Ahmed-1 wrote:ሙዜ የከበረ ሠላምታዬ ካለህበት ይድረስህ!!
የጋዜጠኛው ማስታወሻ የሚለውን አንብቤ የሥነ ጽሁፍ ውበቱን አደነኩ:: አዝናናኝ:: የደራሲው የድርሰት ችሎታ መሰጦኛል:: ከዚያ ባሻገር ዘርማንዘሩን አልፈትሽም .....መችም ያንጎላ ልጅ አይደለም!!
ሰላም አህመድ .....የስነጽሁፍ ዉበቱ አዝናኝነቱ ምናምን ላይ ጥያቄ የለኝም .... እነዚህ ነገሮች በሰዎች የመዝናኛ ፍላጎትና አይነት ላይ የተመረኮዙ ናቸዉ .... እኔም ብዙም አላስደሰተኝም አልልህም .... ተክሉ ተክላይን እያፈላለኩት ነዉ ብልህ ምን ትለኝ ይሆን? ቂቂቂቂ .... ከምሬ ሲያስቀኝ የነበረ ገጸባህሪ(ግለሰብ) ነዉ ... ... ዘርማንዘሩጋም ምንም ጉዳይ የለኝም .... የወደፊት ባለቤቴም የሱዉ ዘር ናት ብልህ ምን ትለኝ ይሆን? ቆንጅዬ ኤርትራዊ .... ይህም እዉነት ነዉ ....
ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ አቋም አለው ብዬ በጭራሽ አላምንም!! ከዚህ ውጭ ኦሮሞን ደግፎ አማራን አጠቃ ወይም ተገላቢጦሹ በደራሲው ላይ ጥርስ አያስነክስም.....በኔ ግምት!
እዚህ ጋ ነዉ ልዩነቱ .... ኢትዮጵያዊ አቋም በቁጥር አላስቀምጠዉም በስሜትና በፍላጎት እንጂ .... .... ለዛም ነዉ ...ከላይ በፕሮፖጋንዳና በማህበራዊ የሞራል እሴት መካከል እየዋዠክ ነዉ ያልኩት ... ሁለቱ እጅግ ..እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ ....
የየትኛውም ፓርቲ ደጋፊ ወይም ተቃውሚ አይደለሁም... እናም የደራሲውን ብዕር እንጂ የፓለቲካ አቋም ከምንም ውስጥ አላስገባሁትምና እለፈኝ::
ቂቂቂቂ ... እንዴታለ ነገር ነዉ .... አስተያየትክን ሰጥተህ ጨርሰሀል እኮ :wink:
ባለፈው የርብቃ ዝምታ በሚለው መጽሀፉ ስለ አማራ የጻፈው እንዳበሳጨህ አነበብኩ:: በዚያ ዙርያ አስተያየቴን ለመስጠት አስቤ ይበልጥ ያስቆጣህ ይሆናል ብዬ በማሰብ ተውኩት:: አሁን ግን በግል ልጽፍልህ ወስኛለሁ!! ካስከፋህ እክሳለሁ :) ::
የቡርቃ ዝምታ ማለትህ ነዉ መሰለኝ ... ስለሱ መጽሀፍ አስተያየትህን ብትሰጠኝ አልከፋም .... ችግር የለብኝም .... ቂቂቂ .... በተደጋጋሚ ለማለት እንደ ሞከርኩት .... መጽሀፉን ትምህርት ቤት እያለሁ ነዉ ያነበብኩት .... መጽሀፉን በተመለከተም ... ከብዙ የኦሮሞ ...የትግራይ ...የደቡብ ልጆች ጋ ተወያይቸበታለሁ .... በጊዜዉም ብዙ ብዙ ስድብ ወቀሳ ... ደርሶብኛል .... ያንተዉም ከዛ በላይ አያስከፋኝም ... እኔን ያስከፋኝ በቡርቃ ዝምታ ዉስጥ ያለዉ .... ከብላክ ኤንድ ኆይቱ ጀርባ የጸሀፊዉ መርዛማ እቅድ ነዉ .... .......... እንዳመታደል ሆኖ ባርቆበታል:: ለ1 ሳምንት ኢንተርኔት አካባቢ ስለሌለሁ ... ከሳምንት በሗላ በግልም ይሁን ፊት ለፊት ....እስከፈለከዉ ድረስ ለመወያየት ፍቃደኛ ነኝ ...
ቂቂቂ ... በነገራችን ላይ ሁላችሁም ይህ መጽሀፍ የተጻፈዉ ለናንተ አይደለም ብላችሁ ምን ልትሉኝ ይሆን? ...ቂቂቂቂ ይህ የደራሲዉ ማስታወሻ የተጻፈዉ ለኪነ ጥበብ ፍጆታ አይደለም .... ታርጌት ኦዲየንሱም አብዛኞቻችሁ አይደላችሁም ....ቂቂቂ .... ፕሊስ በድጋሚ .... 1+1= 2 ነዉ ብላችሁ አታስቡ .... ይህ በሂሳብ እንጂ በፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ አይደለም ... 1+1= 3 ሊሆን ይችላል ...1 ሊሆን ይችላል ... ::
ኤኒዌይ ... ስላዝናናችሁ አመሰግነዋለሁ ...ምንስ ቢሆን ወገኖች አይደለን? :wink:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...