?ሙ#ጭ@ር%ጭ&ር$--->ነፍስ ይማር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby እነሆሰላም » Sat Aug 28, 2010 3:40 am

ትርንጎን የዋጠ ቢመልስ ይሻለዋል

እኔ ዋርካ መጥቼ ማፍጠጥ ደከመኝ. ሱስ አስይዞ መጥፋት በህግ የሚያስቀጣ ይመስለኛል :: Tጂን ለመክሰስ ስራርዋጥ ማን እንድተነፈሰላት አላዉቅም በፍጥነት ቤቴን ከፈተችዉ :: ዶክትሬም የደረሰብኝን መጎዳት በማስገንዘብ ሲጽፍ አይንሽ ሙጭርጭር ላይ ከማፍጠጡ ብዛት የአይንሽ ብሌን ተሞጫጭሯል ነዉ ያለዉ
ለማንኛዉም የዋርካ ቤተስቦቼ ዝምድና ለምቼ ነዉ እስቲ መላ በሉ::
እነሆሰላም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Sun May 02, 2010 7:37 am

Postby ዶዮ ወ ካዛንች » Sat Aug 28, 2010 7:32 am

መላ
ዶዮ ወ ካዛንች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 68
Joined: Mon Jan 18, 2010 5:27 pm

Postby እነሆሰላም » Sun Aug 29, 2010 7:30 am

ዶዮ ወ ካዛንች

አሳቅከኝ ከልቤ ለመላው አመሰግናለሁ
እነሆሰላም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Sun May 02, 2010 7:37 am

Postby ትርንጎ* » Sun Aug 29, 2010 6:46 pm

እነሆዬ ኧረ እኔም መላ ብያለሁ :D አይ ዶይቾ:: እንዴት ነሽልኝ እሙ? የህይወት ማራቶን ይዤልሽ እኮ ነው...እስቲ ከሰሞኑ ጋብ ይላል ብዬ ተስፋ አለኝ: ብቅ እላለሁ:: ለአይንሽ ካሮት ብይበት: "ለአይን የሚሆን ቪታሚኒ አለው" ሲሉ ሰምቻለሁ እትዬ ማንጠግቦሽ:: :D መልካም ሳምንት!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 711
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby እነሆሰላም » Mon Aug 30, 2010 1:41 am

እሰየዉ አይኔ አረፈ

ዶዮ ዘ ካዛንች ይቅርታ አንተ ብማለቴ መላ በጣም ጥማኛለች
ወርሼያታለሁ
እነሆሰላም
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 43
Joined: Sun May 02, 2010 7:37 am

Postby ትርንጎ* » Wed Sep 29, 2010 9:57 am

'ወይ ጉድድድድድ!' ማለት ጀምራለች የኔዋ ቆንጆ...አማርኛ ተወርቶልኝ መሞቱ ነው:: አባባልዋ ሁሌም ስለሚያስቀኝ አሁንማ በማይገባበት ቦታ ሁሉ ይባልልኛል:: ዛሬ እኔም ላጅባት መሰል...አንድ ሰሞን እዚህ ወጣ ገባ ከማለቴ ብዛት የዋርካ ባለቤቶች ደሞዝ ሁሉ ሊቆርጡልኝ ሳያስቡ ቀሩ ብላችሁ ነው :P አሁን እንዲህ ዝር ማለት ሊያቅተኝ:: መቼም ጊዜ ጠፋ የሚለው አባባል በጣም ስለተለመደ ልቤ ጠፋ ልበል መሰል::

እንዴት ናችሁልኝ? በቀደም እዛ የተለመደው ውሀ ዳር ቆሜ ዝናብ ዘንቦ የተቆጣው ማእበል ከድንጋዮቹና ከግንዶቹ ጋር እየተላተመ ሲመለስ እያየሁ ዋርካ ትዝ አለኝ...ዛሬ ገብቼ ስንቱን በሞነጫጨርኩ ብዬ ተመኘሁ:: ግን እኔ እህታችሁ አረጀሁባችሁ መሰል ጋደም እንዳልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ::

እንኩዋን ለአዲሱ አመትና ለመስቀል ያደረሳችሁ:: እቅፍ ድግፍ አድርጎ የአመት ሰው ይበለን!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 711
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ኤልሳ* » Tue Oct 12, 2010 7:55 pm

በሰላም ነው የጠፋሽው ቆንጆ? ቤትሽ እኮ ጭር አለ....
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

Postby ዶዮ ወ ካዛንች » Wed Oct 13, 2010 12:20 am

ላመት ባል እንኳን አንድ ሙክት ሳትጎትቱላት "ጠፋሽ ትርንጎዬ" ማለት ምን ዋጋ አለው?
ዶዮ ወ ካዛንች
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 68
Joined: Mon Jan 18, 2010 5:27 pm

ምን ተሻለኝ!

Postby ስርርር » Sat Nov 20, 2010 7:33 pm

ህዳር ሲታጠን!

ከሰው ልለይ ብዬ! ለህይወቴ ስኬት
እቅድ ማውጫ ግዜ ህዳርን መረጥኩት!

ላላማየ ስኬት ተዘገጃጅቼ
አምና ህዳር ሲታጠን እቅዴን አውጥቼ!

በዚህ አንድ አመት ውስጥ ይህን አደርጋለሁ
ጎጆዬን ቀልሼ ትዳር እተክላለሁ
የአብራኬን ክፋይ ወንድ አስወልዳለሁ
ደግሞም በትምህርቴ ትንሽ እገፋለሁ
ለእማማና አባባ በርኖስ አለብሳለሁ.....

አንዱም ሳይሳካ ውጥኔ የከርሞው
ህዳርን ማጠኑ መጣ የዘንድሮው!
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Nov 22, 2010 8:24 am

ኧረ ትርንጎ : የት ጠፋሽ :?: :?: :?: "ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ" አሉ :: አዲስ ድርስት ባይመጣልሽ እንኳን አለሁ በይ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby Debzi » Mon Jan 17, 2011 8:14 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ኧረ ትርንጎ : የት ጠፋሽ :?: :?: :?: "ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ" አሉ :: አዲስ ድርስት ባይመጣልሽ እንኳን አለሁ በይ ::

ተድላ


እኔም ልክ እንደዚህ ብዬ ልጽፍ ስገባ ለካ ቀድመኸኛል!
Ke akbrot selamta gar!!
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

Postby ትርንጎ* » Mon Apr 11, 2011 9:23 pm

<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ለካስ ሞት እንቅልፍ ነው >>>>>>>>>>>>>>>>>>>

ያለሁበትን አትጠይቁኝ : ገና ለኔውም አልገባኝምና :: ምነው እንደድሮው ጊዜ ኖሮኝ ስንቱን በቀበጣጠርኩት : በሞነጫጨርኩት : በተነፈስኩት :: ግና ድካም አያውቀኝም እል የነበርኩትዋ በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ ማለት ከጀመረ ከራረመ :: የምውለው ሰዎች መሀል ስሩዋርዋጥ ነው : አዎን ጊዜ ጥሎዋቸውም ሆነ ረዝሞባቸው ኧረ የሰው ያለህ የሚሉ ሰዎች መሀል :: በህይወታቸው ትንሽ ጨረር ብፈነጥቅ ብዬ ለዛ ፈገግ ስል : ይህንን ሳቅፍ : ያቺን ሳሻሽ : ይህኛውን ሳባብል እውላለሁ :: ወደቤቴ ስመለስ ሰውነቴ ቢዝልም ልቤ በደስታ ረክቶና ተፍነክንኮ አድራለሁ ::

ነገ አይቀርምና ይነጋዋል :: የኔም ሩጫ ይጀመራል :: ታዲያ ትላንት የሚሰማ ጆሮ አገኘን ብለው ስለህይወት ታሪካቸው: ስለፍቅር ጀብዱዋቸው: ስለልጆቻቸው: ስለቁስላቸው: ሲያጫውቱኝ ከዋሉት ነፍሶች መሀል አንዱ ወይም ሁለቱ እንደተለዩን ስሰማ ልቤ እዝን ይላል:: ሰላም የሰፈነበት ፊታቸውን ሳይ ደግሞ ምናልባት ሞት እረፍት ይሆን እላለሁ:: በቃ የኛ ህይወት ይቺው ነች : እንደንፋስ እፍ ! በኑሮዋችን የምንሩዋሩዋጥባቸውና የምንጨነቅባቸው ነገሮች ሁሉ በስተመጨረሻ በህይወታችን ላይ አንዲትም ቅንጣት ለውጥ እንደማያመጡ መረዳት ይደንቃል:: ገንዘብና ስልጣን ሳይሆን ፍቅር : ጉዋደኛ ሳይሆን ትዳርና ልጅ (አምላክ ከባረከው ): መከበር ሳይሆን እምነት : መልክና ሙገሳ ሳይሆን መልካም አመል: ቀሪ ገንዘቦቻችን ሆነው ሳለ እኛ የምንሮጠው በሌላኛው አቅጣጫ መሆኑ ይገርማል ::

ሞትስ ለምን ይፈራል ? ደክሞን ውለን እንቅልፍ ሊያሸልበን ነው ብለን እንደማንሰጋ ሁሉ ሞትም እንዲሁ በቀኑ ከች ብሎ ያነጉደናል :: ብቻ ሞትን አስፈሪ ያረገው ቀጠሮ አለመስጠቱና እድሜ ሳይመርጥ የፈለገውን መንጠቁ ይሆን ? እንጃ !

እኔ እንዳለሁ አለሁላችሁ : እየተመራመርኩ : እየተፈላሰፍኩ : ምነው ይህን ብፅፍ ያንን ብሞነጭር እያልኩ... በምኞት አለም :: የናንተን ደህንነት አንዳንዴ ሹልክ እያልኩ እየገባሁ እቃኛለሁ :: ሁሌም ሰላም ሁሉልኝ :: በቸር ያገናኘን !

አክባሪያችሁ
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 711
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

ቅቅ

Postby ዋኖስ » Tue Apr 12, 2011 3:36 pm

የሚገርመዉ`ኮ እኒያ ደጋግ ሰዎች ያልሻቸዉ ብቻ አይደሉም አንቺን የሚፈልጉ! የዋርካ ላይ "አዕዋፋት" (ለምሳሌ ዋኖስ) ሁሉ እንፈልግሻለን:: ስለዚህ ጊዜ ለሁሉም ጊዜ እኩል ይሰጥ!! ቅቅቅ

በማዬቴ ብቻ ተደስቻለሁ!
ከምንምና ከማንም በላይ "ራስ ደህና!" ብላለችና ለራስሽም እያሰብሽ! ቅቅቅ ሰላም በይልኝ እነ "ዶለዝን" ቅቅቅ

አክባሪሽ

ዳሞት
ትርንጎ* wrote:<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ለካስ ሞት እንቅልፍ ነው >>>>>>>>>>>>>>>>>>>

ያለሁበትን አትጠይቁኝ : ገና ለኔውም አልገባኝምና :: ምነው እንደድሮው ጊዜ ኖሮኝ ስንቱን በቀበጣጠርኩት : በሞነጫጨርኩት : በተነፈስኩት :: ግና ድካም አያውቀኝም እል የነበርኩትዋ በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ ማለት ከጀመረ ከራረመ :: የምውለው ሰዎች መሀል ስሩዋርዋጥ ነው : አዎን ጊዜ ጥሎዋቸውም ሆነ ረዝሞባቸው ኧረ የሰው ያለህ የሚሉ ሰዎች መሀል :: በህይወታቸው ትንሽ ጨረር ብፈነጥቅ ብዬ ለዛ ፈገግ ስል : ይህንን ሳቅፍ : ያቺን ሳሻሽ : ይህኛውን ሳባብል እውላለሁ :: ወደቤቴ ስመለስ ሰውነቴ ቢዝልም ልቤ በደስታ ረክቶና ተፍነክንኮ አድራለሁ ::

ነገ አይቀርምና ይነጋዋል :: የኔም ሩጫ ይጀመራል :: ታዲያ ትላንት የሚሰማ ጆሮ አገኘን ብለው ስለህይወት ታሪካቸው: ስለፍቅር ጀብዱዋቸው: ስለልጆቻቸው: ስለቁስላቸው: ሲያጫውቱኝ ከዋሉት ነፍሶች መሀል አንዱ ወይም ሁለቱ እንደተለዩን ስሰማ ልቤ እዝን ይላል:: ሰላም የሰፈነበት ፊታቸውን ሳይ ደግሞ ምናልባት ሞት እረፍት ይሆን እላለሁ:: በቃ የኛ ህይወት ይቺው ነች : እንደንፋስ እፍ ! በኑሮዋችን የምንሩዋሩዋጥባቸውና የምንጨነቅባቸው ነገሮች ሁሉ በስተመጨረሻ በህይወታችን ላይ አንዲትም ቅንጣት ለውጥ እንደማያመጡ መረዳት ይደንቃል:: ገንዘብና ስልጣን ሳይሆን ፍቅር : ጉዋደኛ ሳይሆን ትዳርና ልጅ (አምላክ ከባረከው ): መከበር ሳይሆን እምነት : መልክና ሙገሳ ሳይሆን መልካም አመል: ቀሪ ገንዘቦቻችን ሆነው ሳለ እኛ የምንሮጠው በሌላኛው አቅጣጫ መሆኑ ይገርማል ::

ሞትስ ለምን ይፈራል ? ደክሞን ውለን እንቅልፍ ሊያሸልበን ነው ብለን እንደማንሰጋ ሁሉ ሞትም እንዲሁ በቀኑ ከች ብሎ ያነጉደናል :: ብቻ ሞትን አስፈሪ ያረገው ቀጠሮ አለመስጠቱና እድሜ ሳይመርጥ የፈለገውን መንጠቁ ይሆን ? እንጃ !

እኔ እንዳለሁ አለሁላችሁ : እየተመራመርኩ : እየተፈላሰፍኩ : ምነው ይህን ብፅፍ ያንን ብሞነጭር እያልኩ... በምኞት አለም :: የናንተን ደህንነት አንዳንዴ ሹልክ እያልኩ እየገባሁ እቃኛለሁ :: ሁሌም ሰላም ሁሉልኝ :: በቸር ያገናኘን !

አክባሪያችሁ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Apr 15, 2011 5:28 am

ሰላም ትርንጎ :-

ተመስገን ነው : ከአንድ መሥመር አልፎ አንድ አንቀፅ አደረስሽ :: ከወራት (ዓመት) በኋላ ያስነበብሽን ታሪክ (ፍልስፍና) የሚያመራመር ነው :: በርቺልን ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ትርንጎ* » Sat Apr 16, 2011 11:19 pm

<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<እውን ቁዋንቁዋ ያስፈልጋል?>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

ከኮምፒውተሬ ላይ አይኖቼን አንስቼ ወንበሬን ለጠጥኩና ጣራ ግድግዳውን እያማተርኩ የሀሳብ ፈትሌን ተያያዝኩት:: አቤት ስንቱ ቦታ ነጎድኩ: የስንቱን ቤት ቃኘሁ: የስንቱንስ ልብ ፈተሽኩ:: አይኖቼ ከቦዙበት ሲመለሱ ከጠረጴዛዬ ላይ በሚንጨላጨለው መብራት አይኖቹ ሲንቦገቦጉ አየሁዋቸው:: ለካስ ስራዬ ውስጥ ሰምጬ ሳለ ከሁዋላዬ ያለው ፎቴ ወንበር ላይ መጥቶ ተጋድሞዋል:: "እንዴ!" ከማለቴ ፍልቅልቅ ያለ ውብ ፈገግታውን መገበኝ: ተያዝኩ አይነት ማታለያ:: ልቤን እንዴት እንደሚያሙዋሙዋው ያውቃል:: "ተኛ እንጂ" አልኩ...ለመኮሳተር ብፈልግም አልቻልኩም:: በፍጥነት ክንዱን ተንተርሶ ተኛ:: ከተቀመጥኩበት የሚታየኝ ተላጭቶ እያቀመቀመ ያለው ውብ ቅርጽ ጭንቅላቱና እላዩ ላይ ያረፉት አለንጋ ጣቶቹ ናቸው:: እኔ ግን ከዛ አልፌ ውስጡን እየሁት: ቃኘሁት: ወደድኩት::

በህይወቱ አንዲት ሙሉ አረፍተ ነገር እንኩዋን ሲናገር ሰምቼ አለማወቄን አሰብኩና ተገረምኩ:: ታዲያ ምን እንደሚያስደስተው: ምን እንደሚያስከፋው: ምን እንደሚወድ: ምን እንደሚጠላ: ያልወደደውን ሰው: ምን እንደሚያስብ እንኩዋን አይኖቹን አይቼ አውቃለሁ:: "ቁዋንቁዋ ምን ዋጋ አለው" አልኩ ለራሴ:: የማስበው የገባው ይመስል ቀና ብሎ ወደሱ እንድመጣ እጁን አውለበለበልኝ:: 'ተኛ" አልኩ ወደአጠገቡ እየሄድኩ:: እጄን ጎተተኝና ሳጎነብስ እያገላበጠ ሳመኝ:: በጉልበቶቼ ተንበረከኩና አንገቱ መሀል ገብቼ ጠረኑን ሽትትትትት እያደረኩ ደገግሜ ስስመው ክትክት ብሎ መሳቅ ጀመረ:: አቤት እንዴት እንደምወደው...የአለም ቁዋንቁዋ ቢበረዝ ሊገልፀው በማይችል ፍቅር: ከህይወቴ አስር እጥፍ አስበልጬ...አዎን አንድም ቀን በቅጡ አናግሮኝ የማያውቀውን ሰው::

ከተንበረከኩበት ስነሳ እጄን ሊይዘኝ ሞከረ:: "በቃ ተኛ" አልኩ ኮስተር ብዬ:: ውብ ፊቱ ቅጭም አለችና እንደገና ክንዱን ተንተርሶ ተጋደመ:: እንደልማዴ ሆዴ ቢንሰፈሰፍም ጨክኜ ዞር አልኩ:: ነገ በጠዋት ስለሚነሳ የግድ መተኛት አለበት:: ደግሞ አመነታሁ: ለሱ አስቤ እንደሆነ ገብቶት ይሆን? "እ-ወ-ድ-ሀ-ለ-ሁ" እልኩ ከቆምኩበት...እንደወትሮው እወድሻለሁ ለማለት በተኛበት እጁን ሲስም አየሁት: የሚያውቃት ዋና ቁዋንቁዋ::

ወደ ወንበሬ ተመልሼ እንደገና አየሁት:: ለህይወቴ ማደሻ እሱን ያደለኝን ፈጣሪ አመሰገንኩ:: አንዳችም ነገር እንዳይነካብኝም ተማፀንኩ:: በሱ የሚመጣም ነገር ካለ አጥፎ ደርቦ ለኔው እንዲያሸክመኝም ከአምላኬ ጋር ተደራደርኩ:: እነዛ ረጃጅም ውብ ሽፋሽፍቶቹ ከቅንቅልፍ ጋር ትግል ይዘው ክፍት ዝግት እያሉ ሲውለበለቡ አየሁዋቸው...ከዛም ክድን አሉና የልቤን አበባ ይዘውት ወደህልም አለም ነጎዱ::


ዋኖስዬና ተድልሽ እጅ ነስቻለሁ!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 711
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests