የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የዳሞት ግጥሞች

Postby Debzi » Thu Jun 17, 2004 5:11 pm

ግጥሞችህ ይጥማሉ:: እባክህ እዚህ አስፍራቸው::
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

ዉድ ደብዚ....

Postby ዳሞት » Thu Jun 17, 2004 7:59 pm

ዉድ ደብዚ በቅድሚያ በጣም አመሰግናለሁ:: በመቀጠልም እረኛ እንደሌለዉ ፍዬል...ከብት...ተበትነዉ ያስቸገሩትን ግጥሞቸን በአንድ ላይ ለመሰብሰብ በቋፍ ላይ ነኝ:: አምዱን በመክፈትህ ግን ክልብ የመነጨዉን ኢትዮጵያዊ ምስጋና አድርሻለሁ:: እንግዲህ አምዱ እኔ ብቻ ከሆነ እንደ ወጠጤ መሀል የሚገቡትን ትጠብቃለህ እሽ:: እስከዚያዉ ቸር እንሰንብት::አሀዱ ልበላ እዚሁ!!

"መካነ-ሠብ"

አዋሽ መልክአቆንጥር ምነዋ ዝም አልክ:
የነ "ሉሲን" እናት ሰለቸህ መስበክ::
"ቡናም " አለሁ በለን አሰማ ድምጽህን:
ለእምዬ ኢትዮጵያ በኩር ልጂነትህን::
አለም ቢጠራቀም ሁሉም ቢሰበሰብ
እኩያ የሌለሽ አንቺ "መካነ-ሠብ'::
"እንቶፈንቶ" ታሪክ ቢዶለት ቢወራ:
ማን? ይወዳደራል እሙ ካንች ጋራ::(4)
ቅዱሳት መጽሀፍት "ነቃሽ" የሆኑልሽ:
በ"ክልኤ " ድንግል ብዬ ብሰይምሽ:
አሳነስሁት እንጂ ማን በዛብሽ ሊልሽ::
ዛሬ ግን ተረቱ ጀርባ ሰጠሽና
አንድ እናት አንድ ሀገር መባሉ ቀረና:
ረሀብ ችግሩ ማህጸንሽን ሲያዉከዉ:
ለካ ለ"ሙጃሌ" ነበር ቀን የወጣዉ::
"ሙጃሌ" ይመችሽ እምዬ ደከመች:
እርጂናዉ ተጫናት "መንቀልም" ተሳነች::
ከዉስጥ ርሀቡ ከዉጭም ሙጃሌ:
ከፊት እንቅፋቱ ከኋላም "አለሌ"::
መራምድ አቅቶሽ ስትይ ደፋ ቀና:
"ልጨኛዬ" ያልሽዉ ወጣቱ ሳተና:
"የግመል-ሽንት" ሆኗል ባህሪዉ ሳሙና::
እድልሽ ሆነና እድገትሽ የካሮት:
ማህጸንሽ ቆሰለ በ"አራሙቻ" ፍጥረት::
እርግማን አይሉት ወይም ከላይ ቁጣ:
እየተሰለቀ ለ"መግባቢያ-ቋንጣ":
መች እንዲህ ነበረ!!! "በቅሎ-ላይ" ሲወጣ::
ፈረሰኛዉ ልጂሽ ያ ሽምጥ ጋላቢ:
ዛሬ የት እንዳለ ይፍረደዉ ቁልቢ::

ለዛሬ እዚች ላይ ቆም ልበል ና ወደ ፍዬሎቸ ልሂድ መቸም እረኛ ብላችሁ እንደማትሰድቡኝ ተስፋ አደርጋለሁ:: አስታያየታቸሁ ለጀማሪ የግጥም ተማሪ አስተዋጾ አለዉና ቀስ ቀስ ቀስ አድርጋቸሁ ቸብ ቸብ ቸብ አድርጉኝ:: እሽ::

እኅኅህ...ታዲያ ይመቻችሁ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ርቾ » Fri Jun 18, 2004 4:36 am

ዳሞት ግጥምህን ወድጄዋለው በጣም ቆንጆ ነው እና በዚህ ቀጥል በርታ ርቾ ነኝ

ቸር እንሰንብት
ርቾ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Mon Jun 07, 2004 5:34 am

የቀደምት ስራዎቼ "ኤግዚቪሽን ሩም"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 6:35 pm

በቅድሚያ በአንድ ላይ እንዳሰባስባቸዉ ምክራችሁን ለለገሳችሁኝ ጥበብ ወዳድ ወንድሞች ና እህቶች ምስጋናዬ የትየለሌ ነዉ:: በተለይም አምዱን ለከፈትክልኝ ለአቶ ደብዚ ....እንዲሁም ደግሞ መልካም አድናቆትህ ላልተየኝለ ክቡር አቶ አብራራዉ በተለይም ደግሞ ከ እንስት ጸሀፍት ድጋፏ የዘወትር ምርኩዜ ለሆነችዉ ማርስ ምስጋናየ ይድረሳችሁ: ይኽዉ ዛሬ ተሳክቶልኝ በአንድ ለማሰባብሰብ ቅድመ ዝግጂቴን ጨረሻለሁ እናም በተከታታይ ይወጣሉ::


በአካል በህንዳዊነት በመሰልኋት ዉብ ኮረዳ እጀምራለሁ::

" የዉበት አክሊል"

ሀመልማሎ ጸጉር የዉበት አክሊል:
የደም ግባት-ቋት ነሽ የፍቅር ጸዳል:
ዳሌ...ሽንጥ...ተረከዝ ሶስቱ ዉቅራቱ:
" እምቡጥ" ጽጌረዳ ይመስላል ፍካቱ::
ሠዉነቴ ሲርድ አንቺን መመልከቱ:
መች ይሆን? ሚሚረኝ የፍቅርሽ ልክፍቱ::
ዘመኔም ሮጠ እንደ ነፋስ ገፋኝ:
ዛጎልማዉ አይንሽ በፍቅር ሲገርፈኝ::
ተበደልኩኝ ብዬ እንዳልዉል ከችሎት:
አይንሽ አይከሰስ አይቀርብ ከዳኛ ፊት::
ሐር ጥቁር ዞማ ገመደ-ጸጉር:
ወለላ ከንፈርሽ ሚጥም ከስኳር:
ከሷዉ ጋ ቅበሩኝ ስሞት በእግ/ር::(4)
ፍቅሬ ቃል ኪዳኔን ምህላዬን ሰምተሽ:
ከ "አጎጤዎች " መሀል ጉንጬን አንተርሰሽ:
ይዉሰደኝ እንቅልፉ ዘላለም እባክሽ::
ፈቃዱ እንኳ ሆኖ ብሞትም በድንገት:
ነፍሴን ለመቀበል ሲመጡ መላእክት:
ፍቅር ዳኝነቱን ከጸብ ሲሟገትሽ:
"የግርጌ ማህተም" ሊያዩ ሲጠይቁሽ
ዳሞት ይዞት ጠፋ በያቸዉ እባክሽ::
በፍቅር አማልእክት በሀያላን ፍጡር:
አበሳ ስቆጥር በመዉደድ ወታደር:
እኔ ለኔ ብዬ መኖርን ሳልጀምር:
ጥሩ ቁርስነቱን ተስፋን ሳይ በምድር:
እንዲህ አ`ርጎኝ ሄደ የህንዲቷ ፍቅር::
ሁሉን አስተካክሎ የሰጣት እንደሷ:
እንጆሪ ከንፈሯ ጥርስና ምላሷ:
ከላይ መደረቢያዉ ከታችም ቀሚሷ::
ተረከዘ-ሎሚ ብርቱካን አጎጤ
እኔ ገና " ዉርጋጥ" ምዉል ከ"ወጠጤ"::
ፍቅሯ " ገሞራ" ነዉ በ"ፍንዳታ"ዘመን:
እንዲሁ ቁጪ ብዬ ሳስብ በሰመመን::
የቁም እስረኝሽ ነኝ ኮከብ ግዳይ ጥሎሽ:
ምንም አይታክተኝ ብዉል ስከተልሽ::
ዋዉዉዉዉዉዉዉ....
በሌክሰስ መኪናሽ መስኮት ዝቅ ባለበት:
ጸጉርሽ በነፋስ ሀይል እንዲያ ሲርበተበት:
ልቤ ተበትኖ እንዳልሞት በድንገት:
እቅፍ...ጭምቅ..ጭርንቅ ሳምምም አድርጊኝና:
ይዉሰደኝ እንቅልፉ አስተኝኝ ጋቢና::
"ሲት ቤልቱን" ን ፍቺና እንዳለቀ ጉዞው
የልቤን ትርታ ሁሌም ብታደምጪው:
ፍ...ቅ..ሬ ..ወ...ለ..ላ..ዬ እያለ ያዜማል:
ይህን በማድረግሽ አንቺም ታድለሻል:
እኔም ገነት ገባሁ ዋርካም እልል..ብሏል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ሠይፍ አንገት ይቆርጣል ፍቅር...

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 6:40 pm

ሠይፍ አንገት ይቆርጣል ፍቅር...


አይኔም አለቀሰ ድርሽዉን ተወጣ:
በናፍቆት አለንጋ በጂራፍ ተቀጣ::
ክብደቴም ቀነሰ ገባ ሰላሳዎች:
ለዝና ለወሬ ለጆሮ ሳይመች::
"እርር ኩምትር" አለ ልቤም በከፊሉ:
ትዝታን ጎትቶ "ነበርን" በቃሉ::
መለየት ሲያንዣብብ ሰቆቃዉ ሲጫን:
ሠይፍ አንገት ይቆርጣል ፍቅር አንጀትን::(4):roll:
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"ናፍቆት"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 6:46 pm

"ናፍቆት"

ሆዴን ባር ባር ሲለዉ ልቤ እንዲያ ሲረበሽ:
ሰክሮ እንዳደረ ሰዉ ሆዴ ሲቅለሸለሽ:
ናፍቆቴን አልቻልኩም አንቺ እንደምን አለሽ?
ፍቅር ሞተ አሉና ናፍቆት ተቀበረ:
ትዝታም በምሾ ይወረድ ጀመረ::
አፍቃሪም ለፍቅር በትዝታ አነባ:
በናፍቆት መለከት በትዝታ አበባ::
ናፍቆት ተሰወረ ስሙ ብቻ ቀረ:
ፍቅርም አካሄዱን ጉዞዉን ቀየረ:
ናፍቆት ቃል ኪዳኑን ምነዋ! ሰበረ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"ከትዝታ ዋሻ"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 6:49 pm

"ከትዝታ ዋሻ"

ከትዝታ ዋሻ ገዳም ለገደመ:
የፍቅርን ኩዳዴ አርባዉን ለጾመ:
ለሰላም ለፍቅር ሁሉን ላከተመ:
መገነዝ ሆነ እንጂ ምኑን ተከረመ::
ብቸኝነት መንፈስ ሆኖት "ሠይጣን-ጥላ"
ፍቅርም ግርሻት ሆኖ አንዳንዴ ሲጎላ:
ራሱን ከልሎ በድብርት ጃንጥላ:
መኖር ከጀመረ ከሙታን በስተቀኝ ከፍስሀ ኋላ
መብከንከን ሆነ እንጂ ምኑ ሆነ ተድላ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"ቃል በቃል ሲታሰር"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 6:58 pm

ቃል በቃል ሲታሰር"

ቃል በቃል ሲታሰር ጂምሩ ሲጸና:
እድል ገጠመኟን ስትነግር በዝና:
ተስማምቶ ካደረ ዉበት ከቁመና:
ህይወትም በራሷ ስታበራ ፋና:
ጆሮ መስማት ሲተዉ የጣምራን ገበና:
የዉህደት ቃሉ ይቋጭ እንደገና:::roll:
አምላክ ከፈቀደ ያራሱን ህግጋት:
መተሳሰብ ሰጥቶን እንድንሆን ባንድነት:
ሠላምና ጸጋ እንዲሁም ጤንነት:
እንቀይስ በጋራ ለወደፊት ህይወት::
ቃል በቃ ሲታሰር በሀሳብ ስትረካ:
የአብሮነት ሚስጢሩ የሰላም ፋብሪካ:
ይኖራል ዘላለም ሁሌም እንደፈካ::
ትንቢቱ ሲፈጸም መዋሀጃዉ ቀኑ:
ቃሉ በቃል ታስሮ ሲለካዉ ሚዛኑ:
ሁለቱም ጣምራዎች በአብሮነት ሚስጥሩ ከዋሉ ካመኑ
ቃሉም ቃል ይሆናል ሁሌም በዘመኑ:::Roll:
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"ለክብርሽ ተጋደይ"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 7:04 pm

ለ-ለክብርሽ ተጋደይስለ እውነትም ሙቺ:
ክ-ክብሪት ያለ ዘንጉ ክብርሽም ያላንቺ:
ብ-ብል የበላዉቆዳ...ንብ የሌለዉ ቀፎ:
ር- ርጥብ ጭቃ አቡክቶ ከመቅበር አያንስም ሸማዉን አጣጥፎ::
ሽ-ሽንጥሽን ገትሪ ለሀቅም እለፊ
ተ-ተዋርዶ ከመኖር አንገትሽን ሰይፊ::
ጋ-ጋኔንም ፈተነኝ ሰይጣን አሸነፈኝ ብሎ ከመታለል
ደ-ደረጃን ከመጣል ከፎቅ ወደ ወለል:
ይ-ይከበር ..ይዘከር..የመታቀቡ ቃል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"ለዉጥ ከራስ"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 7:11 pm

አይኔ አይኔን ሳያየዉ በአንድ ላይ ሲኖሩ:
አነሳሴን ስቸ ከጠፋኝ መስመሩ:
የታሪክ ምንነት ካልገባኝ ሚስጢሩ:
ምን? ሀሴት ይሰጣል ስምን ማሽቀንጠሩ::
በሰዉ ሀገር ቋንቋ ጥማት ለተያዘ:
ማንነቱን ሽጦ ብእሩ ለነቀዘ:
ከወላጂ እናቱ ስሙን የሰረዘ:
ታሪክ ማጥፋት እንጂ ሌላ ምን ተያዘ::
ከየትነህስ ስባል መልስ ካጣሁ ለራሴ:
በስመ-ኢትዮጵያ በከንቱ ዉዳሴ:
ጡቷን መንከሱ አይደል ጥርስና ምላሴ::
በአነጋገር ለዛ..በቃላት ጋጋታ እየተከሸነ:
"ለዉጥ ከልብስ እንጂ መቸ ከራስ ሆነ::"
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ይቀጥላል...

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 7:12 pm

ይቀጥላል....
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"ጥርስ ልብን አይገልጽም!"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 8:15 pm

ጥርስ ልብን አይገልጽም!

ለበጣ ፈገግታ አልጫ ከንፈር:
የሻጉራ ምልከታ ሾዴ ከሰፈር:
ጥርስና ፈገግታ ምነዉ ልብ ተዋጡ?
ለይስሙላ ብቻ ከንፈር መመጠጡ::
ሌንጨጪን በማሸሽ ከሆነ ሰላምታ:
ለዛዉ ተሟጠጠ ደረቀ ሰላምታ::
ገጥሟችሁ እንደሆን እንዲያዉ እሄ ነገር:
Hey የሚለዉ ቃል "የዘገሮች" ፍቅር::
መልካሙ መለያ ቀርቶ መሳሳሙ:
ትከሻን ቸብ ቸብ ማድረግ ለወንድሙ::
Hey ይለዉና አልያም የሽጉራ:
ምንጥርጥር አድርጎት ዘወር ሲል ሲያመራ:
ይህ ደግሞ የማን ነዉ? ሲል ይጀምርና:
"ግጣሙ" ማን ትሆን ብሎ ያክልና:
ከአፍንጫዉ ተነስቶ ድረስ ኩላሊቱ:
ሽምደዳዉ ምን ይሆን? ወሬዉን መፍጨቱ::
በነጠፈ ለዛ በከረረ አንደበት:
የቅዠት ቃል-ኪዳን መንገዱ የቁስለት:
አልገባኝም እኔስ ቃል የምንገባበት::
ከንፈር ከንፈርን ነዉ የመጠጠዉ እንጂ
መቸስ ተርፎ ያቃል ለልብ ለወዳጂ?
ጥርስ ልብን አይገልጽም ዛሬስ ልተንፍሰዉ:
በ እርሱ መከታነት ያለቀዉ ስንቱ ነዉ::
ብልጪ ድርግም አ`ርጎ አልያም ፈንዘክ:
ዉስጡ ሆደ-መጋዝ የማይል በርከክ::
ጥርስስ ባእድ ሆነ ከንፈር ምን አገባዉ?
ለ አለብላቢ ምላስ ድጋፍ የሚሰጠዉ::
እኔስ የገረመኝ ያይን መደገም ነዉ!
አይቶስ እንዳላየ የማያልፍ ለምን ነዉ?
እንግዲህ ታዳሚ እናንተዉ ጨምሩ:
ጥርስ ነዉ ፈገግታ መልካም ስመ-ጥሩ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"እኔ ነኝ ዘመኑ!"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 8:27 pm

" እኔ ነኝ? ዘመኑ!""

እኔ ነኝ ዘመኑ መላዉን ያጣነዉ:
አለም እየሾረች ጀርባ የሰጠነዉ::
የፊቱን ከኋላ የኋላዉን ከፊት:
መያዝ የሞከረ ዉሀዉን በወንፊት::
በልቡ እየሮጠ ባለበት የቀረ:
እኔ ነኝ ? ዘመኑ ድንጋይ የወቀረ::
እኔ ነኝ? ዘመኑ መላዉን ያጣነዉ:
አለም እየዞረች ጀርባ የሰጠነዉ::
የህይወትን ሽታ መዐዛ የናፈቀ:
ድርብ ግዞት ዉሉን ህጉን ያጸደቀ::
እስትንፋሱን ያጣ እራሱን የቀጣ:
መግመድ የጀመረ ሸማ ያለ ቋንጣ::
እኔ ነኝ ? ዘመኑ ከመስመር የወጣ:
ለአለም ሹረት ሂደት የሆነ ጎባጣ::
አበዉ ይሉ ነበር ያለፈዉ ጥሩ ነዉ:
ወግ ታሪክ ባህሉ ከላይ የወረስነዉ::
ሠላም..ፍቅር ጸጋ የግል ሀብት መሆኑ:
"ለሰዉ ሰዉ" መሆኑ ተስኖት ወገኑ::
እኔ ነኝ? ዘመኑ ለአለም የተገዛ:
እርቃነ-ስጋዬን ብሄድ እንደዋዛ::
ስሜንስ ብሰይም "ጆሊ.ማንጁስ" ብዬ
ያልሆንሁትን ሆኘ ራሴን አቅልዬ:
እኔነኝ? ዘመኑ ለትዉልድ አርአያ:
ለሀገር ገንቢዎች ለጥሩ ቡቃያ::
አበዉ አምላክ ፈቅዶ ካላችሁባገሩ:
እናንተዉ ፍረዱ እናንተዉ መስክሩ:
እኔነኝ? ዘመኑ መልካም ስመ-ጥሩ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"አደዋ!"

Postby ዳሞት » Fri Jun 18, 2004 8:34 pm

"አደዋ!"

አደዋ!

የአፍሪካ የነጻነት ብርሀን ቀንዲል:
የሰላም በር .........................ነበልባል::
የጀግኖች አጥንት ምስክር ቀመር:
ታሪክሽ ለዘላለም ይመስከር ..ይዘከር::
አደዋ! ዋ!
በእኒያ ጥሩር-ለበስ ልጆችሽ ደም ኩራት:
የብረጥ-ልጥ ወኔ ቀስቃሽ ብስራት:
ሆነሽ እንቁ ለነጻነት ማእድናት:
ዛሬም ኑሪ ለአልፋና አሜጋ አመታት::(4)
ታሪክ ታሪክን ሲወልድ አባት በልጁ ሲተካ:
ወኔ በሚዛን ሲወጣ ሲወርድ ዳግም ሲለካ:
ልብ እንደ ቂቤ እየቀለጠ ገደል ሲገባ:
ነጭ ያሸበረ ሆዱ ሳይባባ:
ሀበሻ እኮ ነዉ ነፍቶ ጥሩምባ::
ታዲያ...ዛሬስ....
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ደቢዝ ጥሩ ሀሳብ ነው

Postby Sammyhab » Wed Jun 23, 2004 10:58 am

Debiz እዝግሄር ይስጥሽ !! ተበታትነው የነበሩትን ግጥሞች ሰበሰብሻቸው እንጂ ዳሞት ግጥሞቹን በየሄደበት ነበር የሚዘራቸው ቅቅቅቅ

ዳሞት የአማርኛ ትምህርት ለምን ዋርካ ውስጥ አትሠጥም የምትጠቀምባቸው አንዳንዶች ቃላቶች በጣም ጠለቅ ያለ መልክት ያዘሉ ናቸው እንዲህ አይነቶች ቃላቶች እኔ ወንድምህ ያጥሩኛል እና በደንብ አርጌ አጠናቸዋለሁ እስከነ ትርጉማቸው በል ግፋበት አትጥፋብን

ሰላም እና ጤንነት ላንተው

ከ ሳሚሀብ
====================================
ላይዘልቁት መውደድ ላይጸድቁት መስገድ
ፍቅር ብቻ ነው እውነተኛ መንገድ
====================================

From one of ABONESH-Song's
Sammyhab
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 27
Joined: Mon Dec 01, 2003 6:27 pm
Location: tajikistan

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest