የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

አስታርቁኝ...

Postby ዳሞት » Wed Aug 04, 2004 3:10 pm

ዕራሴን በራሴ ቋጥሬ:

"ኢምንት" ሆኘ አንድ ፍሬ:

ለሠዉ ከሆንሁ ደንታ-ቢስ:

"ሆደ-መጋዝ" ስለት ጥርስ:

ያኔ ነዉ ፍቅር "ጥላሸት" የሚለብስ::

እኮ ያኔ

የ"ጨለማ-አበጋዞች" ሲቆሙ ከጎኔ:

ያኔ ነዉ ፍቅርን ደህና ሁኝ ያልኋት በመጥኔ::

ዳሞት
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ከሰዉ ወዲያ ለሰዉ...

Postby ዳሞት » Thu Aug 05, 2004 4:27 pm

:roll: ከሠዉ ወዲያ ለሠዉ :roll:


ሆዴን ሆድ ሲብሰዉ ሆድ በሆድ ሲከፋ:

ቀኑ ዘንበል ሲል ዘመም ሲል ደፋ:

የሰዉ ልጂ ለሰዉ ነዉ ክንድ አጋሩ ተስፋ::

ጠጋኝ ድጋፍ ሠጪ ወገን አጋር ሲሻ:

ወኔዉ ጥሎት ሲሸሽ...አለሁ ባይ ወጌሻ:

ከኅይወት ዉዝግብ ከዉጣ ዉረዱ:

ከማጣት ከማግኘት ከመጥላት መዉደዱ:

ከትርምስ ኑሮዉ ነፋስ ከሚንጠዉ:

ማረፊያ ወደቡ ለሰዉ ልጂ ያዉ ሰዉ ነዉ::

አቋራጪ ሲፈተሽ ኑሮን ለማሸነፍ:

ችግር ቋጥኝ ሆኖ ከእግር ስር ሲወተፍ:

ልብን ሲቃ ይዟት ዐይን ዕምባ ሲዘራ:

ከሰዉ ወዲያ ለሰዉ ማን? አለ ሚራራ::

ማን? አለዉ ለሰዉ ልጂ ከሰዉ ወዲያ ለሰዉ:

በሀዘን ...በደስታ... በሁሉ ሚደርሰዉ:

ሲስቅ አብሮ ሥቆ እምባ አባሹ ለሰዉ:

አቻ...አጋርም የለዉ ከሰዉ ወዲያ ለሰዉ::


ዳሞት ከዳሞት::(*አ.አ*)

* ማስታወሻነቷ :- በትምህርት ቤት ቆይታዬ

ባሳለፍኋቸዉ ዘመናት ልጨኛ ለሆኑኝ ዉድ ና

ተናፋቂ ጓደኞቼ በሙሉ:: እንዲሁም በተለያየ ቦታ

ለምትኖሩ በጥሩ ስነምግባር መልካም አርዐያነታችሁ

ተምሳሌት ለሆናችሁኝ ተባዕት ና አንዕስት የዋርካ

እድምተኞች ...
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ላስታ » Thu Aug 05, 2004 7:26 pm

እናመሰግናለን ዳሞት !
"Whether you think that you can, or that you can't, you are usually right."
- Henry Ford
lasta _rasta
ላስታ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 59
Joined: Wed Apr 07, 2004 10:00 pm
Location: iraq

ከሠዉ ወዲያ ለሰዉ...

Postby ዳሞት » Sun Aug 08, 2004 2:52 am

ልብን ሲቃ ይዟት አይን ወዳጂን ሲሻ:

ዐይን በዕምባ ተሞልቶ ሲቸገር ለጥቅሻ:

ዐንደበት ሲታሰር ምላስ ሲሆን ዲዳ:

ጣትም ሲርገበገብ ለማምለጥ ከፍዳ:

ክንድን አስለቃቂ የነፍስ-ደራሽ ጋሻ:

የሰዉ ልጂ ለሠዉ ነዉ ጠጋኙ ወጌሻ::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ለሰዉ...

Postby ዳሞት » Tue Aug 10, 2004 4:38 pm

ሠውን ሠዉ ለማለት ቢሹኝም ቁም ነገር:

በድብርት ጃንጥላ ራስን ከመቅበር:

ሳይሻል አይቀርም ከላይ ስቆ ማደር::

ከልብ የመነጨ ፈገግታና ኅሴት:

ለማግኘት የጸዳ -ትዕቢትና ኅኬት:

ኅሜት ና ትምክኅት ተወርዋሪ ምላስ:

ስረ-መሰረቱ ባድማዉ እንዲፈርስ:

አንገት-ለዐንገት ሆኖ ፍቅርን ነዉ መቃመስ::

ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ፈላስፋ » Tue Aug 10, 2004 5:45 pm

ዳሞት
በጣም የምትደነቅ ሰው ነህ:: ትልቅ የስነ ጽሁፍ ስጦታ አለህ:: እነዚህን በህትመት ለማውጣት ብታስብበት ጥሩ ይመስለኛል:;

አክባሪህ
ፈላስፋ
ፈላስፋ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Wed Feb 18, 2004 9:05 pm
Location: united states

ዐንገት...

Postby ዳሞት » Wed Aug 11, 2004 4:22 pm

አንገት ...

የይሉኝታ ምንጩ ..."ሆደ-ቡቡ" መቃ:

የኔ መስታዉቴ ክንድ-ጋሻ-ጠበቃ:

የእኔነቴ ምርኩዝ እንዳልወድቅ ከጪቃ::

ዐንገት አንተ ባትኖር እኔን መች አዉቄ:

መቅረቴ ነበረ ሜዳ ላይ ወድቄ::

ዳሞት ከዳሞት

ማስታወሻነቷ ለይሉኝታ:: * አንገት የተሰራዉ ራስን

አዙሮ ለማየት ነዉና!*
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ሑሉም ቀረ ሀገር...

Postby ዳሞት » Fri Aug 13, 2004 4:36 pm

ሑሉም ቀረ ኃገር....!የኅወትን ጣፋጭ ፍሬ:

ጂምር ተስፋዬን አንግቤ ቋጥሬ:

የኑሮን ቀመር ቀምሬ:

ሣልረታ በአልቧልታ በወሬ:

ወረድሁ ገባሁ ከቀዬ ከመንደሬ::

ሰፈር ወንዙም ተቀበለኝ በደስታ:

በእንኳን ገባህ በዕልልታ:

ሳር ቅጠሉ በነፋሱ ሽዉታ::

ዕኔም ያኔ ቢሰማኝም እርካታ:

ዕንደዛሬዉ ሳይሆን "ነገር-በፈንታ":

ሁሉም ኖረ በጪፈራ በእርካታ::

ግን ዛሬ ሁሉም ሆነ ሰማይ ጠራ:

ዱር ገደሉ ሜዳ ተራራ::

ከኑሮ ዕሾህ ጋሬጣ:

ከኅይወት ተምች አምበጣ:

የኅይወትን ኬላ የኑሮንም ጣጣ

እንድምን ይቻላል? ማለፍ ከዚህ ቁጣ::

የኅይወትን ጥሩ ጂምር በጎ ፍሬ:

ለመታደግ ከነጣቂ ከዱር አዉሬ:

ሳይዘግነኝ እንደ ዕፍኝ ቆሎ-ጥሬ:

ሠዎች ምን ትመክሩኝ? ምን? ይሁን ተግባሬ::

"ምን ያደርጋል!" ሆነ እንጂ አባባሉ ተረቱ:

ዕንዲህ "መብተክተኩ" ዕንደ ጥጥ መባዘቱ:

ሑሉም ሀገር ቀረ! መከበሩ ኩራቱ::


ዳሞት ከዳሞት::

ያለፍኋቸዉ መንገዶች ትዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝ....ብለዉኝ ነዉ:: ይቅርታ::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ባይኖር ኖሮ ተስፋ...

Postby ዳሞት » Sat Aug 14, 2004 2:05 pm

ባይኖር ኖሮ ተስፋ...!


ዙሪያዉ ገደል ሆኖ ጨለማ ሲወርሰን:

ደስታ ከአገር ጠፍቶ ኃዘን ሲጸናብን:

ፈገግታ ተረስቶ ትካዜ ሲተካ:

ኑሮም ሲደበዝዝ ሲመስል ማይፈካ:

ነገም ስትሸሸን:

ከአድማስ ስትርቀን:

ኅይወት እጂግ ከፍታ ዕሬት ስትሆንብን:

ባይኖር ኖሮ ተስፋ የሚያጣፍጥ ኑሮን:

ምድር ትሆን ነበር:

የኅያውያን በድን... የሙታንም መንደር::

ዳሞት ከዳሞት:: (አ.አ)
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ባይኖር ኖሮ ተስፋ...

Postby ዳሞት » Wed Aug 18, 2004 2:09 am

ባይኖር ኖሮ ተስፋ የኅልም ዕራት ስንቅ:

በነገ ምንነት በኃሳብ ባህር ዉስጥ ዕንደዚያ ስጠልቅ:

አለኝ ያልኩት ሲበን ልጨኛዉ ሲጠፋ:

ወዳጂ በወዳጁ ረመጡን ሲጪር ዕሳቱን ሲደፋ:

ምን ይዉጠኝ ነበር ባይኖር ኖሮ ተስፋ::

ይቀጥላል::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ለዳሞት

Postby ማንጤ » Wed Aug 18, 2004 10:08 pm

በእውነት ምን አረ አረ ምን ልበለው
የዳሞት.......መጣጥፍ ልቤን በጣም ነካው
ነካካው..ነጠረ...ልቤም ተደሰተ
ዳሞትን ፍለጋ በአይኖቹ አፈጠጠ
በርታልኝ ያበርታህ :D
ማንጤ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 26
Joined: Sun Aug 15, 2004 8:20 pm
Location: united states

ባይኖር ኖሮ ተስፋ...

Postby ዳሞት » Thu Aug 19, 2004 4:33 pm

አይዞሽ ባይ "ደም-መላሽ" ከጎንሽ ቢጠፋ:

ሊዘንብ ..ሊያርከፈክፍ ..አልያም ሊያካፋ:

አስቦ ከላይ ደጂ...ግንባርሽ ላይ ጽፎ:

"ሊያገምጥሽ" ሲሞክር የ"ተስፋን-ማር-ድፎ"

ከዚህ ከዚህ ሳትይ ኃሳብሽ ተጠልፎ:

ስንክልክል..እንክትክት...ብለሽ ብትቀሪ:

ባይኖር ኖሮ ተስፋ በምድር ስትኖሪ:

መጋትሽ ነበረ "የኅይወት-ቅራሪ"::

እናም....

ተስፋ...

የህሊና ጸብል...የመንፈስ ዕርካታ:

ተመስገን ዕንበልዉ እሱን ለፈጠረ ለላይኛው ጌታ::


ዳሞት ከዳሞት::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

Postby ማንጤ » Thu Aug 19, 2004 11:10 pm

ዳሞቴ
ምነው ምን አጠፋው በጣሙን ዘጋሀኝ
ለላኩልህ አስተያየት መልስ ሳትሰጠኝ
መጣጥፍህ ጣፍጦኝ እኔም አጣጥሜ
በሀሳብ ፈረስ ስጋልብ ደክሜ
ሁሌ ካንተው ጋራ አለሁ ተደምሜ
ዳሞታችን በርታ ብህርህ ይፈታ
መጳፍህ ታትሞ ለማየት እንብቃ
:D
ማንጤ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 26
Joined: Sun Aug 15, 2004 8:20 pm
Location: united states

አሜን::

Postby ዳሞት » Fri Aug 20, 2004 6:52 am

ዐሜን::
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

ዕራሴን ዐጣሁት!

Postby ዳሞት » Fri Aug 20, 2004 5:09 pm

ዕራሴን ዐጣሁት...!በዉል የማላዉቀዉ ታላቁ ፈላስፋ:

በጠራራ ጸኃይ ብርኃኗ ሳይጠፋ:

በዕኩለ-ቀን ቀትር በባትሪ ታግዞ:

"ንጹህ-ሠዉ" እያለ ይፈልግ ነበር በዕጁ ባትሪ ይዞ::

....ከትቢት... ከጉራ... ሂሊናዉ የጸዳ:

ቦታ የሚሰጥ ሰዉ ከልቡ ዉስጥ ጓዳ:

እዉነተኛ ወዳጂ ፍቅርን የተረዳ:

ጊዜ ና ወቅት ዐይቶ ፍጹም የማይከዳ:

እሱ ነዉ "ኅያዉ-ሰዉ" የሰላም-ልጨኛ የክብር እንግዳ

ከዚህ ታላቅ ፍጡር ምኑን ልምሰል እኔ:

ዕራሴን አጣሁት ገባሁኝ ኩነኔ::

ይቀጥላል::

ዳሞት ከዳሞት::
Last edited by ዳሞት on Sat Aug 21, 2004 5:54 pm, edited 2 times in total.
ዳሞት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 19, 2003 12:05 am
Location: ethiopia

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests