የእለቱ ሙዚቃ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ገልብጤ » Sat Jun 30, 2012 6:30 pm

recho wrote:.........

መዘንጊያም ቀን የለሽ የኔ አይናም
አትርቂም ከሀሳቤ የኔ አለም
ዙሪያው ይጨልማል የኔ አለም
ሳጣሽ ካጠገቤ የኔ አለም
በስራውም ሰአት አይረሳሽም ልቤ
ጭንቀትና ሀሳብን የኔ አለም
አርፎ ለመተንፈስ የኔ አለም
በመውደድ መስክ ላይ የኔ አለም
ፍቅርን ለመናፈስ የኔ አለም
ቃልሽ መአዛ ነው እደከመ መንፈስ

ከጎኔ እንዳላጣሽ የኔ አይናም
የኔ እውነተኛ የኔ አይናማ
ማፍቀርና ማመን የኔ አይናማ
ይቁዋጭልን ለኛ የኔ አይናማ
እኔም ባንቺ በቃኝ
ሰው ለመውደድ አለደክምም ዳግመኛ
ሀሳብሽ ተሳክቶ የኔ አይናማ
እስኪወድክ ከክኔ የኔ አይናማ
አብረ ይቁረሱና የኔ አይናማ
ሆድሽና ሆዴ የኔ አይናማ
በምድር መደሰቱም መለየቱም ይሁንልን ላንዴ


ሪኮ አሪፍ ምርጫ ነው ....ይህ ዘፈን የተመረጠላት ማን ትሆን :roll: :roll:
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby recho » Sat Jun 30, 2012 11:26 pm

ገልብጤ wrote:ሪኮ አሪፍ ምርጫ ነው ....ይህ ዘፈን የተመረጠላት ማን ትሆን :roll: :roll:
ለምወዳት ... ለምንሰፈሰፍላት ... በናፍቆቴ ግልትት ላለችዋ እናቴ .. :)
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ማያዬ » Mon Jul 02, 2012 2:48 pm

ስጥ እንግዲህ wrote:ማያዬ ነፍሴ.....ስለም ነው ሁሉ ነገር? እንዲህ ጥፍት ይባላል እንዴ......ሰው ያስባል አይባልም?
ይቺን የአስቴር ጎንደርኛ ብጋብዝሽ ምን ይልሽ ይሆን?

http://www.youtube.com/watch?v=e3jf4gFF ... re=related

ለሁላችንም የተቀደሰ ቀን


ሄይ ስጥዬ ጀለሴ
እንዴት ነህ ነፍሴ....ሁሉም ሰላም ነው እኔ መች ጠፉ በእግር በፈረስ አስፈለግን እኮ ....... የአስቴር ጎንደርኛ አሪፍ ነው

እስቲ ይቺን ልጋብዝህ

http://www.diretube.com/selamawit-gebru ... 3617a.html
''''ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ''''
ማያዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Mon Jan 29, 2007 2:48 pm

Postby መላጣ » Mon Jul 02, 2012 3:58 pm

ስጥ እንግዲህ ሰላም እላለሁ መጣሁ:: ቤትህ ደርቷል በተለይ የማያዬ ምርጫ ላንተ እንዴት ደስ ይላል እባክህ??? ምርጫዋ ዘፈኑን ከሆነ እሰየው ልጅቷን ከሆነ ግን የለሁበትም:: እስኪ ወደፊት ለሀሎ ያብቃችሁ:: :D
http://www.youtube.com/watch?v=ezp5rU2Icuw
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ማያዬ » Tue Jul 03, 2012 1:46 pm

በተለይ የማያዬ ምርጫ ላንተ እንዴት ደስ ይላል እባክህ??? ምርጫዋ ዘፈኑን ከሆነ እሰየው............ልጅቷን ከሆነ..........ግን የለሁበትም::

አንተ መላጣ ምነው ልጁ ያላሰበውን ባታሳስበው....ምቀኛ አታሳታኝ አሉ


ይቺኛዋ መልክታ ደስ ይላል....ማለቴ ዘፈና እሺ መላጣ
http://www.diretube.com/asrebeb-tadege/ ... 5075c.html
''''ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ''''
ማያዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 207
Joined: Mon Jan 29, 2007 2:48 pm

Postby መላጣ » Thu Jul 05, 2012 5:09 pm

መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Sat Jul 07, 2012 5:13 pm

ትዊስት ወደግራ ትዊስት ወደቀኝ
በቅዳሜው ምድር ቢራ ናፈቀኝ
ስጥነት ብቅ ብለህ ጥሜን አርሰኝ:: መልካም ሰንበት::
http://lucyzare.com/Videos.aspx?VDID=376
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ስጥ እንግዲህ » Mon Jul 09, 2012 5:40 pm

ሄይይይይይይ....ማያዬና መላጣ ሁሉ አማን ነው? ሰሞኑን ትንሽ ከሀገር ልጆች ጋር ድድ ለማስጣት ወደ ዳላስ ብቅ ብዬ ስለነበር ለዋርካ ጊዜ ከየት ተገኝቶ: ቀን ቀን ስቴዲዩም ማታ ማታ አበሻ ቤት ቀውጢ ሆነን ነው የሰነበትነው::

ማያዬ በዘፈን ለላክሺው መልሱን በዘፈን ተቀበይ:: http://www.youtube.com/watch?v=06hm0wNm ... re=related

መላጣ....ዳላስ መላጣ ባየሁ ቁጥር አንተ እየመስልከኝ ሳፈጥ ነው የሰነበትኩ: ለካ አንተ ዋርካ ላይ ፓርቲውን አጡዋጡፈህዋል:: እስቲ ዳላስ ከጨፈርንባቸው ሙዚቃዎች አንዱዋን ልጋብዝህ
http://ecadforum.com/ethiopianvideo/201 ... -new-dele/

በሉ እንግዲህ አትጥፉዋ!!!!
ስጥ እንግዲህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1002
Joined: Fri Sep 29, 2006 1:30 pm

Postby መላጣ » Mon Jul 09, 2012 8:38 pm

ሰላም ስጥነት በቃ ዳላስ ላይ መላጣ ባየህ ቁጥር ስትገላመጥ ነበርክ:: ተገላማጩ አንተ መሆንክን ባውቅማ ኖሮ
አስቁሜ እጠይቅህ ነበር ካዳራሹ ወደጎን የቆሙትን መላጣዎች አይተሀቸው ከሆነ ጥቁር መነጥጽር ካደረጉት መላጣዎች አንዱ ነበርኩ አመለጥኩህ :o :o

ማያዬ ይህች ዘፈን ቁም ነገረኛ ክመህኑዋም በላይ አስተማሪነቷን:-
ለጽድቂያ አለው ፀሎት ለቅጽፈት እንዳይሆን
ቂም ይዞ ይቅርታ ምን ይጠቅም ይሆን (ያስተምርስ ይሆን)
በማለት የምታስተምር መሰለኝ እስቲ ረጋ ብለሽ አዳምጪያት :(
http://www.diretube.com/seyoum-moges/ma ... 4b32d.html
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ስጥ እንግዲህ » Tue Jul 10, 2012 4:17 pm

መላጣ........ቆንጆ ሙዚቃ ነው ያመጣህው:: በተለይ የዘፋኙ ድምጽ ከውስጥ የወጣ ኦርጅናል ቅላጼ አለው:: ተስፋ ያለው ድምጻዊ ነው::
መላጣ wrote:ሰላም ስጥነት በቃ ዳላስ ላይ መላጣ ባየህ ቁጥር ስትገላመጥ ነበርክ:: ተገላማጩ አንተ መሆንክን ባውቅማ ኖሮ
አስቁሜ እጠይቅህ ነበር ካዳራሹ ወደጎን የቆሙትን መላጣዎች አይተሀቸው ከሆነ ጥቁር መነጥጽር ካደረጉት መላጣዎች አንዱ ነበርኩ አመለጥኩህ :o :o

ማያዬ ይህች ዘፈን ቁም ነገረኛ ክመህኑዋም በላይ አስተማሪነቷን:-
ለጽድቂያ አለው ፀሎት ለቅጽፈት እንዳይሆን
ቂም ይዞ ይቅርታ ምን ይጠቅም ይሆን (ያስተምርስ ይሆን)
በማለት የምታስተምር መሰለኝ እስቲ ረጋ ብለሽ አዳምጪያት :(
http://www.diretube.com/seyoum-moges/ma ... 4b32d.html
ስጥ እንግዲህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1002
Joined: Fri Sep 29, 2006 1:30 pm

Postby ስጥ እንግዲህ » Fri Jul 13, 2012 4:33 pm

ሰላም...ሰላም...በአርብ ምድር አንደበራ::
እስቲ ይቺን ቆንጆ የትግሪኛ ዘፈን እያንቆረቆራችሁ ነቃ በሉ

http://www.youtube.com/watch?v=AqMVyAEF ... re=related

ጥሩ ድምጽ ሸጋ ቅንብር

በሉ እንግዲህ መልካም አርብ...........
ስጥ እንግዲህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1002
Joined: Fri Sep 29, 2006 1:30 pm

Postby መላጣ » Sat Jul 14, 2012 3:16 pm

በቅዳሜው ለትካዜ ቢጋብዘንም ቅሉ ቢራ ከማንቆርቆር አይገታንም:: መልካም ሰንበት ከቴዲ ጋር!
http://www.ethioclips.com/video/1404/Te ... Album-2012
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Wed Jul 18, 2012 8:17 pm

መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ስጥ እንግዲህ » Fri Jul 27, 2012 2:24 pm

አማን ናችሁ......መላጣ እንዴት ነው ዛሬ ደሞ ያንን ቢራ በጠዋት ተያያዝከው እንዴ? ከትንሽ ሰአት በሁዋላ እመስለሀልሁ::

ዛሬ ያመጣሁልችሁ ከወትሮው ለየት ያለ ነው:: ከ40 አመት በፊት በሸክላ የተቀረጹትን ድንቅ የሙዚቃዎች ስብስብ ነው:: እነዚህን ሙዚቃዎች ሳሰማቸው አንድ ጎረቤቴ ከእነ ባለቤቱ እንባ እየተናነቃቸው ነበር::ለነገሩ እኔም ብዙ ተፈታትኖኛል:: በሉ እንግዲህ ኮምኩሙ:: ብትችሉ ምን እንደተሰማችሁ ወይም ስለ ዘፈኖቹ ያላችሁን አስተያየት ወርወር ብታደርጉ ደስ ይለኛል;;

http://www.youtube.com/watch?v=WfBDKmlg ... ure=relmfu

በነገራችን ላይ ሙላቱ አስታጥቄ ነው የብዙዎቹን ታዋቂ ዘፋኞችን ሙዚቃ ያቀናበረው:: ታድያ ምን ነካው እዘንድሮ ዘፋኞች ላይ?

"ደስ ይላል በጊዜው" ከሚለው የእሳቱ ተሰማ ሸክላ ይቺን ታገኛላችሁ

'ሁሉ እንደነበር መቺ ይገኛል ከቶ
መበላሸቱ አይቀር ውሎ አድሮ ሰንብቶ"
መልካም አርብ
ስጥ እንግዲህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1002
Joined: Fri Sep 29, 2006 1:30 pm

Postby መላጣ » Mon Jul 30, 2012 2:49 pm

ስጥ እንግዲህ ያቀረብከው ቅንብር ደስ የሚልና ዞር ብለን እንድናስብ ከማድረጉም በላይ ብዙ ትውስታዎችን የሚቀሰቅስ ምርጫ ነው:: ምስጋን ይገባኌል!!!

እስቲ ወደ ሲዳሞ ወረድ እንበል :) http://www.youtube.com/watch?v=9UNcF3WCoN4
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest