መልካም የልደት በአል ይሁንልኽ አባታችን ማንዴላ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሾተል » Wed Jul 23, 2008 10:37 pm

በ1834 የእንግሊዝ መንግስት የጠረፍና ባህር ዳርቻ አካባቢዎችን በመቆጣጠር በደቡብ አፍሪካ የበላይነቱንና ቅኝ ገዢነቱን አስታወቀ::ቀጥሎም የባሪያ ነጻነት በማወጅ 60,000 ባሪያዎችን ነጻ በማውጣቱ የተበሳጩት ቦይርስ (የሆላንድ ገበሬዎች)ከእንግሊዝ አገዛዝ ለመራቅ ሲሉ ወደ ሰሜን ምስራቅ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ ከአፍሪካውያን ጋር እየተዋጉና መሬት እያስለቀቁ ተጎአዙ::እነዚህ ቦይርስ ያደረጉት የመስፋፋትና አፍሪካዊያንን መሬት አልባ የማድረግ ታላቅ ጉዞ (Great trek) እንደተሳካ ሁለት ከእንግሊዝ መንግስት ነጻ የሆኑ አሬንጅ ፍሪ ስቴትና ትራንስቫል የሚባሉ ሪፖብሊኮችን መሰረቱ::በዚህ መሰረት በደቡብ አፍሪካ ዳርቻ አካባቢ የሚገኘው በእንግሊዝ መንግስት በቅኝ ግዛትነት የሚገዛው የናታል ግዛት ሲሆን በሁለተኛው በዳች ገበሬዎች የተቋቋሙት ሁለት ሪፖብሊኮች ናቸው::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sat Jul 18, 2009 10:23 am

መልካም የ 91 አመት የልደት በአል ለታጋዮቹ ቁንጮ ለኔልሰን ማንዴላ ክብርነታችን ይመኛል.....

አባታችን ማንዴላ ረጅም እድሜ ከጤንነት ጋር አምላክ እንዲያድልንን ስንመኝ ሀፕይ በርዝደይ ቱ ዩ ሀፕይ በርዝ ደይ ቱ ዩ ሀፕይ በርዝ ደይ ሀፕይ በርዝ ደይ ሀፕይ በርዝደይ ቶ ኔልሰን ማንዴላ እያልን በመዝፈን ነው::

ግምባርህ ላይ በፍቅርና ባክብሮት ከልቤ በመሆን ስሜሀለሁ

ሾተል......ሁሌም የሚኮራብህ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby admasradio » Sat Jul 18, 2009 1:40 pm

ሰላም ሰላም አድማጮች

ዛሬ የኔልሰን ማንዴላ የልደት ቀን መሆኑን ከዚህ ብሎግ ተረድታችሁዋል:: አድማስ ሬዲዮ ደግሞ የማንዴላን የልጅነት ህይወትና የ እስር ቤት ቆይታ በአማርኛ በሰፊው እናቀርብላች ሁዋለን::

አርቲስት አረጋኸኝ ወራሽም ሌላው እንግዳችን ነው::
አድማስ ሬዲዮ
The #1 Ethiopian infotainment radio in USA

Every Saturday from 2-6 pm (Eastern time) @1100AM(Atlanta) .... or LIVE at www.admasradio.info or LIVE from your cell phone (951) 262 4343 code 193902#
admasradio
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 169
Joined: Tue Mar 18, 2008 11:39 pm

Postby ሾተል » Thu Feb 11, 2010 6:13 pm

http://www.youtube.com/watch?v=GzUB2Vag ... re=related

የዛሬ አስር አመት ለተፈታው የነጻነት ታጋይ ለኔልሰን ማንዴላ ይሁንልኝ::

ሾተል ነን....ጀግናን የነጻነት ታጋይን ከልቡ የሚወድና የሚያከብር
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: የኔልሰን ማንዴላ 91ንደኛ አመትቱን አከበረ

Postby ይታየዋል » Fri Feb 12, 2010 1:15 pm

ሾተል wrote:ክቡር ታላቁ ኒልሰን ማንዴላ መልካም ልደት እመኝልዎታለሁ::አምላክ ከዛ የእስር ረመጥ አውጥቶ በዛሬዋ እለት 90 የልደት በአልዎን አምላክ እንድታከብሩ ስላደረገዎ አምላክን ከልቤ አመሰግንልዎታለሁ::አሁንም ሌላ 100 ዘጠና አመቶችን በህይወት አኑሮ ልደትዎን ያስከብርዎ ዘንድ አምላክን እለምንልዎታለሁ::


በህይወት እያለሁ አንድ ታላቅ የነጻነትና ፍትህ ታጋይ ጋ በህይወት ኖሮ አብሬ ከዚች ምድር ጋር በመኖሬ ደስተኛ ነኝ::ከማንዴላ ብዙ ተምሬያለሁ...ተግስትን,ለተነሱለት አላማ መጽናትን ወዘተ....ማንዴላ የትእግስት ምሳሌ ነው...የነጻነት,,,የትግል አባትና ምሳሌ ነው....ማንዴላ ሁሉንም ነው::ማንዴላ አንድነት ነው....ማንዴላ በብቀላ አያምንም....ማንዴላ ይቅርባይነትን ያምላክ ፈቃድን የጠበቀ ታላቅ አስተማሪና ምሳሌ አባት ነው::ማንዴላ ሁሉንም ነው::ጀግናው ማንዴላ...

መልካም ልደት ለክቡር የነጻነት አባት ኔልሰን ማንዴላ ይሁን::

አሜን

ሾተል...........የማንዴላ ልጅ
እንዲያው ትንሽ አታፍርም በአንተ አይነት ውሻ አፍና የወያኔ ቡችላ ታላቁ እና ነጻነትን ለጥቁር ህዝብ ያመጡት
ክቡር ኔልሰን ማንዴላ ሲጠሩ? ትንሽ አይሰቀጥጥህም እንደደሀና ሰው ከከለሰ ዜማዊ ባሪያዎች እና ፍርፍር ለቃሚዎች ጋር ስለታላቁ የነጻነት ሰው ስትደሰኩር?
ውሻ መጀመሪያ ሂድና ነጻናት የሚለውን ቃል ምን እንደሆነ አንብብና ተረዳ አንተ ግን ለድራኩላው እና ስለአፍሪካው ሞሶሎኒው ስለሂትለር አምላክህም ስለመለሰ ሸናዊት አውራ? :oops: :oops: :oops: :oops: :oops: :oops: :oops: :oops: :oops: :oops:
ይታየዋል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 429
Joined: Fri Aug 03, 2007 3:54 am

Postby ስሙ ይናገር » Fri Feb 12, 2010 8:48 pm

ሾተል wrote:http://www.youtube.com/watch?v=GzUB2Vag8UI&feature=related

የዛሬ አስር አመት ለተፈታው የነጻነት ታጋይ ለኔልሰን ማንዴላ ይሁንልኝ::

ሾተል ነን....ጀግናን የነጻነት ታጋይን ከልቡ የሚወድና የሚያከብር


ሾተል ስላስነበብከን የማንዴላ ታሪክ አመሰግናለሁ ምንም እንኳ ታሪኩን ብናውቅም ደጋግመን ብንሰማው የማይሰለቸን ታሪክ ነው ያለው ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ማንዴላን እንዴት አድርገህ ነው ከመለስ ጋር የምታስታርቀው?? መለስን እንደምትደግፍ ስለማውቅ ነው ከምሬ ነው ሾተል ሌላው የዚህ ሰው ታሪክ ከብርቲካን ሚደቅሳ ጋር የሚመሳሰል ነው የሚመሳሰሉትም
ሀ. ሁለቱም የዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው
ለ. ሁለቱም ያጠኑት ህግ ትምህርትን ነው
ሐ. ሁለቱም የነጻነት ታጋዮች ናቸው
መ. በሁለቱም ላይ የእድሜ ልክ ፍርድ ነው የተሰጠው አይገርምም
God is Great
ስሙ ይናገር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1150
Joined: Fri Mar 14, 2008 4:46 pm

Postby ሾተል » Fri Feb 12, 2010 9:49 pm

ስሙ ይናገር
ሾተል ስላስነበብከን የማንዴላ ታሪክ አመሰግናለሁ ምንም እንኳ ታሪኩን ብናውቅም ደጋግመን ብንሰማው የማይሰለቸን ታሪክ ነው ያለው ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ማንዴላን እንዴት አድርገህ ነው ከመለስ ጋር የምታስታርቀው ?? መለስን እንደምትደግፍ ስለማውቅ ነው ከምሬ ነው ሾተል ሌላው የዚህ ሰው ታሪክ ከብርቲካን ሚደቅሳ ጋር የሚመሳሰል ነው የሚመሳሰሉትም
ሀ . ሁለቱም የዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው
ለ . ሁለቱም ያጠኑት ህግ ትምህርትን ነው
ሐ . ሁለቱም የነጻነት ታጋዮች ናቸው
መ . በሁለቱም ላይ የእድሜ ልክ ፍርድ ነው የተሰጠው አይገርምም


እናንተ ያዳምና የሄዋን ወይም የአርዲና የሉሲ ዝርያዎች እረ ባካችሁ ሰውን ታውቁት ይመስል አንጎላችሁን አሳምናችሁ ወደስኽተት አትሂዱ?
ስሙ ይናገር ደግሜ ደጋግሜ ብየዋለሁ አሁንም ይገባኽ ከሆነ ደግሜ እልሀለሁ::እኔ እውነትን እንጂ የምደግፈው የማንንም ድርጅትና ፖለቲከኛ አልደግፍም::እኔ ኢትዮዽያ ተወልጄ ኬንያ በልጅነቴ ተሰድጄ አፈር ከድሜ በልቼ ከወባ ጋር የሞት ድነት ትንቅንቅ አድርጌ እንደማንኛውም ኬንያ በረኻ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ተርቦ ተጠምቶ እንዳለና እንደነበረ እንዲሁም የሚወዳቸውን የስደት ወንድሞቹን በቀን ሁለትም አንድም እንደቀበረና እየቀበረ እንዳለ ስደተኛ ያንን ሁሉ መከራ አይቼ ከእግዚአብሄር ጋር በራሴ ላብና ጥረት ያለማንም ስፖንሰር አውሮፓ ገብቼ ለድጋሚ ስደት የበቃሁ አንድ ተራ የአፍሪካ ስደተኛ ነኝ::ታድያ አፈር ከድሜ ስበላ ወላ ወያኔ በለው መለስ ዜናዊ ወይም ቅንጅት በለው ብርሀኑ ነጋ ወይም ወላጆቼ ሆኑ አገሬ አልደረሰችልኝም::እንዲደርሱልኝም አልተማጸንኩም አልለመንኩምም::በራሴ ጥረት ነው አሁን ላለሁበት የተሻለ ስደት የበቃሁት::ስለዚህ ለማንም መሆንና ማንንም መደገፍ አያስፈልገኝም::እድሜ እከኬን ላራገፈልኝ የኦስትሪያ መንግስት::አክብሮ አንቀባሮ ስራዬን አመስግኖ ሙከራዬን አድንቆና በየለቱ ለጥረቴ ምስክርነት ሲሻው በጋዜጣ ሲሻው በመጽሄት ሲሻው በመጽሀፍ አውጥቶ ስታመም በነጻ አክሞ መብቴን ስፈልግ ጠይቄ እምቢ ብባል በድፍረት እንድቃወመው ፈቅዶ እያኖረኝ ነው::ስራ ሰጥቶኝ ደጎስ ያለ ገንዘብ እየከፈለኝ ይገኛል::

እና ማንም ዝተታም ሲንበራጨቅ እውነቱን ስለተነገረው ወያኔ ነኽ ኢሀዴግ ነኽ ምናምን ቢለኝ ግድ አይሰጠኝም::አይደለሁም ልሆንም አልችልምም::እኔ ከማንም ጋር ሳልነካካ ቀሪ ጊዜዬን በሰላም መኖር የምፈልግና በነጻነት እያሰብኩ መኖር የምፈልግ ሰው ነኝ::ሰው ነኝና የወደፊቱም መናገር ባልችልም ያሁኑ አቁዋሜ ግን ያ ነው::ግን በየትኛውም መድረክ እንደማንኛውም ሰው እድሉ ከተሰጠኝ በነጻነት አስቤ በነጻነት መጻፌንና መናገሬን አላቆምም::የትግራይን ህዝብ ሲሰድቡ ስላጋለጥኩ ክቡር ጀግና የኛ መኩሪያና መከበርያ አትሌቶቻችንን ሲሰድቡ ድምጻቸውን ቀድቼ ለህዝብ ስላሰማሁ እልክ ይዞዋቸው ወያኔ ወያኔ ቢሉ እንዴው እውነት መሰላችሁ?ብሆን ማናባቱ ይከለክለኛል::ወያኔ አይደለም የፈለኩትን ብሆን መብቴ መሰለኝ::ልቤንና ድፍረቴን አቁዋሜን እግዚአብሄር ሆናችሁ ልብና ኩላሊቴን ማወቅ አትችሉም እንጂ ብትችሉ ኖሮ ምንኛ ባወቃችሁኝ ነበር::እኔ ምቾት የማልፈልግ ሲምፕል ህይወት የምኖር ነኝ::የአለም ነገር እየገባኝ ያለ....በራሴ አንጎል ማሰብ የጀመርኩ በተጨበጨበበት ማጨብጨብ ያቆምኩ ነኝ::

ወያኔ ብሆን ኖሮ ይኼኔ በዚህ ብርድ ጊዜ እዚህ አታገኘኝም ነበር::ምን አልባት ሱሉልታ ተራራ ላይ በቀን ከ 40 እስከ 50 ኪሎሜትር ለመሸፈን ረጅም እርቀት ስሮጥ ታገኘኝ ነበር::ነገረ አለሙን ሁሉ ትቼ እሩጫ እሩጫ እሩጫ ስል ታየኝ ነበር::አንተና መሰሎችኽ ሰው ባልዋለበት ዋለ ከሚሉ ጋር ውዬ አታየኝም ነበር::ምን ያደርጋል ልቤ ትልቅ ሳለ የያዘኝ ይዞኝ ኦሎምፒክን በቲቪ እያየሁ አለሁ::እንደኔ በአብድ ጎኑ የተዘጋጋ እድል አዳሜ አያጋጥምሽ....እራሴን በፈለኩት አገኛለሁ ስል ባልፈለኩት አግኝቼው በእስቲ ይሁን ኑሮ እንደምኖር ማን ባወቀልኝ::ከምድረ አህያና ከብት ከማይበስልና ከማይሰለጥን ህዝብ ጋር መች መዋል ያስፈልገኝ ነበር.....የሚያስፈልገኝ መሮጥ መሮጥ መሮጥ...ያቺ ኦሎምፒክ የሚሉዋትን ነገር መንካት....ምን ያደርጋል ደርሼባት ነበር....ግን ህግ አልባ የሆነ አለም ውስጥ እየኖርን ስለሆነ ያንን መቀበል የግድ ነውና ይሁን እስቲ::አሁንም አልመሸም::

እና ልል የፈለኩት ወደዳችሁም ጠላችሁም እንኩዋን መለስ ዜናዊ ወይም ወያኔ አይደለም ቭየና ያለው የኢትዮዽያ ኤምባሲ አያውቀኝም::ነገር ግን ኢትዮዽያ ታውቀኛለች::እኔም እምዬ ኢትዮዽያን አውቃታለሁ::ኢትዮዽያ ደግሞ መሬትዋ ብቻ ሳይሆን ህዝቦችዋ ብሄር ብሄረሰቦችዋ ናቸው::ያ ማለት ከ 90 በላይ ያሉት ብሄሮችዋንና ቋንቋዎችዋን ይጨምራል....ታድያ ከብሄሮችዋ አንዱ ሲሰደብብኝ ሲንቋሸሽብኝ ያመኛል::በዛ ህመም የተነሳ እውነት ውስጥ ስለገባሁ እምሰለኝ ተቃዋሚ ተብዬ ምድረ ሰነቻ የክትፎ ቀን ጅሎች አይን ውስጥ ያስገባኝ::

ወንድ የሆንሽ ያልሆነ ቦታ ከታችሁ እራሳችሁን በቢሆን አለም ከምታስደስቱ የትግራይ ህዝብ ሲሰደብ ለምን ሰደባችሁ ብዬ የሰደባችሁበትን አውዲዮ ቀርጬ በማሰማቴ ይሄ አውዲዮ የኛ አይደለም ወይም እኛ አልተሳደብንም ብላችሁ ሞግቱኝ::ስትዋሹ ማስረጃ አምጡ ይሄ ይሄ ውሸት ነው ስላልኩኝ ያንን ትክክል ነው ስትሉ ሞግቱኝ....ግን አንዴ ወያኔ አንዴ ምናምን ብትሉኝ የምታመጡት ነገር አይኖርም::እንደፎከራችሁ ስታገኙን እንደምትገሉን እንዳቀዳችሁ ትኖራላችሁ::ምንም አላችሁኝ ምን እኔን አታቆሙኝም::

ለእውነት ስል የማደርገው ነገር በእግዚአብሄር ዘንድ ንጹህና ቅዱስ ስለሆነና ከየትም በኩል ምክርና ጥቅም አግኝቼ የማደርገው ስላልሆነ እግዚአብሄር ይጠብቀኛል....እንደገና ጠላቶቼ እኔ ደርስ ሲደርሱ እንድቀድማቸው ሀይልና ጉልበት ከጥበብ ጋር ይሰጠኛል::ወሬ ወይም ቱልቱላ አይደለም እየጻፍኩ ያለሁት::እንኩዋን እርስ በራሳችሁ ካልተደራጃችሁት አንድ ላይ ውላችሁ ዞር ስትሉ ከምትተማሙና ከምትመቀኛኙ ዘመነኛ ታጋይ አይደለም እግዚአብሄር በአቁዋም በሀይልና ጉልበት ከጥበብ ጋር ተደራጅተው ሲነድፉኝና ሲላቸው ኮማ ውስጥ ከተው ሲያሰቃዩኝ ከነበሩትም ቢጫ የበረኻ ወባዎች እግዚአብሄር ጠብቆኛል::

ስለዚህ ሾተል ወይም አምባቸው አባተ ደጀኔ የማንም አይደለም የማንም ሊሆን አይችልም::ግን የእውነትና የህሊናው ነው::

ጨረስኩ::

ሾተል ነን....የራሳችን የህሊናችንና የእግዚአብሄር አምላካችን ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Fri Feb 12, 2010 10:03 pm

ውይ ይቅርታ ይኸንን የት ሆኜ እንደጻፍኩት ሳልነግራችሁ ::ላፕቶፔን ይዤ ሽንት ቤት ሆኜ አይነምድር እየወጣሁ ሳለ ነው ::ወይም በሌላ አማርኛ ወገቤን እየሞከርኩ በነበረ ሰአት ነው ::አንዲት ጉዋደኛዬ የሴት ነገር ሆነና የተለያየ ሾፕ ላትገዛ ልትለካ ወስዳ ስታንገላታኝ ውላ እቤትዋ ወስዳ ሀይክላስ ምግብ አብልታ ሸኝታኝ አሁን ገና እቤቴ መግባቴ ነው ::እኔ ጋር ነው ያደረችው ::ጥሩ ጉዋደኛዬ ስትሆን የብድ አይደለችም ::እንደእህትና ወንድም የሚሉት አይነት ::በዚህ ብርድ ይታያችሁ ከቺኮች ጋር ወጥታችሁ አንዴ ባርኔጣ ሲለኩ እንደገና ሌላ ሱቅ ቀይረው አንዴ ቦላሌ ሲለኩ እንደገና ሌላ ሱቅ ሄደው አንዴ የጆሮ ጌጥ ሲለኩ ሲውሉና እናንተን አስከትለው በዚህ ብርድ ሲያፈጉ ቅር አይላቸውም ::አቤት የእቅዳቸው ብዛት ...አቤት ስመታዊነት ::ብዙዎቹ የሚሉዋቸውን አይሰሙም ታድያ በራሳቸው በተሳሳተ መንገድ ጭረው በሁዋላ ሉዘር ሲሆኑ መጥተው ያለቃቅሳሉ ::ጥሩነቱ የሰውን ልጅ ሰው ከተረዳው ጥሩ ስለሆነ ያ ክብርነታችንን ጠቅሞታል ::

ከ 1 ሰአት በሁዋላ ሀይ ክላስ ቦታ ሳንጭር አንቀርም ::እስቲ ከራሳችን ጋር እንደምንሄድና እንደማንሄድ እንሙዋገት ::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ፍሉሀ40 » Sun Feb 14, 2010 11:29 pm

የማንዴላን ታሪክ ብናውቀውም ባናውቀም ስሙን በማየቴ ገባሁ ነገሩ የወፌ ቆመች አይነት ነው ያደረከው አባባሌ ጥሩ ሄደህ እያለህ ዱቅ አረከው ወደ ልቁ አፍህ ስድብህን ምስህን ረጨህ አበለሻሽህው የፈለገ ቢሆን ቤቱን ለማክበር ዝም ብለህ መቀጥል ነበረብህ የዚህን ታላቅ ሰው ስም አጎደፍከው ለመሆኑ ከዛስ በሀላ የሚያነብ ኢትዮፕያዊ ይኖራል ብዮ አልገምትም እንደው ደከምክ መጀመሪያ ራስህን አጥዳ የሰውን አባትና እናት የሚሳደብ ሰው የራሱን ቤተሰብ የጠላ ነው:: ባለ ብዙ ስም መሆን አያዋጣም ዞሮ ዞሮ የተለመደ ቃል እኮ ነው የምታፈልቀው ባሻ, ቬኑስ, ጅብ, ው.ዘ.ተ. እስቲ ዋንስ ፎር ኦል ተለወጥ ዳ!!! እዚህ ዋርካ ውስጥ ሰው ያንተን ባለጌ አጠያፈ ቃላት ማየት ሰልችቶታል:: እኛ ባህላችንም አይደለም:: ደግሞ የእግዚሀርን ስም ማስቀመጥህ???? ጉድ እኮ ነው ጃል::
Never exaggerate your faults; your friends will attend to that.
Robert c.edward phd
ፍሉሀ40
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sat Jan 09, 2010 3:35 pm

Postby ሾተል » Mon Feb 15, 2010 12:48 am

ፍሉሀ40 wrote:የማንዴላን ታሪክ ብናውቀውም ባናውቀም ስሙን በማየቴ ገባሁ ነገሩ የወፌ ቆመች አይነት ነው ያደረከው አባባሌ ጥሩ ሄደህ እያለህ ዱቅ አረከው ወደ ልቁ አፍህ ስድብህን ምስህን ረጨህ አበለሻሽህው የፈለገ ቢሆን ቤቱን ለማክበር ዝም ብለህ መቀጥል ነበረብህ የዚህን ታላቅ ሰው ስም አጎደፍከው ለመሆኑ ከዛስ በሀላ የሚያነብ ኢትዮፕያዊ ይኖራል ብዮ አልገምትም እንደው ደከምክ መጀመሪያ ራስህን አጥዳ የሰውን አባትና እናት የሚሳደብ ሰው የራሱን ቤተሰብ የጠላ ነው:: ባለ ብዙ ስም መሆን አያዋጣም ዞሮ ዞሮ የተለመደ ቃል እኮ ነው የምታፈልቀው ባሻ, ቬኑስ, ጅብ, ው.ዘ.ተ. እስቲ ዋንስ ፎር ኦል ተለወጥ ዳ!!! እዚህ ዋርካ ውስጥ ሰው ያንተን ባለጌ አጠያፈ ቃላት ማየት ሰልችቶታል:: እኛ ባህላችንም አይደለም:: ደግሞ የእግዚሀርን ስም ማስቀመጥህ???? ጉድ እኮ ነው ጃል::


ፍሉሀ40....በመጀመርያ በአሁኑ ሰአት 7695 ጊዜ ይኼ ክፍል ተከፍቷል::ከዚህ በሁዋላ ላንተ የተዋቡ ሳር መሰል ግጦሾችን ሳበላኽ ይኼ ክፍል ከ 7695 በላይ ሊከፈት ካልቻለ እኔ ከዋርካ ልታገድ....እንደገና እንዳንተ ያለን ንገሩኝ ባይ ስለተናገርኩ ማንዴላ ክብሩን ካጣ እስኪ እንይና እናትኽን ፍል ውሀ ውስጥ ዘፍዝፌ ላንተ ላስነጫት::ታድያ እናትህን ስትነጫት ፍል ውሀው ትን ብሎኽ እላይዋ ላይ አስታውከኽ ሞተኽባት ለቅሶ ትቀመጥ...አመሰግናለሁ

ሾተል ነን.....ንገሩን ያሉትን እንነግራቸዋለን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Sun Jul 18, 2010 8:35 am

የነጻነት አባታችን የኔልሰን ማንዴላ 92ተኛ የልደት በአል ዛሬ በመላው አለም ተከብሮ ይውላል::

አምላክ ሆይ ለኔልሰን ማንዴላ እድሜና ጤና ስለሰጠኸው እናመሰግንሀለን::

አባታችን ኔልሰን ማንዴላ እንኩዋን ለ 92 አመት የልደት በአልኽ አደረሰኽ::

ሾተል ነን....ሀፒ በርዝ ደይ ቱ ዩ ማንዴላ
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby agrani » Sun Jul 18, 2010 6:33 pm

የነጻነት አባታችን መልካም ልደት
agrani
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 116
Joined: Wed Mar 01, 2006 10:32 am

Postby ማሉሜ » Sun Jul 18, 2010 9:04 pm

S.A ሲታገሉ ሁሉም አፍሪካዊ አብሩአቸው ነበር ዛሬግን ያን የረሱት ይመስላል...ለማንኛውም
http://www.news24.com/SouthAfrica/News/ ... p-20100718

ቸር እንሰንብት!!
ማሉሜ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 19
Joined: Thu Jan 28, 2010 10:23 am
Location: ZULU LAND

Postby ሾተል » Sun Jul 18, 2010 9:19 pm

ማሉሜ wrote:S.A ሲታገሉ ሁሉም አፍሪካዊ አብሩአቸው ነበር ዛሬግን ያን የረሱት ይመስላል...ለማንኛውም
http://www.news24.com/SouthAfrica/News/ ... p-20100718

ቸር እንሰንብት!!


በጣም የሚያሳዝን ዜና.....የሚገርመው የአለም ዋንጫው ይጠናቀቅ እንጂ ምድረ ስደተኛና የውጭ አገር ሰዎችን ከደቡብ አፍሪካ ምድር እናጠፋለን ብለው ዝተው ነበር....ይኼው ጀመሩ...ቃላቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ቀደሱ...

የሚገርመኝ የስደተኞች ኮሚሽነር ዛቻውንና ስደተኞቹን ችላ ማለቱ ነው...

እንግዲህ ለወንድም እህቶቻችን መጸለይና የሚቻል ከሆነ ለአለም ህዝብ መጮኽ ነው

የሞቱትን ነፍስ ይማር

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሾተል » Mon Jul 18, 2011 6:00 pm

መልካም ልደት ለአባታችን ኔልሰን ማንዴላ ይሁን::ረጅም እድሜ ከጤንነት ጋር ይስጥልን::


Image

ሾተል ነን....ሐፕይ በርዝ ደይ ቱ ማንዴላ::
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests