?ሙ#ጭ@ር%ጭ&ር$--->ለካስ ትሰማለህ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ከምካሚው » Sun Apr 17, 2011 1:29 am

[quote="ትርንጎ*"][color=darkblue]<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<እውን ቁዋንቁዋ ያስፈልጋል?>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

ሰውየው: ባልቭ: ነው ወይስ: ልጅቭ?? ባል ከ ሆነ: እንዴት: ከንፈር ነሳቭው?? ፅሁፍቭ: ግን: ውብ: ነው::
ከምካሚው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 66
Joined: Sun Mar 23, 2008 12:24 am

Postby ሰላም 1 » Sun Apr 17, 2011 9:23 am

ባልዋ አይደለም ህጻን ልጅዋ ነው ገና 2 አመት ያልሞላው አይደል ትርንጎ :?: በጣም አድናቂሽ ነኝ .
ሰላም 1
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 50
Joined: Tue Jan 11, 2011 1:04 pm

Postby ትርንጎ* » Tue Apr 19, 2011 9:26 pm

<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ማነኝ?>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

ትላንት "አቤት...ከሰውም ሰው...የደግ መጨረሻ" ያለችኝ ምላስ ዛሬ "ሰው መሰለቻችሁ...ይቺ አውሬ" ስትል ሰማሁዋትና ታዘብኩዋት:: አምና "የማትጠገቢ ነገር" ያለችኝ አፍ ዘንድሮ ስሜን እንኩዋን ለመጥራት ስትፀየፍ አየሁዋትና ገረመኝ:: ጠዋት አብራኝ ስትንከራተት የነበረች አይን ማምሻው ላይ መኖሬንም ልትረሳ ስትከጅል አየሁዋትና ተደመምኩ:: ታዲያ ሌሎች "የደግ መጨረሻ" የሚሉ ምላሶች ሲያቆጠቁጡ አየሁና ፈገግ አልኩ...እነሱም ቀናቸው ደርሶ: ወረታቸው በኖ ስሜን እስኪረጋግጡት ድረስ...ህይወት እንደሁ መቀጠልዋ አይቀር::

እናም እራሴን ጠየኩት..ማነኝ ብዬ:: እኔማ እኔው ነኝ:: የትላንትዋ: የጥዋትዋ:: እራሴን ፈተሽኩት...ለሰው ተመቸም አልተመቸም በውስጤ እኔን ቅር የሚያሰኝ ነገር አላገኘሁም:: ታዲያ ጭንቀቴ ለማን ነው? ዛሬ ሲመቸው እስር እስሬ ብሎ ነገ ለሚዘረጥጠኝ ሰው ነውን? ማንነቴን አውቆና ገምግሞ ለቀረበኝ ልቤም እጄም ክፍት ነው:: በወረት ዱብ ዱብ ብሎ ነገ ልጥለፍሽ ለሚለው ደግሞ ኬረዳሽ ነኝ...ጊዜውም ጉልበቱም የለኝምና "ቀረሁብህ/ቀረሁብሽ" ከማለት በስተቀር:: ለዛውስ ለስንቱ ማንነቴን አስረድቼ እዘልቀዋለሁ? አዎን እኔው ነኝ!

ከምካሚውና :D ሰላም በአክብሮት እጅ ነስቻለሁ::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ስርርር » Wed Apr 20, 2011 1:16 am

ውይ እህትዬ አለሽ እንዴ የኔ ቆንጆ? እንክዋንም በሰላም መጣሽ:: እውነቴን ነው የምልሽ ብዙ ግዜ አንቺን ፍለጋ ወደዋርካ ተመላልሻለሁ::

በርቺልን
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ትርንጎ* » Sun May 08, 2011 11:58 pm

<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<እ-ና-ት-ነ-ት>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

"እስዋን የመሰለ እናት ሰጥቶዋቸው..." ይሉብኛል ልጆቼን:: ሙገሳ እንደሆነ ይገባኛል...ግን "እነዚህን የመሰሉ ልጆች ሰጥቶዋት..." ቢባልልኝ እመርጣለሁ:: የህልውናዬ ቁምነገሮች: የማንነቴ መሰረቶች: የልቤ አበባዎች: የኑሮዬ ማእዘኖች...ከእናትነት ማእረጌ በፊት የነበረችውን እኔን እምብዛም አልወዳትም:: ትእግስት የሌላት: በቀላሉ የምትከፋ: ለምን ተነካሁ የምትል...ብቻ በቃ ይህንን ሁሉ ህይወት ትተሽ እንደገና ሌጣ ወጣት ሁኚ ብባል ለቅሶ አልቀመጥም ብላችሁ ነው:: ከነልጆቼ ከሆነ ግን ምናልባት...ኮረዳነትን ማን ይጠላል:: ግን ደግሞ ልጆቼን በዛች ትእግስተ ቢስ ሴት ማሰቃየት አልፈልግም::

ዛሬ የእናቶች ቀን ነው:: እኔ ግን ስለልጆቼ ላወጋ ተነሳሁ:: የመጀመሪያዋንና ሁለተኛውን ልጄን ስወልድ ሀላፊነቱ ከብዶኝ ስቅስቅ ብዬ እንዳለቀስኩ ከዚህ በፊት ያወጋሁዋችሁ ይመስለኛል:: ሌላው ደግሞ የመጀመሪያዋን ልጄን መውለጃዬ እስኪደርስ ድረስ ምንም ሰፍ ያለ ፍቅር አልሰማ ሲለኝ "ክፉ እናት እሆን እንዴ?" ብዬ በልቤ ለሰውም ሳላወራ...ለአባትዋም ጭምር ደብቄ ዝም ማለቴ ትዝ ይለኛል:: ሌሎች እናቶች ሆዳቸው ውስጥ እያሉ ማውራት: ስም ማውጣት: ተገለበጠች/ተገለበጠ አያሉ በስልክም ሳይቀር ሲያውጁ...እኔ እቴ! እንደውም ማካበዱ ያናድደኝ ነበር:: በዛ ላይ እንቅልፌን በጣም እወድ ስለነበር ልጅትዋ ስትወለድ ሌሊት እንዴት እንደምነሳ ሁሉ ሀሳብ ገብቶኝ ነበር...አይ ሞኝነቴ...ይኸው እስከዛሬ እንኩዋን ነቅተው በእንቅልፍ ልባቸው ድምፅ ካሰሙ ከሌላ ክፍል ከተኛሁበት እንዴት ሰምቼ እንደምበር ለራሴውም ይገርመኛል:: ታዲያ ይህ ንቁነቴ ለራሴው ልጆች ብቻ ነው...አብሮን ያያያዘን ኮረንቲ ያለ ይመስል::

እናማ እናትነትን እፁብ ድንቅ ጉዳይ ሆኖ አገኘሁት:: ወረት የማያውቅ ፍቅር...የማይለወጥ...እራስን ቢቻል አስር ጊዜ አሳልፎ የሚያሰጥ...ማንንም የዚህን ያህል እሩብ ወድጄ ከሆነ ጥሩ ነው:: ልጆቼ ማንነቴን ለውጠውታል:: ጥንካሬ ሰጥተውኛል:: እራሴን እንዳሻሽል ብሎም የነሱን ህይወት እንዳሳምር አሁንም የእለት ተእለት ብርታቶቼ ናቸው:: ያለነሱ የሆነ አንድም ነገር: ያለነሱ በህይወቴ የተሳካ አንድም ነገር የለም:: አልፈው ተርፈውም በአንድ ወቅት ህይወቴን አትርፈውልኛል:: ታዲያ "እነዚህን የመሰሉ ልጆች አድሎሽ..." መባል ሲያንሳቸው አይደለምን?! አቤት ደግሞ ሲያማምሩ...ከምር የእናት አይን ሆኖ አይደለም: በቃ የቆዳቸው ቀለም እራሱ የተለየ መስሂብ አለው:: አሁንማ ቁመታቸው ተመዞ አፍጥጬ ማየት እንኩዋን እፈራለሁ...በልቤ "እውነት አሁን እነዚህ የኔ ናቸው?" እያልኩ::

ውድ እናቶች የናንተን ቀን ለመሻማት ብዬ አይደለም:: መልካም የእናቶች ቀን እንዲሆንላችሁ የልብ ምኞቴ ነው:: እቅፍ ድግፍ አድርጎ ከነቤተሰቦቻችሁ የአመት ሰው ይበልልኝ::

ሁሌም አክባሪያችሁ

ወንድምዬ እጅ ነስቻለሁ!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ፍርንትት » Mon May 09, 2011 1:08 am

ትርንጎ እንኳን አደረሰሽ እህታለም :D

ለበአል ብዙም ግድ የለኝም ዛሬ ግን እናቴን ሳስባት ነው የዋልኩትና ይህንን ጽሁፍሽን ሳነብ ደግሞ የበለጠ ውስጤን አሳሰብሽው: ከማንበብ ውጭ ጽፌበት የማላውቀው ቤትሽም ይህችን ጻፍኩ::አፍጥጨ እንኳን ማየት እፈራለሁ ስትይ እናቴም ተመሳሳይ ነገር ስለምትል ደግሞ ገረመኝ:: ከቆይታ በኋላ ስታየኝ እንዲሁ እንዳንች ነው የምትለኝ ''አታይውም ተመችቶታል አምሮበታል ወፍሯል እኮ'' ሲሏት ''እረ ተውኝ እስኪ ዋናው ደህና ይሁንልኝ''ብላ አይኗን መለስ ታደርጋለች:በሙሉ አይኗ እንኳን አታየኝም:የሷ አይን እኔን ቡዳ ሆኖ የሚበላኝ ይመስል::

ልጆችሽን ፈጣሪ ይባርክ ያሳድግልሽም!

ጎዣሜው
ፍርንትት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 456
Joined: Mon Dec 06, 2010 1:28 am

Postby ትርንጎ* » Wed May 18, 2011 3:52 pm

<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ፍቅር እስከመቃብር>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

መጋረጃው በከፊል ተጋርዶዋል:: ወደክፍሉ ሲገባ አራት ጥንድ እግሮች አልጋው ላይ ተደርድረው ይታያሉ:: አዎን...የህይወትን ውጣ ውረድና ሸክም አብረው ሊገፉ ቆርጠው የተነሱ ባልና ሚስት እግሮች:: ጠባቢትዋ አልጋ ላይ በሰላም ተቃቅፈው ተኝተው ሲታዩ አንዳችም ነገር የጨረፋቸው አይመስሉም:: እድሜ ቀለሙን ቢያፈናጥቅባቸውም በጊዜያቸው የተዋቡ ሰዎች እንደነበሩ አሻራቸው ይመሰክራል:: ሁለቱም የተለያየ የጠና ህመም አለባቸው:: ሚስትየዋ አንዳንዴ መደገፊያ ቢያስፈልጋትም ቆማ ስለምትሄድ አስታማሚዋ እስዋ ነች:: ታዲያ ሲተያዩ: ፈገግታ ሲለዋወጡ: ሲቆለማመጡ ለሚያይ መታመማቸውን ይጠራጠራል:: ተረኛው ማን እንደሆነ አይታወቅ እንጂ ህይወት እንደሆነ ፍርድዋን በይናለች:: ግን ደግሞ ለካስ ፍቅር ሞትንም ያሸንፋል...ላደለው! ታዲያ የህይወት ጫና ሲያደክማቸው እንዲህ ተቃቅፈው አረፍ ሲሉ የሚፈናጠቀውን ውበት ማን ጨክኖ ያደፈርሳል?! እንባና ፈገግታ በተቀላቀለበት ስሜት በሩን በዝግታ መለስ አድርጎ ከመውጣት በስተቀር:: ያስቀናሉ! አምላክ ብርታቱን ሁሉ ይስጣቸው::
-------------------

ጎዣሜው ወንድሜ :D አሜን ብዬ እጅ ነስቻለሁ::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ሙዝ1 » Fri May 20, 2011 2:42 pm

ላደለዉ አልሽ? አዎ ላደለዉ ... .... ምንም አይኑረኝ ፍቅር ካለኝ ሁሉም አለኝ ... ታዲያ የሀይስኩል አይነት ፍቅር አይደለም እሱ የሚፋጅ ስሜት ነዉ ....

ይህቺን ፍቅር እስከ መቃብርሽኝ ሳነባት እኔንም ወደ አንድ አጋጣሚ መለሰችኝ .... ከ3 አመታት በፊት ... ስዊዘርላንድ ... ሉዘርን .... ...:: የበረዶ ወቅታቸዉ አልፎ ጸሀይ ፍንጥቅ ብላ የነዋሪዎችንም ስሜት ሀሴት በሀሴት የምታደርግበት ወቅት ነዉ .... በኛ የፋሲካ ወቅት አካባቢ ይመስለኛል ... እኔን'ኳ ብርዱ እየተሰማኝ ነበር ምንም እንኳ ለነሱ ሙቀት ቢሆንም .... ወደ ስዊዝ የጋበዘኝ ድርጂት ደስ እንዲለኝ የማይቆፍረዉ ጉድጓድ አልነበረም .... .. ምንም እንኳን ከሀገሬ ዉጭ ወርቁም ፋንድያ ቢሆንብኝ ,,,, ... እነሱ ግን ደፋ ቀና ይላሉ ... ከደፋ ቀናዉ አንዱ ... በአንድ ምሽት ኦልድ ስዊዝ ሀዉስ የሚባል ቤት የእራት ግብዣ ነበር ... .... ለኔም የታዘዘልኝ እራት የቤቱ ስፔሻል ነዉ:: ሸፉ አጠገብሽ መጥቶ ሁሉንም ነገር እያየሽ .... ይሰራልሻል .... ያ ለነሱ ትልቅ ነገር ነዉ .... ምናለ ባታቀረኑኝ እንዳልኩ ማን በነገረልኝ .... ይልቅ እኔን የሳበኝና አይኔን ያቅበዘበዘዉ .... የሸፉ አርት ሳይሆን ጥግ ላይ ተቀምጠዉ .... አይኖቻቸዉ ፍቅርን የሚያንጸባርቁ ሽማግሌዎች .... .... በስስት ይተያያሉ .... አይናቸዉ ከማሞጭሞጩ የተነሳ የሚታይ ባይሆንም እርስ በርስ ሲተያዩ ግን የሚታየዉ ዉበታቸዉ ነበር ....:: ሸፉ የተናደደብኝ ይመስለኛል ... አንድ ሁለቴም አይኔን ተከትሎ ሂዷል .... የምትታይ ጠንበለል ኮረዳ ባለመኖሯ ... ምናልባትም ጤንነቴን ተጠራጥሯል .... አላወቀ ከእህልም በላይ ሰዉ እንደምወድ ... ::

እራት እየበላንም አይኔ እነሱዉ ጋ ነዉ .... ምግባቸዉ ቀረበ ... ሊበሉ ነዉ ... እንደወጉ ባል ቀዳሚቁን ጉርሻ እንደሚያጎርስ እየጠበኩ ነበር:: አላሳፈሩኝም ... ሚስትዬዋ ለመጉረስ ጠጋ ሲሉ ከአፋቸዉ ፈሳሽ ነገር ወረደ ... ባል ጠብቀዉ አጎረሱ ... ... ከዛም ከጭናቸዉ ላይ ጨርቅ አንስተዉ የሚስትዬዋን አፍ ተንጠራርተዉ ጠራረጉ ... ታድያ አንድ እጃቸዉ ከዘራቸዉን ደገፍ እንዳሉ ነዉ ... ...

ፍቅር ደስ ይላል .... ስትኖሪበት እና ስትኖሪለት ጣፋጭ ነዉ ... የሚገርመዉ ግን በፍቅር የሚኖሩትንም ማየት እንዲሁ ጣፋጭ መሆኑ ነዉ:: እኔም ተጋባብኝ ... አማረኝ ... :: ከእራት በሗላ በነበረዉ የወይን መጎንጨት ክፍለ ጊዜ ላይ እነዛን አዛዉንቶች ማዉራት እንደምፈል ለጋባዦቼ አሳወኩ ....:: ግራ ቢጋቡም እናስፈቅድ ብለዉ አስፈቀዱ ... :: ትንሽ አዉርተዉ ነበር ,,, ግን በጀርመንኛ ስለነበር አልሰማሁትም:: ግን በግርምት እያዩኝ ... ምን እንርዳህ አሉኝ ...::

የመጀመሪያዉ ጥያቄ .... በፍቅር ስንት አመት ቆያችሁ ....
አሮጊቷ ፈጣን በሆነ መልስ ... በጣም ትንሽ ... ማይክሮ ሰከንድ .... አይንህ አንዴ እልም ብሎ እስከሚከፈት ....
ቅኔ አይደለም ... ፍቅር እንደዛ ነዉ .... ብዙ የለዉም .... በፍቅር ሲኖሩ ነዉ የአልበርት አነስታይን የአንጻራዊ ቲየሪ የሚገለጸዉ ... አዎ .... የተገናኙ በአስራዎቹ እድሜ ላይ እያሉ ... ጀርመን ዉስጥ ... አንዱ ሰዉየዉ የጀርመን ዝርያ ሲኖራቸዉ ሴትዮዋ አይሁድ .... በዛዉ ወቅት በተፈጠረዉ የዘረኝነት ችግር ስዊዝ በስደት ገቡ ... ኖሩ ... ለስደት በዳረጋቸዉ ፍቅር ላይ ቂም ሳይቋጥሩ .... ዛሬም ድረስ ለስደትና ለቤተሰብ ናፍቆት የዳረጋቸዉን ፍቅር እየተንከባከቡ ነበሩ:: አምላክ ሞታቸዉን በተመሳሳይ ሰከንድ ያድርግላቸዉ .... አንዳቸዉ የአንዳቸዉን ሞት እንዳይሰሙ... ... አሜን!!!!
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ትርንጎ* » Wed May 25, 2011 6:50 pm

ሙዝነቴ እንደው ምን ላድርግህ? ጣፋጭ ፅሁፍህን አጣጥሜ ስጨርስ ከምር ቅንት አልኩ:: ሁህ...ፍቅር ካሉ እንደዚህ ነው:: ግን ስንቶቻችን ነን ለዚህ አይነት እፁብ ፍቅር የታደልነው? የልብ ምሰሶና ማገር ፍቅር በፍቅር ሆኖ ያንን የሚሞሉበት ሁነኛ ሰው ሲታጣስ? አንዳንዴ ደግሞ "ፍቅር በጭራሽ ይዞኝ አያውቅም" የሚሉ ሰዎች ሲያጋጥሙ ለካስ የባሰ አለ ያስብላል:: እንደው ፍቅር ሲፈልግ ከክቶና ፈጭቶ ብትንትናችንን ያውጣው እንጂ በፍቅር አለም ሳይዳክሩ ማለፍስ... ሰው እንዳልነካ ይቅር::

ሙዝሻ ለካስ ለስላሳ ልብ አለህ :D ስላየሁህ እንዴት ደስ እንዳለኝ::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ዋኖስ » Thu May 26, 2011 2:13 pm

አደብ ገዝቶ ማስተዋል አንድ ነገር ያስተምራል!

ሙዙ! ድንቅ ልምድ አግኝተኃል ብዬ አስባለሁ! !

ሙዝ1 wrote:ላደለዉ አልሽ? አዎ ላደለዉ ... .... ምንም አይኑረኝ ፍቅር ካለኝ ሁሉም አለኝ ... ታዲያ የሀይስኩል አይነት ፍቅር አይደለም እሱ የሚፋጅ ስሜት ነዉ ....

ይህቺን ፍቅር እስከ መቃብርሽኝ ሳነባት እኔንም ወደ አንድ አጋጣሚ መለሰችኝ .... ከ3 አመታት በፊት ... ስዊዘርላንድ ... ሉዘርን .... ...:: የበረዶ ወቅታቸዉ አልፎ ጸሀይ ፍንጥቅ ብላ የነዋሪዎችንም ስሜት ሀሴት በሀሴት የምታደርግበት ወቅት ነዉ .... በኛ የፋሲካ ወቅት አካባቢ ይመስለኛል ... እኔን'ኳ ብርዱ እየተሰማኝ ነበር ምንም እንኳ ለነሱ ሙቀት ቢሆንም .... ወደ ስዊዝ የጋበዘኝ ድርጂት ደስ እንዲለኝ የማይቆፍረዉ ጉድጓድ አልነበረም .... .. ምንም እንኳን ከሀገሬ ዉጭ ወርቁም ፋንድያ ቢሆንብኝ ,,,, ... እነሱ ግን ደፋ ቀና ይላሉ ... ከደፋ ቀናዉ አንዱ ... በአንድ ምሽት ኦልድ ስዊዝ ሀዉስ የሚባል ቤት የእራት ግብዣ ነበር ... .... ለኔም የታዘዘልኝ እራት የቤቱ ስፔሻል ነዉ:: ሸፉ አጠገብሽ መጥቶ ሁሉንም ነገር እያየሽ .... ይሰራልሻል .... ያ ለነሱ ትልቅ ነገር ነዉ .... ምናለ ባታቀረኑኝ እንዳልኩ ማን በነገረልኝ .... ይልቅ እኔን የሳበኝና አይኔን ያቅበዘበዘዉ .... የሸፉ አርት ሳይሆን ጥግ ላይ ተቀምጠዉ .... አይኖቻቸዉ ፍቅርን የሚያንጸባርቁ ሽማግሌዎች .... .... በስስት ይተያያሉ .... አይናቸዉ ከማሞጭሞጩ የተነሳ የሚታይ ባይሆንም እርስ በርስ ሲተያዩ ግን የሚታየዉ ዉበታቸዉ ነበር ....:: ሸፉ የተናደደብኝ ይመስለኛል ... አንድ ሁለቴም አይኔን ተከትሎ ሂዷል .... የምትታይ ጠንበለል ኮረዳ ባለመኖሯ ... ምናልባትም ጤንነቴን ተጠራጥሯል .... አላወቀ ከእህልም በላይ ሰዉ እንደምወድ ... ::

እራት እየበላንም አይኔ እነሱዉ ጋ ነዉ .... ምግባቸዉ ቀረበ ... ሊበሉ ነዉ ... እንደወጉ ባል ቀዳሚቁን ጉርሻ እንደሚያጎርስ እየጠበኩ ነበር:: አላሳፈሩኝም ... ሚስትዬዋ ለመጉረስ ጠጋ ሲሉ ከአፋቸዉ ፈሳሽ ነገር ወረደ ... ባል ጠብቀዉ አጎረሱ ... ... ከዛም ከጭናቸዉ ላይ ጨርቅ አንስተዉ የሚስትዬዋን አፍ ተንጠራርተዉ ጠራረጉ ... ታድያ አንድ እጃቸዉ ከዘራቸዉን ደገፍ እንዳሉ ነዉ ... ...

ፍቅር ደስ ይላል .... ስትኖሪበት እና ስትኖሪለት ጣፋጭ ነዉ ... የሚገርመዉ ግን በፍቅር የሚኖሩትንም ማየት እንዲሁ ጣፋጭ መሆኑ ነዉ:: እኔም ተጋባብኝ ... አማረኝ ... :: ከእራት በሗላ በነበረዉ የወይን መጎንጨት ክፍለ ጊዜ ላይ እነዛን አዛዉንቶች ማዉራት እንደምፈል ለጋባዦቼ አሳወኩ ....:: ግራ ቢጋቡም እናስፈቅድ ብለዉ አስፈቀዱ ... :: ትንሽ አዉርተዉ ነበር ,,, ግን በጀርመንኛ ስለነበር አልሰማሁትም:: ግን በግርምት እያዩኝ ... ምን እንርዳህ አሉኝ ...::

የመጀመሪያዉ ጥያቄ .... በፍቅር ስንት አመት ቆያችሁ ....
አሮጊቷ ፈጣን በሆነ መልስ ... በጣም ትንሽ ... ማይክሮ ሰከንድ .... አይንህ አንዴ እልም ብሎ እስከሚከፈት ....
ቅኔ አይደለም ... ፍቅር እንደዛ ነዉ .... ብዙ የለዉም .... በፍቅር ሲኖሩ ነዉ የአልበርት አነስታይን የአንጻራዊ ቲየሪ የሚገለጸዉ ... አዎ .... የተገናኙ በአስራዎቹ እድሜ ላይ እያሉ ... ጀርመን ዉስጥ ... አንዱ ሰዉየዉ የጀርመን ዝርያ ሲኖራቸዉ ሴትዮዋ አይሁድ .... በዛዉ ወቅት በተፈጠረዉ የዘረኝነት ችግር ስዊዝ በስደት ገቡ ... ኖሩ ... ለስደት በዳረጋቸዉ ፍቅር ላይ ቂም ሳይቋጥሩ .... ዛሬም ድረስ ለስደትና ለቤተሰብ ናፍቆት የዳረጋቸዉን ፍቅር እየተንከባከቡ ነበሩ:: አምላክ ሞታቸዉን በተመሳሳይ ሰከንድ ያድርግላቸዉ .... አንዳቸዉ የአንዳቸዉን ሞት እንዳይሰሙ... ... አሜን!!!!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ሙዝ1 » Sun May 29, 2011 9:22 am

ትርንጎሻ እና ዋኖስ ስላነበባችሁልኝ አመሰግናለሁ ...

ዋኖስ .... ቂቂቂ ልምድ አግኝተህበታል አልከኝ .... ቂቂቂ ፍቅር በተሞክሮ የምታገኘዉ ነገር አይደለም .... ፍቅር ልክ እንደሞት ሁሉ ነግሮህ አስፈቅዶህ የሚመጣ ነገርም አይደለም ... ወይንም ደግሞ ፈልገህ ልክ እንደ ትርንጎ ልብህን ከፍቅር ማገርና አቋም ገንብተህ ስለተቀመጥክ የሚገኝ ጸጋ አይደለም .... ይመጣል .... ዝፍቅ ብለህበት ታገኘዋለሁ .... ያስደስታል .... ያማል .... ደስ የሚል ህመሙ ዘልቆ ተሰምቶህ ግን ደግሞ ከህመምህ ለመዳን አንዳችም ሙከራ ሳታደርግ ስታገኘዉ ያኔ ፍቅርን እያወከዉ ነዉ ....

ትርንጎሻ .... አዎ እጅግ በጣም ለስላሳ ልብ ነዉ ያለኝ .... ከልጅነቴ ጀምሬ ፍቅር ባለበት ሁሉ መገኘትን እወዳለሁ ... ማፍቀርም ደስ ይለኛል ... አስታዉሳለሁ ልጆች እያለን ከትምህርት ቤት መልስ ... ወይንም ክረምት ላይ የምንጫወታቸዉ ጨዋታዎች ሁሌም ሴቶች በሚገኙበት ቦታ ቢሆን እመርጣለሁ .... ወንዶቹ በጋ ላይ ኳስ ... ክረምት ላይ ዳጥ ... በጭቃና በአንዳዉላ ጦርነት ስንገጥም .... ሁሌም እንስቶች ሰኞ ማክሰኞ ..... በሚጫወቱበት ቢሆን እመርጣለሁ .... እመርጣለሁ ብቻ ሳይሆን ያኔም ኢንፍሎዌኝሻል ስለነበርኩ አደርገዋለሁ:: በነዛ የጨቅላነት እድሜዬ .... በለምለም ሳር ላይ ከአንዷ የሰፈር ኮረዳ ላይ ጋደም ብዬ ባሳልፍ ምኞቴ ነበር .... አስቢ ወሲብ ምን እንደሆነ በማላዉቅበት ጊዜ .... ምናልባትም ወሲብ እራሱ ቢመጣ ለማምለጥ እግሬ አዉጭኝ በምልበት እድሜዬ ላይ ሴቶች ዙሮያ መሆን እንዴት ያምረኝ ነበር? .... ... ትንሽ እድሜዬ ከፍ እያለ ወደ አስራዎቹ ስጠጋም እንዲሁ .... በሙሉ ጨረቃ ወክ ማድረግ .... ቂቂቂ .... ከምር በምሽት ሌላ ሴት ማግኘት ስለማልችል .... ሙሉ ጨረቃ በምትሆንበት ወቅት የቤት ሰራተኞችን ጎርጉቼ ከቤት እንዲወጡ አድርጌ ግጥም አነብላቸዉ ነበር .... የፍቅር ወግ አይነት ነገር ...

በኋላም በደንብ ካደኩኝ .... በስጋም በመንፈስም እየጠነከርኩ ስሄድ በሴሰኝነት ቢቆጠርብኝ ... እንዲሁ ነበርኩ .... አንድም ቀን ግን የፍቅር ሰዉ እንጂ ሴሰኛ ነኝ ብዬ አስቤ አላዉቅም ... :wink:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ትርንጎ* » Sun May 29, 2011 2:52 pm

:D :D :D አይ ሙዝነቴ: የሙሉ ጨረቃዋ ንባብ ገደለችኝ:: ትርጉሙን ባናውቀውም መውደድ ከልጅነት የሚጀምር ይመስለኛል:: ፍቅር ያማል አልከኝ...እንክት አድርጎ...ሁህ! ያስነባዋል እንጂ...መድሀኒት የሌለው ነገር:: ግን ደግሞ እሱም አብሮ ይመስለኛል ጉልበት የሚሰጠው...የሚያጣፍጠው:: ኧረ እንደው ተወኝ...አታስለፍልፈኝ:: ስንቱን አሰብኩት:: እኔም ፍቅር የተቀባ ነገር ሁሉ እንደጉድ ይስበኛል... አምላኬንም ተዝቆ በማያልቅ ፍቅር ልቤን ስለሞላው አመሰግነዋለሁ:: ሰላም ሁንልኝ::

ዋኖስዬዬዬ እጅ ነስቻለሁ!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ትርንጎ* » Sat Jul 02, 2011 9:44 pm

"ሞተች" አሉኝ:: "ምን?"...ክው አልኩ: አይምሮዬ መጨረሻ መቼ አንዳየሁዋት እያውጠነጠነ:: ከአንድ ቀን በፊት...እና በአንዴ እንዲህ እልም:: ወድቃ የተሰበረ አንገትዋ ላይ የተደረገላት መደገፊያ እየቆረቆረ ስላስቸገራት በወረቀት እንደጠቀጠቀችው በሹክሹክታ ድምፅዋ ነግራኝ ነበር:: በዚሁ ሾክሹዋካ ድምፅ ያጫወተችኝን አስታወስኩ:: ባልዋ እስዋ በወደቀች በሳምንትዋ እሱም ወድቆ ሆስፒታል እንደገባ ...ከዛም በሳምንቱ ሞቶ አንገትዋን ደግፋ ለቀብር እንደሄደችም ትዝ ይለኛል:: ታዲያ ከዚያ በሁዋላ እንደው አትናገረው እንጂ ቀልብዋ ተገፎ ነበር...ግን ሞትዋን ከሳምንት በሁዋላ ማን ያስባል? ግን ደግሞ ለአመታት አብረው የኖሩ ባልና ሚስት ተከታትለው መሄዳቸው ገረመኝ...ያውም በመውደቅ:: መቼም ሞት እሰይ አይባልም...ግን ለሁሉም ነገር ምክንያት ይኖረው ይሆን? ቤተሰቦቻቸው ይህንኑ አስበው ነው መሰል አላካበዱትም...እንኩዋን በቀላሉ አብረው ሄዱ አይነት:: መፅናናቱን ይስጣቸው:: ለሙዋቾቹም ነፍስ ይማር:: እንደው አይምሮዬ ላይ ተንጉዋለልና 'የኔስ መጨረሻ ደቂቃ እንዴት ትሆን?" ብዬ ትንሽ ተፈላሰፍኩ...ሞቴን አሳምረው አለ ያገሬ ሰው...ትልቅ አባባል! በቸር ያገናኘን!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ትርንጎ* » Mon Jul 11, 2011 7:31 pm

<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ውሸት በአንዱ ጾታ ይብስ ይሆን?>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
ይህንን ጥያቄ ያቀረብኩት ፈረንጆቹ "politicaly correct" የሚሉዋትን ፈሊጥ ልሞክራት ብዬ ነው እንጂ በሀበሽኛ መጠየቅ ያማረኝ "ለምን የኛ ወንዶች ይዋሻሉ?" ማለት ነው:: ግን ደግሞ 'የኛ" የምትለዋ ቃል ጠባብ አስተሳሰብ እንዳትመስልብኝ እንደው በደፈናው "ወንዶችዬ እንደው እምብርታችሁን የተያዛችሁ ይመስል ለምን ትቀላምዳላችሁ?" ብል ወገኖቼን አስቀይም ይሆን ብዬም ሰጋሁ::

ታዲያ እንዴት ናችሁልኝ? "ደግሞ ምን ይዘሽብን መጣሽ" እንዳትሉኝ:: እንደው የመዘባረቅ ጉዳይ በዛብኝና ገርሞኝ ነው:: የማይሌጄን ጉዳይ መቼም ታውቁታላችሁና የምውለው እንደኔው ጠና ካሉ ሰዎች ጋር ነው:: ታዲያ ከአንድም ሁለት ሰው ላይ የማያስፈልግ ቀሽም ውሸት አየሁና ገረመኝ:: አንዱ ባለፈው ሳምንት...ሌላኛው ዛሬ:: ከምር ግን ዝምታ ማንን ገደለ:: በቃ ጭጭ...መናገር ያልፈለጉትን ነገር:: እኔ አብዝቼው ይሆን? እንደው ያከበርኩትን ሰው ውሽት ዘጭ አድርጌ እንዳይ እያደረገኝ ተቸገርኩ...ከዛ ደግሞ የድሮውን በማጣቴ ልቤን ክብድ ጭንቅ ይለዋል: ጥፋቱ የኔው ይመስል:: አንድ እዚህ ዋርካ የሚመጣ ጉዋደኛዬ የነገረኝ አጭር ቁም ነገር ልቤ ውስጥ ዛሬ ስትብሰለሰል ዋለች:: 'የምትወጃቸውንና የምታከብሪያቸውን ሰዎች በጣም ቀርበሽ ውስጣቸውን ለማወቅ አትሞክሪ: ሁላችንም የተደበቀ ጉድፍ አይጠፋንምና' ...ዛሬም የሆነው ይኸው ነው:: ታዲያ ልቤ ክብድ...ቅርርርር ነገር...

ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ሁለት ጉዋደኛ አጣሁ: ማለቴም በቃ የድሮዎቹን እነሱን:: መናገሬ እንደሁ አይቀርም... ቅሬታዬ ይቀንስልኝ ብዬ ነው እንጂ:: መቼም ማስመሰል አልችል... እንኩዋን ፊቴን የሚያይ ሰው ይቅርና በስልክ ውስጥ በአነጋገሬ እያዛለሁ:: ኧረ በቴክስት እንኩዋን "ምን ሆነሻል?" ያለኝ ሰው አለ...ቀጭ ቀጭ ያለች የአንድ ቃል መልስ ሳበዛ...ሌላ ቀን ከዋርካ ፖስት መለስ ያለ ትረካዬን አሳጥሬ:: ለማናቸውም እንኩዋን ኖራችሁል: የኔ መተንፈሻዎች:: አትጥፉ!
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 709
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ጎማ እግሩ » Tue Jul 12, 2011 2:38 am

ትርንጎአችን!

መቼም አጠራሬን እንደማትከፊበት እርግጠኛ ነኝ:: አንቺ የማታውቂያቸው ብዙ አድማጮች እንዳሉሽ ሳትገነዘቢው አትቀሪም:: ጭጭ ከሚሉት አንዱ ነኝ:: ዛሬ ግን እኔንም የሚከነክነኝን ነገር አነሳሽውና አረፍሽ:: አገር እያለን አቶ እከሌ ትልቅ ሰው ወ/ሮ እከሊት ትልቅ ሰው ብለን ስንላቸው የነበሩ አንዳንድ መኳንንትና ወይዘራዝርት በቅርብ ስለማናውቃቸው አክብሮታችንን ለግሰናቸው እንኖር ነበር:: ከራሴ ልነሳልሽና እዚህ ባለሁበት አገር አዲስ ሆኜ ስመጣ ዶ/ር እክሌ እንጂኒየር አከሌ የተባሉ የሀገሬን ስዎች ሳይ ነገ እነርሱ የደረሱበትን የዕውቀትና የኑሮ ደረጃ ግምጅቼ ስለነሱ ያለኝ ግምት ከፍተኛ ሆኖ ነበር ኑሮዬን የጀመርኩት::

መቼም ውጭ ተመጥቶ ፍላጎቱና ጥረቱ ካለ በትምህርት የተፈለገውን ያህል መድረስ ይቻላልና:: እነዛ ብርቅየ የነበሩ አንቱ የተባሉትን ያገሬን ሰዎች ብቅርብ የማየት የማነጋገር ዕድሉ ሲገጥመኝ ትላንት ስለነሱ የነበረኝ ግምት እየዘቀጠ እየወረደ ሲሄድብኝ አንቺ እንዳልሸው ችግሩ የኔ ይሆን እያልኩ አሰላስላለሁ:: ስለ ኅብረተሰብ ማህበራዊ ግንኙነትና ሥነ-ልቦናዊ ሳይንስ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ዕውቀት ሲያስጨብጥ የሚውለው ፕሮፌሰር በቤተሰቡና በወገኖቹ ላይ ሸፍጥ ሲሰራ ማየት እንዴት ይጨንቃል መሰለሽ:: አሁን አሁንማ ተማርኩ አወቅኩ ከሚለው ሰው የሚወጣውን ውሸት መስማት እያስጠላኝ አለመቅረብ ላይ ነኝ:: እና ያንቺ ብቻ ስሜት አይደለም:: ደህና ሁኚልን:: በነገራችን ላይ ባለቤቴ የዋርካ አድንቂሽ ነች እሷም ሰላም ትላለች::ትርንጎ* wrote:<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ውሸት በአንዱ ጾታ ይብስ ይሆን?>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
ይህንን ጥያቄ ያቀረብኩት ፈረንጆቹ "politicaly correct" የሚሉዋትን ፈሊጥ ልሞክራት ብዬ ነው እንጂ በሀበሽኛ መጠየቅ ያማረኝ "ለምን የኛ ወንዶች ይዋሻሉ?" ማለት ነው:: ግን ደግሞ 'የኛ" የምትለዋ ቃል ጠባብ አስተሳሰብ እንዳትመስልብኝ እንደው በደፈናው "ወንዶችዬ እንደው እምብርታችሁን የተያዛችሁ ይመስል ለምን ትቀላምዳላችሁ?" ብል ወገኖቼን አስቀይም ይሆን ብዬም ሰጋሁ::

ታዲያ እንዴት ናችሁልኝ? "ደግሞ ምን ይዘሽብን መጣሽ" እንዳትሉኝ:: እንደው የመዘባረቅ ጉዳይ በዛብኝና ገርሞኝ ነው:: የማይሌጄን ጉዳይ መቼም ታውቁታላችሁና የምውለው እንደኔው ጠና ካሉ ሰዎች ጋር ነው:: ታዲያ ከአንድም ሁለት ሰው ላይ የማያስፈልግ ቀሽም ውሸት አየሁና ገረመኝ:: አንዱ ባለፈው ሳምንት...ሌላኛው ዛሬ:: ከምር ግን ዝምታ ማንን ገደለ:: በቃ ጭጭ...መናገር ያልፈለጉትን ነገር:: እኔ አብዝቼው ይሆን? እንደው ያከበርኩትን ሰው ውሽት ዘጭ አድርጌ እንዳይ እያደረገኝ ተቸገርኩ...ከዛ ደግሞ የድሮውን በማጣቴ ልቤን ክብድ ጭንቅ ይለዋል: ጥፋቱ የኔው ይመስል:: አንድ እዚህ ዋርካ የሚመጣ ጉዋደኛዬ የነገረኝ አጭር ቁም ነገር ልቤ ውስጥ ዛሬ ስትብሰለሰል ዋለች:: 'የምትወጃቸውንና የምታከብሪያቸውን ሰዎች በጣም ቀርበሽ ውስጣቸውን ለማወቅ አትሞክሪ: ሁላችንም የተደበቀ ጉድፍ አይጠፋንምና' ...ዛሬም የሆነው ይኸው ነው:: ታዲያ ልቤ ክብድ...ቅርርርር ነገር...

ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ሁለት ጉዋደኛ አጣሁ: ማለቴም በቃ የድሮዎቹን እነሱን:: መናገሬ እንደሁ አይቀርም... ቅሬታዬ ይቀንስልኝ ብዬ ነው እንጂ:: መቼም ማስመሰል አልችል... እንኩዋን ፊቴን የሚያይ ሰው ይቅርና በስልክ ውስጥ በአነጋገሬ እያዛለሁ:: ኧረ በቴክስት እንኩዋን "ምን ሆነሻል?" ያለኝ ሰው አለ...ቀጭ ቀጭ ያለች የአንድ ቃል መልስ ሳበዛ...ሌላ ቀን ከዋርካ ፖስት መለስ ያለ ትረካዬን አሳጥሬ:: ለማናቸውም እንኩዋን ኖራችሁል: የኔ መተንፈሻዎች:: አትጥፉ!
Rights go hand in hand with responsibility, with dignity, with respect for oneself and for the other.
ጎማ እግሩ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 864
Joined: Wed Jun 20, 2007 1:49 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests

cron