early_bird ! wrote:....... የአክተሩ አተዋወን ግን ብዙ ፊልሞች ለይም አይቼዋለሁ በግሌ በጣም ይደላኛል.............. :)
በርድ፣
ሰለሞን ቦጋለ፣ ብዙ የአማርኛ ፊልሞች ውስጥ ሲሰራ አይቼዋለሁ። ቀደም ሲል በሬዲዮ ትያትር ተሳትፎው ስሙን ያስጠራ ተዋኒ ነው። ከሱና ከቤተሰቦቹ ጋር የቀረበ ትውውቅ አለኝ። ከቀድሞው ትዳሩ አንድ ሴት ልጅ አለችው። የልጁ እናት ራስዋ ገነት ነው ስምዋ። በ1997 ታህሳስ በቁልቢ በዓል ምክንያት ድሬዳዋ ሄጄ በነበርኩብት ወቅት ሰለሞንን በዝና የሚያውቁት የድሬ ወጣቶች ሲከቡት አይቼ
''ታዋቂነት እንዴት ነው፣ ምን ይሰማሀል?'' ብዬ ጠየቅሁት።
''በባዶ ኪስ ምን ዋጋ አለው።'' በማለት ነበር የመለሰልኝ። በወቅቱ የተወጋ ልብ የተሰኘው ሰለሞን በሁለተኝነት የኮከበበት ፊልም ክፍለሀገሩ ውስጥ ይታይ ነበር። ተዋኒነት እንደ ሌላው የጥበብ ዘርፍ ሁሉ በእሁኑ ጊዜ ገንዘብ የሚያስገኝ ሙያ አይመስለኝም።
ይሁን እንጂ ለሙያው ካላቸው ፍቅር ብዙ ወጣቶች የሚመኙት ስራ ሆኖአል። ሰለሞን ራሱ ዩንቨርስቲ ውስት የሚሰጥ የፊልም ስራ ኮርስ እየወሰደ እንደነበር ነግሮኛል።
የፊልም ታሪክ እንድም በገጽባህሪ የሚዘወር ሊሆን ይችላል፣ ሁለትም በትልም። character driven vs plot driven ይሉታል ጠበብቶቹ። 11ኛው ሰአት በዋናው ገጽባህሪ ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ በዋናው ገጽባህሪ የሚዘወር ታሪክ ነው። ስለሆነም ዋናው ገጽባህሪ ላይ ስራ መሰራት አለበት። ገጽባህሪውን ተመልካቸ እንድያዝንለት፣ እንዲወደውና እንዲመሳሰለው መደረግ አለበት።
ሰለሞን ኤፍሬም የሚባል ስምና የፎቶግራፍ አንሽነት ስራ ከመሰተቱ በስተቀር ባህሪው ብዙ አይታወቅም። የቅድመ ትረካ ህይወቱ የለውም። ቤተሰብ? ጉዋደኛ? የሚታወቅ ነገር የለም። የትምህርት ደረጃውን፣ የስራ ልምዱን አናውቅም። የእረፍት ጊዜው እንዴት ነው የሚያሰልፈው? ኖንቼ አስተሳሰቡን፣ እምነቱን፣ ፖለቲካዊ አቅዋሙን የሚገልጹ ነገሮች አልሰማንም፣ ኣላየንም።
እነዚህ ነገሮች በቀጥታ ይሁን በተዘወዋሪ፣ ሁሉም ባይሆኑ በከፊል ለተመልካች የሚገለጡበት ሁኔታ ቢታሰብበት ተመልካች ገጽባህሪውን የማቅረብና ለሱም የመወገን ስሜት ያድርበታል። ገጸባህሪውን ስናውቀው፣ ስንወደው ነው ቁጭ ብለን ፊልም እንድናይ የምንሆነው።
ተመልከች ኤፍሬምን እንደ ገጸባህሪ እንዲያዝንለት ወይም እንዲወደው የሚያስችል ደራሲው ምን የተጠበበው ነገር አለ? ዋናው ገጸባህሪ መሆን ብቻ ኮ አይበቃም። ገጸባህሪው እንድናዝንለት ራሱ ሲያዝን፣ እንዲወደድ ራሱ ሲወድ ማየት አለብን። ገነትን መውደዱስ? እንዳትይኝ በርድ። ገነት ወጣት ነች። ዘመናዊ ነች፣ ውብ ነች ማንም ሊወዳት ይችላል። እስዋን መውደድ ልዩ ትኩርት አያሰጠውም። በዚህ ላይ ገነትን ለማግኘት ምንም ውጣ ውረድ አልነበረበትም። ቢኖርበት ኖሮ አዎ ትንሽ አዘኔታ (audience sympathy) ያገኝ ነበር።
ይልቅ ኤፍሬም ከሀመር ብሄሬስብ ፎቶግራፍ ያንሳትን ውቢቱን ልጅ ቢያፈቅር ኖሮ እኔን ይስበኝ ነበር። የባህል መካልሉን የጣሰ ፍቅር .... ዋው! በልብስ ለባሽና በማይለብሱ፣ በዘመናዊነትና በተፈትሮዋዊነት፣ መሀል ያለውን ቅራኔ ሊያሸንፉ ሲታገሉ በመሀል ሀመራዊትዋ ብትሞት አብሪያት በስሜት እሞት ነበር። ደራሲው እዛ ድረስ ሄዶ ይህን አማራጭ ለምን እንዳላስበበት ይገርመኛል።
በርድ፣ በአጠቃላይ ማለት የምፈልገው ሰለሞን እንደ ተዋኒ ጎበዝ ነው። የተሰጠውን ባህሪ ሆኖ ጥሩ ይሰራል። ችግሩ ያለው ደራሲው ጋር ነው። ደረሲው ኤፍሬምን ከተመልካች ጋር የሚያስተሳስረው ባህሪያት አላላበሰውም። አስቢው ሰው ሲገደል አይቶ ዝም ከሚል ድንጋይ ጋር ምን ጉዳይ ይኖረኛል። አቦ ተይኝ!!!