yekolo wrote:I've read his book, የቡርቃ ዝምታ, and I can tell you that it was pure garbage. Not only interms of content but also literary style.
ለሎቹንም መጣጥፎቹን አንበቤያለሁ... ከብርሀኑ ዘሪሁን ጋር ማወዳደር is a huge exaggeration if not a crime.
ትክክል እኔም እንዳንተ ነው የምለው::
እስቲ አንዴ ከበዓሉ ግርማ ልብ ጋር ከመቃብር ቃለመጠየቅ ያረኩትን ላቅርብ::
ቃለ መጠየቅ ከበዓሉ ግርማ ልብ ጋር ከመቃብር::
እኔ:- ሰላም ጤና ይስጥልኝ አቶ በዓሉ ግርማ ጥሪዬን አክብረው ስለተገኙልኝ ከልብ አመሰግናለው::
በዓሉ ግርማ:-እኔም ከልብ አመሰግናለው
እኔ:- በመጀመሪያ በዓሉ ግርማ ማነው?
በዓሉ ግርማ:- በዓሉ ግርማ ማለት እኔ ነኝ, እኔ ማለት በዓሉ ነኝ::
እኔ:- ቅቅቅ አይ ያንማ እኔ አውቃለው: እንዴው የት ተወለዱ ስለቤተሰብዎ አመጣት ማለቴ ነው ለአንባቢም ለማያቅዎት እንዲያውቅዎት ለማረግ ነው::
በዓሉ ግርማ:- ወደ እዛ ዘር ቆጠራችው የምትወስደኝ ከሆነ ከአሁኑ ብናቆም እመርጣለው: ምክንያቱም እኔ በኖርኩበት ዘመን ኢትዮጵያዊነቴን እንጂ ዘሬን የሚባልመት ዘመን ስለነበርረባክህ አደራ እዛ ውስጥ እንዳታርመጠምጠኝ::
እኔ:- ዋው ኧረ ቤናትዎት እኔ በዛ ወስጄው አይደለም ግድ የለዎትም ብዙ ሰው ያቅዎታል ያን እንዳይባሉ እጥራለው:: አሁን ይንገሩኝ በዓሉ ግርማ ማለት ማነው?
በዓሉ ግርማ:- የተወለድኩት ከእናቴ ከው/ሮ ያዳኒ ዳባ አቦ ሚያዚያ 16 ቀን 1928 ዓ.ም ሱጴ ነገዎ ቦሮ የገጠር ከተማ ውስጥ ተወለድኩኝ::...
እኔ:- እምም በኦሮሚያ መጽሃፍ የተነሳ ብዙ ሰው ትውልድዎ ከኤርትራ ይመስለው ነበር:...
በዓሉ ግርማ:- አታቁዋርጠኝ ያም ቢሆን እኮ አገሬ ነው! ወይም ነበር! ...
እኔ:- እሺ እሺ ይቅርታ ያርጉልኝ ስለ አባትዎ አልነገሩኝም::
በዓሉ ግርማ:- አዎን ያው እናዳልኩህ ከናቴ ከላይ እንደተጠቀሰውና ከአባቴ ከህንዳዊው ነጋዴ ሚስተር ባቡና ነበር የተወለድኩት:: ሱጴ የምትገኘው በቀድሞው ኢሊባቡር ጠቅላይ ግዛት መቱ አውራጃ ከመቱ ከተማ ደቡባዊ ምስራቅ በግምት 35 ኪ.ሜ ርቃ የምትገኝ የገጠር ከተማ ናት::
እኔ:- አሃ! አቶ ግርማ አባትዎት አይደሉም ማለት ነዋ ታዲያ?
በዓሉ ግርማ:- አዎን ወላጅ አባቴ አይደሉም የስጋ ዝምድናም የለኝም ያሳደጉኝ ናቸው:: እኔ ለትምህርት ስደርስ በትውልድ መንደሬ በሱጴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከ1 እስከ 4 ከተማርኩኝ በውሃላ አሳዳጊ አባቴ አቶ ግርማ እኔ በትምህርት አቀባበሌ በጣም ጠንካራ ሆኜ ስለተገኘሁኝ ወደ አዲስ አበባ በማምጣት በቀድሞው ዘነበ ወርቅ ት/ቤት በአዳሪ እንድማር አደረጉ:: ከ5 እስከ 8ኛም በአጥጋቢ ውጤት አጠናቀቅሁኝ:: ከዚያም ጎበዝ ተማሪዎችን ብቻ ወደ ሚቀበለው ጄነራል ዊንጌት ግብቼ ከ9 እስከ 12 ትምህርቴን በአጥጋቢ ሁኔታ በሚገባ አጠናቀኩኝ ከዛም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲት ተቀበሉኝ እዛም በአርት ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ቀጥሎም ወደ አሜሪካን በመሄድ በጋዜጠኛነት የማስተሬት ዲግሬዬን አግኝቻለው::
እኔ:- ከዛስ ወደ ትውልድዎ ወዲያው ነው የተመለሱት? ስራዎትስ?
በዓሉ ግርማ:- አዎን ወደትውልድ አገሬ ተመልሼ በቀድሞው ማስታወቂያና መርሃ ብሔር ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተመድቤ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ, የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ, ቤንግሊዘኛ ቋንቋ ይዘጋጅ የነበረውን ሐዲስ የተሰኘች መጽሄት ዋና አዘጋጅ በመሆንለጋዜጠና መጽሄት ብዙ ስራ ሰርቻለው::
እኔ:- (ለአንባቢ:- በአሉ ግርማ ቁመናና የግርማ ሞገስ ያላቸው ነበር ከላይ ነግረውኝ ያላሰፈርኩት ወይም የረሳሁት ነገር ቢኖር: አቶ ላዓሉ ግርማ ወላጅ አባታቸውን አያቁም ነበር:: ገና በልጅነታቸው ሕንዳዊው አባቱ ወደ ሀገሩ ህንድ(ቦንቤ) ተመልሱዋ)::
እኔ:- ሌላስ የሰሩት ? መቼስ ነው የድርሰት ስራ የጀመሩት?
በዓሉ ግርማ:- መጀመሪያ ድርሰቱን ላስቀድም:: ድርሰት የጀመርኩት በ1960ዎቹ ዓ.ም ነበር:: ከአድማስ ባሻገር, የህሊና ደወል, ሐዲስ, የቀይ ኮከብ ጥሪ, በመጨረሻም ኦሮማይ የተሰኘ መጽሃፎች ለአንባቢ አበርክቻለው ወይም ጽፌያለው::
እኔ:- (ለአንባቢ:- ከአቶ በዓሉ ግርማ ጋር ያለኝን ቃለ መጠየቅ እቀጥላለው:: ከጥያቄዎቹም ላቀርብላቸው የተዘጋጀሁት የአሁኑን የኢትዮጵያን ፖለቲካም ሆነ የወደፊት እጣ ፈንታዋ ምንድን እንደሚሆን ግመታቸውን, የአለም ለውጥ በአፍሪካ ላይ እያመጣ ስላለው, የዘር ልዩነት, ስለኤርትራና እና ስለኤርትራ ኢትዮጵያዊነት, እንዲሁም ከደርግ ጋር ብዙ በቅርበት ያገለገሉ (በተለይ ለመንግስቱ ሃይለማሪያም የቅርብ ታማኝ በነበሩበት ግዜ ያዩትንና የገጠማቸውን:: እንዲሁም በተለይ ሰሞኑን ስሙ እየተነሳ ስላለው ስለተስፋዬ ገብረዓብ ያላቸው አስተያየት ከሳቸው ጋር መመሳሰል እና አለመመሳሰል, ሌላም ሌላም እንደተመቼኝ ከልባቸው ጋር ከመቃብር ያቀረብኩላቸውን አቀርባለው, ስለወደፊቱ ምርጫ ማን እንደሚያሸንፍ የመሳሰሉትን አቀርባለው ከግዜ ጋር::) ደህና ቆዩኝ