ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው!

Postby ጣዕም » Sat Aug 15, 2009 6:45 pm

የቶሮንቶና አካባቢው ነዋሪዎችን በድጋሜ ለማዝናናት የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ዝግጅታችውን ዕሁድ ኦገስት 23 2009 ያቀርባሉ:: በቦታው በመገኘት ለመዝናናት ተዘጋጁ.. http://www.haddisnigat.org
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

Postby brookk » Mon Aug 17, 2009 2:24 pm

Code: Select all
የቶሮንቶና አካባቢው ነዋሪዎችን በድጋሜ ለማዝናናት የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ዝግጅታችውን ዕሁድ ኦገስት 23 2009 ያቀርባሉ :: በቦታው በመገኘት ለመዝናናት ተዘጋጁ


ያስቀመጥከውን ዌብ ሳይት ክሊክ ከማድረጌ በፊት -- እናንተው እራሳችሁ ያላችሁበት ዝግጅት መስሎኝ - አንተን በመድረክ የማይበት አጋጣሚ ተፈጠረ ብዬ በደስታ ፈገግ ብዬ ነበር ::
ከምር ግን ክርስትያንም ይኖርበት ይሆን ብዬም ልጠይቅህ ነበር -- ቢሆንም ግን እስቲ እንሞክረዋለን -- ሳቅ በሳቅ ለመሆን ::

ምነው ግን ሁላችሁም አንድ ላይ ተግተለተላችሁ ?
ታምራት ዘፋኙ, እነሻምበል በላይ ሌሎችም ሰሞኑን ቶሮንቶን ሊያጣብቧት ነው :: ሁሉንም የምንገባ ከሆነ ግን ከሰርን ማለት ነው :lol: :lol:

ጣዕሙ -- በስፖንሰርነቱ ውስጥ ካለህበት ግን በናንተም እንዳይደገም አንድ ቅሬታ ላስመዝግብ ::
ባለፈው እነቢኒያም -- ሸምሱን ያመጡ ጊዜ የተካሄደው ትኬት ሽያጭም ሆነ በሩ ላይ የሰዉ አገባብ ሁኔታ እጅግ አሳፋሪ ነበር ::
በስርዓት ሰልፍ መያዝ ከምር ሞኝነት ይመስላል :: ሰልፉ በብሉር ስትሪት ኖርዝ በኩል ባለች ትንሽ ስትሪት ኮርነር ላይ ሁሉ ታጥፎ የሄደና የረዘመ ነበር :: ሰዉ የተሰለፈው አንድ ሰዓት ቀድሞ መጥቶ ነበር : በብዛት ቀድሞ የገባው ግን በኋላ የመጣውና ቀጥታ በትኬት መቁረጫው በፊት ከሰልፍ ውጭ የቆመውና በትውውቅ የሚተማመነው ብቻ ነው :: እናም ያሰጠላ ነበር ግርግሩ :: ፕሊስ ይህ እንዳይደገም - የሰዉ ቁጥር እንደዛ የሚበዛላችሁ ከሆነ :: "የአበሻ ቀጠሮ" ጋር የሚመሳሰሉ መጥፎ ባህሪዎቻችንን እንድናስወግድ እስቲ እናንተ መሪ ሁኑ ::

ታምራትንና ላንተ ስል ደግሞ :lol: :lol: ይህንን ኮሜዲ ለማየት ሞክራለሁ :: እንደተለመደው አንተንና ክርስትያንን በዐይን አያችሁ ይሆን እንዴ ብዬ ልመኝ :: እስቲ የዛ ሰው ይበለን -- መቀነቱ አሁንም ካልጠለፈን ::
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

ጉድ ነው

Postby ዋኖስ » Mon Aug 17, 2009 4:24 pm

ሄሎ ዉዶች የጥንቶቹ

ጣዕም ታዲያስ! እናንተ ሥራችሁን አልፈታችሁም ጎበዞች ናችሁ!! በርቱ!

ብሩክ! አንተ ብቻም አይደለህ በቦታዉ የምትገኘው "ተጋባዥ" እንግዳም ሁሉ አለ!! ቅቅቅ ከመጣሕ ጉድህ ነው! መቼም!! ተጋባዥ እንግዳው ጣዕምና አንተን ማየት ይፈልጋል!!

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby brookk » Mon Aug 17, 2009 5:07 pm

ዋኖሴው የዳሞት ልጅ - የጥንቱ የጧቱ
አሁኑኑ ሳቅ በሳቅ ሆንኩልህ --- ጉድህ ፈላ ስትለኝ :: ምን የኔ ብቻ የጣዕሙም ሊፈላ ነው -- የክርስትያንንስ ድምጹንም ሰምቻለሁ - አልያዝ ያለው ጣዕሙ ነበር -- ራሱን ሊደብቅ ቢሞክርም ትኬቱን ሲያሻሽጥ ጋማውን እለዋለሁ ::

"ተጋባዥ" እንግዳው አንተ እንዳትሆንና ከነጥምጥምህ እንዳላይህ :: እኛስ እኛ ነን - ምን እንዳይቀርብን :: ሚስት የለንም ብለን አልዋሸን :: ይብላኝ ለናንተ አይነቱ -- አንዴ ተማሪ አንዴ ወያኔ ሲገባ የናቴን ጡት የቦንቡ ፍንዳታ አስጣለኝ ብላችሁ ለዋሻችሁት :lol:

"ምጣና" እንይህ እስቲ
ዋኖሴ ያንን የጥንቱን -- እንደልባችን እንጣጥ እንጣጥ ያልንበትን ጊዜ በማስታወስ እጅ ነስቻለሁ -- አይጥፉ እባክዎትን -- እኔን ክርስትያኖና ብርሀናዊት ከሚላፉበት ቦታ አያጡኝም :lol:
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby ጣዕም » Mon Aug 17, 2009 10:11 pm

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ብሩኬ ወዳጄ
ደህና ነህ ወይ? በጣም ደስ አለኝ ጎራ በማለትህ:: ምነው ግን የቅርብ ሩቅ ሆንክ? ባለፈው ዓመት ለምልክት ቅጠልያ ቀለም ጨርቅ አንጠልጥየ በር ላይ ብጠብቅህ የውሀ ሽታ ሆንክብኝ:: እንደው የመተያያችን ጊዜ እራቀብኝ:: መጪው ዕሁድ ግን ሳንተያይ አንቀርም ቀልቤ ነግሮኛል: ቅቅቅ ክርስቲያንም በቃ ሁሌ እንደፎከረ ነው;;
እንልከው የሁላችን መግተልተል የኮሚኒቲ አባላትን ከማሰልቸት አልፎ ኪስን ያራቁታል:: መቸም የመጀመሪያ አዘጋጆቹ እኛ ነበርን ሆኖም ሌሎችም በግላቸው ከእኛ በኍላ እንሞክር በማለት እንዳየህው የተለያየ ዝግጅት ሊያደርጉ ደፋ ቀና ይላሉ:: ብቻ ሁላችንም ይቅናን:: ሌላ ምን ይባላል ወገን::

ኮሜዲያን ክበበው ገዳ በመጣ ወቅት የነበረዉን የትኬት ሽያጭና የበር ላይ ችግር አይነት በእኛ በኩል እንዳይደገም በማሰብ አንድ ሰው ትኬት ከሁለት ሰው በላይ መግዛት እንደማይችል በቅድሚያ በዕለቱ ለማሳሰብ እንጥራለን:: ዝግጅቱም በስዓቱ እንደሚጀመር ስፖንሰር ካደርጓቸው ድርጅቶች ማረጋገጫ አግኝቻለሁ:: አይዞንን ብቻ አንተ ገተልተል አድርገህ አምጣቸው ውዶችህን; ቅቅቅ

እስቲ እባክህ አሁን እንኳን እንገናኝ:; እኔን አታጣኝም
ቸር እንሰንብት
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

Postby ጣዕም » Mon Aug 17, 2009 10:25 pm

ሰላም ሰላም ዋኖሴ
እንዴት ነህ ወገን ደህና ነህ ወይ? የሳይቨር ልጆች የጥንቶቹ ትናፈቃላችሁ:: እንጀራ ፍለጋ ደፋ ቀና ስንል የስንት ወዳጆች ትውውቅ ተዘነጋ:: ዋኖሴ; ዋርካ ስል ስራዎችህን አነባለሁ በርታልኝ::

መቸም እንዳቅማችን እንሞክራልን:: ምንም እንኳን ጊዜና አጋጣሚው እየጠፋ እንደምንፈልገው ባይሆንም በየወሩ ወቅት እየጠበቅን እርስ በእርሳችን እንሳሳቃለን እንማማራለን:: አልፎ አልፎም ይህን የመሰለ ዝግጅት በማቅረብ ወገኖቻችን ጋር እንዝናናለን:: መቸስ የጣይቱ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ምስጋና ይግባቸው ወደፊትም የእኛንም ጭምር ደብለቅ እያደርግን እንቀጥላለን:: ቅቅቅ

እንግዶቻችንን በናፍቆት እንጠብቃለን:: ቅቅቅቅ ጠርቀምቀም ብላችሁ ኑ! ከመግቢያው በር ላይ ደግሞ ምልክት ይዠ እጠብቃችኍለሁ::

እስከዛው ቸር ይግጠመን
If there is a book that you want to read, but it hasn't been written yet, you must be the one to write it.
--Toni Morrison
ጣዕም
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat May 01, 2004 2:02 am
Location: canada

Postby ዋኖስ » Wed Aug 19, 2009 12:54 am

አመሰግናለሁ! ጣዕም! ተጋባዥ እንግዳዉ ቤትህ ሊመጣ ይችላል ተዘጋጂ! ቅቅቅ ብሩክ ግን ካለ አይመጣም! ቅቅቅቅ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው!

Postby የግልነስ » Wed Aug 19, 2009 3:35 am

ጣዕም wrote:የቶሮንቶና አካባቢው ነዋሪዎችን በድጋሜ ለማዝናናት የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ዝግጅታችውን ዕሁድ ኦገስት 23 2009 ያቀርባሉ:: በቦታው በመገኘት ለመዝናናት ተዘጋጁ.. http://www.haddisnigat.org


*************************************************

ስላም ጣእምዩ እንዴት ነህልኝ ብሮ :?:
እነ አለምፅሀይን (ጣይቱ መአከልን) ስላም በልልኝ መቼም የቅርብ እሩቅ ከሆንኩኝ ስነበትኩኝ ከነሱም ጋር አይገርምህም...............ምንለበት እኔም እንደ ብሩክ መገኝት ብቸል ሀሪፈ ነበር........................

ዋኖስቻን እንዴት ነህልኝ ብሮ :?: ሁሉም አማን አገሩ ስፈሩ መንደሩ አረ ሁሉም ቅቅቅቅቅቅቅቅ ስላም ነው ያቺን ቤት ከዘጉብን ቦሀላ መተያየት ጠፋ ይገርማል

ከብዙ መውድድድ ጋር
የግልልልልልልል
የግልነስ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 862
Joined: Thu Feb 03, 2005 2:42 am
Location: united states

Postby brookk » Wed Aug 19, 2009 1:57 pm

Code: Select all
ኮሜዲያን ክበበው ገዳ በመጣ ወቅት የነበረዉን የትኬት ሽያጭና የበር ላይ ችግር አይነት በእኛ በኩል እንዳይደገም በማሰብ አንድ ሰው ትኬት ከሁለት ሰው በላይ መግዛት እንደማይችል በቅድሚያ በዕለቱ ለማሳሰብ እንጥራለን :: ዝግጅቱም በስዓቱ እንደሚጀመር ስፖንሰር ካደርጓቸው ድርጅቶች ማረጋገጫ አግኝቻለሁ :: አይዞንን ብቻ አንተ ገተልተል አድርገህ አምጣቸው ውዶችህን ; ቅቅቅ


ክበበው የሚለው ስሙ አስቸግሮኝ ነበር ሸምሱ ያልኩት:: ክበበው በመጠኑ አስደሰተን -- በመጠኑ! አጠረ ዝግጅቱ :: ለዕረፍት የሚሄድበትም ጊዜ በዛ --- ቢሆንም ግን በመጠኑ ዴስ ብሎን አመሸን --- :lol: :lol: የትኬት አሻሻጩንና የስፖንሰሮቹን ብቃት ሳስበው ግን --- አልፎ አልፎ -- "ዘፋኝ አመጣን" ምናምን ብለው ሲያስተዋውቁ ባልሄድስ የሚል ሀሳብ ብልጭ ይልብኛል :: መቼ ይሆን "እኛ" --- "እኛ" ለሆነው ነገር ክብርና ስርዐትን ምንሰጠው ?
ለመሆኑ ሙቪ ወይም ሬስቶራንት ስንሄድ ከምንይዘው ሰልፍ (ከሌሎች ጋር) ንቅንቅ እንላለን ? ሰውነታችን ሳይሆን ዓይናችን ከመስመር ዝንፍ የሚልብን ስንቶቻችን ነን ::
አወኩሽ ናኩሽ --- ድክመታችን !

ጣዕሙ ምናልባት ከስፖንሰሮቹ መሀል አንዱ አንተ ከሆንክ (እንደሌለህበት ፍንጭ ብትሰጥም) እድሉ አላችሁና እስቲም እኛም እንደ"ሌሎቹ" በስርዐት እንድንገባ አድርጉ ::

ዋኖስ -- አንተ እንግዳ ይኑርህ እንጂ -- አይዞን ዕንግዳህን ቀና ብለን አናይም --- ከምር ግን -- ምናልባት የሚለውን ሀሳብ ትቼ የግድ መሄድ አለብኝ ብዬ ወስኛለሁ :lol: :lol: ከመጣህ ቅዳሜ ጧት ማርያም ቤተክርስትያን ቼክ አድርገኝ ቅቅቅ እሁድማ አልቀርም ::
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby ክርስትያን06 » Wed Aug 19, 2009 4:19 pm

ሰላም ሰላም ሁላችሁም:

ደስ የሚል ዜና ነው... ዘንድሮስ አያመልጠኝም ብዬ ለራሴ ምያለሁ..... ሰንኮፍ ካላገጠመኝ....ጣዕማችን....እንግዲህ አንተን ፍለጋ አይኔን በራፍይ ላይ ማጎረጥረጤ አይቀርም::

ብሩኬ አንተንስ ማወቅ አያቅተኝም.. በአካል ባላይህም ከሰው መሀል ለይቼ የማውቅህ ይመስለኛል... ስማ ደግሞ እንዳለፈው እንዳትጠፋ አደራ.. :(

ዋኖሴ እንግዳችን ስለሆንክ በቀይ ስጋጃ ምንጣፍ እንቀበላለን አንተ ብቻ ምጣ::

በሉ እንግዲህ እዚያው እንገናኝ ..

ብሩኬ ስትደርስ ስልክ ምታልኝ::
ክርስትያን06
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 601
Joined: Fri Sep 08, 2006 5:15 pm

Postby brookk » Mon Aug 24, 2009 2:22 pm

"ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው"

3:00 pm ዝግጅቱ የሚጀመር ሲሆን 2:30 pm በሩ ይከፈታል ይላል ማስታወቅያው ::
አረፈድን ብለን ተጣደፍን --- 2:55 ደረስን ትኬታችንን ቆርጠን --- ቦታ መምረጥ ሳንቸገር የሚመቸን ቦታ ተቀመጥን ::
------
ደከም ያለ ጭብጨባ ተሰማ ----- ለማንኛውም ዝግጅቱ ተጀመረ ::
በአበሻ ምድር እንመራሀለን ብለው የተቀመጡ ጥቂቶች በወጣቱ ትውልድ ላይ ያደረሱት በደል1 -- ስደት -- ሽሽት ትውስታ ..... ሩጫ,
አዎ ሽሽት የችግራችን ሁሉ መፍትሄ መሆኑን ያስታወሰ መልዕክት በዝግታ በአዕምሯችን ተሰራጨ -- አለምጸሀይ ወዳጆ የወጣቱን ትውልድ መከራ ከቤተሰቧ ታሪክ ጋር, ሳይጠገብ ያጣችውን የወላጆቿን ፍቅርና --- በድንገት ህይወታቸው ይቺን ምድር ለአንዴና ለመጨረሻው ሳይሰናበተው ያስረከቧትን የወንድሞቿን አደራ -- ልጅ መውለድ አምሯት -- በሀላፊነቷ ምክንያት አምልጧት የሚሰማትን ስሜት በዕንባ ታጅባ ስታሰማን ተመልካቹ አብሯት በጸጥታ ያነባ ጀመር --- ጌትሽ ወንድሟ በለጋ እድሜው ብሄራዊ ውትድርና ሸሽቶ አሜሪካ ከመድረሱ በፊት በሱዳን በረሀ ያጋጠመው ችግርና የልጅነት ፍቅሩን አንስቶ ከህመም ስሜቱ ታግሎ ሲያወራ ሳየውና በአካባቢዬ የተቀመጡት ሰዎች ፍጹም በስሜት የተሞላ ለቅሶ ስመለከት ---- የዝግጅቱን ርዕስ እንደገና ለማየት ተገደድኩ ---

ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው ---- ወይ አለመገጣጠም አልኩ ---- በርግጥም ውነተኛ ታሪካችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ዝግጅት ነው ---- "ወንዶች" አሉ ጠንካሮች ናቸው : ለቅሶን ይታገሉታል ---- ድሮ ቀረ --- ወንዶቹም አለቀሱ --- በዝግጅቱ ተመሰጥኩ - በታሪኩም ከልብ አዘንኩ --- እንባን ግን ተቆጣጠርኩት -- ድሮ የተወራላቸው "ወንዶች" ውስጥ እራሴን አገኘሁት :lol:
የጣይቱ የኪነጥበባት ማዕከል ---- ሐዲስ ንጋት የቶሮንቶውም ምንኛ ድንቆች ናችሁ :: የምታፈሱትን ጊዜና ጉልበት -- ካለው የሰሜን አሜሪካ ኑሮ ጋር ሳስበውና የሌሎችንም የአገሬ ሰዎች እገዛ ደረጃ ስገምተው በእጅጉ አከበርኳችሁ :: ቀናሁባችሁም ::
በርቱ
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby ሊስትሮው » Mon Aug 24, 2009 5:40 pm

brookk wrote:"ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው"---- በርግጥም ውነተኛ ታሪካችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ዝግጅት ነው ---- "ወንዶች" አሉ ጠንካሮች ናቸው : ለቅሶን ይታገሉታል ---- ድሮ ቀረ --- ወንዶቹም አለቀሱ --- በዝግጅቱ ተመሰጥኩ - በታሪኩም ከልብ አዘንኩ --- እንባን ግን ተቆጣጠርኩት -- ድሮ የተወራላቸው "ወንዶች" ውስጥ እራሴን አገኘሁት :lol:


.................... ደረቅ ............ :cry:
ሊስትሮው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 233
Joined: Tue Feb 03, 2004 11:30 pm

Postby brookk » Mon Aug 24, 2009 8:45 pm

ሊስትሮው wrote:
.................... ደረቅ ............ :cry:


ታድያ በየሜዳው ዝም ብለን እንልቀቀው? :shock:
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby ሊስትሮው » Tue Aug 25, 2009 3:27 pm

brookk wrote:
ሊስትሮው wrote:
.................... ደረቅ ............ :cry:


ታድያ በየሜዳው ዝም ብለን እንልቀቀው? :shock:


ኡፕስ ለካ ሜዳ ላይ ነበራቹ ኔ ደሞ ኮ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ መስላቹኝ :) ......ቢሆንም ቢሆንም ግን ምን አለህ ቢደማህ :P ......አረ ባክ ያቺ በረሮ የሆነበት ስሟን ያየሁ መስሎኝ :?: መቸም ስራዋ ገነት አያስገባት ንዳው ትለፋለች ንጂ :D
ሊስትሮው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 233
Joined: Tue Feb 03, 2004 11:30 pm

Postby brookk » Tue Aug 25, 2009 4:22 pm

ሊስትሮው
ምናለ ቢደማህ ? ትቀልዳለህ
ሜዳና አዳራሽ አሁን ምን ልዩነት አላቸው ? አዳራሹም ሰፊ --- ሜዳውም ልቅ
እኛ የለመድነው --- ሰው ሳያየን -- ሳይታዘበን ወደውስጥ ገባ ብለን --- ጠበብ ያለውጋ ነው --- ስቅስቅ ብለን ምናፈሰው አባ! ዕንባችንን

በረሮማ ደከመች -- አረጀች እሷም --- ሄዶ ሄዶ መቼም ማርጀት አይቀር :lol: :lol: ተለወጠች እንደድሮም መዝለል ተወች
ቢሆንም በጣሙን ናፍቃሀለች --- እራስህን በራስህ በሷ ስም እንድትስምም ጋብዛሀለች
በል ኢንጆይ ዩርሰልፍ

በነገራችን ላይ ሰሞኑን በጣም ተከስተናል -- አትጥፋ
አርዕስቱን ግን አትርሳ --- ቶሮንቶ ዳግም በሳቅ ሊፈነዳ ነው - ነው የሚለው :: ከለቅሶው በኋላ ሳቅ በሳቅ ሆነን ነበር --- ጣዕሙንም በአካል አየሁት --- ማለፊያ ልጅ ነው ቅቅቅ ክርስትያኖ ድምጡ አልተሰማም :: እኔም ስልክ አልመታሁም --- ግን አዳራሹ ውስጥ ስጣራ ነበር -- ብቅ ብለው አስተያየት ቢሰጡ ብዬ ነበር --- እነሱ እንደኔ ስራ የፈቱ አይመስልም :lol:
ድራማው የተጀመረበት ሰዐት ግን በአበሻው አቆጣጠር ነበር :lol: :lol: ግን በዝግጅቱ ተካስን
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests