የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby Debzi » Wed Jun 23, 2004 1:18 pm

ዘንድሮ ለስንቱ ትርኪ ምርኪ አዲስ አርስት ሲከፈት ቁም ነገሩኮ ተረሳ:: ጥሩ አጻጻፍ በስድ ንባብ ይሁን በግጥም መልክ ማን የማይወድ አለ? አስተሳሰብ ያበለጽጋሉ አዲስ ቅላት ያስተምራሉ:: እኔም ካገር ከወጣሁ በኋላ የተፈጠሩ የሚመስሉ አዳዲስ ቃላቶች አያለሁ ምናልባት ሳሚሀብ ለዚህ አንድ አርስት ለመፍጠር ብትተባባረኝና ተማሪውም የሚጠይቅበት አዋቂውም የሚያስተምርበት መንገድ ብንፈጥር ጥሩ ነው::

መልካም ቀን
ደብዚ
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

ድጋፍህ...

Postby ዳሞት » Wed Jun 23, 2004 2:47 pm

ድጋፍህ ምርኩዜ ጋሻዬ ነዉና:
ለ"ርትኡ" አንደበትህ ይድረስህ ምስጋና::
እናንተ ባትኖሩ "እጄን" መች አዉቄ!
አድርጌዉ ነበረ ለጥሬ መዝገኛ ያዉም ለቦለቄ::
እንግዲህ ጣቶቼ "ትካር "ቢጤ ጻፉ:
ብላችሁ ታዳሚን አይንካችሁ ክፉ::
የቱ ነዉ አዲሱ "የከሳቴዉ" ቃል?
ስታይ ያገኘከዉ ከግጥሙ መሀል::
ልትክበኝ ፈልገህ ልትለኝ ልጨኛ
ሰይመከኝ አረፍክ መምህር ለአማርኛ::
የአማርኛው መምህር የቅኔዉ ቀንዲል:
እንዳይሰሙ ዳግም እንዲህም ስትል:
የኔማ ስራዬን ታዉቀዉ የለም ወይ
ፍዬል ተከትዬ ስለቅም እንኮይ::
እሂን የተማርኩት "ለወንጠፍት" ከሰጡኝ ከፍዬሌ ጌታ
ጣቴን እየሳቡ "በ" በል ሲሉኝ ማታ::
ይህቺን በማወቄ ተገርመዉ አለቃ:
አብሮ አደግ ልጆችን እያሉ "ሞሽላቃ"
ተሳድበዉ ኮርኩመዉ ጆሮአቸዉን አሽተዉ
ለዚህ ላደረሱኝ "ነፍስ ይማር" ለሳቸው::ሳሚ በል ወንድሜ አለቃ ይቆጡኛል ፍዬሎች ከጠፉ ባይሆን በኋላ ልመለስ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"እሪ በይ ጦማሬ!"

Postby ዳሞት » Wed Jun 23, 2004 8:05 pm

እሪ በይ ጦማሬ!

እሪ በይ ጦማሬ ይስማሽ አገር ሁሉ:
ይደለቅ ከበሮ ይመታ ቃጪሉ::
የጥበብ አዋጁ እምቢልታዉ ይነፋ:
ድምጽሽ ይስተጋባ ፍቅርሽ በአገር ይስፋ::
ለአልፋ ና ኦሜጋ ጥበብ እንቁዬ ናት:
ቅኔ ድጓ ግጥሙ እንዲሁም ተምሳሌት:
የ"ትዉፊት" ሀብታችን ከአያት ከቅድመ-አያት::
እሪ በይ ጦማሬ በአለም አጽናፍ ሁሉ:
ያሬዳዊ ዜማሽ ቅኝትሽ በሙሉ:
ከሚስጢርሽ-ባህር ልዋል ከመሀሉ::
ይህ ልዩ ሀብታችን ከምስራቅ አፍሪካ:
"ዳግም-ልደት ጥሪ" ሰይመሽ በዋርካ:
ታቋድሽናለሽ ጥበብሽን ትረጪ:
ይጥፋ ብለሽ እያልሽ የ"ጥበብ-ምላጪ":
የ"ጥበብ-ነቀዞች" እነ "ወገብ-ነጭ"::...(ወገበ-ነጭ)
እሪ በይ ጦማሬ ቃልሽን ከፍ አ`ርጊና:
ሰፈርሽ እንድትሆን የ"እዉቀታት" መዲና::
እንግዲህ ታዳሚ ጦማሬን አድምጡ:
ከአህጉራት ሁሉ ዋርካ የምትመጡ::
ድንቅ ድንቅ ነገር የታምእራት እቃ:
ሆኖ ህሊናችሁ የጥበብ ጠበቃ
እናንሳ ባንዲራ የጥበብ ምልክት:
ለተተኪዉ ትዉልድ ለመጪዉ ፍጥረታት::


ዳሞት ከዳሞት -የፍዬል እረኛዉ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

እሪ በይ ጦማሪ...

Postby ዳሞት » Sun Jun 27, 2004 1:48 am

እሪ በይ ጦማሬ እንደገና ዛሬ:
አልያ ላግዝሽ አይነካም ክብሬ::
ገና በልጂነት ድሮ በዘመኔ:
በጥበብ እርዛት ሳይጠወልግ ጎኔ:
"ሀ" ብዬ ቆጥሬ በነጩ ጠመኔ:
ከትልቁ ዋርካ እዚያ ከሰፈሬ
ዛሬ ብድርሽን ሰጠሁሽ ለጠኔ! (2) :roll:
እምዬ! .......
እሪ በይ ...እሪ በይ! እሪ በይ! አሁንም:
ይዉጣ ሽማግሌ ይሰብሰብ ካህኑም::
"እዉሱ" ይታወስ "ያሰለጠሽ" ማነዉ?
ያሁን "የእንግዴዉ-ልጂ" ወጣቱ ክፍል ነው?
ይላቁልኝ ብለሽ ያልሻቸዉ ተማሩ:
በየ ባእድ ሀገር እንደወጡ ቀሩ:
መግባታቸዉ ላይቀር አገርቤት ለቀብሩ::
ታዲያ!
አንጀትሽ በረሀብ ሲጨማተር አይተዉ:
እምዬ ጎንሽን ካላሉሽ ደሳሰዉ:
"ሾተላይ" ለሆንሽዉ ለወላድ መካኑ:
ካልተረዳዱልሽ ወገን ለወገኑ:
ምን ፋይዳ ይሰጣል ማልቀሱ ማዘኑ::
እስኪ ቀስቅሱልኝ እነዚያን" አናብስት"
የእዉቀት ማህደራት የጥበብ ሰራዊት::
ዛሬስ የት ገብተዉ ነው ድምጻቸዉ ጠፋብኝ:
የጥበብ እርዛት ጎኔን ሲጠናብኝ::
ዐስቀርተዉ እንደሁ ከ"ቅኔአቸዉ ፍትፍት:
ከ እምዬ ዝማሬ የቀለሟን ወተት::
ከተጠማሁ ቆየሁ ዘመናት አለፉ:
ቀድታችሁ አምጡልኝ በዚያ የምታልፉ::
ስራችሁ ለጽድቅም ለገነት በር መግቢያ:
እንዲሆን አዉቃችሁ ኗሪ መጠለያ:
ሳትሞት ለሞተችዉ ለ እምዬ ኢትዮጵያ:
ከጥበብም ዉሀ ከሰላም እንጀራ:
በሳህና ቋጥሩና ላኩላት አደራ::
አይኗ ጣራ ካየ ቆይታለችና:
"በከፋፍለህ-ጉንፋን"ጉሮሮዋ ደርቆ እንዳትጠጣ ቡና
ልብሷን ማለቅለቂያም የላትም ሳሙና:
ተስማምቶ በበላት "በመታት-አገና::""
ስለዚህ...
አንጀቱ ያላችሁ ከልብ ለምትራሩ:
በድሎት ያላችሁ በዉጭ የምትኖሩ:
እጃችሁ ይዘርጋ ቤትም-ያፈራዉን:
ምን ሰራሁ? ለማለት ዋስትና እንዲሆነን::


ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት::


Have fun Guys! Peace 4 All!
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

እሪ በይ...

Postby ዳሞት » Sun Jun 27, 2004 3:20 am

እሪ በይ አማዬ! አይበቃኝም ዛሬ:
በሰሜን በደቡብ በሸዋ በትግሬ::
ቢሻሽ መሀል አገር አልያም ጠረፍ:
ችግርሽ ይሰማ ዳግም ይለፈፍ::
"ብቅለትሽ" የታሉ ጥንት የዘራሻቸዉ:
የ"ታሪክ- ጎተራ" የሰራሽላቸዉ:
ቅኔ ና ድጓዉን "ያስኮተትሽላቸዉ:
ዜማ ዝማሬዉን መዋሲት የመሩ:
የሰላም-ልጨኛሽ የጥበብ መምህሩ::
እንስሳትም ሳይቀር ያዜሙለት ቦታ:
ፍርድ የሰጠሽበት ትልቁ ኮረብታ::
ዛሬ የት? ደርሶ ነዉ ጠፋብኝ ከበሩ:
የጥበብሽ ብሂል መለያ ቀመሩ::
አዝእርትሽ ሁሉ ለ እዉቀት የታደለ:
መቃ ወረቀቱ ቅጠሉ የት? አለ::
የብራናዉ ዳዊት ጠባቂ መላእክሽ:
አምላክ በጸጋነት ሲጀመር የሰጠሽ
የአፍሪካዋ-ጮራ ታሪክ ያገነነሽ:
"ዘመነ-አልፋ" ይሁን ሁሌም ቃል ኪዳንሽ:: (2)
የአብራክሽ ክፋዮች ያላቸዉን ወኔ:
እድሉን ብታገኝ ብታይማ እንደኔ:
ሲኖሩ ዉጭ ሀገር ተናንቀዉ ባንድ ላይ:
በሞት በደስታቸዉ በቀብራቸዉም ላይ:
የማን? ናቸዉ ሲባል ስምሽም ሲጠራ:
እያወዳደሩ ከአለም ህዝቦች ጋራ:
እጹብ ድንቅ ያስብላል ታሪክሽ ሚያኮራ::

ግና....ግና...!

ብብትሽ ዉስጥ ያሉት እነዚያ ሁለቱ:
አራሙቻ ፍጥረት መርዝን የተጋቱ:
ስራቸዉ አያድርስ! ታሪክ ይዉቀሳቸዉ:
"ቀሚስሽን" ቀደዱት ሌላዉ ሲቀራቸዉ::
እንግዲህ ልጂ ካለሽ ልቡ የቆመራ:
የሰላምን ፀበል ሚረጭ የሚዘራ:
እምዬ! አትርሻቸዉ ጸሎትሽን አደራ::


ዳሞት ከዳሞት::

ይቀጥላል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ወንድሚ ዳሞት

Postby Monica**** » Sun Jun 27, 2004 1:33 pm

ያገሪ ልጅ ዳሞት የጦቢያው የጥንቱ:
እስኪ ተርትልን አይን እንኮን ቢከፍቱ
ያቺ የጀግኖች አገር ያቺ የውበት መንደር
እንደ ድፎ ዳቦ ትቆራረስ ጀመር?
የእምዪ ልጅ በርታ እኒማ ምን አቅም አለኝ?
አንተው እንደጀመርክ አንተው ተርክልኝ
አምላክ ይሂን አይቶ ብርታቱን ይስጥልኝእባካችሁ እንዳትስድቡኝ የመጀመሪያዪ ነው! ዳሞትዪ በርታ ወንድሚ
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ዋናው » Sun Jun 27, 2004 5:06 pm

ሰላም ላንተ ዳሞት

ግጥሞችህን ሳነብ አበሻዊነት ማንነት እድገትነትና ትውልድነት ተጣምረው ልቤን ወደውሀላ ያሸፍቱታል ...ቃላት ተጎንጉነው ሲሾረቡ ምን ያህል ክሽሽሽሽሽ!!!! እነደሚልብኝ ታቅ የለ...
የተዋጣልህ የሪያል ስቲክ ጸሀፊ ነህ ....ዛሬ ዛሬ በፎረም ውስጥ ባልጌዎች በዝተው ዋርካ ባሳዘነን ሰሀት እልፍ ብሎ እንዳንተ አይነቱን ግጥም አግኝተን ጥበባዊ ጥማታችንን ስናረካ ብህርህ አይንጠፍ ነው የምነልህ .....ማለፊያ ስራ
በተረፈ ባንተ ግጥም ገብቼ ይሄንን አቃና ይሄንን ቀልብስ ማለቱ እኔ ለምከተለው የግጥም ዘየዬ /መንገድ/ አይሆንምና በርታ ከማለት ሌላ የምለው የለኝም አሁንም ቃላት ይርቡልህ ::

ከብዙ ብዙ ማድነቅ ጋር
________________________ዋናው_________________________
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

ምስጋና ያጥረኛል...

Postby ዳሞት » Sun Jun 27, 2004 8:40 pm

ምስጋና ያጥረኛል የምለዉም የለኝ:
ሞኒ ና ዋንዬ እግ/ር ያክብርልኝ::
ቃላት ተጎንጉነዉ ሲሾረቡ አይቼ:
በሳልሳዊ ንድፍህ በዚያ ተሳስቼ:
ጀምሬ ማዜሙን ስንኟን ቋጠሮ:
የልቤን ዉስጥ እሳት ረመጥ ሮሮ:
ብቻ ማንባት ሆነ የኔማ ዘንድሮ::
ሞኒ ድጋፍሽም ስኳር ናት አንኳር:
ሀሳብሽ በቂ ነዉ ለዚያች ደሀ አገር::
በተለይ በተለይ ሂስሽ ግጥም መሆን:
አመልካች ነዉና ትእዛዝ ማክበርሽን:
ወደር-አልባዉ ግጥምሽ ጪራሽ አርክቶኛል:
ሁለገብ መሆንሽን በግልጽም ያሳያል::
ዋንዬ መልእክትህ ሰባራ ጠጋኝ:
እንደ ስእል ቅብህ እንዲህ ሲያስዉበኝ:
ቤቴ መኖሪያዬ ጥበብ በሆነኝ::በጣም አመሰግናለሁ:: ድጋፋችሁ ከዚህ የበለጠ እንድጥር ያደርገኛል ስለሆነም "ጥበብን በሽልም
ያዉጣሽ በሉልኝ""

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ላስታ » Sun Jun 27, 2004 9:01 pm

ዳሞት ..ዳሞት..ዳሞት
እስቲ አቤት በል ካለህበት

የግጥም አጻጻፍህ ይዘቱ
የስንኝህ አወራረድ ፍሰቱ
ያለው ዜማ ወበቱ
ጉድ የሚያሰኝ ነው በውነቱ


በርታ
"Whether you think that you can, or that you can't, you are usually right."
- Henry Ford
lasta _rasta
ላስታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Apr 07, 2004 10:00 pm
Location: iraq

አቤት አቤት አቤት!

Postby ዳሞት » Sun Jun 27, 2004 9:17 pm

አቤት! አቤት! ላስታ የ እኔ እመቤት:
ከጥበብ ጥላ ስር ከምድራዊ ገነት::
ጥሪሽን ሰምቼ ብቅ ከማለቴ:
ሂስሽን አይቼ ቢርድ ሰዉነቴ:
ለካ ደስታ ኖሯል ያነገብሽዉ በጂሽ:
ለግጥም ተማሪዉ ለዚያ ለውዳጂሽ::
ግሩም ድንቅ ስንኝሽ እኔንም ማርኮኛል:
እግ/ር ይስጥልኝ እጂግ አኩርቶኛል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ላስታ » Sun Jun 27, 2004 9:20 pm

ተቀብያለሁ ዳሞት !ወንድ ነኝ
"Whether you think that you can, or that you can't, you are usually right."
- Henry Ford
lasta _rasta
ላስታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Apr 07, 2004 10:00 pm
Location: iraq

ለጾታ ሙስና...

Postby ዳሞት » Sun Jun 27, 2004 9:38 pm

ለጾታ ሙስና ቢኖርማ ኖሮ:
ከርቸሌ ነበርኩኝ እኔማ ዘንድሮ::
በጣም ዝቅ ብዬ ነዉ ስጠይቅ ይቅርታ:
መቸም ቅር አይልህ ወንድም የኔላስታ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

አቤት ጉድ ይገርማል!

Postby ዳሞት » Tue Jun 29, 2004 3:52 pm

አቤት ጉድ ይገርማል!

"ስቴሪዮ-ታይፕ" በሚሉት ደንቀራ:
በምኔ ደርሰህ ነዉ እያለ ሲያቅራራ:
ደግሞ አንተ ምኑ ነህ !!የትናንቱ "ፋራ":
ብሎት እርፍ ይላል እንዲያ ሲገሰላ:
ተጠርንፎ ያለዉ በ"ኑሮ-ወሸላ""::
እረ ለመሆኑ ስለ ራስ "ቅፈላ":
በሽታ አይደለም ወይ? ችግር አሜኬላ::
ትናንት ከአንድ ቦታ ተወልደን አድገን:
በሆነ አጋጣሚ ዉጩን ረግጠን:
ያንን "ሰኞ-መደብ" ዳዉጃ ረስተን::
በዉጪዉ አለም ላይ ሺህ ዘመን ብንኖር:
ብንዳር ብንኳል ብንጪንም ክብር:
ያቺ "መካነ-ሰብ" ኢትዮጵያ እንዴት ትቅር? (4)
በ እቅፍ ላይ ተቀምጦም ከ እምዬ ከጪኗ:
ቅማል- ትኋን ሆኗል ማይጠፋ ከጎኗ::
ሰርዶ አይብቀል አይነት እንዳለች አህያ:
በ"እኔን ስሙኝ አይነት" የነገር-ጉፋያ:
ሆድን ከመቆዘር በአጓጉል እብሪት:
መስራት ይሻል ነበር ኑሮን ለመምራት::


ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት::
Last edited by ዳሞት on Tue Jun 29, 2004 6:35 pm, edited 1 time in total.
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

አቤት ጉድ

Postby ዳሞት » Tue Jun 29, 2004 6:34 pm

አቤት ጉድ ይገርማል!


ቧልትም ስራ ሆኖ የሰዉ ትዳር መናድ:
በሻይ በቡናም ሲጓዙም በመንገድ:
ምነዋ! በቀረ ራስን ማግነኑ:
መኮፈስ መጀነን.. ሰው ያለ መጠኑ::
አቤት ጉድ ይገርማል! ሰይጣንም ለጉዱ:
ሲኦል ሆይ! እያለ ሲጸልይ መንገዱ:
እነ-ወሬ ቁርሱን "ልብሰ-ብርሀናትን":
ሲሰልቁ ደርሶ ሲያልሙት ወሬዉን:
ልጆቼ! እናንተ ባትኖሩ ለኔስ ማን ነበረኝ?
አለም እንደ ጥላ ከቅጠል ሲያቀለኝ
ብሎ ጸለዬና ነገሩን ሲያሳርግ:
አባት ሆይ ሳጥናኤል! ....
እንግዲህ ልጆቼ እንዳይጥማቸዉ ወግ:
ሰላምን አደፍርስ አንደበት ዲዳ አ`ርግ::
ብሎ መርቋቸዉ በሌሊት ጨለማ:
አንዱም እቤት ሆኖ ሌላዉም ከማማ:
"በቁም ይቃዣሉ ልጆችሽ እማማ::
ስለዚህ ...
ከጥንቱ በረከት ከረድኤት ፍትፍቱ:
ከሽምብራዉ እሸት ከማር ከወተቱ:
ያልተበረዘዉን ያልተከለሰዉን የሰላም ጪላንጪል:
እርጪን በላያችን ሰላም እንድንዉል::ዳሞት ከዳሞት

ይቀጥላል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ዳሞት ያገሪ ልጅ

Postby Monica**** » Wed Jun 30, 2004 2:28 pm

ደህና ከረምክልኝ ዳሞት ወንድም አለም?
እኒም አለሁልህ ደግ ደጉን በማለም
በል ቀጥል ጥሁፍክን ወደር የለህ መቸም
ናፋቂው ቃላትህ ይድናል ማንንም


ወይ ጉድ እንዳትገሉኝ ምንም ቢት አልመታ አለኝ :evil: :evil: :evil:
ያለውን የስጠ ንፉግ አይባልም ብሎ የለ የአገሪ ስው ሲተርት :lol: :lol: :lol:
ዳሞት አትጥፋብን

አክባሪህ

Monica****
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests