August 10, 2018
ጊዜው እንዴት ይሮጣል ዘመዶቼ፡ ዋርካ ላይ እንዴት ታይፕ እንደሚደረግ በመማር ላይ እገኛለሁ...ወይ ጊዜ፡፡ የድሮዋ ትርንጎ አሁን ያለመነጥር ንቅንቅ ባትልም ሰልጥና youtube ላይ መደናበር ጀምራለች፡፡ አቤት ስንት የሚሞነጫጨር ታሪክ አለ ዘንድሮ፡ የምንተነፍሰው አየር ላይ ሁሉ ፊደላት ሲንሳፈፉ ውለው ያድራሉ፡፡ ለማናቸውም እንኩዋን የዛሬ ሰው ያለን፡፡ ድሮ ለማውቃችሁ በፍቅር ለጥ ብዬ እጅ ነስቻለሁ፡፡
የምታውቁኝ ፖለቲካው ላይ የለሁበትም፡ ግና ደግሞ የአገር ጉዳይ ፖሊቲካ ከሆን ዘ>ንድሮ ማን የሌለበት አለ??? ይቺ የፈነጠቀች ብርሃን ሁላችንንም አሰከረችን እኮ፡ በየጎዳናው ላይ እስክስታ ወረድን...ዘመን ደጉ፡፡ እናማ የልቤን ብተነፍስ ብዬ ብእሬን ሞርጄ መሞነጫጨር ጀምሬያለሁ፡፡ ለዚህ ያደረሰን ፈጣሪያችን ከፍ ከፍ ይበል!!!
ህልም ወይስ እራእይ
https://www.youtube.com/watch?v=HhZliwP1mh4
ታለፈ ያ ዘመን
https://www.youtube.com/watch?v=expYoC70o_4
....................................."የዋርካ ውበት"....................................
ድሮ ለታ...አዎን ያኔ ወጣት ቢጤ ነኝ እያልኩ እፎክር በነበረበት ጊዜ "የፓልቶክ ውለታ" ብዬ እንድ ግጥም ፅፌ ነበረና ይህ አርእስት እሱን አስታወሰኝ:: አሁን ዋርካ ምን ውበት አላት ትሉኝ ይሆን? እንግዲህ እየሳበች የምታመጣን ወይ በውበትዋ ነው...አሊያም ሱስ የሚያስይዝ እዚም አላት::እኔ ውበትዋን መርጫለሁ:: እንደስማችንና እንደመልካችን መዥጎርጎርዋ የቀስተ ደመና ውበት ሰጥቶዋታል...ሁሌም አዲስ: ለአይን የማይታክት: ጥለውት ሲሄዱ ደግሞ የሚናፈቅ ውበት::
ዋርካ ላይ ሆድ ሲብሰኝ ተንፍሼባታለሁ...ፃፊ ፃፊ ሲለኝ ጭሬባታለሁ...ተምሬባታለሁ....በድንቅ ጸሀፊዎች ተደምሜባታለሁ...ከፍቶኝ ጎብኝቻት አስቃ ሸኝታኛለች:: ሁሉን አሙዋልቶ ሰጥቶዋታል ለማለት ባልደፍርም መርጦ የማንበብ መብታችን በጣም ደስ ይለኛል:: ታዲያ መርጦ የማንበብ ስል እገሌ ብቻ ነው ጥሩ የሚጽፈው ወይም እገሌ ሁሌም መጥፎ ነው የሚጽፈው ብል ፍርደ ገምድልነት ነው:: መጥፎ መጥፎነቱ ለማን ነው? ጥሩውስ? መዳቢውስ ማነው? እኔ የምወደውን የስነፅሁፍ ፎረም "እዛ ስገባ ነርቬ ነው የሚጠቀጠቀው" የሚል ሰው አጋጥሞኛል:: እኔም አንዳንድ ሰዎች በሚሰጡት አስተያየት ጠምጃቸው (እነሱ እኮ መፈጠሬንም አያውቁ :D) ሁዋላ ግን ቀስ ብለው አስምጠውኝ ሲጠፉ ቅር ቅር የሚለኝ ዋርካውያን አሉ::
አንድ ሰሞን እግዚዮዮዮ የሚያስብል ፅሁፍም በፀሀፊው ተጠቁሜ እየተከታተልኩ ሳነብ ነበር...በውኑ አለም ቢሆን "እዚህ ምን ልትሆኚ መጣሽ' የሚያስብል አይነት ፅሁፍ...ከማሳፈሩ የተነሳ ጥቁር የፀሀይ መነፅርና ሻሽ አከናንቦ የሚያስኬድ አይነት ክፍል:: ግን ሰው ነኝና እስከመጨረሻው በጉጉት ነው የተከታተልኩት...እድሜ ለዋርካ ሻሽም አልገዛሁ:: ታዲያ እኔ ጸሀፊውን ባለጌ ነው ብል አጉል መመፃደቅ አይሆንብኝም?
የዋርካ ውበት ሁላችንም ነን:: እስቲ አሁን ሁሉም ፀሀፊ: ወይ ፖለቲከኛ: ወይ ስፖርተኛ: ወይ ቀልደኛ: ወይ ተፈላሳፊ: ወይ ተቺ: ወይ ገጣሚ: ወይ አኒሜተር: ወይ ደፋር: ወይ አይን አፋር: ወይ ስለወሲብ ጀብዱ አውሪ: ወይ ታሪክ አዋቂ: ወይ አንባቢ ብቻቻቻ ቢሆን ኖሮ (ሁህ) ዋርካ ዋርካ መሆንዋ ቀርቶ ትፈጠርስ ነበር? እንዴት ያሰለች እንደነበር ይታያችሁ::
ይህን ሁሉ ምን አስለፈለፈኝ? እንጃልኝ...ሰሞኑን ሳስበው የነበረ ነውና መተንፈስ ፈለኩ:: በዋርካ ተማረው የጠፉ ጉዋደኞቻችን ልክ በውን የማውቃቸው ይመስል ናፈቁኝና ድንገትም ቢያነቡኝ በማለትም ነው:: ልዩነትን አንጥላ-ያሳድጋልና: መብታችንን የተጋፋውን መጋፈጥን አንፍራ-እሱም ሰው ነውና: የተሰማንን ከመተንፈስ ወደሁዋላ አንበል-ጤና ይሰጣልና: ተናግሮ አናጋሪውን ደግሞ በዝምታ ማለፍ እንማር-ለሱ ቅጣት ነውና...በአጭሩ ለመቅጽበት ብልጭ ብላ ለምታልፍ ህይወት ጣጣ አናብዛባት
ለማለት ያህል:: ግን እኔ ይህን ሁሉ እጠቀምበት ይሆን? :arrow:
ጽሁፍ ቢበዛ በዋርካ ታክሲ አይጫንም:: እንደው ሙጭርጭር ያልኩዋት ስመጣ ስመጣ ከጉዋሮ እያወጣሁ ብተነፍስባት ብዬ ነው:: እገሌ ከገሌ አልልም...ሁላችሁንም እወዳችሁዋለሁ:: እነዛን ረባሽ ጎረምሶችማ እንዴት እንደምወዳቸው...የሰው አለካከፋቸው እራሱ ለዛ አለው:: ጸሀፊዎቻችንም እጃችሁ ወርቅ ይሁን:: ወጣት እህቶቻችንም ስለህይወት የምትሰጡት ትርጉምና ጨዋነታችሁ እንዴት ያረካኛል መሰላችሁ... ህይወታችሁ ይባረክ:: ፖለቲከኞቹም በምንም ተሙዋገቱ በምንም ለኢትዮጵያችን ካላችሁ ፍቅር የተነሳ ነውና ትልቅ ክብር እሰጣችሁዋለሁ:: የሰማችሁትንም ሆነ ያያችሁትን ሁሉ እንዳያመልጠን አምጥታችሁ የምታካፍሉንስ...ለመልካም ስራችሁ ግንባር ግንባራችሁን ስሜያለሁ::
አብሮ የተፈጠረ እግርና እግር እንኩዋን ይጋጫልና ግጭት ሲመጣ አትሸበሩ...ደግሞ ለሚያልፍ ነገር:: አንዳንዴም ጥል ሲኖር እኮ ነቃ ያደርጋል:: :lol: የተኛውን ይቀሰቅሳል::
ዛሬን እንዳታልቅ ሙጥኝ ብዬ ዋልኩዋት...ግና ጉድ አረገችኝ:: ፅሁፌ ስንብት መሰለና የራሴው ሆድ ባባብኝሳ...ከዋርካ ጨክኜ የምቀር ይመስል:: ለተወሰነ ጊዜ እያለሁ የለሁምና ነው ኮታዬን ለመጨረስ ይመስል ምክሬ የረዘመው:: በቸር ያገናኘኝ::
ውድድድድድድ የምታደርጋችሁ እህታችሁ