የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የቋሳ-ፍቅር ምልሰት ጦማር....

Postby ዳሞት » Sun Jul 11, 2004 6:28 am

መልስ ለልጂነት ፍቅሬ!

አቤት! ተመስገን:-
በህይወት መኖርሽን እንዳምን:
በዚያ በማዉቀው የጣቶችሽ ፍሬ:
ተቀሽረዉ የላክሽልኝ ፍቅረ-ሚጥሚጣ በርበሬ:
እጄ ገብታ ዛሬ ብስራቱን ተበሰሩ አልኩ ለሰፈሬ::

ፍቅሬ!

የልጂነት እዉነታ ገላጪ ደብዳቤሽን:
በማነብ ጊዜ አንዳች ስሜት ዉስጤን:
ሲቆርጠኝ ተሰማኝ አንጀቴን::
ረሀብ...ስቃይ...ችግር...ቁሩ:
አይጣል ነዉ ብቻ ለሚኖሩ::

ማሬ!

መቸም የስደት ትንሽ የለዉ:
በቀጣይ ደብዳቤሽ ሰፋ አድርገሽ ጻፊዉ::
ዉሀ ይሁን እምባ ፊቴን ሲያርሰኝ ብቻ:
ከመቅጽበት ተፈራርቀዉ ፍቅር ና ጥላቻ:
ባዶ-ህይወት ...ወና ፍቅር...ህሊናዬ እያለ:
በቁም-ቅዠት ልቤ ክንፍ አለ.... ዋለለ::
ህሊና በፍቅር-መንፈስ ካልታጀለ:
ከናፍርም ለግል-ግጣሙ ካልዋለ:
ህይወት ተረት እንጂ ሚስጥሩ ላይ የት? አለ::

ፍቅሬ!

ገላዬም በአልባሳት ቢዋብ...ከርሴም በጮማ ቢሞላ:
ባዶመንፈስ ሆኖብኛል እርቃን ገላ ወና ነገር ባዶ ጎላአይጣል ነዉ::

ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ባህታዊው » Mon Jul 12, 2004 9:50 pm

ስላም ዳሞት የኒ ወንድም!
ግጥሞችህ በጣም ልብ የሚነኩና አዝናኝም ናቸው.
መልካም ስራ በዚሁ ቀጥል

አክባሪህ
ባህታዊው ከደብረሊባኖስ
ባህታዊው
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Sun Jan 11, 2004 10:46 am

አወይ! ጉዴ ፈላ

Postby ዳሞት » Tue Jul 13, 2004 7:04 am

ከደብረ-ሊባኖስ ከባህቱ ቦታ:
ከጾለት መፍለቂያዉ ሰኔ-ጎለጎታ:
ባንዱ ጆሮ ፍቅሬን በዚያኛዉ ዉዳሴ:
ሲያዳምጥ የኖረዉ ይዞ በትረ-ሙሴ:
ይሄዉ ደረሰልኝ ሳታመልጠኝ ነፍሴ::
እባክህ ባህቱ ካለች እዚያ ገደል:
ሹክ በለኝ ጆሮዬን ወሮታ እንድከፍል::
አለም በቃኝ ላለ ቢሆንም ያ ደብር:
ብረት -ጠረንገሎ ሀያል ሰዉ ነዉ ፍቅር:
መነኩሴ ከገዳም ጎሽ ያስወጣል ከዱር::


ዳሞት ከዳሞት::

አመሰግናለሁ ባህቱ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

የጥምቀቱ ድሪ...

Postby ዳሞት » Thu Jul 15, 2004 5:14 pm

"የጥምቀቱ ድሪ"

አሪቲ... ሰረጡ.. ኮኮሱን ታጅላ:
ጋሜ...ቁንዳላዉን ጸጎሯን ተስተካክላ:
ጣቷን አዲስ አረብ ተሙቃ እንሶስላ:
በጉንፍ ቀሚሷ በተዋበዉ ጥልፍ:
በረጂም መቀነት በተጌጠ ቁልፍ:
እስክስታ ስትወርድ ጥምቀተ- ባህሩ:
ያስደስት ነበረ ዘፈኑ መዝሙሩ::


ይቀጥላል ::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

የጥም...

Postby ዳሞት » Sat Jul 17, 2004 9:50 pm

የዘገሊላዋ የጥምቀቷ ቆንጆ:
ቀሚስ ሽብሽቦዋ ቢመስልም ከረጆ:
ከአሁኑ ተሻለኝ እምብርት ከሚያሳየዉ:
ጪኗን እንደብቅል ጸሀይ ካሳረረዉ::


ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

የጥም....

Postby ዳሞት » Mon Jul 19, 2004 4:08 pm

የጥምቀቷ ፍሬ ከቦርሳ ቦርሳ አታዉቅ:

"ኮዝሞቲክስ ሊፕስቲክ" ብላ ማትጨነቅ:

"ለአጎጤ- ቆብ የላት" እግ/ር እንደሰራት:

"ግልገል-ሱሪ" የለ ሁሌም እንዳማራት:

እዚህ ከአጠገቤ ያሉትን እንስታት:

ፍርደ-ገምድል ሳልሆን እንዲያዉ ለሁለት ወራት:

ቦታ ብንቀያይር ምን አለበት በእዉነት!!

ጪር ባለ ገጠር ዉስጥ "ኢቲክሱን"ተምረዉ:

ምን? አለበት ዘመድ ዉጤቱን ብናየዉ::

ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

...ዋርካን በሲባጎ...

Postby ዳሞት » Wed Jul 21, 2004 4:28 pm

...ዋርካን በሲባጎ...


ልጂ ሆኜ ገና ጥንት:

አይ ነበር:: ሲሳብ ሲባጎ በመሬት::

በዚያስ ዘምን" መሬት- ላራሹ" ተባለ:

እዚህ ዋርካስ ምን አለ?

ገመድ ስበን ሀረግ ቆጥረን:

መሀል አገር ሌላዉ ሱዳን:

ሩቅ-ምስራቅ...አልፈን ሰሜን:

ስንል ቆየን::

አሁን ደግሞ ቀዬ ወርደን ታች ሰፈር:

በስመ-አንድ-ቦታ እያልን "መቆዘር"

የት ይሆን የሚያስከደን እስኪ አስቡት በቁም ነገር::

ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ቃል ወይንስ.....?

Postby ዳሞት » Sun Jul 25, 2004 9:39 pm

:roll:~~~ ቃል ወይንስ .....?~~~:roll:


ቃልም ካልሰመረ ካልሆነ ቁምነገር:

ለምንስ ጀመርነዉ ልንሰራ ያን ነገር::

ዕንዲያዉ ለሠዉ ይመሰል ከሆነማ ስራ:

ምን ዉጤት ሊኖረዉ ምን ፍሬ ሊያፈራ::

ቃልማ ያዉ ቃል ነዉ:

አንዴ ከአፍ የወጣዉ:

ትልቁ ችግር ግን ተግባር መሆኑ ነዉ::

በቃል ያለምነዉን በሥራ እንከዉነዉ:

የኛ መታወቂያ ሥማችን ያኔ ነዉ:

በሠራነዉ ስራ ቃሉን ቃል ብለነዉ::


ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ጥልፍልፍ

Postby ዳሞት » Mon Jul 26, 2004 6:07 pm

:roll:~~> ጥልፍልፍ~~~>:roll:

መስመር አይሉት ጠመዝማዛ:

መንገድ አይደል ፈዛዛ:

ትርጉም የለዉ ድፍን ብሎ:

ወደፊት አይታይ ጪፍን ብሎ:

ዉጣ ዉረዱ ታላቅ ስቃይ:

ገና ከወዲሁ ሲታይ::

ብቻ ጥልፍልፍ ነዉ መንገዱ:

ወደ ሕይወት ሲሄዱ::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ጫጩት ና ጪልፊት

Postby ዳሞት » Wed Jul 28, 2004 1:29 pm

:roll: ጫጩት ና ጪልፊት :roll:

ጫጩት ና ጪልፊት ምሳሌያቸዉ ጥሩ:

ልቡን ለከፈተ ሚሻ ከሚስጥሩ::

ጫጩት ሁለት እግር ያች ትንሽ ድንቢጥ:

ልትጪር...ልትፈልስ. ..ከእናቷ ስታመልጥ:

ስትቦርቅ...ስትዘል...ስትል ፈንደቅ -ፈንደቅ:

እንደወጣች ቀረች መቸም ጎዷ ማያልቅ::

ጪልፊትም ጊዜዉን ቀኑንም ጠብቆ:

"ከምድር-ይመታል" አንገቷን ጨርንቆ::

"አያ! አይምሬዉ"ደግሞ የጪልፊት ተምሳሌት

"ከጉድጓድ ይከታል" ከተኛንበት ቤት::

ስለዚህ ጫጩት ሆይ!

የሁለት እግሯን "እጣ" ሳንቀበል በፊት:

ጪረን ሳናወጣ "ዳቦ-መድፊያ" ትኬት:

እግርን ማሰር ይሻል በትልቅ ሰንሰለት::

ዳሞት ከዳሞት::

*** የዳቦ ቅርጫቱን ደፋ" ከሚለዉ የተወሰደ አማርኛ:: ==== ጫረ...ሞተ...ደየመ...አረገ....ቅቅቅ ወዘተ::***
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ቋሳ...

Postby ዳሞት » Fri Jul 30, 2004 2:19 pm

ፍቅሬ ድምጽሽ ጠፋ!

ፍቅሬ ድምጽሽ ጠፋ ምንድን ነዉ ነገሩ:

ሀሳቡ በዛብሽ ጠናብሽ ችግሩ?

"የመስቅል-ወፍ" ሆነሽ ብቅ ብለሽ አንድ ጊዜ:

ልቤን ሰቅለሽ ጠፋሽ ሳልበቃ ኑዛዜ::

ለእኔ ካህን አንቺ...ለአንቺ ካህን እኔ:

"ዝንየቱ" ሲመታኝ ሲጠልፈኝ ከጎኔ:

ሀጢያቱ በዛብኝ ለማን ልታይ እኔ::

ድምጽሽም ተስፋዬ እራት ድርጎዬ ነዉ:

"አምቦለኩን መጫር" የተዉሽዉ ለምን? ነዉ::

ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ላስታ » Fri Jul 30, 2004 7:41 pm

እያነበብነው ነው ያንተን ጥሩ ስራ
ዳሞት ሆይ በርታለን ሀገርህን አኩራ
ጥበብህ ማርኮኛል ማራኪ ነው በውነት
ከጎንህ አልለይም ሀሳብን በመስጠት

አድናቂህ ላስታ
"Whether you think that you can, or that you can't, you are usually right."
- Henry Ford
lasta _rasta
ላስታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Apr 07, 2004 10:00 pm
Location: iraq

Postby Debzi » Sun Aug 01, 2004 4:35 pm

አንተ የዳሞቱ ፍቅረኛህ ብዛቱ

ግጥሙ ለማነው ለየትኛይቱ?

እኔማ ዳር ቆሜ እንዲሁ አደንቃለሁ

እንዳንተ አይነት ወዳጅ ከየት አገኛለሁ
Debzi
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1918
Joined: Sun May 02, 2004 12:34 am
Location: Los Angeles, CA

ምስጋና...

Postby ዳሞት » Mon Aug 02, 2004 4:49 pm

ደብዚና ላስትዬ ምክራችሁ ዝናብ:

ምስጋናዬን ሳቀርብ በደስታ ከልብ:

ይሆነኛል እና የአመት ስንቅ ቀለብ::

እናንተም አትጥፉ እኔም አለሁ ዋርካ:

የ"ጥበብን ዳቦ" ልደፋ ሳቦካ::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

አስታርቁኝ ከራሴ...

Postby ዳሞት » Tue Aug 03, 2004 3:31 pm

አስታርቁኝ ከራሴ!


ብስጪትጪት... ብስክስክ ደርሶ ያደርገኛል:

ሰላም ያለዉ ኅይወት ከወዴት? ይገኛል::

ጥርሴ ከከንፈሬ ዐመል ከተዋጣ:

እንዴትስ? ሊታኘክ ...እንዴትስ? ሊጠጣ::

እራሴም ከእግሬ ጋ ቆዬ ከተጣላ :

እኔ እለብስ እኔ እለብስ ያችን አንድ ነጠላ::

በጧት ቀስቅሶ ደግ ካላሰማኝ:

የህሊና ዕረፍቱ ምንስ? ዋጋ ሊያገኝ::

ቅዠት አይሉት የቁም እንቅልፍ:

አንዱ ከአንዱ ሲተራመስ ሲጠላለፍ:

በአጪር በረጂም ዐላማ ስንከንፍ:

"ጥመቱ" ሳይታወቅ መንደድ ሆነ እንደጧፍ::

"ንደቱስ" ጥሩ ነበር:

የ"ጋን-መብራት" ባይሆን ባይቀበር::

ታዲያ!

እልምት የለዉ መቆሚያ:

የ-ዉኃ-ላይ ኩበት ...የማዕበል ዉጤት:

እሳቦቴ ሆኖ የነኝህ ተምሳሌት:

እንዴትስ? ልሸምግል ዕንዴትስ? ልጨምት::

ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests