ሀያሲያን በእንድ የኪነጥበብ ስራ ላይ የሚስነዝሩት አሉታዊ አስተያየት እውን በገበያቸው ላይ አሉታዊ ተስእኖ ያመጣል?
ይህን ጥያቄ ሰራዊት ፍቅሬ ወደ አገርቤት ሳይመለስ ቢመልስልን ጥሩ ነበር። አይመስልሽም ... በርድ? ትላንት ኦባማን አየሽው? የአለም ፕሬዝድንት አይመስልም!!!!!
ወደ ጥያቄው ..........
የኔ መለስ ግን አዎ ያመጣል እና አይ አያመጣም ነው። እንደ ሂሱ አቀራረብና እንደ መልስ አሰጣጡ ነው የሚሆነው ለማለት ነው።
ሂሱ በቅንነት የቀረበ ሙያዊ አስተያየት ከሆነ አንባቢ ልዩ ትኩርት ሰጥቶ ያነብበዋል። የተጠቆሙትን ጠንካራና ደካማ ነጥቦች ላይ ምልከት ያደርግና የራሱን ፍርድ ከመስጠቱ በፊት ኪነ ጥበብኛው የሚስጠውን መለስ ይጠብቃል። የጠበቡ ስራ የገበያ እጣ-ፈንታ እንግዲ አሁን ይመስለኛል። መልስ አሰጣጥ ላይ።
መልሱ፣
እስኪ አንተ ሰርተህ አሳየን!
ድሮም አበሻ ሲባል ሰው የሰራውን ከማጣጣል በቀር ምን ያውቃል!!1
ምቀኝነት ነው! ቅናት ነው! ተንኮል ነው!
የሚል ከሆነ አንባቢው ምልከት ባደረገባቸው ነጥቦች ላይ ተመርኩዞ የራሱን ፍርድ ወዲያው ይሰጣል። የሀያሲው አስተያየት በብዛት ነቀፋ ከሆነ፣ ሰው የጥበብ ስራውን ለማየት የሚኖርው ጉግት ሊቀዘቅዝ ይችላል።
በእንጻሩ ኪነጥበበኛው ለተሰጠው በጎ አስተያየት አመስግኖ አለአግባብ የተነቀፈበት ላይ ሙያውዊ መልስ ቢሰጥበት፣ ሀያሲው ማስተዋል የተሳነውን ነጥቦች አንድባንድ ዘርዝሮ ቢሞግት፣ ያመንባቸውን ጉድለቶች ወደፊት እንደሚያሻሽል ቢገልጽ፣ ተጨማሪ አስተያይት ለመቀበልና መልስም ለመስጠት እሁንም ፈቃደኛ መሆኑ ቢገልጽ አንባቢው የራሱን ፍርድ ለመስጠት አይቸኩይልም። ማናቸው ነው ልክ? እስኪ እኔ ራሴ ሊየው የሚል አቅዋም ይይዛል። ካየም በሁዋላ ከሌላው የጠበቡ አፍቃሪ ጋር ይወያይበታል፣ ይከራከርበታል።
አንዲህ የመወያያ ርእስ የሆን የጥበብ ስራ፣ መጽሀፍ ከሆን ተደጋግሞ ይነበባል። ፊልም፣ ትያትር ወይም ስእል ከሆነ ደግሞ ተደጋግሞ ይታያል። እንደ ሬክላም ሙዳሴ ብቻ ሳይሆን ድክመትንም የሚጠቁም ሂስ ከማስታወቂያ የበለጠ ህዝብን ይስባል። በተለይ ጠንካራ ቃላት የሚለዋወጡበት ሂስና መላሽ ህዝብን ወደ ጥበቡ መድረክ የመሳብ ሀይል አለው ብዩ አምናለሁ።
በዚህ ክፍል በአንዳንድ ፊልሞች ላይ ሂስ ተሰንዝሮአል። መልስ የሰጠ ሰው ግን እስካሁን የለም። መልስ ቢሰጡና ትንሽ ክርክር ቢነሳ አንባቢው ፊልሙን ደግሞ ማየት እንደሚፈልግ አልጠራጠርም። ሂስና ምላሹ ብዙ ሰው እሚደርስበት ስፊ መድረክ ላይ ሲሆን ሚዘን የሚሰብር ገበያ ይቀሰቀሳል ብዬ ነው የማምነው፣ እንጂ እንደሚፈራው ኪሰራ የሚጋብዝ አይመስለኝ።