ፊልሞች በፓስወርድ መነጥር ስር/

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ፊልሞች በፓስወርድ መነጥር ስር/

Postby password » Fri May 23, 2008 8:37 pm

ሰማያዊ ፈረስ
አዘጋጅና አቅራቢ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ደራሲ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ኮከብ ተዋኒ/ ሰራዊት ፍቅሬ

ገምጋሚ /ፓስወርድ

መግቢያ

ስለ ሰማያዊ ፈረስ አስተያየት ከሰጡ ተዋኒያን መሀል አንዱ 'ሰራዊት ፍቅሬ በፊልሙ አባይን ማነጋገር ችሎአል ' በማለት አድንቆታል። የካስትሮ ምስክር ቸጉቬሮ ካልሆነ .

ከተመልካችም እንዲሁ በጎና ቀና አስተያይት የሰጡትን ያህል የነቀፉም አይጠፉም። የፊልም አስራር ጥበብን መሰረት ባደረገ መልኩ ፊልሙን የገመገመ ጽሁፍ ግን እስካሁን አላነበብኩም።

ግምገማ በተለይም የፊልሙን ድክመት አጉልቶ የሚያሳይ ከሆን በፊልም ሰሪዉ አካል በኩል በበጎ አይታይም።
ይህ የሚሆንበት ዋናው ምክንያት ግልጽ ይመስለኛል። ሰማያዊ ፈረስን የሚያክል ፊልም ለመስራት የሚጠይቀው መስተዋጽኦ ቀላል አይደለም። የፊልም ጥባብን የሚያራምድ መሬት ባልተደላደለበት ወቅትና ቦታ ከስክሪፕት እስክ ስክሪን ያለውን እልህ አስጨራሽ ጉዞ በሚገባ አጠናቆ ፊልምን ለህዝብ ማቅረብ ጊዜ፣ ጉልበትና በጭካኔ የተጠራቀመችውን ወይም በስንት ደጅ ጥናት የተገኘችን የብድር ገነዘብ የሚያሙዋጥጥ በጣም ከባድ ስራ ነው። ይህን በመገንዘብ ገምገሚዎችና ሀያሲዋች ከነቀፋና አሉታዊ ትችት ከመሰንዘር ይታቀባሉ። የፊልሙ አቅራቢዎች ያወጡት ወጭ፣ የተበደሩት ገንዝብ፣ የፊልም ሰራተኞችና ተዋንያን ድካም፣ የልዩ ልዩ እቃና ቦታ ኪራይ ሳይከፈል ፊልሙን ከገበያ ውጭ ሊያደርግ የሚችል ማንኛውም ነገር በጥንቃቄ መሆን አለበት። ይህን ከባድ ጉዞ ጨርሰው እንደገና ሌላ ፊልም ለመስራት በቂ ቀሪ ሃሞት የሚኖራችው እንደነ ሰራዊት ፍቅሬና የቀዝቃዛ ወላፈን ደራሲና አዘጋጅ፣ ቴዎድሮስ ተሾመ ዓይነቶች ብርቱ ሰዎች ብዙ አይመስሉኝም። ስለሆነም የሚገባቸው የሞራልና የፈይናንስ ድጋፍ ሊጉዋደል አይገባም። ይህን የምናደርገው በሁለት ቀላል መንገዶች ነው።

፩ኛ ፊልማቸውን በመግዛትና በማየት
፪ኛ ፊልማቸው ኮፒ ሆነ ሲሽጥ፣ ሻጩን ለህግ በማጋለጥ።

በተረፈ ሰማያዊ ፈረስ አሁን ለህዝብ በነጻ የተለቀቀ ስለመሰለኝ፣ ፊልሙን ከተለያይ መአዘን በመመልከት ግምገማዬን አቀርባለሁ። ግምገማው ከእንግዲህ በፊልሙ ገበያ ላይ የሚኖረው ጫና ሚዛን የሚደፋ አይሆንም። ከደፋም ገበያውን እንደገና የሚቀሰቅስ ነው የሚሆነው, ብዬ አምናለሁ ።

ግምገማን ከሂስ ጋር የሚያምሳስሉ አሉ። በኔ እምነት ግን ሁለቱ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። ሂስ የግል አስተያይት ሲሆን ግምገማ በተወስነ መስፈርት፣ አሰራርና ልምድ ላይ ተመስርቶ፣ የማሻሻ አማራጭ እያሳየ የሚቀርብ ትንተና ነው። ከዚህ በታች የማቀርበው አስተያየት የግምገማ ስልት የተከተለ ይሆናል። አላማዬ በአገራችን የሚሰሩ ፊልሞች ጥራት እንዲጠበቅ የበኩሌን ለማለት ያህል እንጂ የአንድን ፊልም ስራ ለማወደስ ወይም ለማጣጣል አይደለም። ሰማያዊ ፈረስን የመረጥኩት ለህዝብ በነጻ ስለተለቀቀ ብቻ ነው። ሌላ የተለ ምክንያት የለኝም።

ግምገማው በሚከተሉት ርእስ ነገሮች ላይ ይሆናል።

1. ታሪክ Film Story
2. ገጸባህሪያት፣ Character and characterazation
እድገት፣ Character development
አላማ Character's goal
ተነሳሽነት Mativation
3. ጭውውት Dialog
4. ግጭት Conflict
5. ልብ ሰቀላ Suspense
6. ትልም Plotግምገማው የፊልም ስራን ቴክኒካዊ ክፍልን አያካትትም።

ይቀጥላል።
Last edited by password on Fri Oct 15, 2010 12:20 pm, edited 14 times in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Fri May 23, 2008 9:11 pm

ሰማያዊ ፈረስ
አዘጋጅና አቅራቢ ሰራዊት ፍቅሬ
ደራሲ ሰራዊት ፍቅሬ
መሪ ተዋኒ ሰራዊት ፍቅሬ

ገምጋሚ / ፓስወርድ

ክፍል 1.

1. የፊልሙ ታሪክ ። ሰማያዊ ፈረስ ስለ ምንድን ነው?

ሰማያዊ ፈረስ ደራሲው አባይን ያናገረበት ወይም ያዳመጠበት ፊልም መሆኑን የሚያመለክት አባይ ነክ ታሪክ አላየሁበትም። ሰማያዊ ፈረስ የተባለው አባይ ወንዝ ከሆነ ርእሱ ከታሪኩ ጋር ግንኙነት የለውም ማለት እደፍራለሁ። ከታሪኩ ጋር የሚስማማ ርእስ ምረጥ ብባል ከዚሁ ፊልም ሳልወጣ ፍሬ ስላም ለድርሰትዋ የመረጠችውን፣ የናት ጡት ነካሽ፣ የሚለውን አወጣለት ነበር። ምናልባትም የፊልሙ የመጀመሪየ ረእስ ያ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አለኝ, የታሪኩ ዋና መስመር የሀገርንና የህዝብን ጥቅም በእፍቅሮተ ነዋይ በመለወጥ ወንጀል ፈጽመው ስልሚያዙ ሰዎች ስለሆነ።

ፊልሙ ሲጀምር በተሾመ የሚመራ አምስት ስዎች የያዘ አንድ ማፊያ መሰል ቡድን፣ ለውጭ ሰዎች ተቀጥሮ የእቶ እስክንድር አባተን ሳይንሳዊ ጥናት ለመስለብ ሲመካክርና እቅድ ሲያወጣ እናያለን። የሚያልቀው ይሄው ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ሲውል እንጂ የእስክንድር ጥናት ተሰፋ እንደሰጠን አባይ ወንዝን አትንኖ ዝናብ ሲያዘንብ አይደለም።

በእርግጥ ደራሲው የነካካው የኣባይ ጉዳይ በቀላሉ የሚታይ ነገር አይደለም። ከስክሪኑ በስተጀርባ አንድ ትልቅ አሳሳቢና ቁጭት ቀስቃሽ ጥያቄ መለጠፉን ማንም አይስትም። አባይን የሚየክል ስንቱን አብልቶና አተጥቶ ተርፎ ባህር የሚገባ ወንዝ እያለን እንዴት በረሀብ የታወቅን ተመጽዋቾች እንሆናለን የሚለው፣ እስካሁን ምላሽ ያላገኘው፣ የብዙሀን ጥያቄ አለ። ደረሲው ጥያቄውን በተለያየ ምስል አንስቶ አሳይቶናል። መላኩ በቲቪ ስለ አባይ የሚያየው፣ ጴጥሮስም እቤቱ የሰቀለው የፉዋፉዋቴው ስእል፣ በመጨረሻ እስክንድር ራሱ በአካል ሄዶ ጢስ ኣባይን ሲጎበኝ የምናየው እንደ ሰጋር ፈረስ እየተቅበጠበጠ የሚወርደው የውሀ ፉዋፉዋቴ አንዳች የቁጭት ስሜት ይቀሰቅሳል። ፊልሙ በአሁኑ ሰዓት በነጻ ለህዝብ መለቀቁ ምናልባት አሁን ከተከሰተው የረህብ ችግር ጋር አዛምደን እንድናይ ሊሆን ይችላል።

ሰማያዊ ፈረስ የምርምር ፊልም አይደለም። ስለ ስክንድር ሳይንሰዊው ጥናት ብዙ የሚናገረው ነገር የለም። በኔ እምነት ሰማያዊ ፈረስ የወንጀል ፊልሞች ውስጥ የሚመደብ ፊልም ነው። የስክንድርን አላማ ከግብ ለማድረስ ከሚያሳየው ትይንት ይበልጥ የተወሰኑ ሆዳሞች ራሳቸውን ከሀገር አስቀድመው ለግል ጥቅም ሲሩዋሩዋጡና በመጨረሻም ዘብጢያ ሲወርዱ ነው የሚየሳየው።

ዋናው ገጸ ባህሪ እስክንድር እንድመሆኑ መጠን፣ የታሪኩ ዋና መስመር የሱን አላማ ከግብ ማድረስ ሆኖ በሂደት እነተሾመ እንቅፋት ሲሆኑበት ማሰየት ነበረበት። እንደዚያ ከሆነ ፊልሙ መከተል የነበረበት ሻል ያለ መንገድ አለ። ይኸውም ፊልሙ በሀገራችን በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ችግርና በመካያው የሚጠፋውን የኢትዮጵያዊያን ህይወት ከዶክመንታሪ ፊልሞች ቀንጭቦ በማሳይት ቢጅምር፣ በጣም ሀይለኛ የሆን የተመልካች ስሜት መቀስቀስ በቻለ ነበር። ወዲያው ስክንድር ''ከእንግዲህ አንድ ኢትዮጵያዊ በረሀብ አይሞትም'' በማለት ወስኖ ሲነሳ ቢታይ ተመልከች ሁላ በተሰፋና በጉግት እሱን መጥቀበቅ ይጀምር ነበር። ስክንድር አውሮፓን ጥሎ ሀገሩን ከድርቅ ችግር ሊታደጋት ሲመጣ ቦሌ አ ማ ድረስ መጥቶ የተቀበለው ሰው ባይኖርም፣ ፊልም ተመልካቹ ከአይሮፕላን ማረፊያ ሲወጣ በጭብጨባ ይቀበለው ነበር። ከዚያ በሁዋላ ፊልሙ እስክንድርን በዋናነት እያሳየ እስከ አላማው መሳከት ወይም አለመሳካት ድረስ መዝለቅ ነበረበት፣ እንጂ እነ ተሾመ ሲያዙ ማብቃት አልነበረበትም። ፊልሙ ስለ ወንጀል፣ አላማው ወንጀለኞቹን ማስያዝ ከሆነ ግን ርእሱ የናት ጡት ነካሽ ተብሎ ባለው መልክ መቅረቡን መቀበል ይቻላል።

በስክንድር መሪ ተዋኒነት መታየት ስለነበረባቸው ትእይንቶች ወደፊት በትልም፣ በግጭትና በልብ ሰቀላ ርእሶች ስር እጠቃቅሳለሁ።
Last edited by password on Sun May 25, 2008 2:17 am, edited 2 times in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ብራንጎናትርን » Fri May 23, 2008 10:55 pm

በጣም ደስ የሚል ሂስ ነው! ይቀጥል:: 8) ፊልም ዋርካ ላይ ሲተች ብዙም አላየሁም::

አድናቂህ

ብራንጎ
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
ብራንጎናትርን
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 736
Joined: Fri Dec 29, 2006 6:31 pm

Postby ሲታ!!! » Sat May 24, 2008 5:21 am

Password በጣም ሀሪፍ ግምገማ ነው:: ባነሳሀቸው ነገሮች እስማማለሁ::

ደራሲው ውሀውንአትኖ ዝናቡን በማዝነብ እና ከሱጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትቶ ወደወንጀሉ ባብዛኛው ያተኮረው : ያኛው ብዙ ስራ : ብዙ ማሰብ እንዲሁም more creative መሆንን ስለሚጠይቅ ይመስለኛል :: እናም በቀላሉ ሊወጣው የሚችለውን መረጠ : የፊልሙን ታሪክ አበላሸው::

እስኪ በነካ እጅህ ሰለዚሁ ፊልም ስለሲኒማ ጥበቡ ( cinimathograpy) የሚሰማህን ጨምረህ አጫውተን:: እንደሚታወቀው ጽሁፎ (script) እና ሲኒማ ጥበብ ይለያያሉ:: በ oscar እና በመሳሰሉት እንደምናውቀው የፊልሙ ዳይሪክተር በ ሲኒማ ጥበቡ ሲደነቅ script writer ደግሞ በሌላ catagory ነው የሚታየው:: በሲኒማ ጥበቡ የተደነቀ እና የተሸለመ ፊልም በ script እዚህ ግባ የማይባል ሊሆን ይችላል::

ሲታ
ሲታ!!!
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Sat Dec 29, 2007 7:32 am

Postby password » Mon May 26, 2008 2:39 am

ፊልም / ሰማያዊ ፈረስ
አቅረቢ/ ሰረዊት ማልቲሚዲያ ፕሮደክሽን
አዘገጅ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ደረሲ/ ሰራዊት ፍቅሬ

ገምጋሚ / ፓስወርድ

ክፍል ሁለት።

ገጸ ባህሪያትና እድገታቸው

አንድ የፊልም ታሪክ ሃሳብ ከተወጠነ በሁዋላ ቀጣዩ ስራ ያን ታሪክ ሊሰሩ የሚችሉ ገጸ ባህሪያት መፍጠርና መሳል ነው። ፊልም፣ ተመልካችን በስሜት ወጥሮ እንዲይዝ ታቅዶ የሚስራ ስለሆነ፣ ስሜት እንዲቀስቀስ፣ እንዲወጠርና እንዲዘና የሚያደርጉ ተሪኩን የሚሰሩ ገጸ በህሪያትን በሚገባ መሳል ያስፈልጋል። የምንደሰተውም ሆነ የምናዝነው፣ የምንተክዘውም ሆነ የምንስቀው በገጸ ባህሪያቱ በኩል ስለሆነ በተወሰነ ደረጃ ልናውቃቸውም ይገባል።

የምንወዳቸው ገጸባህሪያት አላማ ሲሳካ ደስ ይለናል። ሲከሽፍባቸው ይከፋናል። አደጋ ሲያንዣብብባቸው ስጋት ያድርብናል። ተመልካች እንዲህ የሚሰማው ፊልሙ እውነት ሲመስለው ብቻ ነው። ፈጠራ መሆኑን ቢያውቅም ፊልሙን በሚየይበት ቅጽበት እውነተኛ መስሎ እንዲታየው ከተደረገ የገጸባይሪያቱ ስሜት እየተሰማው ይቆያል። አንድ ፊልም ያን ማድረግ ከቻለ ተዋጥቶለታል ማለት ይቻላል። የተመለካች ስሜት መሳብ ካልቻለ ግን ችግር አለበት ማለት ነው። ከችግሩ አንዱ የገጸባህሪያት አሳሳልና አበለጻጽግ ወይም እድገት በቂ ሳይሆን ሲቀር ነው።

ለገጸ ባህሪያት እድገት ዋናው መሰረት ኮከብ ገጸባህሪው ተጨባጩ አላማው ላይ ለመድረስ ያለው ተነሳሽነት ነው። ኮክብ ገጸባህሪው ወደ ተጨባጭ አላማው በሚያደርገው ጉዞ የሚገጥመው ውጣ ውረድ ነው የሱንና የሌሎቹ ውላዊ ባህሪ እየተገለጠልን የሚመጣው።
ተጨባጩ አላማ ያልኩት ያለምክንየት አይደለም። ሁሌም ውስጣዊ የሆነ ሌላ ስውር ኣላማ ወይም ፍላጎት ስለሚኖር ነው። ያ በገጸ ባህሪው ውስጥ ያለ፣ ለተመልካች የማይታይ፣ ስነልቦናዊ ረሀብን የማስታገስ ፍላጎት ነው።

ለምሳሌ የስክንድር ተጨባጭ ኣላማ ወንዝ አትንኖ ዝናብ ማዝነብ ነው። ስውር ኣላማው ግን ለአስራ አራት ዓመታት ያለመውንና የደከመበትን ጥናት ውጤት በተግባር ሲተረጎም በማየት የሚያገኘው የመንፈስ እረፍትና እርካታ፣ የሳቁበትንና የተሳለቁበትን በማሳየት እልህን መወጣት፣ ከዚያም ከህዝብ ክብርና ሞግስ ማግኘት ነው። ሰው አንድ በጎ ስራ ሲስራ ከንጹህ ሰብዓዊና ወገናዊ ስሜት በመነሳት ያደረገው እንደሆነ እንጂ የራሱን ግለዊ ስሜት ለማርካትም እንዳደረገው አያምን ይሆናል። ግን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ በግልጽም ሆነ በህቡዕ የግል ጥቅም ጨርሶ የሌለበት በጎ ስራ አለ ማለት የስቸግራል። በመሰረቱ ያ ስውር አላማ ወይም ውስጣዊ ፍላጎት ነው ገጸባህሪውን እረፍት ነስቶ ለተገባርና ለውጤት የሚገፋፋው። ፊልም ከተጨባጩ ኣላማ አልፎ የስውር ፍላጎትን መሳካትና የውስጣዊ ጥማት መርከትን ሲየሳይ ደረጃው ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ይሆናል።

የገጸባህሪውን ስውር ፍላጎት መሳካት መዳሰስ የሚችል ፊልም ለመስራት ገጸባህሪያት፣ በተለይም ዋና ዋናዎቹ በደንብ መሳል አለባቸው። ተሳለ, ማለት በፊልም ቁዋንቁዋ ተመልካቹ የገጸባህሪውን ጸባይ፣ ዐመል፣ ፍላጎት፣ እንዲሁም ከታሪኩ በፊት ያሳለፈውን ህይወት ከሞላ ጎደል ሲያውቅ፣ ፍርሀቱን ጭንቀቱን፣ እልሁን፣ ፍቅርና ጥላቻውን ሲረዳ፣ ጠንካራና ደካማ ጎኑን ሲገነዘብ ነው።

ገጸባህሪው ከተሳለ በሁዋላ እንድንወደው ወይም እንድንጠላው፣ እንድንጨክንበት ወይም እንድናዝንለት እንዲሁም ውስጠ ምስጢሩን እንድናውቅ ሊያደርጉን የሚችሉት ከእፉ የሚወጡት ቃላትና ሲስራቸው የምናየው ተግባራት ስለሆኑ የሚናገሩትንና የሚያደርጉት ታሪኩ ሊያስተላልፍ በምንፈልገው ስሜት መሰረት መሆን አለበት። በሰማየዊ ፈረስ ታሪክ ዋናው ገጸባህሪ እስክንድር እባተ ነው። ተመልካቹ የሱ ዓላማ ግቡን ሲመታ ማየት ይፍልጋል። ስለዚህ ተመልካቹ ስክንድርን እንዲወደው፣ ለስክንድር እንዲቆርቆር፣ እንዲጨነቅና እንዲያዝን ማድረግ ያስፈልጋል። ያን ስሜት ከመጀመሪያው መቀስቀስ ይቻልበት የነበረበት ትይንት የቦሌ አ ማ ትይንት ነው።

እስክንድር ከ14 አመታት በሁዋላ አገሩ ሲገባ የተቀበለው ወዳጅ ዘመድ አልነበረም። እዚህ ላይ ደረሲው አዘኔታ ለመቀስቀስ ጥሩ ምክንያት ተጠቅሞአል። በፊልም ስራ፣ አንድ የሚታዘንለት መሪ ገጸባህሪ መፍጠር ትልቅ ጥበብ ነው። በዘዴ ከተስራበት ተመልከችን በስሜት መያዝ ያስችላል። ስክንድርን የሚቀበለው ሰው አለመኖሩ ብዙ መግለጽ የሚችል ትይንት ነው። አገሪቱ ባሳለፈችውን መራር የጦርነት፣ የአብዮትና የረሀብ ዘመናት ወዳጅ ዘመዶቹ በሞት ማለቃቸውንና በስደት መጥፋታቸውን ሊጠቁም የሚችል ነበር። ያ መገለጥ የሚችለው በስክንድር ስሜትና ቦሌ አ መ መውጫ ላይ በነበረው ህዝብ ንጽጽር ነበር።

አስረጅ።
ከውጭ የሚመጡት ኢትዮጵያዊያንን ዘመድ ወዳጅ እየተቀበል አቅፎ ሲስማቸው ቢታይ (ትይንቱ ከእስክንድር ግንባር አንጻር ቢታይ) እና እሱ የሚሳሳምና የሚተቃቀፈውን ህዝብ እታዘበ በትዝታ እንደሄደ፣ አፉ ትንሽ ተከፍቶ፣ አይኑ እንባ ሲያቀር ቢታይ፣ ከዚያም እንባውን እየታገለ፣ ከሻንጣ ተሽካሚዎችና ታክሲ ነጂዎች ጋር መነጋገር እቅቶት ቢታይ የተመልካቹን ልብ ይነካ ነበር ብዬ አምናለሁ።

ያ ስንት መናገር የሚችል አይን እንደ ፓይለት በጥቁር መነጽር ተሸፍኖ፣ እስክንድርም የ14 ዐመት ናፍቆት እንዳለበት እንግዳ ሳይሆን እንደ ዱባይ ተመላላሽ ምንም ሰይደናበርና ግርምታ ሳይታይበት ወጣ። የቦሌው ትይንት ላይ ተመልካቹ ለስክንድር ማድረግ የሚችለው ልዩ ስሜታዊ አቀባበል እምልጦአል።

እንደ ሰማያዊ ፈረስ አይነት ፊልም ላይ ዋናውን ገጸባህሪ ተወዳጅ ማድረግ የግድ ይላል። አልያ ፊልሙ አይሰራም። በገሀዱ አለም ለምንወዳቸው እንደምናስብና እንደምንቆረቆር በፊልምም ገጸባህሪውን ከወደድነው እናስብለታለን፣ እንጨነቅለታለን።

አንድን ገጸ ባህሪ ተመልካች እንዲወደው፣ ደራሲው ምን ማድርግ አለበት? መልሱ ቀላል ነው። ገጸባህሪው በጎ ስራ ሲስራ ማሰይት፣ ለተበደለ ሲቆረቆር፣ ለተገፋ ሲያዝን፣ ለሀቅ ሲዋደቅ። በቃ። እንዲህ አይነት ሰው ተወዳጅ ነው። ቀልደኛና ተጫዋች፣ ደፋርና ብልህ ገጸባህሪም ይወደዳል።

ተመልካች የሰማያዊ ፈረስን መሪ ገጸባህሪ፣ እስክንድር አባተን እንዴት ያየዋል? ምን ያህል ይወደዋል? እስክንድር እሚወደድ ሰው ነው? ምን ያህሉ ተመልካች ነው የሱን አይነት ህይወት፣ ምኞትና አላማ ያለው? ተመልካች ከራሱ ህይወት ጋር የሚመሳስል ነገር ማየት ይወዳል። ሰማያዊ ፈረስ ውስጥ ከብዙሀኑ ተመለከች ህይወት ጋር የሚመሳስል ኑሮ ያለው ገጸባህሪ አለን?

ሰማያዊ ፈረስ ላይ ''እስክንድር ከለማኙ ጋር ትይንት'' እስክንድርን ተወዳጅ ለማድረግ የተሞከረበት ትይንት ይመስለኛል፣ እስክንድር መመጽወቱና ከለማኙ ጋር መወያየቱ፣ መቃለዱ። ቀልደኛ ሰው ይወደዳልና። ግን ትይንቱ የተፈለገውን ስሜት ሳይሆን ተቃራኒውን ሳይጭር አልቀረም። ስክንድር የያዘውን አይነት መኪና የሚይዙ ግለ ሰቦች በሰፊው ተመልካች ዘንድ ተወዳጅነታቸው ምን ያህል ነው? ፓጃሮ፣ ፎርዊል መኪና ወዘተ ከሙስናና ከዘረፋ ጋር የሚዛመድ ምስልን ነው የሚሰጠው። መኪናውን ከደሀው ወጣት ጋር ማየትና ማስተየይት፣
የእስክንድር ንግግር / ''እንዴት ነው ጤነኛ እጅና እግር እያለህ ልመና'' ብሎ ማለቱ፣
''ዝናብ ጠፋ ተሰደድን፣ ማዘርና ብራዘር እኛው፣'' ሲለው ብር ብቻ ሰጥቶት መሄዱ ተወዳጅነት የሚፈጥር ድርጊያ አይደለም።

በዚህ አጋጣሚ ፊልሙ ማሳየት የነበረበት ለእስክንድር ተነሳሽነት መሰርት የሚሆን ትይንት ነበር። እስክንድር ድሀውን ወጣት
/ ''ና 'ሲኪ ና እጫውተኝ''/ ብሎ ወጣቱን መኪና ውስጥ አስግብቶ የድርቅንና የረሀብን ችግር ከቀመስው ወጣት አፍ መስማት ነበረበት። ወጣቱ ታሪኩን ሲያወራ ፊልሙ ቃሉን ተከትሎ የረሀብን መቅስፍት የሚያሳይ ከዶክሜንታሪ የተቀነጨበ ትይንት ለተወስን ደቂቃ ቢያሳየን፣ ቀጥሎ የስክንድር አይን በርበሬ መስሎ እንባ ሲያቀር ቢታይ፣ ተቆርቁዋሪነቱና ወገን ወዳድነቱ ብቻ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተርፍለት ነበር።
እስክንድር ሊታደጋቸው የመጣላቸውን ሰዎች፣ የወጣቱ እናትና ወንድምን፣ ፊልሙም አለሳየን፣ ዋና ገጸባህሪም ሊያየቸው አልተጨነቀም። ስለዚህ ተመልከቹ እስክንድርን መኪና ቢገጨው ባይገጨው፣ ተሾመ ቢገድለው ባይገድለው ስሜት አይሰጠውም። አይወደውማ። ስክንድር ያለው ተወዳጅነት ካለ ከወካዩ ተዋኒ ከሰረዊት ፍቅሬ ቁመናና መልከቀናንት፣ ፈገግታና አነጋገር ያገኘው ነው።

ይቀጥላል።

ፓስወርድ.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Tue May 27, 2008 5:53 pm

ሲታ!!! wrote:Password በጣም ሀሪፍ ግምገማ ነው:: ባነሳሀቸው ነገሮች እስማማለሁ::

ደራሲው ውሀውንአትኖ ዝናቡን በማዝነብ እና ከሱጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትቶ ወደወንጀሉ ባብዛኛው ያተኮረው : ያኛው ብዙ ስራ : ብዙ ማሰብ እንዲሁም more creative መሆንን ስለሚጠይቅ ይመስለኛል :: እናም በቀላሉ ሊወጣው የሚችለውን መረጠ : የፊልሙን ታሪክ አበላሸው::

እስኪ በነካ እጅህ ሰለዚሁ ፊልም ስለሲኒማ ጥበቡ ( cinimathograpy) የሚሰማህን ጨምረህ አጫውተን:: እንደሚታወቀው ጽሁፎ (script) እና ሲኒማ ጥበብ ይለያያሉ:: በ oscar እና በመሳሰሉት እንደምናውቀው የፊልሙ ዳይሪክተር በ ሲኒማ ጥበቡ ሲደነቅ script writer ደግሞ በሌላ catagory ነው የሚታየው:: በሲኒማ ጥበቡ የተደነቀ እና የተሸለመ ፊልም በ script እዚህ ግባ የማይባል ሊሆን ይችላል::

ሲታ

ሲታ

ከመግቢያው ላይ እንደገለጽኩት ግምገማው ቴክኒካል ክፍሉን አይዳስስም ብዬ ነበር። የምገመግመው ከተውኔቱ ጽሁፍ ጋር ቀጥተኛ ግንኝነት ያላቸውን ርእሰነገሮች እንጂ cinematographyን በተመለከተ ጠለቅ ያል እውቀት ስለሌለኝ ብዙ ማለት ያስቸግረኛል። የፊልም ስራ ባለብዙ ዘርፍ ጥበብ ስለሆነ ለየዘርፉ ባለሙያው ሲተችበት ይሻላል። አልያ መቀባጠር ነው የሚሆነው።

ደራሲው ወደ ወንጀሉ ያተኮረው፣ ያኛው ብዙ ማሰብ ስልሚጠይቅ ይሆናል ስላልከው ጉዳይ፣

ችግሩ ያ አይመስለኝም። ውሀ አንደተነነ ማስመስልና ዝናብ ማስዘነብ ማሳየት የሮኬት ሳይቲስት መሆን አይጠይቅም። ያን በፊልም ማሳየት ካልቻልክ ጭራሹን ፊልም የሚባል ነገር መሞከር አልነበረብህም። ሳይንሱ፣ ማለትም የሶላር ኢነርጂን በመጠቀም ውሀ መንፍላትና ያን እንፋሎት ከተወሰነ ቦታ ሄዶ እንዲዝንብ ማድረግ መቻሉን ተመልካቹ እንዲያምን ስራዊት የተጠቅመው ጥሩ ዘዴ አለ። ፊልሙ ሲጀምር፣ የወንጀለኞቹ መሪ, ተሾመ, በእኒመሺን ፊልም እየታገዘ ለቡድኑ ያብራራውን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ያ foreshadowing ማለትም ቅድመ ጥቆማ መሆኑ ነው። ግን በቂ አልነበረም። በተጨማሪም እነ ተሾመ ከዶለሩ እንጂ ከዝናቡ ጉዳይ ስሌለላቸው ሳይንሱን የማብራራቱ ነገር በነሱ አያምርም። ያን ማብራራት የነበረበት ስክንድር ራሱ ነው። በእኒመሺን ፊልም ከማስርዳት፣ ተኣመኒነት ለማጠንከር በላቦራቶር ወስጥ ቁንጽል ሚኒ ኤክስፔርመንት ማሳየት ይመርጡዋል።

ለምሳሌ ያህል 'BACK TO THE FUTURE. የተሰኘውን ግሩም ፊልም እንውሰድ። ያን crazy scientist ታስተውሳልህ። Martyን ከ1935 back to the future፣ ወደ 1985 ለመላክ የሚያስችለውን ቴክኒክ ላብ ውስጥ በመጫወቻ እቃዎች ነው የሚያሳየን። ያ experiment ሁለት አላማ አለው። እንዱ ከዚያ ቴክኖሎጂ ካልዳበረበት ዘመን በጊዜ ጉዙ ማድረግ የመቻሉ ነገር አጠራጣሪ ስለሆነ ማስተማመኛ እንዲሆን ቅድመ ጥቆማ foreshadowing, ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ያን የተራቀቀ ውስብስብ ሳይንስ አንድ ተመልካች ሊረዳው በሚችል መጠን ቁመቱን፣ ክብደቱን፣ ፍጥነቱንና ውስጠ ፍጥረቱን ማሳነስ ነው። በትንሹ ሲሆን ሲለሚገባን።

ደረሲ ሰራዊት ፍቅሬ ወደ ወንጀሉ ያመዘነበት እንዱ ምክንያት በመጀመሪያ ታሪኩ ስለምን እንደሆነ ለይቶ ያወጣው የታሪክ መስመር ካለመኖሩ ይመስለኛል። ሰማየዊ ፈረስ፣ የአባይን ወንዝ በማትነን አገሩን ለማልማት ስለሚፍልግ ምሁር ነው የሚል የነጠረ መስመር አልያዘም። መስመር ስለልያዝ ታሪኩ ወደ ወንጀሉ ተንጋደደበት ነው የምለው።

ሁለተኛው ምክንያት ከዋናው ገጸባህሪ ግብ ጋር የተያየዘ ነው? የአንድ ገጸ ባህሪ ግብ ግልጽ ካልሆነ ታሪኩ እንደ አባይ ወንዝ ራሱ በቀደደው ቦይ ነው የሚፈሰው። ከእንዲህ ኣይነት አቅጣጫ-አሳች ችግር ራስን ለመጠበቅ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ጥሩ መልስ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።

፩ የዋናው ገጸ በህሪ ዋና ግብ ምንድን ነው?
መልሱ የወንዝ ውሀ እትንኖ ዝናብ ማዝነብ።

፪ ለምን ዝናብ ማዝነብ አስፈለገው?
መልሱ በድርቅ ምክንያት የሚጎዳውን ህዝብ ለመታደግ

፫ ገጻባህሪው ባይሳካለት ምን ይፈጠራል? ማን ይጎዳል? ማን ይሞታል? ይህ ነው ዋናው ጥያቄ what is at stake? if there is nothing at stake , no body cares about the project or the character.

ሰማያዊ ፈረስ እነዚህን ጥየቄዎች ለመመለስ ካለመሞከሩ ላይ ይመስለኛል፣ ችግሩ። ገጸባህሪውን የሚያንሳሳው motivation ጉዳይ አለመዳበሩ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Tue May 27, 2008 5:54 pm

ሲታ!!! wrote:Password በጣም ሀሪፍ ግምገማ ነው:: ባነሳሀቸው ነገሮች እስማማለሁ::

ደራሲው ውሀውንአትኖ ዝናቡን በማዝነብ እና ከሱጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትቶ ወደወንጀሉ ባብዛኛው ያተኮረው : ያኛው ብዙ ስራ : ብዙ ማሰብ እንዲሁም more creative መሆንን ስለሚጠይቅ ይመስለኛል :: እናም በቀላሉ ሊወጣው የሚችለውን መረጠ : የፊልሙን ታሪክ አበላሸው::

እስኪ በነካ እጅህ ሰለዚሁ ፊልም ስለሲኒማ ጥበቡ ( cinimathograpy) የሚሰማህን ጨምረህ አጫውተን:: እንደሚታወቀው ጽሁፎ (script) እና ሲኒማ ጥበብ ይለያያሉ:: በ oscar እና በመሳሰሉት እንደምናውቀው የፊልሙ ዳይሪክተር በ ሲኒማ ጥበቡ ሲደነቅ script writer ደግሞ በሌላ catagory ነው የሚታየው:: በሲኒማ ጥበቡ የተደነቀ እና የተሸለመ ፊልም በ script እዚህ ግባ የማይባል ሊሆን ይችላል::

ሲታ

ሲታ
ለ'አስተያየትህ አመሰግናለሁ.

ከመግቢያው ላይ እንደገለጽኩት ግምገማው ቴክኒካል ክፍሉን አይዳስስም ብዬ ነበር። የምገመግመው ከተውኔቱ ጽሁፍ ጋር ቀጥተኛ ግንኝነት ያላቸውን ርእሰነገሮች እንጂ cinematographyን በተመለከተ ጠለቅ ያል እውቀት ስለሌለኝ ብዙ ማለት ያስቸግረኛል። የፊልም ስራ ባለብዙ ዘርፍ ጥበብ ስለሆነ ለየዘርፉ ባለሙያው ሲተችበት ይሻላል። አልያ መቀባጠር ነው የሚሆነው።

ደራሲው ወደ ወንጀሉ ያተኮረው፣ ያኛው ብዙ ማሰብ ስልሚጠይቅ ይሆናል ስላልከው ጉዳይ፣

ችግሩ ያ አይመስለኝም። ውሀ አንደተነነ ማስመስልና ዝናብ ማስዘነብ ማሳየት የሮኬት ሳይቲስት መሆን አይጠይቅም። ያን በፊልም ማሳየት ካልቻልክ ጭራሹን ፊልም የሚባል ነገር መሞከር አልነበረብህም። ሳይንሱ፣ ማለትም የሶላር ኢነርጂን በመጠቀም ውሀ መንፍላትና ያን እንፋሎት ከተወሰነ ቦታ ሄዶ እንዲዝንብ ማድረግ መቻሉን ተመልካቹ እንዲያምን ስራዊት የተጠቅመው ጥሩ ዘዴ አለ። ፊልሙ ሲጀምር፣ የወንጀለኞቹ መሪ, ተሾመ, በእኒመሺን ፊልም እየታገዘ ለቡድኑ ያብራራውን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። ያ foreshadowing ማለትም ቅድመ ጥቆማ መሆኑ ነው። ግን በቂ አልነበረም። በተጨማሪም እነ ተሾመ ከዶለሩ እንጂ ከዝናቡ ጉዳይ ስሌለላቸው ሳይንሱን የማብራራቱ ነገር በነሱ አያምርም። ያን ማብራራት የነበረበት ስክንድር ራሱ ነው። በእኒመሺን ፊልም ከማስርዳት፣ ተኣመኒነት ለማጠንከር በላቦራቶር ወስጥ ቁንጽል ሚኒ ኤክስፔርመንት ማሳየት ይመርጡዋል።

ለምሳሌ ያህል 'BACK TO THE FUTURE. የተሰኘውን ግሩም ፊልም እንውሰድ። ያን crazy scientist ታስተውሳልህ። Martyን ከ1935 back to the future፣ ወደ 1985 ለመላክ የሚያስችለውን ቴክኒክ ላብ ውስጥ በመጫወቻ እቃዎች ነው የሚያሳየን። ያ experiment ሁለት አላማ አለው። እንዱ ከዚያ ቴክኖሎጂ ካልዳበረበት ዘመን በጊዜ ጉዙ ማድረግ የመቻሉ ነገር አጠራጣሪ ስለሆነ ማስተማመኛ እንዲሆን ቅድመ ጥቆማ foreshadowing, ሲሆን ሁለተኛውና ዋናው ያን የተራቀቀ ውስብስብ ሳይንስ አንድ ተመልካች ሊረዳው በሚችል መጠን ቁመቱን፣ ክብደቱን፣ ፍጥነቱንና ውስጠ ፍጥረቱን ማሳነስ ነው። በትንሹ ሲሆን ሲለሚገባን።

ደራሲ ሰራዊት ፍቅሬ ወደ ወንጀሉ ያመዘነበት እንዱ ምክንያት በመጀመሪያ ታሪኩ ስለምን እንደሆነ ለይቶ ያወጣው የታሪክ መስመር ካለመኖሩ ይመስለኛል። ሰማያዊ ፈረስ፣ የአባይን ወንዝ በማትነን አገሩን ለማልማት ስለሚፍልግ ምሁር ነው የሚል የነጠረ መስመር አልያዘም። መስመር ስላልያዝ ታሪኩ ወደ ወንጀሉ ተንጋደደበት ነው የምለው።

ሁለተኛው ምክንያት ከዋናው ገጸባህሪ ግብ ጋር የተያየዘ ነው? የአንድ ገጸ ባህሪ ግብ ግልጽ ካልሆነ ታሪኩ እንደ አባይ ወንዝ ራሱ በቀደደው ቦይ ነው የሚፈሰው። ከእንዲህ ኣይነት አቅጣጫ-አሳች ችግር ራስን ለመጠበቅ ለሚከተሉት ጥያቄዎች ጥሩ መልስ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።

፩ የዋናው ገጸ በህሪ ዋና ግብ ምንድን ነው?
መልሱ የወንዝ ውሀ እትንኖ ዝናብ ማዝነብ።

፪ ለምን ዝናብ ማዝነብ አስፈለገው?
መልሱ በድርቅ ምክንያት የሚጎዳውን ህዝብ ለመታደግ

፫ ገጻባህሪው ባይሳካለት ምን ይፈጠራል? ማን ይጎዳል? ማን ይሞታል? ይህ ነው ዋናው ጥያቄ what is at stake? if there is nothing at stake , no body cares about the project or the character.

ሰማያዊ ፈረስ እነዚህን ጥየቄዎች ለመመለስ ካለመሞከሩ ላይ ይመስለኛል፣ ችግሩ። ገጸባህሪውን የሚያንሳሳው motivation ጉዳይ በደንብ አለመዳበሩ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሚላግሮ » Tue May 27, 2008 10:41 pm

ግምገማህን እየተከታተልኩት ነው ተደስቼበታለው
በርታ እኔም ብዙ ነገሮችን ለማወቅ እየረደሁኝ ነው ያሉት
እንዲህ ጊዜህን መስዋት አድርገህ ለጥበብ መጨነቅህ ለራሱ
ምን ያህል የጥበብ ሰው እንደሁንክ ያስረዳል ::
በርታ ወዳጄ ብዙ አይኖች እየጠበቁህ ነው::
ሚላግሮ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 28
Joined: Mon Feb 21, 2005 1:16 pm
Location: united states

Postby password » Fri Jun 06, 2008 1:37 am

ሚላግሮ wrote:ግምገማህን እየተከታተልኩት ነው ተደስቼበታለው
በርታ እኔም ብዙ ነገሮችን ለማወቅ እየረደሁኝ ነው ያሉት
እንዲህ ጊዜህን መስዋት አድርገህ ለጥበብ መጨነቅህ ለራሱ
ምን ያህል የጥበብ ሰው እንደሁንክ ያስረዳል ::
በርታ ወዳጄ ብዙ አይኖች እየጠበቁህ ነው::

ሚላግሮ

ለአስተያየትህ አመሰግናለሁ።

ግምገማውን በተመለከት ብዙም አስተያዬትና መልስ ስላላይሁ፣ ያንተን ሳይ ለፊልም ጥበብ ልዩ ዝንበሌ ያለህ መሰለኝ፣ ካልተሳሳሳትኩ።
እናም ካነሳነው ርእስ ሌላም ፊልምና ጥበቡን በተመለከት, (በተለይ screenplay,) ከኔ ገር ለመወያይት ወደ ሁዋላ አትበል።

ቀጠዩ ግምገማ በሚለጥቀው ገጽ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Fri Jun 06, 2008 2:13 am

ፊልም /ሰማያዊ ፌረስ
አቅረቢ/ ሰረዊት ማልቲሚዲያ ፕሮደክሽን
አዘገጅ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ደረሲ/ ሰራዊት ፍቅሬ

ገምጋሚ / ፓስወርድ

ክፍል 2
ካለፈው የቀጠለ
ገጸባህሪያትና አደረጃጀታቸው።

ስክንድር ተወዳጅ ባህሪ አይደለም ብያለሁ፣

እሱ ተወደጅ ካልሆነ ፊልሙን ተወዳጅ ማድረግ እጅግ ከባድ ነው። የሰማያዊ ፈረስ አይነት በዋናውን ገጸባህሪ ህይወት ዙሪያ የሚጠነጠን ታሪክ ገጸባህሪው በተመልካች ውስጥ የሚያሳድረው ስሜት ወሳኝ ነው። ተመልካች እሱን የሚመሰል፣ እንደሱ የሚያስብ፣ እንደሱ የሚመኝ፣ እንደሱ የሚፈራ፣ እንደሱ የሚጫወት ባጠቃላይ እንደሱ ወይም እሱ በቅርብ እንደሚያውቃቸው ሰዎች የሚኖር ሰው ጋር በቀለሉ ራሱን ያመሳስላል። ከምግብ ስጋን ከመጠጥ ሽቫስን የሚጠላ የለም, ግን ወገኑን ከረሀብ ችግር ሊታደግ የመጣ ጀግና ገና ግቡን ሳይመታ በውስኪ የሚጥለቀለቅ ከሆነ የተመልከቹን ልብ ማግኘት ቀላል ይሆንለታል ብዬ አልገምትም።

ተመልካች ለገጸበህሪው እንዲሳሳ ማድረግ በፊልም ተውኔት ውስጥ በጣም የተለመደ ዘዴ ነው። በተሳካ ሁኔታ ከተቀናበረ ተመልካችን የመያዝ ከፍተኛ ሀይል እንደ አለው ይታመንበታል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ገጸ ባህሪውን በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ ነው፣ ያለፈ ህይወቱን ወይም እሁን የሚገኝበት ሁነታ ተመልካቹን ልብ በሚነካ መልኩ በማሳየት።
ምሳሌ First Blood ላይ John Rambo የተመልካቹን ልብ ''audience sympathy'' ያገኘው በዚህ መልክ ነው። ፊልሙ የሚጀምረው እሱ ጉዋደኞውን ፍለጋ መጥቶ፣ የጉዋደኛው እናት አለም እንደ ዱሮ፣ እንደ ደጉ ዘመን እንደልሆነች፣ ጉዋደኞቹንም ሰማያዊ ጅብ እንደበላቸው ነግረውት ሲመለስ ነው። ያዝናል። ያሳዝናል።
የሀዘንና የብቸኝነት ስሜት ነው ከራምቦ እንድንወግን የሚያደርገን።

እስክንድር ከውጭ እንደመጣ እምስት ኮከብ ሆቴል ከሚገባ አደገበት ሰፈር ሄዶ፣ ያ ዱሮ ኮራ ብሎ ይታይ የነበረ ቤታቸው ሽረሪት እድርቶበት፣ ደራ ብሎ ይሞቅ የነበረ ግቢያቸው ፈርሶ፣ ሳር ቅጠሉ ያውቀው የነበረ እስክንድር አሁን አንድ የሚያውቀው ሰው ማጠቱ፣ ድሮ የሚየውቀው ሰፈር ወድሞ፣ ሰው ተራቁቶ ቢያገኝ፣ አብሮ አደጎቹን ፍልጋ ጎራ ብሎ አንዱንም ሲያጣ፣
የእናቱን፣ ጉዋደኛ እመት ጤንፍየለሽን አግኝቶ ስላሉትና ስለሌሉት ሲነግሩት፣ በመጨረሻ አዝኖ ሲመለስ ማሰየት ልዩ በጀት የሚጠይቅ አይመስለኝም። የተመልካችን ስሜት መያዝ እንደሚችል ግን አያጠራጥርም።

ሁለተኛዋ ዋና ገጸባህሪ ፍሬሰላም ነች። እስዋስ በተመልከቹ ውስጥ የምታሳድረው ስሜት ምን አይነት ነው? የምትወደድ ወይስ የምትጠላ ነች? ባህሪዋ፣ አስተዳደግዋ፣ ስራዋ፣ ቤተስቦችዋ፣ ጉዋደኞችዋ ለተመልከች የሚታወቁበት ትይንት ታይቶአል?

በኔ አመለካከት ፍሬሰላም ከሌሎቹ ገ/ ባህሪያት በተሻለ ሁኔታ ተቀርጻለች። ደራሲ ነች። በስነጽሁፍ ተመርቃለች። ቀደም ሲል በጻፈችው መጽሀፍ ምክንያት ታስራ ነበር። ከርቸሌን ታውቀዋለች፣ የምትፈራው አትመስልም። ድርሰቶቼን እንባቢ አልተረዳልኝም ብላ ትበሳጫለች። ከአንድ እህትዋ በቀር ሌላ የቅርብ ዘመድ የላትም። እህትዋ የህክምና ባለሙያ ናት። ፍሬሰላም እህትዋን ተጠግታ ነው የምትኖረው።

ፍሬሰላም እነተሾም በወጠኑት ባለቡዙው ሚሊዮን ብር ወንጀል ውስጥ እንድትሳተፍ ሊያደርጉዋት የሚችሉ ሁኔታዎች አሉ። እንዱ በደራሲነት ሙያዋ ሰርታ ራስዋን ማስተዳደር አለመቻልዋ ሊሆን ይችላል። ሌሎች ደረሲያን እንደሚያድርጉት ሌላ ስራ መስራት ያልቻለችበት ምክንየት ግልጽ ባይሆንም፣ የነተሾመ ሴራ ከተሳካ እስክ ስድስት ሚሊዮን ብር የምታገኝበትን ተልእኮ ስለሆነ ለመሳተፍ አላቅማማችም። ግን ለገንዘብ ስትንገበገብ ወይም ለሀብት ስትቁዋምጥ አለመታየትዋ ከሌሎቹ ለየት ያለች መሆንዋን ያስገነዝባል።

ከስክንድር ጋር ከተዋውቅች በሁዋላ ፍቅር እያሸነፋት ስትሄድ እናያለን። ስለ ወንዝ ማትነንና ዝናብ ማዝነብ ፕሮጅክቱ ከስክንድር አፍ ስትሰማ ደግሞ የሀገር ጥቅም ተቀዳሚነትን ስትገነዝብ ትስተዋላለች። የባህሪ ለውጥ እናይባታለን፣ ወላዋይነት ሳይሆን ማደግዋንና መለወጧን። ሚሊዮን ብር መጀመሪያ ያታልላል፣ ቆየት ሲሉ ግን ከሚሊዮን የሚበልጡ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ነው፣ በፍሬሰላም በኩል የምናየው።

ሌሎቹን ባህሪያት በተመለከተ ብዙ የሚባል ነገር ይኖራል። እዚህ ላይ ግን ዳበስ አድርጌ ብቻ ነው የማልፈው። ያ ማለት ተራቸው አነስተኛ ነው ማለት አይደለም። ታሪኩን ወደፊት ለማራመድና የተመልካችን ስሜት ለመያዝ የሁሉም በገጸባህሪያት ተራና አላማ በተቻል ግልጽ አድርጎ ማሳየት ጠቃሚ ነው። ሰማያዊ ፈረስ ያለነ ተሾመ ሊቆም አይችልም። ስለሆነም በደንብ መሳል አለባቸው።

የነተሾም ቡድን አባላት አኑዋኑርና ባህርየት በጣም ከመመሳስሉ የተንሳ እንዱን ከሌላው በመልክ በቀር በሌላ መስፈርት መለየት ያስቸግራል። እንዱ ችኩል ሌላው እርጎ፣ እንዱ ጨካኝ ሌላው ርህሩህ ቢሆኑ ኖሮ ባህሪየቱ ጎልተው ይወጡ በነበርና በተለዩ። እነዚህ ግን እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሚስቶቻቸው፣ ቤቶቻቸው፣ መኪኖቻቸው ጭምር ይመሳሰላሉ። አያሳምንም።

ለምን?

ሌባ ሲባል ሁሉ ጨካኝ አይደለማ። ሌባ ሁሉም ደፋር አይደለማ። ሌቦች ሁሌ በሁሉም ነገር አይስመሙማ። እነሱም በውስጣቸው ቅረኔ አለባቸው። በመሀላቸው አለመተማመንም ይኖራል። ያ ወጥቶ ሲታይ ባህሪያቱ ውን ብቻ ሳይሆኑ በተመልካች ትዝታ ውስጥ ለረጅም ጊዜ መቆየትም ይችላሉ።

አርማጌዶን የሚባለው ፊልም ውስጥ ከዊልስ ብሩስ ጋር የሚስሩትን ነዳጅ አውጮዎች ያስታውሱዋል። አንዱ ከሌላው የሚለይበት ባህሪ በጥንቃቄ ተነድፎ እንደተዘጋጀ ያስታውቃል። ተመሳሳይ ገጸ ባህሪ አይታዩበትም። አንዱ ቀልደኛ ሌላው ቁምነገረኛ፣ አንዱ ፈሪ ሌለው ደፋር፣ ወዘተ ናቸው። ገጸ ባህሪያት ተመሳሳይ ከሆኑ፣ ለታሪኩም ለበጀቱ ሲባል አንዱን ማስወጣት ይሻሻል። አለበለዚያ ለሁሉም የተለየየ የጀርባ ታሪክ፣ እስትደድግና የህይወት አላማ በመስጠት የተለየዩ ባህሪያት እንዲሆኑ ማድርግ። ያኔ ነው ሲስማሙ ብቻ ሳይሆን ሲጨቃጨቁም ማየት የምንችለው። ብሎም እውነታን በማንጸባረቅ ተመልከች መማረክ ----
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Fri Jun 06, 2008 2:14 am

ድግ

Postby ባሻሽብሩ » Sun Jun 08, 2008 10:22 am

ወዳጄ ፓስወርድ ግምገማህን ወደድኩት መውደድ ብቻ አይደለም መሳተፍም ሞከርኩ:: በመጀመሪያ ታሪኩ ላይ ያስቀመጥካቸውን አንዳንድ አስተያየቶች በተመለከተ ጥቂት ልበል......
የፊልሙ ታሪክ.........''ሰማያዊ ፈረስ ስለ ምንድን ነው ?""
ብለሀል ስለምን እንደሆነ ጠፍቶህ አይደለም::ገብቶህ ብዙ ብለሀል ለዚህም አድንቄሀለሁ::ግን''....ሰማያዊ ፈረስ ደራሲው አባይን ያናገረበት ወይም ያዳመጠበት ፊልም መሆኑን የሚያመለክት አባይ ነክ ታሪክ አላየሁበትም።....''እንዴት? አባይን ለማዝነብ ነው አላማው::የውጭ ሰዎችንም ስቦ ቅጥረኛ እንዲገዙ ያረገው ይሄው ነው::ቅጥረኛ ገዢዎቹ ማን እንደሆኑ ያልተጠቀሰው በጥርጣሬ ሀሳብ ተማልካችን ሰቅዞ ለመያዝ ነው::ማን ይሆን ግብጾች?ወይስ ሌላ ፈጠራውን ፈላጊዎች? እርግጥ ፍንጭ ይሰጣል::ተጨማሪ ''....ሰማያዊ ፈረስ የተባለው አባይ ወንዝ ከሆነ ርእሱ ከታሪኩ ጋር ግንኙነት የለውም ማለት እደፍራለሁ።...''ብለሀል ይህ የራስህ ሀሳብ ነው በደራሲው ዘንድ ወሀውን አትንኖ ሰማይ ላይ ከወጣ በሁዋላ ነው የሚዘንበው የኢንጂነር እስክንድር ግኝትም ወሀውን አትንኖ ሳማይ ማውጣት ነው::የሌሎችን ትኩረት የሳበውም ይሄው ነው::የታሪኩ አንኩዋር ጨብጥም ይሄው ነው::ስለዚህ""..........ከታሪኩ ጋር የሚስማማ ርእስ ምረጥ ብባል ከዚሁ ፊልም ሳልወጣ ፍሬ ስላም ለድርሰትዋ የመረጠችውን፣ የናት ጡት ነካሽ፣ የሚለውን አወጣለት ነበር።.....'' ብለሀል::በመጀመሪያ ላልወለዱት ልጅ ስም ማውጣት ወይም ለሰው ፈጠራ ርዕስ ማውጣት አይሆንም አይታሰብም:: ሌላው የገረመኝ ""....የታሪኩ ዋና መስመር የሀገርንና የህዝብን ጥቅም በእፍቅሮተ ነዋይ በመለወጥ ወንጀል ፈጽመው ስልሚያዙ ሰዎች ስለሆነ።......''ከላይ እንደገለጽኩት ታይቶ የማይታወቀውን ወንዝን አትንኖ የማዝነቢያ ሲስተም/ፈጠራ/ነው ያ-ያጉዋጉዋቸው ናቸው ጥናቱን ለማግኘት የሚሩዋሩዋጡት ይህ ፈጠራ ባይስባቸው ዞር ብለው ባላዩት ሌላው ብዙ ትኩረት የሰጠው አባይ ላይ መሆኑ ነው እዛው ድረስ ሄዶ ማጥናት ያስፈለገው ለረጅም ጊዜ የተመራመረበትን ንድፍ ይዞ ሀገሩ የመጣው ያለበት ሀገር ወንዝ ጠፍቶ አይመስለኝም::ደራሲው ታሪኩን በአባይ ላይ ለማረግ ነው::ስለዚህ የታሪኩ ምሶሶ አባይ ነው::
ወዳጄ ፓስወርድ ""...ፊልሙ ሲጀምር በተሾመ የሚመራ አምስት ስዎች የያዘ አንድ ማፊያ መሰል ቡድን፣ ለውጭ ሰዎች ተቀጥሮ የእቶ እስክንድር አባተን ሳይንሳዊ ጥናት ለመስለብ ሲመካክርና እቅድ ሲያወጣ እናያለን። የሚያልቀው ይሄው ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ሲውል እንጂ የእስክንድር ጥናት ተሰፋ እንደሰጠን አባይ ወንዝን አትንኖ ዝናብ ሲያዘንብ አይደለም።....''ብለሀል እንደሀሳብ ስናየው ልክ ሊመስል ይችላል::አጨራረሱን እንደህንድ ፊልም ያረገውና ተረት...ተረት ይሆን ነበር::ከቀማኞች መትረፉን ካሳየህ ቀጣዩ የተመልካች ግምት መሆን አለበት::ለተመልካቹ የሆነ የቤት ስራ ካልተወ ምኑ ነው ትውስታው?ለምሳሌ በዕኔ ግምት ቀማኛ ከሌለ እንቅፋት ከሌለ ተግባር ላይ ይውላል እላለሁ::አንተ ደግሞ ሌሎች ቀማኞች ቢነሱበትስ ትላለህ......ይሄ ነ የቤት ስራው::
በአባይ ጉዳይ አይደለም ጭብጡ የእናት ጡት ነካሽ በሆኑ ዙሪያ ነው ለሚለው ሀሳብህ ራስህ ወረድ ብለህ የጻፍከው መልስ ይሆናል እንየው ''.....በእርግጥ ደራሲው የነካካው የኣባይ ጉዳይ በቀላሉ የሚታይ ነገር አይደለም። ከስክሪኑ በስተጀርባ አንድ ትልቅ አሳሳቢና ቁጭት ቀስቃሽ ጥያቄ መለጠፉን ማንም አይስትም። አባይን የሚየክል ስንቱን አብልቶና አተጥቶ ተርፎ ባህር የሚገባ ወንዝ እያለን እንዴት በረሀብ የታወቅን ተመጽዋቾች እንሆናለን የሚለው፣ እስካሁን ምላሽ ያላገኘው፣ የብዙሀን ጥያቄ አለ። ደረሲው ጥያቄውን በተለያየ ምስል አንስቶ አሳይቶናል። መላኩ በቲቪ ስለ አባይ የሚያየው፣ ጴጥሮስም እቤቱ የሰቀለው የፉዋፉዋቴው ስእል፣ በመጨረሻ እስክንድር ራሱ በአካል ሄዶ ጢስ ኣባይን ሲጎበኝ የምናየው እንደ ሰጋር ፈረስ እየተቅበጠበጠ የሚወርደው የውሀ ፉዋፉዋቴ አንዳች የቁጭት ስሜት ይቀሰቅሳል።....'' ከዚህ በላይ ምን ማስረጃ አለ?ገበሬው ተፈናቅሎ ለልመና ወቶ""አንድ ብር ላይ ያለው ወንድሜ ናፈቀኝ...........ሰማይ ገጌ ምድር ፈቄ አለብንና....እዛው ጎጃም ሄዶ ባይሆን እንኩዋን ትኩረት አልሳበም ይባላል አባይ አጠገብ ገበሬው ሲለምን ያሳየው ቁጭትን መጫር ብቻ ሳይሆን እንዲንር ያረገዋል::
እቀጥላለሁ
i like contact to any ethiopians
ባሻሽብሩ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 324
Joined: Sun Apr 29, 2007 5:56 am
Location: no

Postby password » Tue Jun 10, 2008 5:17 pm

ባሻ አንደጻፈው
ወዳጄ ፓስወርድ ግምገማህን ወደድኩት መውደድ ብቻ አይደለም መሳተፍም ሞከርኩ ::

ግምግማዬን ስለወደድከው በጣም አመሰግናለሁ። በተሳትፎህም ደስተኛ ነኝ። የሚያነብህ ሰው መኖሩን ማወቅ ራሱ ያስደስታል።

.''ሰማያዊ ፈረስ ስለ ምንድን ነው ?""
ብለሀል ስለምን እንደሆነ ጠፍቶህ አይደለም ::ገብቶህ ብዙ ብለሀል ለዚህም አድንቄሀለሁ

ይህ ለትችቴ መንደርደሪ እንዲሆን ያስቀመጥኩት እንጂ ማብራሪያ ፈልጌ ያቀረብኩት ጥያቄ እይደለም።

ወዳጄ ፓስወርድ ""...ፊልሙ ሲጀምር በተሾመ የሚመራ አምስት ስዎች የያዘ አንድ ማፊያ መሰል ቡድን፣ ለውጭ ሰዎች ተቀጥሮ፣ የእቶ እስክንድር አባተን ሳይንሳዊ ጥናት ለመስለብ ሲመካክርና እቅድ ሲያወጣ እናያለን። የሚያልቀው ይሄው ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ሲውል እንጂ የእስክንድር ጥናት፣ ተሰፋ እንደሰጠን፣ አባይ ወንዝን አትንኖ ዝናብ ሲያዘንብ አይደለም። ....''ብለሀል / እንደሀሳብ ስናየው ልክ ሊመስል ይችላል ::አጨራረሱን እንደህንድ ፊልም ያረገውና ተረት ...ተረት ይሆን ነበር ::
::

ይህ የክርክር መስመር ገበያ ያለው አይነት አይደለም። በመሰረቱ ፊልሙ በዋናነት ስለ አባይ መሆኑን የሚያሳስይ ኣባይ ነክ ነገር አላየሁም ስል መጨረሻ ላይ የጥናቱን ውጤት ስላለየሁ ብቻ አይደለም። መሀልም ውስጥ በቲቪና በስእል አባይ ለጥቂት ሴኮንዶች፣ ያውም ከታሪኩ ግንኙነት በሌለው ትእይንት ውስጥ፣ ከመታየቱ በቀር የትልም አካል ሆኖ ታሪኩን ሲያራምድ ሆነ ሲያጣጥፍ፣ ገጸባህሪያቱን ሲያነጋግር ሆነ ሲያጨቃጭቅ አላየሁም። ስለ ውሀ ማትነን ማውራት ስለአባይ ተወራ ማለት አይደለም። የተወራው ለማንኝኘውም ወንዝ ለነጊቤ፣ ፊንጫ፣ ሚሲሲፒ አማዞን ሊሆን ይችላል። ኣባይን ልዩ ያደረገ ነገር የለም።

ከቀማኞች መትረፉን ካሳየህ ቀጣዩ የተመልካች ግምት መሆን አለበት ::ለተመልካቹ የሆነ የቤት ስራ ካልተወ ምኑ ነው ትውስታው ?ለምሳሌ በዕኔ ግምት ቀማኛ ከሌለ እንቅፋት ከሌለ ተግባር ላይ ይውላል እላለሁ ::አንተ ደግሞ ሌሎች ቀማኞች ቢነሱበትስ ትላለህ ......ይሄ ነ የቤት ስራውእኔ ሌሎች ቀማኝኞች ቢነሱበትስ አልልም። እሱ ችግር ከአሁን በሁዋለ በጥበቃ ይፈታል። ጥናቱ ላይ ነው የኔ ጥያቄ። ጥናቱን በተግባር ለመተርጎም ብዙ ነገር እንደሚያስፈልግ ጥቂት ነጥቦች ልጥቀስ.

1 ጥናቱ እስካሁን የልተደረሰበት ጥበብ መሆኑ ስለተነገረን
2 ጥናቱ መቶ በመቶ እንዳልተጠናቀቀ እስክንድር ራሱ መናገሩ፣
3 መሳካቱን እንደሚጠራጥር ለፍሬስላም መንገሩ

እነዚህ ነጥቦች የሚያሳድሩብን ጥያቄ አለ? ይሳካለት ይሆን? የሚል ጥያቄ። ደራሲው ምናልባት ለልብ ሰቀላ የተጠቀመበት ዘዴ ሊሆን ይችላል። ከሆነም ደግሞ የጉዳዩን መጨረሻ ማሳየት ይኖርበታል። የቤት ስራ ምናልባት ንኡስ ትልሞች ላይ ይሰራ ይሆናል። ዋናው ትልም ላይ ግን ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት አለባቸው።

እነ ተሾም ለእስክንድር ጥናት ትልቁ ችግር እይደሉም። ፊልሙ ወደ ማብቂያው እስኪቀረብ እስክንድር ራሱ እነተሾመ መኖረቸውንም አያውቅም። ለስክንድር ትልቁ ጭንቀት የጥናቱ መሳካት፣ አለመሳከት ነው።
ሶላር ኤኔርጂ ባሻህ ጊዜ የምታገኘው የሀይል ምንጭ አለመሆኑ፣
ውሃን ካተነንክ በሁዋላ መጨበጪያ ከሌለው ንፋስ ጋር የሚደረገው ''ትግል''፣
ከዳመነልህስ በሁዋላ በፈለክው ክልል ማዝነብ፣

እነዚህ እነተሾመን ስላስወገድክ ብቻ የሚፈቱ ችግሮች አለመሆናቸውን የሚየውቅ ተመልከች ባለበት ዘመን አጨራረስህን እንደ አጀማመርህ ካላሳመርክ ለመበረታተት ያህል የሚሰነዘሩ በጎ ቃላት ብቻ፣ አይደለም አበይን የቄራን ወንዝ አያሻግርም።

ባሻ ይህን እጭር ትይንት ላስታውስህ,

እነተሾመ በቁጥጥር ስር ናቸው። ታስረው መኪና ውስጥ ይታያሉ። አንድ ጄኔራል ወታደራዊ እንደለበሱ እስክንድርና ፍሬ ከቆሙበት ድረስ መጥተው የክብር ሰላምታ ከሰጡ በሁዋለ ወደ መኪናቸው ይመለሳሉ። እስረኞቹ ሲወሰዱ እስክንድርና ፍሬ ቆመው እስከ መጨረሻ ይመለከቱና ፊልሙ ያልቃል። ይህ አጨራረስ፣ ፊልሙ ለወንጀሉ ክፍል ክብደት እንደሰጠው ከሚያመሳክሩ ትእይንቶች አንዱ ነው።

በእንጻሩ ሌላ ትይንት በአይነ ህሊናህ ተመልከት፣

እስክንድር፣ የተቁዋረጠ ጥናቱን ሲቀጥል፣ ፍሬ ስታግዘው ትንሽ ካየን በሁዋላ እንድ ደርቆ የነቃቃ በጣም ሰፊ የእርሻ መሬት፣ ሳር ቅጠል ያረረበት ጋራ፣ ሰው ከእንሰሳ አጥንቱ ያገጠጠበት መንደር ማሳየት፣
ከዚያ ሰማይ ሲዳምን፣ ሲነጉድና ሲዘንብ
በዝናቡ ምድር ስትለመልም፣ በሺ የሚቆጠር ህዝብ መስክ ላይ ወጥቶ፣ ወደ ሰማይ እያየ ሲጨፍር፣ እስክንድርና ፍሬ መስኩ ላይ, ከህዝቡ ጋር በዝናብ ርሰው ''አባይ ተንኖ'' የሚልውን መዝሙር እየዘመሩ ፊልሙ ቢጨርስ፣

በኔ እምነት ታሪኩ ሙሉ ክብ ባይሆንም ትንሽ አቅጣጫው ይቀና ነበር ብዬ እገምታለሁ።

የሚቀጥለው ግምገማዬ በቃለ ባህሪያት DIALOG ላይ ይሆናል።
በቅርብ እመለሳለሁ።

ፓስወርድ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ዋናው » Wed Jun 11, 2008 12:58 am

ሠላም ማለፊያ ቃል

እጅግ ረቂቅ የሆነ ምልከታህን ሳላደንቅ ባልፍ የጥበብ አድባር ትጣላኛለች ብዬ ዛሬ ብቅ ልኩኝ: ባረፍድም::
እንደዚህ ዓይነቱን ድንቅ ቅኝት ቀድመው አግኝተው ቢሆኑ ስንቶቹ የተሳካለት ስራ በሠሩ: እናም ጊዜ ላንተ አድልታልህ ብዙ ብዙ በቃኘህ ብዬ ተመኘው::

ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby password » Fri Jun 13, 2008 3:08 pm

ሰላም ዋናው። ለአስተያየትህ አመሰግናለሁ። ቀጣዩን ርእስ የምጀምረው፣ ፈቃድህ እንዲሆን በመተማመን፣ በአንተ ስራ ነው።

ፊልም /[ ሰማያዊ ፈረስ[
አቅረቢ/ ሰራዊት ማልቲሚዲያ ፕሮደክሽን
አዘገጅ/ ሰራዊት ፍቅሬ
ደረሲ/ ሰራዊት ፍቅሬ

ገምጋሚ / ፓስወርድ

ክፍል ሶስት ጭውውት (ቃለ ባህሪ) Dialogue

''የሚወዱኝ ይመስልሻል ?''

''ዘካር ......መውደዱ የኔ ድርሻ ነው ። የነርሱ ድርሻ ልጃቸው የወደደችውን መተዋወቅ ብቻ ነው ::''

ውብ ቃለ-ባህሪ የተናጋሪውን ነፍስ የሚያሳይ መስኮት ነው ይባላል። ከላይ የተጠቀሰው ከጥላ አልበ የተቀነጨበ ነው። በአድማጭ ወይም በአንባቢ የትውስታ ማህደር ውስጥ ቦታ ይዞ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አባባል ነው ብል ማጋነን አይሆንም። ውብና ልዩ የሚያደርገው ለጥያቄ ቅልብጭ ያል ጥሩ መለስ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ቁዋንቁዋው ቀላልና ግልጽ በመሆኑም ነው። መልሱ ከጥያቄው ልክክ ብሎ ስለሚገጥም እውነት ይመስላል። ህዝብ ጆሮ ቢደርስ ወዲያው ለቀም የሚደረግና በሰፊው መባል የሚጀምር አይነት ይመስለኛል። catch phrase አንደሚሉት አይነት።

ቃለ-ባህሪ ወይም ጭውውት እውነት መምስል አለበት፣ በተራው ጊዜ እንድምናወራው፣ እንድምንለፈልፈው፣ እንድምንጨቃጨቀው፣ እንድምንተባተበው፣ እንድምንጮኽው።
ለምሳሌ ያህል ከድያና ''አጅሬው'' የጨለፍኩትን እንመልከት
'ዲዬ !'
'አቤት '
'አመንሽኝ እንዴ ?'
'ምኑን ?'
'ስለ ታዲ የነገርኩሽን ?'
'እንዴ !'
'ዛሬ ቀኑ ምንድነው ?'
'ምንድነው ?'
'ምስኪን ዲዬ በጠበጥኩሽ አይደል ?'
'ጆኒ የቀልድህን ሆኖ ከሆነ አንተን አያርገኝ እንዲህ አይነት ቀልድማ አትቀልድም !'
'አልቀለድኩም !'
'ታዲያ !'
'በቃ ቀኑን አስታውሺና እነግርሻለሁ ::'
'ቅዳሜ ነዋ !'
'ሌላስ ?'
'በል አትለፋደድብኝ ልተኛበት ::'
'እስካሁን አልነቃሽም ?'
'ምንድነው እሱ ጆኒ ? ከነገርከኝ ንገረኝ ያለዚያ ግን ደክሞኛል ልተኛበት !'
'April the fool!'

ፍሰቱን፣ ቀላልነቱንና እውነት መሳይነቱን ያስተውሉዋል። ሳንበው ከውኑ ዓለም በቴፕ የቀዳችው ይሆን እስከማለት ነበር የደረስኩት።

የፊልም ባህሪያትም እንዲያ ነው መነጋገር ያለባቸው። ሰማያዊ ፈረስ ውስጥ የሚደነቅ ጭውውት አድምጫለሁ። እስክንድርና ፍሬስላም በሚገናኙባቻው ትይንቶች፣ በእብዛኛው ማለት ይቻላል፣ የሚነጋገሩት ቃል እንከን ላወጣበት አልቻልኩም፣ በተለይ የሆቴሉ በረንዳ ትይንቶች ውስጥ ያለው ጭውውት ተፈጥሮዋዊና እውነት መሳይ ነው።

ጭውውታቸውን እውነት ካስመሰሉት ዘዴዎች አንዱ፣ አንዱ ሲናግር ሌላው አቁዋርጦ የሚገባው፣ ነገር ነው። በውኑ ኣለም እንደምናደርገው ማለት ነው። ይህ ዘዴ ጭውውቱን የተሸመደደ የተውኔት ቃል አያስመስለውም። የተዋኒውንም ብቃት የሚፈትን ነው። ስራዊትና ዝናሽ በዚህ ረገድ ድርሻቸውን በሚገባ እንደተወጡ አያጠያይቅም።

ተሾምም ከባለቤቱ ጋር የሚነጋገረው ጭውውት ቆንጆ ነው።

ለምሳሌ. የመኝታ ቤቱ ትይንት እንውሰድ።

መኝታ ቤት፣ ተሾመና ባለበቱ ሊተኙ አልጋ ላይ ወጥተዋል

ቅድስት
ምን ታስባለህ ተሼ፣ ችግር አለ እንዴ?

ተሾም
ችግር ጠፍቶ ያውቅ ይመስል፣ ምን ትጠዪቂኛለሽ

ቅድስት
እረ ተመስገን፣ ምንም አልጎደለ

ተሾመ
አንቺማ ምን ይገበሻል

ብሎ ተሾመ ፊቱን አዙሮ ይከናነባል።

ቅድስት
በል ፊትህን እታዙርብኝ

ተሾመ በመስለቸት እየዞረ
እፍፍፍ ይኽው።

በማለት ከሀብቱ በስተጀርባ ያለውን ስላምና ፍቅር አልባ፣ የተሰላቸ ህይወት ማንጸባረቅ ችሎአል።

ሌሎችም ግሩም ጭውውቶች አሉ። ለምሳሌ ጴጥሮስ ከሚስቱና ከልጁ ጋር፣ እንዲሁም መላኩ ከሚስቱ ጋር። ተቃራኒ ጾታዎች መሀል የተደመጠው ጭውውት የሚደነቅ ሲሆን፣ በአንጻሩ በወንዶች መሀል የነበረው ድክመት ነበረበት። እንዳንድ ትይንቶች ላይ የሚደመጡት ጭውውቶች እውነታን የሚየንጸባርቁ፣ የገጸ ባህሪያትን ማንነት የሚገልጡ ወይም ተሪኩን የሚያራምዱ ናቸው ማለት ያስቸግራል።

ይቀጥላል
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests