የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

አቤት ጉድ ይገርማል!

Postby ዳሞት » Wed Jun 30, 2004 3:32 pm

አቤት ጉድ ይገርማል!ትናንት ጉድ ዛሬም ጉድ ነገም ጉድ:
ጉድ ማለቂያ የለዉ ሲሳብ እንደገመድ::
እረ ለመሆኑ! ከእህት ከወንድሙ:
ከአንድ አብራክ ከወጡት ከስጋ ከደሙ:
ከእምዬ ልጆቿ ዘመን ካመጣቸዉ:
ከቶ ለምን ይሆን አለመስማማታቸዉ?
እባካችሁ ሰዎች ሚስጢሩን ፍቱልኝ:
ነገር ከኋላ እንጂ ከፊት አስቸገረኝ::
ትልቁ "ቀሚሷን" የኔ ነዉ ይለኛል!
ትንሹ "ወተቷ" ለኔ ይገባኛል:
ሲሉኝ ሲያንገላቱኝ ሲንጡኝ ከረሙ:
ኑሮ ማጣፈጫዉ ጠፍቶብኝ ቅመሙ::
አሁንስ የቀረው"ጋራጂ ሴል" ላይ ማዋል
እንቁ ቅርሶችማ ድሮ ተሽጠዋል::
እስኪ ለምሳሌ ትንሹን ልናገር:
ከአስር አመት በፊት ምን ተሰርቶ ነበር?
እረ! በሉ ተዉት ሁሉን ቢናገሩት:
ሆድ ባዶ ይቀራል ይሆናል ራቁት::ዳሞት ከዳሞት::

ይቀጥላል
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

"ትዳር-አልባ ጎጆ!"

Postby ዳሞት » Thu Jul 01, 2004 3:17 pm

"እንቶፈንቶ-ትካር!" ቅመም-አልባ ክሽን:
ወና ምድረ-በዳ ሲለካ በመጠን:
"የቋሳ" መፍለቂያ ትልቁ ምንጫችን::
"ትዳር አልባ-ጎጆ" ትንሹ "ዘብጥያ":
ፍርድ የሌለዉ ግዞት "የኑሮ-ካዉያ"::
አይሞቀኝ አይበርደኝ ያዉ እንደትናንቱ:
መሻሻል የሌለዉ ከቀን ከሌሊቱ::
ሀሳቤን ሳወጣ-...ሳወርድ ከጣራ ላይ:
ስቋጥር ስፈታ ተኝቸ አልጋዬ ላይ:
መስራቴን ሳላዉቀዉ አከላቴ ደቆ:
"ትዳር-አልባ ጎጆ"! ሆነብኝ እንቆቆ::
ልጄ አልቦረቀበት ወይ ዘመድ አላየዉ:
ትልቁ "ቪላዬ" ደስታ-አልባ ወና ነዉ::


ዳሞት ከዳሞት

ይቀጥላል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ትዳር አልባ-ጎጆ...

Postby ዳሞት » Fri Jul 02, 2004 4:46 pm

አዉዳመት ሲመጣ ትንሳኤ-ፋሲካ:
ጨፌዉ ሲነሰነስ ሰንደሉም ሲሰካ:
በጉም ሲሞናደል ገብቶ መሀል ሳሎን:
አበዉም ተነስተዉ ሲሉ ይቅር በለን:
ትልቁ"ቪላዬ" በዚህ አልታደለም!
እጂግ ቢማርክም ቢዋብም በቀለም::
ትዳር አልባ-ጎጆ ስንካሳሩ ብዙ:
በሀሳብ ያሰጥማል በዚያ በመዘዙ::
ዘመድ ተሰብስቦ ሲጫወቱ አይታይ:
ቡና ሻይ ብሎ ማዉጋት ከወንድም ላይ::
ዘወትር ያ "ሽቦ" መከረኛ ነገር
ዛሬስ ምን ይዘሀል? እያሉ መኮርኮር::
መልካቸዉን ሳላይ ድምጹን እንደሰማሁ:
ዘመድ ማሰላሰል መቃዠቱን ጀመርሁ:
ደግሞ ምን ተሰማ ምን ይሆኑ ብዬ:
እንዳይ ነጋ የለም ሲነጋ ደዉዬ:
እንኳን አደረሰህ! ትንሳኤ ነዉ ዛሬ:
ብለዉኝ አረፉ ታላቁ መምህሬ:
ጥንት የረሳሁትን ከወጣሁ ካገሬ::
ትዳር አልባ-ጎጆ! ይህን ሁሉ የማታዉቅ:
መተኛት መቀመጥ መልበስና ማዉለቅ:
ይህ ብቻ ነዉ ለሷ መሆኗ ፎቅ በፎቅ::

አይይይይይይይይ.....! እናንተዬ:-

ታዲያ!
ዉጭ ሀገር ያላችሁ ምትኖሩ በ"ቪላ":
ቢሮም የምትሰሩ አልያም "ሽቀላ"
"ትዳር አልባ ጎጆ" ሆኗል አሜኬላ:
ስለዚህ.....
በትልቅ ጃንጥላ በትዳር ጥላ ስር:
መሰባሰብ ያሻል መቆም ለቁም ነገር::

ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት:
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ቤርያ » Fri Jul 02, 2004 6:25 pm

ግሩም ነው! ይቀጥል ብያለሁ:: ምርቃቴም ይኸው....
ቤርያ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Fri Jun 11, 2004 6:34 pm

ትዳር አልባ-ጎጆ...

Postby ዳሞት » Fri Jul 02, 2004 7:02 pm

ታላቋም እህቴ ሰላሳ ቢዘላት:
አመሏ ሆነብኝ ብጥብጥ "ዉሀ- ፍትፍት"::
አንደኛዉ አጎቴም ሲዞር ሲያተራምስ:
"አረንጓዴ_ማብቀል" የቀረዉ አሁንስ:
ነጩንና ጥቁሩንስ አምስሎ ሰርገኛ:
አይንሽ-ላፈር ይላል -የትዳር-ቀበኛ::
አሁን "ሰረሰሩ" ሲመስል ደጋን:
ሰዉነቱ ሟሾ ሰቀር ብቻዉን:
ያፈላልግ ጀመር ሊያገባ ሚስቱን::


አቤት ጉድ! እናንተዬ!

እኔ በአለሁበት በአንዲት ትንሽ ሰፈር:
አሳቦ መዝፈኑ አሳቦ መጨፈር:
"ትካር" ሆኗል መሰል መሳቢያ ቁምነገር::
እረ ለመሆኑ! በጊዜዉ የት ነበርን?
ለአባትና ለእናት ሲወድቅ ያ ካህን::
"ሲለምኗት ቀርታ" እንዲሉ አይነት ነገር:
ዛሬ ምን ይሰራል እድሜንስ ማጭበርበር::
የሰኔ ሚካኤል 25ኛ ነዉ!!
እያልን ከመለፈፍ አርባ በመጠጊያው:
ለትዳር ማጎብደድ ማንን ነዉ ያደማዉ?
ከንፈርሽን አምስለሽ የበሰል እንጆሪ:
እድሉ ይሰጥሽ ዉቢት ተናገሪ:
ችግሩ ምንድነዉ ትዳሩ ተፈራ:
ላለመሳካቱ የሆነ ደንቀራ::
አጎቴ ምንድን ነዉ? እስኪ አንተ ንገረኝ:
ትዳር አልባ- ጎጆ በጣሙን መረረኝ::
ከአንተ ከታላቄ ምንድነዉ `ምማረዉ:
አንሶላ መግፈፉን ቀሚስ መከተል ነዉ?

እህምምምምምምምም......

እንዲህ አይነት ነገር እስከ መቼ አጎቴ?
ስጋዬ ተሟሾ ስሄድ ነዉ በአጥንቴ!
በል አንተም ተመለስ ይብቃህ ማሳደዱ:
ዉቢትን እሽ በል ይሻላል ከብርዱ::
እኔ ቀልድ አይደለም እዉነቴን ነዉ አጎት:
ትዳር አልባዉ ጎጆ ይሁን ባለ እመቤት::

ዉቢት!....
እንግዲህ አጎቴ ልቡ ተመልሷል:
ሀበሽን ሊያገባ በትዳር ላይ ምሏል::
በይ አንቺም ተመለሽ ሀበሽ ማጥላላቱን:
መቀነትሽን-ፍቺ አምጪዉ የትዉፊቱን:
"እርጣት"ም ሳትደርሽ ይኑርሽ አንድ ህጻን::


ዳሞት ከዳሞት::

ይቀጥላል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ትዳር አልባ ጎጆ...

Postby ዳሞት » Sat Jul 03, 2004 3:35 pm

ብለን ተስማምተን ነገሩን ቋጭተን:
ለአጎቴ እንድትሆነዉ "ጉንፍ"ን አጨን::
ሽር ጉዱ በዛ ያ ቀንም ደረሰ:
ጥሎሹ ተጣለ ቀሚስ አለበሰ::
ሰርጉም ተሰረገ ደመቀ በእምቢልታ:
ሙሽሮች ታጀቡ ቀለጠ በእልልታ::
በሰርጉም ማግስት ዘመድ ተበተነ:
ያለንበት ቦታ ጊዜ ዉድ ስለሆነ::
ታዲያ!....
ብቻቸዉን ቀሩ ትዳሩ ሊጀመር:
በስተርጂና ሚስቱን ሊሞሽር ሊቀሽር::
ሳምንቱም አለፈ በፍቅር አፍላ ላይ:
የሰርጋቸዉ ፎቶ አልበሙ እስከሚታይ::
ከእለታት አንድ ቀን ጮከች አንድ ነገር:
ሄሎ! ማን ልበል እመቤት ማለት በቁምነገር:
ሚስትም !
ዕዕ..ዕዕ....ዕዕ...አለችና ነገር ለማስቀየር:
ለካ ዉሽማዋ -እቁባቷ ነበር::
ባልም !
ማሰላሰል ጀመር ከዚያች ቀን ጀመሮ:
እንዴትስ ይሆናል ለምን ተሞክሮ:
እያለ ሲፎክር ሲገሰላ ከርሞ:
ሌላ ጥሪ መጣ ይግረማችሁ ደግሞ::
ባልም ተፈላጊ ሆነ በየአቅጣጫዉ:
አንዱ ለአንዱ ስርቆ እንግዲህ እሄ ነዉ::
ጉዱ ይፋ ወጣ ሚስትም ቅምጥ አላት:
ባልም ፊታዉራሪ ሆኗል ባለ-ሁለት::
የስራ ጊዜያቸዉ "ስኬጁሉ" ወጥቶ
እቤት ሚገኙበት ረፍቱ ተባዝቶ:
በዚህ ሰአት ደዉይ እያለ ቅምጡን:
የሞቀዉ ትዳሩን ቦረቦረዉ ዉስጡን::
ሚስትም በፈንታዋ አሁን ባሌ የለም:
ማዉራት እንችላለን ስለ ከንፈርህ ጣዕም::
እያሉ ችርቻሮ ንግዱን አጧጡፈዉ:
"አያ! ስም-አይጠሬን" አጂርን ሸምተዉ:
ከሞታቸው ይልቅ ልደታቸዉ ብሶ:
ቀኑን ይጠብቃል አእምሮዉ ቀዉሶ::

ዳሞት ከዳሞት::

ይቀጥላል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

እንቁላል ሲገማ ....

Postby ዳሞት » Mon Jul 05, 2004 10:03 pm

:roll:~~~~Alert!~~~~~~~> :roll:


እንቁላል ሲገማ ምን ይባላል ድሮ!
ራሱን አይቀይር ወይ አይተካ ሽሮ:
ቦታዉን መስጠት ነዉ ማስቀመጥ ከጓሮ::
ሌላ ምን ይሆናል ከዉስጥ መሽተት በቀር:
ለናቱም አይበጃት አይጠቅምም ለሀገር::


ዳሞት::
Last edited by ዳሞት on Tue Jul 06, 2004 6:01 pm, edited 1 time in total.
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

እንቁላል ሲገማ...

Postby ዳሞት » Tue Jul 06, 2004 12:32 am

በእርግጥ ባይታወቅ የእንቁላል ልጂነት:
እናት ትሆናለች ለነጫጩት ፍጥረት::
ቀድሞ የተገኘ ማን እንደሁ ባላቅም:
ጊዜ ለሱ ጠሪዉ መሆኑ አይካድም::
ወቅትም ይፈዉሳል ዘመናት ያደማል:
በጊዜዉ ካልሆነ ሁሉም እጂ እጂ ይላል::


ዳሞት::
:roll: Alert!
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ሳቅ-በሳቅ አረርሁኝ!

Postby ዳሞት » Wed Jul 07, 2004 5:46 pm

:roll: ~~~~>alert~~~> :roll:ሳቅ-በሳቅ አረርሁኝ!

ፊቷን አስመስላ ከ እንጆሪ የቀላ:
ጥርሷንም አግጥጣ ሆናብኝ ግስላ:
ጸጉሯን አዘርዝራ አምስላ መጥረጊያ:
በአንድ እጇ ማንኪያዉን በዚያኛዉ መጠጊያ
ድንገት ሳታስበዉ ቤት በመድረሴ:
ብላ ጠየቀችኝ የት አለ ቀሚሴ::
ቅርጫት አትደፋበት ቅርጫት የለ ባገር:
ሳሎኑን ከ"ኪችን" ታደባልቅ ጀመር::
ግመሬዉ ዝንጀሮ "የሙዳይዋ"ን ሌባ:
አየሁት አልጋ ስር ወደ ዉስጥ ስገባ::
ዉሻ ገዛሽ እንዴ? እንደ ፈረንጆቹ:
ብየ ስጠይቃት ታዩኝ ጣቶቹ::
አቤት! ጉድ በማለት እኔም በፈንታዬ:
nine-one-one ብዬ ፖሊሱን ደዉዬ:
ችግሬን ዘርዝሬ ካስረዳሁ በኋላ:
ለምኘ አግባብቸ በስንት ቅፈላ:
ፖሊሱ መጣልኝ ቤቴን ሊጎበኘዉ:
ትልቅ አሻንጉሊት ከአልጋዉ ስር ሲያገኘዉ:
ሳቅ-በሳቅ አረርሁኝ: ዳግም በሁኔታዉ::

ይቀጥላል::( ለፈገግታ ብቻ)

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ለአድሮ ቃሪያዉ...

Postby ዳሞት » Thu Jul 08, 2004 5:35 pm

ለአድሮ-ቃሪያዉ ልጄ!

ተግሳጽ ና ምክር ላይደርሱ ከጆሮህ:
እናትህ ና እኔ ስንቱን ደከምንልህ::
ድሮም እንዳይሆን ነዉ ቁም ነገር ላላደርስ:
ሳስታምም መክረሜ ትልቁን አጋሰስ::
ብልጥ ከሰዉ ዉድቀት ይማር ነበር ድሮ
አንተ ግን ሆንክብን ዉስጠ-ክፍት ከበሮ::
አደቡን ግዛልን ልጃችን ተዉ በቃ:
ድሮም ለከት የለዉ ባለጌ ሲነቃ::

ዳሞት ከዳሞት::

:roll:~~~~~~~~Alert!~~~~~~>
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ቋሳ-ፍቅር

Postby ዳሞት » Fri Jul 09, 2004 4:15 pm

ቋሳ-ፍቅር!


በልጂነት ገና በ እምቡጥ ለጋ ዘመኔ:
ያስቀመጥሽዉ ድብቅ ፍቅር ከልብ-ሳጥኔ:
ህልም ቅዠት ሆነብኝ ጋደም ስል በጎኔ::

ፍቅሬ!

ታስታዉሻለሽ? ያኔ ስወጣ ካገሬ:
"ሞት-ይለየን" ያልነዉ ቃል-ኪዳንሽ መፈክሬ:
ጉዞ ስጀምር በረጂሙ አዉቶቡስ ተሳፍሬ::
አይንሽ ከአይኔ እስኪሰወር በእምባ እስኪሞላ:
አይሽ ነበር እኔም ዞሬ አንገቴ አስኪቀላ::

ዋ! ፍቅሬ!

ህያዉ ፍቅር የእዉነቱ... የልጂነት የጥንቱ:
መቸም ቢሆን አይሽርም ቁስለቱ...ንድፍቱ::

ማሬ!
ያን "የቃል- ኪዳኑን" አርበኛ "የጽሀይን" ባለ እንጀራ:
ምኑ? ለየን እኔን ከሱ ጋራ::
የኔም ህይወት"ፊክሽን" ሆኗል ትኩሳቱ የናረ:
ያ! ህያዉ ፍቅርሽ ወና ሆኖ ከቀረ::
አንድንዴስ አምላክን ማመስገኑን ትቸ መጸለዩን:
ሆነሽኛል የእለት-ተእለት "የዘወትር ጸሎቱን::
እስኪ ወደኋላ መለስ ልበልና...
ልቃኘዉ ያን ለምለም ቦታ...የፍቅር-ኩሽና::
የአእዋፋትም ዝማሬ...የዛፎቹ ሽዉታ:
የእረኛዉም ድርብ ዜማ ...ያ ቀጪኑ ስርቅርቅታ:
ሁሌም አይለዩኝ ነጋ መሸ እስከማታ::

እኅኅኅኅኅ..... ሆነና ቀሪዉም ድርሻ ህይወቴ:
ብለብስም አይደምቅብኝ ብበላም ጠብአይል ካንጄቴ::ዳሞት ከዳሞት::
Last edited by ዳሞት on Sun Jul 11, 2004 5:14 am, edited 2 times in total.
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ቋሳ ፍቅር...

Postby ዳሞት » Fri Jul 09, 2004 4:56 pm

ቋሳ ፍቅር!

ያ ቀጭን ዜማ የዋሽንቱ:
የክራሩ ድርደራ ቅኝቱ:
እንጫወት የነበረዉ በሌሊት ጨረቃ በድምቀቱ:
ሁሌም አይሽርልኝ ቁስለቱ ንድፍቱ::

መሯሯጡ ድብብቆሽ አላሊሆ ጨዋታዉ:
ገመድ መዝለል ..ሠኞ-ማክሰኞ ቡረቃዉ:
እስኪ አስቢዉ ማሬ! የቱ ነዉ የሚረሳዉ::
አእምሮዬ "ነጭ-ወረቀት" በሆነበት በዚያ ሰአት:
የታተምዉ "ድንቁ -ህያዉ-ፍቅርሽ" በልጂነት:
ሁሌም ቋሳዉ አይጠፋም ለአያሌ አመታት-ዘመናት::

ማሬ!
ብልሽ እንደ ወንዜ ቋንቋ እንዳገሬ:
ደስ ይለኛል "ቃሉም" ተጣብቆ ከከንፈሬ::
ሌሊት በዶፍ ዝናብ ጊዜ አንሶላ መጋፈፉ:
እርስ በርስ መተናነቅ ላለመስማት የመብረቅን ክፉ:
አንዳችን በአንዳችን ዉስጥ እንደበቅ እስኪመስል:
አንቺ ለኔ እኔም ለአንቺ እስክንመስል ጉብል:
ይህ ሁሉ አለ ምልሰቱ የጥንት የጥዋቱ አሻራ:
የፍቅርሽ ጉልላት ከትሞበት የነበረ ጎራ::

ፍቅሬ!

ታዲያ ይህ ሁሉ ነገር ተመሳጥሮ:
እንደምን? ይቻላል ሰዉ ካለፍቅር ኑሮ::
እንዴትስ ? ይዘለቃል በባዕድ አገር ኑሮ:

@ ~~~~>:roll: ለህያዉ ፍቅር ስትል ስደትን... ረሀብን..ስቃይን ..ለመረጠችው የልጂነት ፍቅሬ ከተጻፈ የፍቅር_ጦማር ተቀንጭቦ የተወሰደ::(በዳሞት) ~~> :roll:

ዳሞት ከዳሞት::
Last edited by ዳሞት on Sun Jul 11, 2004 5:16 am, edited 1 time in total.
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ለቋሳ-ፍቅር ምልሰቱ...

Postby ዳሞት » Sun Jul 11, 2004 2:59 am

የቋሳ-ፍቅር ምልሰቱ!


ያች የልጂነት ፍቅሬ :
...ሹክ ያልኋችሁ በጦማሬ:
ደህነነቴን ስትሰማ ከብዕሬ:
ፈነደቀች እንደ እምቦሳ እንደበሬ::
እናም...

ስደቱን...ስቃዩን...ናፍቆቱን:
እንዲህ ገለጠችዉ እዉነቱን::

እኅኅኅኅህ....እንዳልሁ ስለ አንተ እንዳሰብኩኝ:
ይኽዉ ዛሬ ድምጽህን ሰማሁትኝ::
ምድርን የዘረጋህ ሰማይን ያለካስማ:
ተመስገን ፈጣሪዬ! ከቦታህ ካለህማ::
እረ! ለመሆኑ ፍቅሬ!
ጥላ ጋሻ ከለላዬ... ጅምሬ
ናፍቆቱ...እርዛቱ...ስቃዩ...ሰቀቀኑ:
ብሶብኛል በየቀኑ::
.እኅህ...እኅህ. እኅኅ...ፍቅሬ!
የስጋዬ ተስፋ ...የመንፈሴ ፍሬ:
አንተ እኮ ነህ ለዕኔ:
እባክህ አትራቀኝ ከጎኔ::

እኒያ ያልካቸዉ ቦታዎች በሙሉ:
ነከሩኝ ወስደዉ ከፍቅር- ምልሰት ከመሀሉ::
እንዴት ልቻል!!!... ወንድሜ የነፍስ የስጋዬ ፍሬ:
ረመጥ ነበር አዝዬ የተለየሁህ ከአገሬ::

ታዲያ!
የሚሆን መስሎኝ አማራጭ አመንሁበት በስደቱ:
ግና ...ግና..ግና... አልለቅሽ አለኝ ንድፍቱ::
ነበር ያለችኝ በብዕሯ ....የንጹህ ፍቅር ስሜትን:
መለየት ጥቁር-አይኑን ያጠላበትን እዉነትን::


እኔስ ፈራሁ ራሷን ታጠፋ ይሆን? አምላኬ ከጪንቀት አዉጣኝ::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ላስታ » Sun Jul 11, 2004 4:31 am

ዳሞት ግጥሞቸህን እየተከታተልኩ ነው ::
በጣም የሚደነቅ ተሰጦ ነው ያለህና ተጠቀምበት::
"Whether you think that you can, or that you can't, you are usually right."
- Henry Ford
lasta _rasta
ላስታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Apr 07, 2004 10:00 pm
Location: iraq

ምን ላድርግ ላስታ....?

Postby ዳሞት » Sun Jul 11, 2004 5:25 am

ምን ልድርግ ላስታ....?


ፍቅር ሲደራ ሲበረታ....መች ክፉ ይጠፋና:
ስደትን ችግርን...መጋፈጡ ከፍቅር-ቀጠና::


አመሰግናለሁ:: ድጋፍህ/ሽ አይለየኝ::

ዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests