መልካም የልደት በአል ይሁንልኽ አባታችን ማንዴላ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

መልካም የልደት በአል ይሁንልኽ አባታችን ማንዴላ

Postby ሾተል » Fri Jul 18, 2008 11:12 am

ክቡር ታላቁ ኒልሰን ማንዴላ መልካም ልደት እመኝልዎታለሁ::አምላክ ከዛ የእስር ረመጥ አውጥቶ በዛሬዋ እለት 90 የልደት በአልዎን አምላክ እንድታከብሩ ስላደረገዎ አምላክን ከልቤ አመሰግንልዎታለሁ::አሁንም ሌላ 100 ዘጠና አመቶችን በህይወት አኑሮ ልደትዎን ያስከብርዎ ዘንድ አምላክን እለምንልዎታለሁ::

በህይወት እያለሁ አንድ ታላቅ የነጻነትና ፍትህ ታጋይ ጋ በህይወት ኖሮ አብሬ ከዚች ምድር ጋር በመኖሬ ደስተኛ ነኝ::ከማንዴላ ብዙ ተምሬያለሁ...ተግስትን,ለተነሱለት አላማ መጽናትን ወዘተ....ማንዴላ የትእግስት ምሳሌ ነው...የነጻነት,,,የትግል አባትና ምሳሌ ነው....ማንዴላ ሁሉንም ነው::ማንዴላ አንድነት ነው....ማንዴላ በብቀላ አያምንም....ማንዴላ ይቅርባይነትን ያምላክ ፈቃድን የጠበቀ ታላቅ አስተማሪና ምሳሌ አባት ነው::ማንዴላ ሁሉንም ነው::ጀግናው ማንዴላ...

መልካም ልደት ለክቡር የነጻነት አባት ኔልሰን ማንዴላ ይሁን::

አሜን

ሾተል...........የማንዴላ ልጅ
Last edited by ሾተል on Sun Jul 18, 2010 8:31 am, edited 6 times in total.
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jul 18, 2008 11:31 am

Image
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jul 18, 2008 11:36 am

Image
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jul 18, 2008 3:14 pm

ኔልሰን ማንዴላ

ኔልሰን ማንዴላ በትራንስካይ ክፍለ ሀገር በምትገኘው ኡምታታ ከተማ አካባቢ ሀምሌ 18 ቀን 1918 አ.ም ተወለደ::አባትየው የጎሳ ባላባት ሲሆኑ አራት ሚስቶች ነበሯቸው::ማንዴላ ከሶስተኛው ሚስታቸው የተወለደ ነው::ያወጡለት ስም ሮህሊላህላ ሲሆንበቦሳ ቋንቋ ረባሽ,በጥባጭ (trouble maker) የሚል ነበር::ወጣቱ ማንደላ ኡምታታ ከተማ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማረ በሁዋላ ሚሽን ኮሌጅ ለመማር ወደ ፎርት ሄር ተጉዋዘ::በፎርት ሄር ኮሌጅ ከሌሎች አካባቢ ከመጡ ጥቁርና ነጭ ተማሪዎች ጋር በመተዋወቅ ለወደፊት ህይወቱ መሰረት የጣሉለት ሁኔታዎችን አገኘ::ፎርት ሄር ኮሌጅን እንዳጠናቀቀ ወደ ጆሀንስበርግ ከተማ በሚገኘው ዊትወትር ስትራንድ ዩኒቨርስቲ በመመዝገብ የህግ ትምህርቱን በ1943 አ.ም ቀጠለ::በወቅቱ ነጭና ጥቁር አብረው እንዲማሩ የሚፈቅዱት የእንግሊዞች ዩኒቨርስቲዎች ብቻ ስለነበሩ ብዙ ነጭ ጉዋደኞችን ማፍራት ቻለ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jul 18, 2008 3:28 pm

ማንዴላ ህግ በመማር ላይ በነበረበት ወቅት ከነጮች ያልተጻፉ ህጎች አንዱ "ሴቶችና አፍሪካውያን የህግ ባለሙያ ጠበቃና ዳኛ መሆን አይችሉም" የሚል ነበር::ማንዴላ ይህን ጭፍን የነጮች የበላይነት ጽንሰ ሀሳብ በመዋጋት የህግ ዲግሪውን አገኘ::ህግ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት ከዋልተር ሲሲሉ ጋር ተዋወቀ::ዋልተር የANC መሪዎች አንዱ ሲሆን የሚኖረው ከጆሀንስበርግ ወጣ ብላ በምትገኘው በኦርላንዶ ከተማ ነበር::ዋልተር ባለቤቱን አልበርቲናን ሲያገባ በሰርጉ እለት የተገኙት የANC መሪ ዶክተር ዞማ ለሙሽራይቱ "ያገባሽው ሰው ከዚህ በፊት ያገባ ሰው ነው::ያገባውም ፖለቲካ ነው" በማለት አስደንግጠዋታል::የ ANC ታጋዮች በህቡእ የሚገናኙትና የሚወያዩት ኦርላንዶ በሚገኘው የዋልተር ሲሲሉ ቤት ውስጥ ሲሆን እስከ እኩለ ለሊት ድረስ እየሰሩ ያመሻሉ::ስለሆነም ማንዴላ የዋልተር ሲስሉ ቤት የሁልጊዜ መገኛው ሆነ::የዋልተር ሚስት አልበርቲና ጆሀንስበርግ ከተማ በሚገኘው አጠቃላይ ሆስፒታል በነርስነት ከዘመዱዋ ከኤቪሊን ጋር ትሰለጥን ነበር::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jul 18, 2008 3:33 pm

በእረፍት ቀናት ከነዋልተር ሲሲሉ ቤት አልበርቲና ጋር የምትመጣው ኮረዳ ኤቪሊን ከቤተኛው ከኔልሰን ማንዴላ ጋር በመተዋወቅ ፍቅርን መሰረቱ::ከጥቂት ጊዜ በሁዋላም ተጋብተው ልጆች ወለዱ::

በ 1947 አ.ም ማንዴላ የትራንስካይ ANC የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆኖ በመመረጥ የትግሉን ደረጃ አሳደገ::በ 1948አ.ም በተደረገው ምርጫ ስልጣን ላይ የወጣው የናሺናሊስት ፓርቲ የወሰዳቸው ጨቁዋኝ እርምጃዎች አፍሪካውያን የመረረ ትግል እንዲያደርጉ ገፋፋቸው::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Jul 18, 2008 3:41 pm

ANC አዲስ የትግል አቅጣጫ እንዲቀይስ ምክንያት ሆነው::ዋልተር ሲሲሉ አልበርት ሶቡክዌ,ኦሊቨር ታምቦ,ኔልሰን ማንዴላና ሌሎች የ ANC መሪዎች ነበሩ::ከነዚህ አንዱ የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶክተር ዞማ ሆነ::ስለሆነም ድርጅቱ አመራሩን ከነዚህ ሀይሎች በማጥራት እንቅስቃሴውን አፋፋመ::

ማንዴላ በዚህ ትግል ምክንያት ለቤተሰቡ የሚሰጠው ትኩረትና ጊዜ እየተጣበበ በመምጣቱ ከትዳር አለም ውጭ ሆነ::በትግሉ ወቅት ANC የወጣት ክንፍ እንዳለው ሁሉ የሴት ክንፍም ነበረው::በ ANC የሴት ክንፍ ውስጥ ከሚታገሉ ወጣት ሴቶች አንዱዋ ማድኪዜላ ዊንፍሬድ (ዊኒ) ነበረች::ማንዴላና ዊኒ በዚህ መስመር ተዋውቀው በ 1958 አ.ም ትዳር መሰረቱ::ማንዴላ በከፍተኛ የአገር ክህደት ወንጀል ተከሶና የእድመ ልክ እስራት ተፈርዶበት በ1964 አ.ም ሮቢን ደሴት እስር ቤት ገባ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby Superego » Fri Jul 18, 2008 3:59 pm

"ወዳጄ" ሾተል እንድምን አልህ? ደህን ሰንብትሀል?

የኔልሰን ማንዴላ 90ኛ የልደት ባአላቸውን በማስምልከት እዚህ ጎራ ማለትህ ጥሩ አድርገሀል:: አንተ እንዳልከው ከኔልሰን ማንዴላ ህይወት ብዙ እንማራለን:: ለመማር ዝግጁ ከሆን ማለቴ ነው::

Long Walk To Freedom የተሰኘው በኔልሰን ማንዴላ የተጻፈው የህይወት ታርኩን (ታሪካቸውን) የሚያትት መጽህፍን የሚያክል ታላቅ autobiography ሳንብ የተሰማኝ ስሜት ጥልቅ ነብር:: ወደአማርኛ ተትርጉሞ ለሀግሬ ጎበዝ ኢንዲያነበው ቢደረግ እንዴት ድንቅ ነግር ይሆን? እስቲ ከቻልክ ጎብዝበት::

በተርፈ መልካሙናን ትምህርታዊ ጭዋታህን ግፋበት::

መልካም 90ኛ የልደት በአል ለኔልሰን ማንዴላ::

አክባሪህ
Superego
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 149
Joined: Fri Aug 26, 2005 11:37 pm
Location: ethiopia

Postby Superego » Fri Jul 18, 2008 4:00 pm

"ወዳጄ" ሾተል እንድምን አልህ? ደህን ሰንብትሀል?

የኔልሰን ማንዴላ 90ኛ የልደት ባአላቸውን በማስምልከት እዚህ ጎራ ማለትህ ጥሩ አድርገሀል:: አንተ እንዳልከው ከኔልሰን ማንዴላ ህይወት ብዙ እንማራለን:: ለመማር ዝግጁ ከሆን ማለቴ ነው::

Long Walk To Freedom የተሰኘው በኔልሰን ማንዴላ የተጻፈው የህይወት ታርኩን (ታሪካቸውን) የሚያትት መጽህፍን የሚያክል ታላቅ autobiography ሳንብ የተሰማኝ ስሜት ጥልቅ ነብር:: ወደአማርኛ ተትርጉሞ ለሀግሬ ጎበዝ ኢንዲያነበው ቢደረግ እንዴት ድንቅ ነግር ይሆን? እስቲ ከቻልክ ጎብዝበት::

በተርፈ መልካሙናን ትምህርታዊ ጭዋታህን ግፋበት::

መልካም 90ኛ የልደት በአል ለኔልሰን ማንዴላ::

አክባሪህ
Superego
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 149
Joined: Fri Aug 26, 2005 11:37 pm
Location: ethiopia

Postby ሾተል » Sat Jul 19, 2008 5:45 pm

ዊኒ ማዲኪዜላ ማንዴላ


ማዲኪዜላ ዊልፍሬድ (ዊኒ) በ 1934 አ.ም በአፍሪካዊያን ደረጃ ሀብታም ከሚባሉ ቤተሰቦች ተወለደች::ቆንጆና ተግባቢዋ ዊኒ ከትምህርት ቤት ጀምሮ የነጮችን የበላይነት ሁኔታ ከመቃወሙዋም በላይ ተደራጅቶ የመታገል ፍላጎትዋ ከፍተኛ ነበር:ANC የሴቶች ማህበር ሲመሰረት አባል በመሆን የፓርቲውን ተልእኮ በሴቶች ውስጥ ለማሳካት ጥረት ከሚያደርጉት ሴት ታጋዮች አንዱዋ ሆነች::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jul 19, 2008 5:51 pm

ስለሆነም ሴቶችን በማንቃትና በማደራጀት ተግባር ላይ በመሳተፍ ላይ እንዳለች ከእውቁ አፍሪካዊ የህግ ባለሙያ የ ኤ ኤን ሲ ታጋይ ከኔልሰን ማንደላ ጋር ተዋወቀች::

ቆንጆና ቀልጣፋዋ ዊኒ ባጭር ጊዜ ውስጥ የማንዴላን ልብ በፍቅር ተቆጣጠረችና በህጋዊ መንገድ ባልና ሚስት ሆኑ::

ሁለቱ ታጋዮች ባንድነት በመኖር እየከፋ የመጣውን ጭቆናና ዘረኝነት በየፊናቸው ተዋጉ::ማንዴላ በሻሮቬል ከተማ እልቂት (67 ጥቁሮች የተገደሉበትንና በ 180 የቆሰሉበት) አመጽን አነሳስተኻል በመባል የእድመ ልክ እስራት ተፈርዶበት ሮበል ደሴት እስር ቤት በመግባቱ ዊኒ ብቸኝነት ቢሰማትም ትግሏን አጠናክራ ቀጠለች::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jul 19, 2008 5:56 pm

ዊኒ በምትሰጠው የትግል አመራር የተበሳጨው የነጮች ዘረኛ መንግስት ከ 1969-1970አ.ም ለሁለት አመት በእስር ቤት ውስጥ እንድትማቅቅ አድርጎአታል::ከእስር ቤት እንደወጣችም ክትትሉ ቀጥሎ አላንቀሳቅስ ቢላትም በህቡእ በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኝ መሆንዋን የተረዳው ዘረኛው መንግስት የግዞት ፍርድ በመስጠት ገጠር ውስጥ ከህዝብ ተለይታ እንድትኖር ከ1977-1985 አ.ም ለ 8 አመታት እንድትጋዝ አድርጓል::

ዊኒ በ 1985 አ.ም ወደ ሶዌቶ በመመለስ የ ኤ ኤን ሲ የሴቶች ማህበር ፕሬዚደንት በመሆን ትግሉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱና የነጮች መንግስትም ጥንካሬ እየተፈረከከ በመምጣቱ የበኩልዋን አስተዋጾ አድርጋለች::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jul 19, 2008 6:05 pm

ከ 1988-1989 አ.ም ባለው ወቅት ዊኒ ባንድ ጥቁር ወጣት ግድያ ምክንያት ተከሳ ፍርድ ቤት ቀረበች::ክሱ አንድ ወጣት ጥቁር በክህደት ተጠርጥሮ በዊኒ የግል ጠባቂዎች ከታፈነ በሁዋላ ቤትዋ ድረስ ተወስዶ ሰቆቃ ከተፈጸመበት በሁዋላ ተገሎዋል የሚል ነበር::ለዚህ ክስ ጠበቃ ሆኖ የቀረበው ሰው የ ኤ ኤን ሲ አባልና ማራኪ ሰው ነበር::በሁለት አመት የክርክር ጊዜ ውስጥ ማራኪው ጠበቃና ዊኒ በድብቅ ከባልና ሚስት ያላነሰ ግንኙነት ፈጠሩ::ይህ ግንኙነት በክሱ ነጻ ከሆነች በሁዋላ እንደቀጠለ ከአንድ አመት በሁዋላ የፖለቲካው አየር ተለወጠ::ያልታሰበና ያልተጠበቀ ነገር ተፈጸመ::የዘረኛው መንግስት ፕሬዚደንት ደ ክላርክ ማንዴላን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ፈቱ::በትኩስ ፍቅር ላይ የምትገኘው ዊኒ ለ 27 አመታት ፍቅርን ለተጠማው ታጋይ ባለቤቷ እንክብካቤና ፍቅርን መስጠት ተሳናት::ባሏን በሌላ ወንድ የተካችው ታጋይ ሴት ስላደረሰችባቸው የስነ ልቦና ጫና ሲገልጹ " ከእስር ቤት ከወጣሁና ቤቴ ከገባሁ ከጥቂት ቀናት በኋላ በቤቴ ውስጥ ራሴን የአለም ብቸኝነት ያጠቃውና የተገለለ ሰው አድርጌ ቆጠርኩ::በዚህ ድርጊትም እስር ቤትን እንድናፍቅ ተገደድኩ::" ብለዋል::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jul 19, 2008 9:22 pm

በ1990 አ.ም ከእስር የተፈቱት ማንዴላ ከባለቤታቸው ከዊኒ ጋር ትርጉም የሌለው ኑሮ እስከ 1992 አ.ም ድረስ ከኖሩ በሁዋላ ከባለቤታቸው ተለያይተው መኖር ጀመሩ::ሆኖም ህጋዊ ፍቺ የተፈጸመው በ 1996አ.ም ነበር::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jul 19, 2008 10:02 pm

ማንዴላ የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስና አዲሲቱ ደቡብ አፍሪካ

በ1989አ.ም ስልጣን ላይ የወጡት የደቡብ አፍሪካ ነጮች መንግስት ፕሬዚደንት ደ ክላርክ ለሁሉም የደቡብ አፍሪካ ህዝቦች የሚበጅ ሀሳብ ይዘው ቀረቡ::ይህ አዲሱ ሀሳብ ትግሉን እያጠናከረ ከመጣውና የታጠቀ ክንፍ መስርቶ ከሚፋለመው ኤ ኤን ሲ ጋር መደራደር ሆነ::

ሆኖም ለመደራደር የድርጅቱ መሪ ከእስር መልቀቅ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ኔልሰን ማንዴላ ተፈቱ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests