ፊልሞች በፓስወርድ መነጥር ስር/

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby password » Wed Jan 21, 2009 9:20 am

ሀያሲያን በእንድ የኪነጥበብ ስራ ላይ የሚስነዝሩት አሉታዊ አስተያየት እውን በገበያቸው ላይ አሉታዊ ተስእኖ ያመጣል?

ይህን ጥያቄ ሰራዊት ፍቅሬ ወደ አገርቤት ሳይመለስ ቢመልስልን ጥሩ ነበር። አይመስልሽም ... በርድ? ትላንት ኦባማን አየሽው? የአለም ፕሬዝድንት አይመስልም!!!!!

ወደ ጥያቄው ..........

የኔ መለስ ግን አዎ ያመጣል እና አይ አያመጣም ነው። እንደ ሂሱ አቀራረብና እንደ መልስ አሰጣጡ ነው የሚሆነው ለማለት ነው።

ሂሱ በቅንነት የቀረበ ሙያዊ አስተያየት ከሆነ አንባቢ ልዩ ትኩርት ሰጥቶ ያነብበዋል። የተጠቆሙትን ጠንካራና ደካማ ነጥቦች ላይ ምልከት ያደርግና የራሱን ፍርድ ከመስጠቱ በፊት ኪነ ጥበብኛው የሚስጠውን መለስ ይጠብቃል። የጠበቡ ስራ የገበያ እጣ-ፈንታ እንግዲ አሁን ይመስለኛል። መልስ አሰጣጥ ላይ።

መልሱ፣
እስኪ አንተ ሰርተህ አሳየን!
ድሮም አበሻ ሲባል ሰው የሰራውን ከማጣጣል በቀር ምን ያውቃል!!1
ምቀኝነት ነው! ቅናት ነው! ተንኮል ነው!
የሚል ከሆነ አንባቢው ምልከት ባደረገባቸው ነጥቦች ላይ ተመርኩዞ የራሱን ፍርድ ወዲያው ይሰጣል። የሀያሲው አስተያየት በብዛት ነቀፋ ከሆነ፣ ሰው የጥበብ ስራውን ለማየት የሚኖርው ጉግት ሊቀዘቅዝ ይችላል።

በእንጻሩ ኪነጥበበኛው ለተሰጠው በጎ አስተያየት አመስግኖ አለአግባብ የተነቀፈበት ላይ ሙያውዊ መልስ ቢሰጥበት፣ ሀያሲው ማስተዋል የተሳነውን ነጥቦች አንድባንድ ዘርዝሮ ቢሞግት፣ ያመንባቸውን ጉድለቶች ወደፊት እንደሚያሻሽል ቢገልጽ፣ ተጨማሪ አስተያይት ለመቀበልና መልስም ለመስጠት እሁንም ፈቃደኛ መሆኑ ቢገልጽ አንባቢው የራሱን ፍርድ ለመስጠት አይቸኩይልም። ማናቸው ነው ልክ? እስኪ እኔ ራሴ ሊየው የሚል አቅዋም ይይዛል። ካየም በሁዋላ ከሌላው የጠበቡ አፍቃሪ ጋር ይወያይበታል፣ ይከራከርበታል።

አንዲህ የመወያያ ርእስ የሆን የጥበብ ስራ፣ መጽሀፍ ከሆን ተደጋግሞ ይነበባል። ፊልም፣ ትያትር ወይም ስእል ከሆነ ደግሞ ተደጋግሞ ይታያል። እንደ ሬክላም ሙዳሴ ብቻ ሳይሆን ድክመትንም የሚጠቁም ሂስ ከማስታወቂያ የበለጠ ህዝብን ይስባል። በተለይ ጠንካራ ቃላት የሚለዋወጡበት ሂስና መላሽ ህዝብን ወደ ጥበቡ መድረክ የመሳብ ሀይል አለው ብዩ አምናለሁ።

በዚህ ክፍል በአንዳንድ ፊልሞች ላይ ሂስ ተሰንዝሮአል። መልስ የሰጠ ሰው ግን እስካሁን የለም። መልስ ቢሰጡና ትንሽ ክርክር ቢነሳ አንባቢው ፊልሙን ደግሞ ማየት እንደሚፈልግ አልጠራጠርም። ሂስና ምላሹ ብዙ ሰው እሚደርስበት ስፊ መድረክ ላይ ሲሆን ሚዘን የሚሰብር ገበያ ይቀሰቀሳል ብዬ ነው የማምነው፣ እንጂ እንደሚፈራው ኪሰራ የሚጋብዝ አይመስለኝ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby early_bird ! » Wed Jan 21, 2009 9:56 pm

:lol: ቺርስ ለ ኦባማ እንደጉድ ተደስተናል !! ፓስ ...የሰራዊትን ቃለ መጠይቅ አሁን እየሰማሁት ነው ....ድምጹኮ...ሲልጠኝ... :wink: :lol: ሄሮሽማ ምን አይነት ፊልም ይሁን ደሞ እሱ :roll: እስቲ ልጨርሰውና ከችላለው
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby በጎሲያ » Sat Jan 24, 2009 12:16 am

ፓስ
ድንቅ ምልከታ ብያልው::
በጎሲያ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 93
Joined: Mon Dec 29, 2003 8:48 pm

Postby password » Sun Jan 25, 2009 6:13 pm

early_bird ! wrote::lol: ቺርስ ለ ኦባማ እንደጉድ ተደስተናል !! ፓስ ...የሰራዊትን ቃለ መጠይቅ አሁን እየሰማሁት ነው ....ድምጹኮ...ሲልጠኝ... :wink: :lol: ሄሮሽማ ምን አይነት ፊልም ይሁን ደሞ እሱ :roll: እስቲ ልጨርሰውና ከችላለው

ሄሮሺማ ፣ ሰራዊት እንዳብራራው ከሆነ አፍሪካ ምድር ላይ የሚራገፍ የኒዩክሌር ዝቃጭ ሊያስከትል ሰለሚችለው ችግር ነው። ድራሲው ራሱ ሰራዊት እንደሆነ ተናግሮአል። ዳይሬክትሩን አላውቅም ግን እሱ ራሱ ይመስለኛል። ፕሮዲዩስሩ የታወቀ ነው። ክቡርነታቸው ናቸው። ሾተልን ማለቴ አይደልም፣ ይገባሻል።

ከርእሱ እንደምገነዝበው ቀላል ፊልም አይመስለኝም። ፊልሙ፣ የኒውክሌር ዝቃጭ የሚያፈነጥቀው ሬዲዮአከቲቭ ለሰውና ለእንሰሳ፣ ለእጽዋትና ለተክል፣ ለአካባቢና ለአየር ምን ያህል ከፍተኛ ጉዳት እንዳለው ለማሳየት ከሞከረ እጣፈንታውን ካሁኑ መተንበይ ይቻላል። የሰራዊት ፊልም ፕሮዳክሽን ከምፓኒ የፋይናስ አቅምና አጠቃላይ የሙያው ልምድ ይህን አይነት ፊልም ለማምረት የሚፈቅድለት አይመስለኝም።

ኪሱን በምን አወቅህ እንደምትዪኝ ይገባኛል። ከባድ ጥየቄ ነው። በአጠቃላይ የካምፓኒው ዋናው ስራ ማሰታወቂያ ስለሆነ፣ ከዚህ በመነሳት ግምት መውሰድ ይቻላል። በቅርቡ ከውጭ የፊልም ደርጅት ጋር በመተባበር ደህና የውጭ ምንዛሬ መጨምደዱም ይፋ ሆኖአል። ይሁን እንጂ በዚያ ርእስ ጥሩ ፊልም ለመስራት አቅምና ልምዱ አለ ብዬ አላምንም።

አስቢው እስኪ በርድ፣ ፊልም ሰርተው ከጨረሱ በሁዋላ ራሳቸው ባለቤቶቹ እየዞሩ የሚያሳዩ ከሆነ የፋይናንስ አቅማቸው ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መገመት ያስቸግራል ትያለሽ? ሰራዊት፣ አሜሪካ የመጣሁት የሂሮሺማን የተወሰኑ ትይንቶች ለማንሳት ነው ብሎአል። እቺ እኔጋ አትስራም። አይደለም አሜሪካ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኩዋን ተዋኒያንን ከነጉዋዛቸው ተሸክመሽ ከቦታ ቦታ፣ ከክፍለሀገር ክፍለሀገር እየተዘዋወሽ ፊልም መስራት ገንዘብና ጊዜ ብቻ ሰይሆን ናላና ገላ ላይ የራሱን መልከት አሳርፎብሽ ነው የሚሄደው። ሰራዊት ፊልሞቼን እየዞርኩ ለማሳየት ነው ቢል ራሱንና ከምፓኒውን ዝቅ የሚያደርግ መስሎት፣ አድማጩን መዋሽት የመረጠ መሰለኝ። ሞኝ ደራሲ መጻፍ ስለቻለ ብቻ አንባቢናውን የሚያሞኝ ይመስለዋል። ፊልም ሰሪዎችም እንደዚያ ይሆኑ?

የአገራቸን ፊልም አንሺዎች በሁለቱ እግሮቻቸው እስኪቆሙ ቀላል ግን መሳጭ የፍቅር ፊልሞች መስራት ሲችሉ ለምን ውስብስብ የወንጀል፣ የቴክኒክ፣ የሳይንስ ታሪክ እንደሚመርጡ አይገባኝም። የፍቅር ፊልም እንደ የፍቅር ልቦለድ መጽሃፍ የራሱ የሆነ ልዩ መስህብ አለው። ፍቅር የያንዳንዱን ሰው ህይወት የሚነካ ሰለሆነ በደንብ ከተሰራ ተመልካች ደጋግሞ የሚያየው መሆኑን ከውጭ ፊልሞች ታሪክ መማር ይቻላል። ባለፉት 15 ዓመታት ከተመረቱት የፍቅር ፊልሞች ቢያንስ በዓመት አንዱ 100 ሚሎዮን ዶላር በማስግባት የሰው አይን ያላስፈጠጠ የለም። ብዙዎቹ የተትረፈረፈ ትርፍ ማስገባታቸው የሚታወቅ ነው። ከሌላው የፊልም ታሪክ አይነቶች የፍቅር ፊልም ጎበዝ ተወኒያን ከመጠየቁ በቀር ይህን ያህል ልዩ ቦታ፣ ብዙ ቁሳቁስና ውድ ስፔሺያ ኢፌክት የሚፈልግ አይደልም።

በተለይ የገጸባህሪን እድገት፣ የውስጥ ግጭትና ለተመልካች የሚያስተላልፈው ልዩ መልእክት ጠለቅ ያሉ ከሆነ የፍቅር ፊልም መስራቱ በጣም ያዋጣል እላለሁ። በኢትዮጵያ የተመረቱትን ሁሉንም የፍቅር ፊልሞች አላየሁም። ያየሁዋቸው እንደ ፍቅር ሲፈርድ አይንቶቹ ግን ጥልቀት ይጎላቸዋል።

በርድ ጥልቀት ስል ገብቶሻል? ቆይ በምሳሌ ላስረዳሽ።
ፍቅር ሲፈርድ ላይ ታስታውሺ እንድሆን፣ የጆዋና አባት አሊጋ ሄድው "ሁለት መቶ ሺ ብር እንካ፣ ጆዋናን ተዋት" ይሉታል።
"ጆዋናን በገንዝብ አልለውጣትም" ሲል አሊ በቆራጥነት ይመልስላቸዋል። ይሄ የአሊን ማንነት በመጠኑ ሊያሳይ ይችላል። ፍቅሩን በገንዝብ የማይለውጥ ሰው መሆኑን። አሁን ከዚህ በላይ መሄድ ስንሞክር ነው ጥልቀት የምነለው። ፍቅርን በገንዘብ ሳይሆን በሌላ ፍቅር ስንፈትሸው። እንዴት በዪኝ።

አሊ በጣም የሚወዳት እህት አለችው፣ እሱ ትምህርቱን እስኪጨርስ እስዋ እየሰራች ታኖረው የነበረች። አሚና እንበላት፣ ለጊዜው ስምዋን ስለረሳሁት። አሚና ፊልሙ ላይ በአንድ ወንጀለኛ ትገደላለች። ግን ለዚህ ምሳሌ ከሙታን እናንሳትና የአካል ጉዳት ብቻ እንደደረሰባት እናድርጋት። የውጭ ህክምና ካልተደረገላት በቀር የደረሰባት የአካል ጉዳት ከወገብ በታች ሽባ የሚያደርጋት ስለሆነ አሊ ሊያሳክማት ገነዘብ እያጠራቀመ ነው። ግን በሱ ደሞዝ አንድ መቶ ሺ ብር ለማሰባሰብ 20 ዓመቶች ይፈጅበታል። አሚና ደሞ በሁለት ዓመቶች ውስጥ ህክምና ካልተደረገላት በቀር የመዳን እድል አይኖራትም። አታሳዝንም?

ይህ በእንዲ እንዳለ የጁዋና አባት ሁለት መቶ ሺ ብር ተሸክመው ቢመጡ የአሊን ማንነት የሚፈትን ሁኔታ እናይ ነበር። ባህሪውን ጠለቅ ብለን እናየው ነበር። ጥልቀት ማለት ያ ነው። ሙያው አዲስ ስለሆነ ስያሜው ምናልባት አልተለመደ እንደሆ ብዪ ነው። ማብራራቴ... አሁንስ ገባሽ?

ትያቄ ጣል አድርገሽ ምን ውስጥ ነው ያስገባሽ?

በዪ ቻዎ፣ አትጥፊብኝ።

ፓስ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

ሰፈ/ፍሲ- ካምፓራዳ ተመሳስሎ

Postby እንሰት » Mon Jan 26, 2009 5:25 am

password wrote:ማንጤ፣በኛ ፊልሞች የምናየውን ግን ግራ ያጋባል።
ድራሲው ፕሮዲዩሰር ይሆናል፣ ካሹ ስላለው። ፕሮዲዩሰሩ ፊልሙን ዳይሬክት ካለደርግሁ ይላል፣ ባለቤቱ ስለሆነ። ሶስት ቁልፍ ቦታ በልልኝ። ከዚያ አንድ ቆንጆ ቦታ ይቀራል፣ እሱም ላይ አይኑን ይጥላል። በእግር ኩዋስ ጨዋታ ጎል አግቢው ከሌላው ተለይቶ ስሙ እንደሚጠራ ሁሉ በፊልም ዋናው ገጸባህሪ ከሌላው በተለየ ስሙ ይጠራል። ቦታው ዝና የሚያስገኝ ነው። እና ሚስተር ዳይርክትር ፖሮዲዩሰር ዋናው ተወኒ ሆኖ ቁጭ ይላል። አልቀ። ፊልሙም ተጨመላልቆ ቁጭ። ጥሩ ምሳሌ የሰራዊት ፍቅሬ ሰማያዊ ፈረስ ነው። ደራሲው፣ ፕሮዲዩሰሩ፣ ዳይሬከትሩና ዋናው ትዋኒ ራሱ ሰራዊት ፍቅሬ። ፊልሙ ምን ሆነ ...... ጥሬ። ሞቲቭ የለው፣ ልብሰቀላ የለው፣ ምን የለው። ይህ ሁሉ ድክመት በእንድ ሰው ስለሚሰራ ብቻ ነው።

ይድረስ password;

አንባቢህ ነኝ:: ስለ ሂሳዊ አመለካከትህ ሚዛናዊነት ምንም እንከን አላገኘሁም:: ፊልም አዘጋጆቹ ቢያዩት ሊደስቱ ይገባል ባይ ነኝ:: ቀጥል በርታ!!

ይህ ከላይ ያልከው ጉዳይ ግን በካምፓራዳም የታየ ነው ለጥበብ መኮንን; እስክንድር; ፍቅሬ እና ያሬድ ሁሉም ውስጥ አሉበት በተለይ ድርሰቱ ላይ:: የመዋጮ ድርሰት ከላይ storyline ለመፈለግ እንደተቸገርከው አይነት ውስጥ ይከታል::
በቴክኒክ ላይ ላለው ደግሞ
ለምሳሌ ያሬድን ብንወስድ የፎቶ ዳይሬክተር የሳውንድ ኤዲተር እና አኒሜሽን ላይ ይሰራል "ገሊላም" እንዲሁ ተጨማሪ ነገር አላት ፊልሙ ላይ::
አድናቂህ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby early_bird ! » Wed Jan 28, 2009 7:47 pm

[list=]እትት በረደኝ በርድ ይሞቃል ወይ........እያለ ይቀጥላል ያለሁበት ሀገር ብርድ 3 ጋቢ 2 ባል የግድ ይላል..... :P :P
ፓስነት አማን ነህልኝ ? ያንተን ጥሁፍ በትኩሱ እንደወረደ ሳላነብ የዋልኩበት ግዜ የለም ....እንደው ክብርነታችው ያንን አለንጋ ጣታችውን አውሰውኝ ቢሆን ....አይሆንም እንጂ ቢሆን........ :lol: የመልስ ምት ከጎል እስከ ጎል ይሆን ነበር :wink: የኔኑ ጣት ደግሞ ፒያኖ ለይ የመፍጠኑን ይህል ፒሲ ለይ ሲሆን ይዝለፈለፋል.............አይይይይይ
እኔ ምለው ሂሮሽማ ድንቅ ፊልም እሚወጣው አይመስልህም.... ? ፈጠራው ውብ ነው ወጣ ያለነገር ይሞክራል የኢኮኖሚዋ ነገር አስቃኛለች ... :lol: አንዳንድ የግል ባንኮች ስፖንሰር መሆን ጀምረዋል ሲባል ሰምቼ ነበር ገበያውም እኮ አሁን ሞቅ ያለ ነው........ማለቴ የፊልሙ.. :roll: የኪሳራው ነገር ብዙ አይሰማም....
አረ የባቢሌስ ጉዳይ የት ደረሰ ? ስለሱ አወጋሻለሁ ያልከው ጨዋታ ነበር አይደል ....? ፊልሙስ ተጨርሶ ይሁን ? ልበር ነው :arrow: :arrow:

[/list]
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby early_bird ! » Wed Jan 28, 2009 8:05 pm

እንዴ ጥፌ ጥፌ አልሄድ አለኝሳ.. :evil: :evil:
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby sonaf » Wed Jan 28, 2009 9:55 pm

እትት በረደኝ በርድ ይሞቃል ወይ ........እያለ ይቀጥላል ያለሁበት ሀገር ብርድ 2 ጋቢ 2 ባል የግድ ይላል

የት ነው ወዳጀ?
i c u.
sonaf
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Fri Oct 19, 2007 3:07 pm
Location: uk

Postby ስሙ ይናገር » Wed Jan 28, 2009 11:10 pm

password wrote:
early_bird ! wrote::lol: ቺርስ ለ ኦባማ እንደጉድ ተደስተናል !! ፓስ ...የሰራዊትን ቃለ መጠይቅ አሁን እየሰማሁት ነው ....ድምጹኮ...ሲልጠኝ... :wink: :lol: ሄሮሽማ ምን አይነት ፊልም ይሁን ደሞ እሱ :roll: እስቲ ልጨርሰውና ከችላለው

ሄሮሺማ ፣ ሰራዊት እንዳብራራው ከሆነ አፍሪካ ምድር ላይ የሚራገፍ የኒዩክሌር ዝቃጭ ሊያስከትል ሰለሚችለው ችግር ነው። ድራሲው ራሱ ሰራዊት እንደሆነ ተናግሮአል። ዳይሬክትሩን አላውቅም ግን እሱ ራሱ ይመስለኛል። ፕሮዲዩስሩ የታወቀ ነው። ክቡርነታቸው ናቸው። ሾተልን ማለቴ አይደልም፣ ይገባሻል።

ከርእሱ እንደምገነዝበው ቀላል ፊልም አይመስለኝም። ፊልሙ፣ የኒውክሌር ዝቃጭ የሚያፈነጥቀው ሬዲዮአከቲቭ ለሰውና ለእንሰሳ፣ ለእጽዋትና ለተክል፣ ለአካባቢና ለአየር ምን ያህል ከፍተኛ ጉዳት እንዳለው ለማሳየት ከሞከረ እጣፈንታውን ካሁኑ መተንበይ ይቻላል። የሰራዊት ፊልም ፕሮዳክሽን ከምፓኒ የፋይናስ አቅምና አጠቃላይ የሙያው ልምድ ይህን አይነት ፊልም ለማምረት የሚፈቅድለት አይመስለኝም።

ኪሱን በምን አወቅህ እንደምትዪኝ ይገባኛል። ከባድ ጥየቄ ነው። በአጠቃላይ የካምፓኒው ዋናው ስራ ማሰታወቂያ ስለሆነ፣ ከዚህ በመነሳት ግምት መውሰድ ይቻላል። በቅርቡ ከውጭ የፊልም ደርጅት ጋር በመተባበር ደህና የውጭ ምንዛሬ መጨምደዱም ይፋ ሆኖአል። ይሁን እንጂ በዚያ ርእስ ጥሩ ፊልም ለመስራት አቅምና ልምዱ አለ ብዬ አላምንም።

አስቢው እስኪ በርድ፣ ፊልም ሰርተው ከጨረሱ በሁዋላ ራሳቸው ባለቤቶቹ እየዞሩ የሚያሳዩ ከሆነ የፋይናንስ አቅማቸው ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መገመት ያስቸግራል ትያለሽ? ሰራዊት፣ አሜሪካ የመጣሁት የሂሮሺማን የተወሰኑ ትይንቶች ለማንሳት ነው ብሎአል። እቺ እኔጋ አትስራም። አይደለም አሜሪካ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኩዋን ተዋኒያንን ከነጉዋዛቸው ተሸክመሽ ከቦታ ቦታ፣ ከክፍለሀገር ክፍለሀገር እየተዘዋወሽ ፊልም መስራት ገንዘብና ጊዜ ብቻ ሰይሆን ናላና ገላ ላይ የራሱን መልከት አሳርፎብሽ ነው የሚሄደው። ሰራዊት ፊልሞቼን እየዞርኩ ለማሳየት ነው ቢል ራሱንና ከምፓኒውን ዝቅ የሚያደርግ መስሎት፣ አድማጩን መዋሽት የመረጠ መሰለኝ። ሞኝ ደራሲ መጻፍ ስለቻለ ብቻ አንባቢናውን የሚያሞኝ ይመስለዋል። ፊልም ሰሪዎችም እንደዚያ ይሆኑ?

የአገራቸን ፊልም አንሺዎች በሁለቱ እግሮቻቸው እስኪቆሙ ቀላል ግን መሳጭ የፍቅር ፊልሞች መስራት ሲችሉ ለምን ውስብስብ የወንጀል፣ የቴክኒክ፣ የሳይንስ ታሪክ እንደሚመርጡ አይገባኝም። የፍቅር ፊልም እንደ የፍቅር ልቦለድ መጽሃፍ የራሱ የሆነ ልዩ መስህብ አለው። ፍቅር የያንዳንዱን ሰው ህይወት የሚነካ ሰለሆነ በደንብ ከተሰራ ተመልካች ደጋግሞ የሚያየው መሆኑን ከውጭ ፊልሞች ታሪክ መማር ይቻላል። ባለፉት 15 ዓመታት ከተመረቱት የፍቅር ፊልሞች ቢያንስ በዓመት አንዱ 100 ሚሎዮን ዶላር በማስግባት የሰው አይን ያላስፈጠጠ የለም። ብዙዎቹ የተትረፈረፈ ትርፍ ማስገባታቸው የሚታወቅ ነው። ከሌላው የፊልም ታሪክ አይነቶች የፍቅር ፊልም ጎበዝ ተወኒያን ከመጠየቁ በቀር ይህን ያህል ልዩ ቦታ፣ ብዙ ቁሳቁስና ውድ ስፔሺያ ኢፌክት የሚፈልግ አይደልም።

በተለይ የገጸባህሪን እድገት፣ የውስጥ ግጭትና ለተመልካች የሚያስተላልፈው ልዩ መልእክት ጠለቅ ያሉ ከሆነ የፍቅር ፊልም መስራቱ በጣም ያዋጣል እላለሁ። በኢትዮጵያ የተመረቱትን ሁሉንም የፍቅር ፊልሞች አላየሁም። ያየሁዋቸው እንደ ፍቅር ሲፈርድ አይንቶቹ ግን ጥልቀት ይጎላቸዋል።

በርድ ጥልቀት ስል ገብቶሻል? ቆይ በምሳሌ ላስረዳሽ።
ፍቅር ሲፈርድ ላይ ታስታውሺ እንድሆን፣ የጆዋና አባት አሊጋ ሄድው "ሁለት መቶ ሺ ብር እንካ፣ ጆዋናን ተዋት" ይሉታል።
"ጆዋናን በገንዝብ አልለውጣትም" ሲል አሊ በቆራጥነት ይመልስላቸዋል። ይሄ የአሊን ማንነት በመጠኑ ሊያሳይ ይችላል። ፍቅሩን በገንዝብ የማይለውጥ ሰው መሆኑን። አሁን ከዚህ በላይ መሄድ ስንሞክር ነው ጥልቀት የምነለው። ፍቅርን በገንዘብ ሳይሆን በሌላ ፍቅር ስንፈትሸው። እንዴት በዪኝ።

አሊ በጣም የሚወዳት እህት አለችው፣ እሱ ትምህርቱን እስኪጨርስ እስዋ እየሰራች ታኖረው የነበረች። አሚና እንበላት፣ ለጊዜው ስምዋን ስለረሳሁት። አሚና ፊልሙ ላይ በአንድ ወንጀለኛ ትገደላለች። ግን ለዚህ ምሳሌ ከሙታን እናንሳትና የአካል ጉዳት ብቻ እንደደረሰባት እናድርጋት። የውጭ ህክምና ካልተደረገላት በቀር የደረሰባት የአካል ጉዳት ከወገብ በታች ሽባ የሚያደርጋት ስለሆነ አሊ ሊያሳክማት ገነዘብ እያጠራቀመ ነው። ግን በሱ ደሞዝ አንድ መቶ ሺ ብር ለማሰባሰብ 20 ዓመቶች ይፈጅበታል። አሚና ደሞ በሁለት ዓመቶች ውስጥ ህክምና ካልተደረገላት በቀር የመዳን እድል አይኖራትም። አታሳዝንም?

ይህ በእንዲ እንዳለ የጁዋና አባት ሁለት መቶ ሺ ብር ተሸክመው ቢመጡ የአሊን ማንነት የሚፈትን ሁኔታ እናይ ነበር። ባህሪውን ጠለቅ ብለን እናየው ነበር። ጥልቀት ማለት ያ ነው። ሙያው አዲስ ስለሆነ ስያሜው ምናልባት አልተለመደ እንደሆ ብዪ ነው። ማብራራቴ... አሁንስ ገባሽ?

ትያቄ ጣል አድርገሽ ምን ውስጥ ነው ያስገባሽ?

በዪ ቻዎ፣ አትጥፊብኝ።

ፓስ።

በጣም የማደንቅህ ታላቅ የጥበብ ሰው ነህ:: ሁሉንም ግምገማህን በአትኩሮት ከሚከታተሉ አንባቢዎችህ አንዱ ነኝ:: የምታቀርባቸውን አስተያየቶችህን በፊልሙ ውስጥ እያስገባሁ መየት ከጀመርኩ ቆየሁ ፊልምን ከመውደድ ባለፈ ጥበቧን አልረዳላትም ነበር:: እንዲያውም ምኑን ፓርት ስወድ እንደነበረ ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስበው ይገርመኛል; ከሀገራችን ፊልሞች በጣም አደንቀው የነበረውን ሰማያዊ ፈረስ የመጀመሪያውን ፖስት ስታደርግ ነበር ተከታትዬ ማንበብ የጀመርኩት እናም ይገርመኝ ነበር አስተያየትህ ሁሉም ነገር በትምህርት መገንባት እንዳለበት ለራሴም ተረዳሁ:: አሁንም አስተያየቴን ልሰጥህ ያነሳሳኝ ነገር

ጥልቀት ስል ገብቶሻል? ቆይ በምሳሌ ላስረዳሽ።

ይህንን አንተ ባስቀመጥከው መንገድ ሳየው የተሻለ ፊልም ይወጣው ነበር:: በዙ ከተናገርከው ውስጥ ነው ጥቂቷን ኮት ማድረጌ
የፊልም ሰዎቻችን ይህንን አስተያየት እግረመንገዳቸውን እንኳ ወደ ዋርካ ጎራ ብለው ቢያዩ ጥሩ ስራ ይሰሩልን ነበር እያልን ከጓደኞቼ ጋር እንጫወት ነበር::

ግን የምልህ ለምን በኢሜላቸው ግጥም አድርገህ አትጽፍላቸውም?
እኔ አንድ ነገር አስቤ ነበር ግጭት ብለህ በሰማያዊ ፈረስ ላይ ያቀረብከውን ኮፒ አድርጌ በ PDF format አድርጌው በኢሜል ልልክለት ወስኛለሁ ግን ያንተን ፍቃድ ስላላገኘው ለጊዜው አልላኩትም ነገር ግን ወደዋርካ መምጣት ለማይችሉ የቅርብ ጓደኞቼ እየላኩላቸው ነው ከዋርካ ያገኘሁት ብዬ:: እንዲያውም አንዳንዶች ከዚያ ወዲህ ወደ ዋርካ ብቅ እያሉ እንደሆነ ነግረውኛል:: ባጠቃላይ በርታ አንተም ከቻልክ ወደሙያው ገብተህ ጥሩ ነገር ማየት እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ
አድናቂህ ነኝ
God is Great
ስሙ ይናገር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1150
Joined: Fri Mar 14, 2008 4:46 pm

Postby early_bird ! » Thu Jan 29, 2009 1:24 am

sonaf wrote:
እትት በረደኝ በርድ ይሞቃል ወይ ........እያለ ይቀጥላል ያለሁበት ሀገር ብርድ 2 ጋቢ 2 ባል የግድ ይላል

የት ነው ወዳጀ?

አላስካ ተሚባለው መንደር ነኝ .........የአሳ ማጥመድ ስራ ታክሎበት ምንደምመስል ሳለኝማ......... :roll:
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby early_bird ! » Thu Jan 29, 2009 1:33 am

ስሙ ይናገር wrote:
password wrote:
early_bird ! wrote::lol: ቺርስ ለ ኦባማ እንደጉድ ተደስተናል !! ፓስ ...የሰራዊትን ቃለ መጠይቅ አሁን እየሰማሁት ነው ....ድምጹኮ...ሲልጠኝ... :wink: :lol: ሄሮሽማ ምን አይነት ፊልም ይሁን ደሞ እሱ :roll: እስቲ ልጨርሰውና ከችላለው

ሄሮሺማ ፣ ሰራዊት እንዳብራራው ከሆነ አፍሪካ ምድር ላይ

የሚራገፍ የኒዩክሌር ዝቃጭ ሊያስከትል ሰለሚችለው ችግር ነው። ድራሲው ራሱ ሰራዊት እንደሆነ ተናግሮአል። ዳይሬክትሩን አላውቅም ግን እሱ ራሱ ይመስለኛል። ፕሮዲዩስሩ የታወቀ ነው። ክቡርነታቸው ናቸው። ሾተልን ማለቴ አይደልም፣ ይገባሻል።

ከርእሱ እንደምገነዝበው ቀላል ፊልም አይመስለኝም። ፊልሙ፣ የኒውክሌር ዝቃጭ የሚያፈነጥቀው ሬዲዮአከቲቭ ለሰውና ለእንሰሳ፣ ለእጽዋትና ለተክል፣ ለአካባቢና ለአየር ምን ያህል ከፍተኛ ጉዳት እንዳለው ለማሳየት ከሞከረ እጣፈንታውን ካሁኑ መተንበይ ይቻላል። የሰራዊት ፊልም ፕሮዳክሽን ከምፓኒ የፋይናስ አቅምና አጠቃላይ የሙያው ልምድ ይህን አይነት ፊልም ለማምረት የሚፈቅድለት አይመስለኝም።

ኪሱን በምን አወቅህ እንደምትዪኝ ይገባኛል። ከባድ ጥየቄ ነው። በአጠቃላይ የካምፓኒው ዋናው ስራ ማሰታወቂያ ስለሆነ፣ ከዚህ በመነሳት ግምት መውሰድ ይቻላል። በቅርቡ ከውጭ የፊልም ደርጅት ጋር በመተባበር ደህና የውጭ ምንዛሬ መጨምደዱም ይፋ ሆኖአል። ይሁን እንጂ በዚያ ርእስ ጥሩ ፊልም ለመስራት አቅምና ልምዱ አለ ብዬ አላምንም።

አስቢው እስኪ በርድ፣ ፊልም ሰርተው ከጨረሱ በሁዋላ ራሳቸው ባለቤቶቹ እየዞሩ የሚያሳዩ ከሆነ የፋይናንስ አቅማቸው ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መገመት ያስቸግራል ትያለሽ? ሰራዊት፣ አሜሪካ የመጣሁት የሂሮሺማን የተወሰኑ ትይንቶች ለማንሳት ነው ብሎአል። እቺ እኔጋ አትስራም። አይደለም አሜሪካ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኩዋን ተዋኒያንን ከነጉዋዛቸው ተሸክመሽ ከቦታ ቦታ፣ ከክፍለሀገር ክፍለሀገር እየተዘዋወሽ ፊልም መስራት ገንዘብና ጊዜ ብቻ ሰይሆን ናላና ገላ ላይ የራሱን መልከት አሳርፎብሽ ነው የሚሄደው። ሰራዊት ፊልሞቼን እየዞርኩ ለማሳየት ነው ቢል ራሱንና ከምፓኒውን ዝቅ የሚያደርግ መስሎት፣ አድማጩን መዋሽት የመረጠ መሰለኝ። ሞኝ ደራሲ መጻፍ ስለቻለ ብቻ አንባቢናውን የሚያሞኝ ይመስለዋል። ፊልም ሰሪዎችም እንደዚያ ይሆኑ?

የአገራቸን ፊልም አንሺዎች በሁለቱ እግሮቻቸው እስኪቆሙ ቀላል ግን መሳጭ የፍቅር ፊልሞች መስራት ሲችሉ ለምን ውስብስብ የወንጀል፣ የቴክኒክ፣ የሳይንስ ታሪክ እንደሚመርጡ አይገባኝም። የፍቅር ፊልም እንደ የፍቅር ልቦለድ መጽሃፍ የራሱ የሆነ ልዩ መስህብ አለው። ፍቅር የያንዳንዱን ሰው ህይወት የሚነካ ሰለሆነ በደንብ ከተሰራ ተመልካች ደጋግሞ የሚያየው መሆኑን ከውጭ ፊልሞች ታሪክ መማር ይቻላል። ባለፉት 15 ዓመታት ከተመረቱት የፍቅር ፊልሞች ቢያንስ በዓመት አንዱ 100 ሚሎዮን ዶላር በማስግባት የሰው አይን ያላስፈጠጠ የለም። ብዙዎቹ የተትረፈረፈ ትርፍ ማስገባታቸው የሚታወቅ ነው። ከሌላው የፊልም ታሪክ አይነቶች የፍቅር ፊልም ጎበዝ ተወኒያን ከመጠየቁ በቀር ይህን ያህል ልዩ ቦታ፣ ብዙ ቁሳቁስና ውድ ስፔሺያ ኢፌክት የሚፈልግ አይደልም።

በተለይ የገጸባህሪን እድገት፣ የውስጥ ግጭትና ለተመልካች የሚያስተላልፈው ልዩ መልእክት ጠለቅ ያሉ ከሆነ የፍቅር ፊልም መስራቱ በጣም ያዋጣል እላለሁ። በኢትዮጵያ የተመረቱትን ሁሉንም የፍቅር ፊልሞች አላየሁም። ያየሁዋቸው እንደ ፍቅር ሲፈርድ አይንቶቹ ግን ጥልቀት ይጎላቸዋል።

በርድ ጥልቀት ስል ገብቶሻል? ቆይ በምሳሌ ላስረዳሽ።
ፍቅር ሲፈርድ ላይ ታስታውሺ እንድሆን፣ የጆዋና አባት አሊጋ ሄድው "ሁለት መቶ ሺ ብር እንካ፣ ጆዋናን ተዋት" ይሉታል።
"ጆዋናን በገንዝብ አልለውጣትም" ሲል አሊ በቆራጥነት ይመልስላቸዋል። ይሄ የአሊን ማንነት በመጠኑ ሊያሳይ ይችላል። ፍቅሩን በገንዝብ የማይለውጥ ሰው መሆኑን። አሁን ከዚህ በላይ መሄድ ስንሞክር ነው ጥልቀት የምነለው። ፍቅርን በገንዘብ ሳይሆን በሌላ ፍቅር ስንፈትሸው። እንዴት በዪኝ።

አሊ በጣም የሚወዳት እህት አለችው፣ እሱ ትምህርቱን እስኪጨርስ እስዋ እየሰራች ታኖረው የነበረች። አሚና እንበላት፣ ለጊዜው ስምዋን ስለረሳሁት። አሚና ፊልሙ ላይ በአንድ ወንጀለኛ ትገደላለች። ግን ለዚህ ምሳሌ ከሙታን እናንሳትና የአካል ጉዳት ብቻ እንደደረሰባት እናድርጋት። የውጭ ህክምና ካልተደረገላት በቀር የደረሰባት የአካል ጉዳት ከወገብ በታች ሽባ የሚያደርጋት ስለሆነ አሊ ሊያሳክማት ገነዘብ እያጠራቀመ ነው። ግን በሱ ደሞዝ አንድ መቶ ሺ ብር ለማሰባሰብ 20 ዓመቶች ይፈጅበታል። አሚና ደሞ በሁለት ዓመቶች ውስጥ ህክምና ካልተደረገላት በቀር የመዳን እድል አይኖራትም። አታሳዝንም?

ይህ በእንዲ እንዳለ የጁዋና አባት ሁለት መቶ ሺ ብር ተሸክመው ቢመጡ የአሊን ማንነት የሚፈትን ሁኔታ እናይ ነበር። ባህሪውን ጠለቅ ብለን እናየው ነበር። ጥልቀት ማለት ያ ነው። ሙያው አዲስ ስለሆነ ስያሜው ምናልባት አልተለመደ እንደሆ ብዪ ነው። ማብራራቴ... አሁንስ ገባሽ?

ትያቄ ጣል አድርገሽ ምን ውስጥ ነው ያስገባሽ?

በዪ ቻዎ፣ አትጥፊብኝ።

ፓስ።

በጣም የማደንቅህ ታላቅ የጥበብ ሰው ነህ:: ሁሉንም ግምገማህን በአትኩሮት ከሚከታተሉ አንባቢዎችህ አንዱ ነኝ:: የምታቀርባቸውን አስተያየቶችህን በፊልሙ ውስጥ እያስገባሁ መየት ከጀመርኩ ቆየሁ ፊልምን ከመውደድ ባለፈ ጥበቧን አልረዳላትም ነበር:: እንዲያውም ምኑን ፓርት ስወድ እንደነበረ ዛሬ ላይ ቆሜ ሳስበው ይገርመኛል; ከሀገራችን ፊልሞች በጣም አደንቀው የነበረውን ሰማያዊ ፈረስ የመጀመሪያውን ፖስት ስታደርግ ነበር ተከታትዬ ማንበብ የጀመርኩት እናም ይገርመኝ ነበር አስተያየትህ ሁሉም ነገር በትምህርት መገንባት እንዳለበት ለራሴም ተረዳሁ:: አሁንም አስተያየቴን ልሰጥህ ያነሳሳኝ ነገር

ጥልቀት ስል ገብቶሻል? ቆይ በምሳሌ ላስረዳሽ።
ፍቅር ሲፈርድ ላይ ታስታውሺ እንድሆን፣ የጆዋና አባት አሊጋ ሄድው "ሁለት መቶ ሺ ብር እንካ፣ ጆዋናን ተዋት" ይሉታል።

ይህንን አንተ ባስቀመጥከው መንገድ ሳየው የተሻለ ፊልም ይወጣው ነበር:: በዙ ከተናገርከው ውስጥ ነው ጥቂቷን ኮት ማድረጌ
የፊልም ሰዎቻችን ይህንን አስተያየት እግረመንገዳቸውን እንኳ ወደ ዋርካ ጎራ ብለው ቢያዩ ጥሩ ስራ ይሰሩልን ነበር እያልን ከጓደኞቼ ጋር እንጫወት ነበር::

ግን የምልህ ለምን በኢሜላቸው ግጥም አድርገህ አትጽፍላቸውም?
እኔ አንድ ነገር አስቤ ነበር ግጭት ብለህ በሰማያዊ ፈረስ ላይ ያቀረብከውን ኮፒ አድርጌ በ PDF format አድርጌው በኢሜል ልልክለት ወስኛለሁ ግን ያንተን ፍቃድ ስላላገኘው ለጊዜው አልላኩትም ነገር ግን ወደዋርካ መምጣት ለማይችሉ የቅርብ ጓደኞቼ እየላኩላቸው ነው ከዋርካ ያገኘሁት ብዬ:: እንዲያውም አንዳንዶች ከዚያ ወዲህ ወደ ዋርካ ብቅ እያሉ እንደሆነ ነግረውኛል:: ባጠቃላይ በርታ አንተም ከቻልክ ወደሙያው ገብተህ ጥሩ ነገር ማየት እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ
አድናቂህ ነኝ

ሰላም ስሙይናገር ሀሳብህን እጋራልሁ ገና ከመጀመርያው የ ፓስን..ግምገማ እንዳነበብኩ ነበር እኔም እንዳንተ ግምገማው ለፊልምም ሆነ መጻፍ ደራሲዋች ይደርሳቸው ዘንድ በልቤ የተመኝሁትም ጥቆማ ያረኩትም...ፓስወርድ ዋርካ ውስጥ በትምርት ሰጪነቱ ትልቅ ቦታ እንዳልው የብዙቻችን አስተያየት እንደሚሆን እተማመናልሁ :idea:
ፓስ....እጅህን አይቆርጥመው ዛሬ ቤትህ ዋልኩ ይበረርለት ደግሞ........ :arrow: :arrow:
“Make the Most of Yourself, For that is all there is of you.”
early_bird !
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 143
Joined: Mon Sep 08, 2008 4:21 pm
Location: Always On The Move.....

Postby password » Thu Jan 29, 2009 10:53 pm

የፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ፊልም

ጤዛ

በብሄራዊ ትያትር።

የዶቺቨሌው ጌታቸው ተድላ የዘገበውን ያዳምጡ......

ድረገጹ ከተከፈተ በሁዋላ
]ኢትዮጽያዊ ፊልሞችን መስራት ይጠበቅብናል
የሚለውን ፈልገው ይጠቁሙበት።.

http://www.dw-world.de/dw/article/0,,3961111,00.html
Last edited by password on Thu Jan 29, 2009 11:16 pm, edited 1 time in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby Truth... » Thu Jan 29, 2009 11:00 pm

ሰላም ፓስ

ጽሁፎችህ በጣም አስተማሪዎች ናቸው ወድጃቼዋለሁ:: እጅህ አይንጠፍ

ወዳጅህ ትሩዝ
Yes
Truth...
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 175
Joined: Mon Dec 22, 2008 2:47 am

Postby password » Thu Jan 29, 2009 11:51 pm

በጎሲያ ..እንሰት.. በርድ፣ ስሙይናገርና ትሩዝ

ዋው ታነቡኛላችሁ ማለት ነው? በርድ እንኩዋን ተንኮስ እያደረገች ነው የምታስለቀልቀኝ። ነቅቼባታለሁ።

ትሩዝ፣ ግሩም ማይክሮ ፊክሽነኛው። አንተ ደሞ ምን ታደርጋለህ እዚህ። አንተ እንኩዋን ሞራል ስትሰጠኝ እንጂ እዚህ ክፍል የምትማርው ነገር ይኖራል ብዬ አላምንም።

ስሙይናገር፣ የጠቃቀስካቸው ነጥቦች ለፊልም ስራ መሰረታዊያን ናቸው። ግጭት ከሌለ ታሪክ የለም። ታሪክን የሚያራምደው ግጭት ነው።

እንደ 'ግጭት' የመሳሰሉ አንዳንድ ስያሜዎችን የማብራራው እኔ ራሴ እቸገርባቸው ስለነበር ነው። ስያሜዎቹን ከእንግሊዝኛው ቃመ የተተርጎሙ ከምሆናቸው በተጨማሪ ሙያው ራሱ በተግባር የተጀምረው በቅርብ ስለሆነ በምሳሌ ማስረዳት የተሻለ መገባበት ይፈጭራል የሚል እምነት አለኝ።

በልቦለድም ሆነ በፊልም ያለ ግጭት ታሪክን ለማራመድ በጣም ያስቸግራል። ልቦለድ ላይ ምናልባት በስነጽሁፉ ውበትና በመልእክቱ ልእልና high concrpt አንባቢን መያዝ ይቻላል። ፊልም ላይ ግን ከባድ ነው።

እመለሰልሁ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ዋናው » Fri Jan 30, 2009 12:50 am

password wrote:ዋው ታነቡኛላችሁ ማለት ነው?

ሠላም ክቡር ፓስ
ጥያቄህ ገርሞኝ ነው ምን ዓይነት ሠፊ ዕውቀቶችን ለሠዎች እያደረስክ መሆንህን በዚህ አጋጣሚ ብነግርህ ደስ ይለኛል...
አሁን አሁንማ ቀሽም የሆሊዉድ ፊልሞችንም ሳይ ይሄንን ሙቪ ፓስ አይቶት ይሆን ማለት ጀመሪያለው
እስቲ በርታ ወዳጄ....
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests