አዘጋጅና አቅራቢ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ደራሲ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ኮከብ ተዋኒ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ገምጋሚ /ፓስወርድ
መግቢያ
ስለ ሰማያዊ ፈረስ አስተያየት ከሰጡ ተዋኒያን መሀል አንዱ 'ሰራዊት ፍቅሬ በፊልሙ አባይን ማነጋገር ችሎአል ' በማለት አድንቆታል። የካስትሮ ምስክር ቸጉቬሮ ካልሆነ .
ከተመልካችም እንዲሁ በጎና ቀና አስተያይት የሰጡትን ያህል የነቀፉም አይጠፉም። የፊልም አስራር ጥበብን መሰረት ባደረገ መልኩ ፊልሙን የገመገመ ጽሁፍ ግን እስካሁን አላነበብኩም።
ግምገማ በተለይም የፊልሙን ድክመት አጉልቶ የሚያሳይ ከሆን በፊልም ሰሪዉ አካል በኩል በበጎ አይታይም።
ይህ የሚሆንበት ዋናው ምክንያት ግልጽ ይመስለኛል። ሰማያዊ ፈረስን የሚያክል ፊልም ለመስራት የሚጠይቀው መስተዋጽኦ ቀላል አይደለም። የፊልም ጥባብን የሚያራምድ መሬት ባልተደላደለበት ወቅትና ቦታ ከስክሪፕት እስክ ስክሪን ያለውን እልህ አስጨራሽ ጉዞ በሚገባ አጠናቆ ፊልምን ለህዝብ ማቅረብ ጊዜ፣ ጉልበትና በጭካኔ የተጠራቀመችውን ወይም በስንት ደጅ ጥናት የተገኘችን የብድር ገነዘብ የሚያሙዋጥጥ በጣም ከባድ ስራ ነው። ይህን በመገንዘብ ገምገሚዎችና ሀያሲዋች ከነቀፋና አሉታዊ ትችት ከመሰንዘር ይታቀባሉ። የፊልሙ አቅራቢዎች ያወጡት ወጭ፣ የተበደሩት ገንዝብ፣ የፊልም ሰራተኞችና ተዋንያን ድካም፣ የልዩ ልዩ እቃና ቦታ ኪራይ ሳይከፈል ፊልሙን ከገበያ ውጭ ሊያደርግ የሚችል ማንኛውም ነገር በጥንቃቄ መሆን አለበት። ይህን ከባድ ጉዞ ጨርሰው እንደገና ሌላ ፊልም ለመስራት በቂ ቀሪ ሃሞት የሚኖራችው እንደነ ሰራዊት ፍቅሬና የቀዝቃዛ ወላፈን ደራሲና አዘጋጅ፣ ቴዎድሮስ ተሾመ ዓይነቶች ብርቱ ሰዎች ብዙ አይመስሉኝም። ስለሆነም የሚገባቸው የሞራልና የፈይናንስ ድጋፍ ሊጉዋደል አይገባም። ይህን የምናደርገው በሁለት ቀላል መንገዶች ነው።
፩ኛ ፊልማቸውን በመግዛትና በማየት
፪ኛ ፊልማቸው ኮፒ ሆነ ሲሽጥ፣ ሻጩን ለህግ በማጋለጥ።
በተረፈ ሰማያዊ ፈረስ አሁን ለህዝብ በነጻ የተለቀቀ ስለመሰለኝ፣ ፊልሙን ከተለያይ መአዘን በመመልከት ግምገማዬን አቀርባለሁ። ግምገማው ከእንግዲህ በፊልሙ ገበያ ላይ የሚኖረው ጫና ሚዛን የሚደፋ አይሆንም። ከደፋም ገበያውን እንደገና የሚቀሰቅስ ነው የሚሆነው, ብዬ አምናለሁ ።
ግምገማን ከሂስ ጋር የሚያምሳስሉ አሉ። በኔ እምነት ግን ሁለቱ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። ሂስ የግል አስተያይት ሲሆን ግምገማ በተወስነ መስፈርት፣ አሰራርና ልምድ ላይ ተመስርቶ፣ የማሻሻ አማራጭ እያሳየ የሚቀርብ ትንተና ነው። ከዚህ በታች የማቀርበው አስተያየት የግምገማ ስልት የተከተለ ይሆናል። አላማዬ በአገራችን የሚሰሩ ፊልሞች ጥራት እንዲጠበቅ የበኩሌን ለማለት ያህል እንጂ የአንድን ፊልም ስራ ለማወደስ ወይም ለማጣጣል አይደለም። ሰማያዊ ፈረስን የመረጥኩት ለህዝብ በነጻ ስለተለቀቀ ብቻ ነው። ሌላ የተለ ምክንያት የለኝም።
ግምገማው በሚከተሉት ርእስ ነገሮች ላይ ይሆናል።
1. ታሪክ Film Story
2. ገጸባህሪያት፣ Character and characterazation
እድገት፣ Character development
አላማ Character's goal
ተነሳሽነት Mativation
3. ጭውውት Dialog
4. ግጭት Conflict
5. ልብ ሰቀላ Suspense
6. ትልም Plot
ግምገማው የፊልም ስራን ቴክኒካዊ ክፍልን አያካትትም።
ይቀጥላል።