early_bird ! wrote:ፓስነት ...የናፍቆት ሰላምታዮን ላደርስ ነው ብቅ ያልኩት ጥፍትብለሀል'ኮ ...........ሰላም ነው ?? ሰለ ጤዛ ፊልም ያለህን አስተያየት ለመስማት ጥድፍ ብዮ የ ዋርካን አይን አይን ሳይ የውሀ ሽታ ሆነህ ቀረህ........ :roll: :roll: :roll:
በርድ
እንዴ ነሽ? ባያሌው....
ጠፋ ብልም ስላንቺ ሳልጠይቅ ውዬ አላውቅም :lol: ሾተልም ጠይቀው, በህልሜ አይቻታላሁ ደህና ነች...አታስብ ብሎኝ ነበር.......
ድህንነትሽ ስለማውቅ ተረጋግቼ ነው የምገኝ።
እናንተ ውሃ ከምትቀዱበት ምንጭ ውሃ የሚጠጣ፣ ነጋ ማዝለቂያ የተባለ ታዋቂ የብእር ሰው መኖሩን አውርቼሽ ነበር። ታስታውሻለሽ?
እስኪ እሱን የሚያውቅ ሰው፣ የሚያውቅ ሰው... ጉዋደኛ ታውቂ እንደሆን አጠያዪቂልኝ። አባክሽ!!!!
በተረፈ ጤዛ ከፌስቲቫል ትርኢት ወደ መደበኛው ሲንሲማ አዳራሽ ገብቶ በህዝብ መታየት ከጀመረ በሁዋላ እንወያይበታለን። መገምገምና መወዳደር ያለበት ግን ፊልም ከማይሰራባቸው ከአፍሪካ አገሮች ፊልም ጋር ነው ብዬ አላምንም። ተቀማጭነቱ ዩኤስ የሆነ፣ ሆሊውድን በልበ ሙሉነት የሚተች፣ ታዋቂ የፊልም ምሁርና መምህር የሰራውን ፊልም አፍሪካ ውስጥ በሚኖሩ ፣ በአፍሪካ በጀት ከሚንቀሳቀሱ ከነሰራዊት ፍቅሬና ቴዎድሮስ ካሳሁን ጋር ማወዳድር አይመችም።
የፊልሙ ታሪክና መቸት ኢትዮጵያ ይሁን እንጂ፣ ከአፍሪካ ፊልሞች ጋር መፈረጅ ነበረበት ትያለሽ, ማለት "ድመትን ከድመቶች, ነብርን ደሞ ከነብሮች .........."?