ:ባል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1276
Joined: Mon Oct 22, 2007 8:41 am
Location: dictation:donation: duration:information: foundation: gas station:relation: rotation:vacation

Postby የሚሚ:ባል » Mon Jan 07, 2008 5:03 pm

:wink: :twisted: u know what i mean!
Image
የሚሚ:ባል
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1276
Joined: Mon Oct 22, 2007 8:41 am
Location: dictation:donation: duration:information: foundation: gas station:relation: rotation:vacation

Postby ሰልማ1 » Wed Jan 09, 2008 1:49 pm

ቅቅቅ ቆይ እናንተ ለመሆኑ ሰውየው Shilpa Shettyን እንዴት እንደሳማት አይታችኌል.. ዴም እንዲህም ይሳማል እንዴ :lol: :lol: :lol: :lol:
ናፍቆት እንደጻፈቸው
ከሚያስቁኝ ነገሮች አንዱ የሀበሻ ወንድነት ነው

ቅቅቅ የእኛ ወንድነት ያስቅሻል gal you should see Indian guys
እኔ የምር የህንዶች ነገር ግራ ያጋባኛል ... በአንድ በኩልበቴክኖሎጂ የመጠቁ እንደ Bangalore አይነት Hi-tech cities አሏቸው ኒኩሊየርም እስከመስራት ደርሰዋል
በሌላ በኩል ፍጹም ኍላ ቀር የሆኑ ልክ Bride Burnning(kitechen Fire) ልማድ አላቸው ትምህርት ያልደረሰበት አፍሪካ ውስጥ የማይካሄድ ዘግናኝ የሆነ ልማድ ....
የሙሽራዋ ቤተሰቦች ጥሎሹን ከፍለው ካልጨረሱ ባሏ gasoline በሰውነቷ ላይ አርከፍክፎ ከእነ ነፍሷ ያቃጥላታል
በአመት እስከ 5000 የሚደርሱ የህንድ ሴቶች በዚህ መንገድ ሂወታቸውን ያጣሉ ይባላል

Shyboy ባለፈው ያልኩህን ልጅ ፌስ አደረግኩት ግን ምንም ለውጥ የለውም :lol: :lol: :lol: የሆነ አድክም ልጅ ነው

በተረፈ እኔም እስቲ የእኔን all time favourite movies ሙቪ ልጋብዝህ CASABLANCA this movie is indisputably one of the landmarks of the American cinema, although an accidental Hollywood masterpiece and THE BABEL(the two young boys remind me my younger brothers )

በተረፈ ባለፈው ሙቪ subscribe አድርጌ ነው የምመለከተው ምናምን ያልክ ይመስለኛል እናም ስብስክራይብ ከምታደርግ ለምን እዚህ ሊንክ ገብተህ የፈለግከውን ሙቪ አትመለከተም http://www.ovguide.com/ አዳዲስ ቲያትር ላይ የሚወጡ ሙቪወችን ሁሉ ማየት ትችላልህ joox has a better quality

እና ይህን የጎጃም ሙዚቃ ጋብዠሀለሁ hope you will enjoy it http://www.youtube.com/watch?v=NZGkkHrI ... re=related
senisebiyorom
ሰልማ1
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1304
Joined: Sun Aug 05, 2007 2:11 am

Postby recho » Sun Jan 13, 2008 12:06 pm

ሰልማ1 wrote:ቅቅቅ የእኛ ወንድነት ያስቅሻል gal you should see Indian guys


እንዲሁም የህንድ ሴቶችንም ! አንዱ ወዳጄ ሲያጫውተኝ ... በህንዶች እንቅስቃሴ የሚባል ነገር ነገር ነውር ነው አሉ እንትን ላይ .. እና አንዲትዋ እዚህ እኛ አገር መጥታ ሀበሻ ወንድ ትይዝና .. መሀል ላይ አስቁማው አሉ ... Hey Ababa are u f**ing or dancing ? :lol: ሻይቦይ አይንህን ያዝ ይሄ ለሳልማ የተሰጠ መልስ ነው ..
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests

cron