የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የተቀደደ ሕልም

Postby ዋኖስ » Sat Dec 18, 2010 5:40 pm

የተቀደደ-ሕልም፤


በሕይወት ሽንቁር ዉስጥ አጮልቄ አይቼ፣

ገላሽን ዳሰስኩት፤ ነካሁት በእጆቼ።

እንደተመኘሁት ባይበዛም ደስታዬ፣

ሐሴትን ለመርገጥ በቃሁ በፈንታዬ።

ግና የከለለሽ ዓለት፤ የሰወረሽ ፈፋ፣

ግዙፉ ቀንሶ፣ ሽንቁሩ ሲሰፋ፣

እጆቼ ሲያጥሩብኝ፤ ገላሽ ከዓይኔ ራቀ፣ ጎንሽ ከኔ ጠፋ።


ዳሞት ከዳሞት

ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Feb 06, 2011 8:07 am

ቢቻል ምን አለበት !

ይህንን የዛሬውን ከቶም ላለማየት

ዳግመኛ መወለድ ቢቻል ምን አለበት

ቢመጣ ልጅነት ተመልሶ ዳግም

እድሜን ወደ ኋላ መልሶ ላለመድገም

በፈለጉት ጊዜ የእድሜ ዘመን ላይ

የኋሊት መዘወር ቢቻል ይህን ጉዳይ

ሀ ብሎ ጭንቅላት ቢመለስ ቢያሰላ

ዳዴ ማለት ቢኖር እንዲያ ወደ ኋላ

ካብሮ አደግ ጓደኛ መሄድ ትምህር ቤት

ጭቃ አቡክቶ ማደግ አፈርን በመፍጨት

በጠፍጣፋ አለት ላይ ሸርተቴ መጫዎት

ውሀ እየተራጩ ሌባ ፖሊስ ማለት

ይህ ሁሉ ቢመለስ ዳግም ምን አለበት

እንዳለፈ ባይቀር ተመልሶ ቢያዩት

ያን መልካሙን ጊዜ የጊዜ ቁንጮ ዘውድ

ነበረ መመለስ መመለሱ ባይገድ

ይህንን የዛሬውን ከቶም ላለማየት

ዳግመኛ መወለድ ቢቻል ምን አለበት ?

ታናሽ ለታላቁ ታዛዥ ከሆነበት

እድሜ እንኳን በራሱ ክብር ካላጣበት

ችሎታ ከውቀት ጋር ከሚያስከብሩበት

በዘር ሐረግ ቋንቍ ከማይታሙበት

ባባቱ ስም ብቻ ልጅ ከሚጠራበት

ባያት በቅድም አያት ከማይማልበት

ሕግ ስራትና ደንብ ትርጉም ካገኙበት

ሰው በሰውነቱ ደግሞም በዜግነት

እንደ አቅም ችሎታው ሠርቶ እሚኖርበት

ባንድነቱ ጸንቶ ካለ አንዳች ጭንቀት

በሃዘን በደስታ በመከራውም ሞት

የመጣው ቢመጣ ካለመለያየት

በሰላም በፍቅር ኑሮ እሚገፋበት

ያንን ደግ ዘመን የምድር ምድረ ገነት

ምናል ቢቻል ኖሮ መልሶ ለማየት

በየስራ መስኩ እንደየችሎታው

እንደየ እውቀቱ ክህሎቱ በሰጠው

አቅሙ እንደፈቀደ እንደ ሥራ ድርሻው

እንደ ፍላጎቱ ምርጫ ዝንባሌው

ነጋዴው ከገበያው ገበሬውም ከርሻው

ወታደር ከድንበር ሃኪሙም ከመርፌው

መምህሩም ማስተማር ነበረ ግዴታው

ሹፌር መካኒኩም እሱም እንደ ሌላው

ሕግ አስከባሪ እና ዳኛውም ጠበቃው

የሃይማኖት መሪ ቄሱም ሆነ ሸካው

ዘፋኝ አቀንቃኙ አሊያም ደራሲው

ሸክላ ሰሪው እና ብሎም አንጥረኛው

አልቃሽ ሆነ አዝማሪ መቃብር ቆፋሪው

ለማኙም እንዲሁ ወይም ሰርቶ በላው

ወዛደርም ይሁን ጎዳና ላይ ኗሪው

አናጺ ግንበኛ ወይ ደግሞ ሊስትሮው

ልብስ ሰፊው ሆነ አለዚያ ሸማኔው

ያ ፓይለቱስ ቢሆን ባየር ላይ በራሪው

ቀያሽ ማሃንዲሱ እንዲሁም ዘበኛው

ዝሙት አዳሪና የቤት ሰራተኛው

ይህን የዛሬውን ከቶም ላለማየት

ዳግመኛ መወለድ ቢቻል ምን አለበት ?

ግና

ብቃት ተሞክሮ አንዳችም ሳይኖረው

ካለውቀት ችሎታ ከሆነ እሚሰራው

ለውድቀት ድህነት ቀደምት ተጠያቂ እሱ ነው

ላገር ወገን ሸክም ዋነኛው እሱ ነው

አላዋቂ ሳሚ ዜሮ ፊታውራሪ

ቢቀር እሽሩሩ አላዋቂ ሰሪ

እያየን ባይናችን ንፍጡን መለቅለቁን

ኋላ ቀር ተመጽዋች ሲያደርገው ትውልዱን

ሳያገባው ገብቶ ሲያምስ ወገን ዜጋን

ሲያስኬዳት በዳዴ ድፍን አገሩቱን

እሚቻል ከሆነ እውነቱን መናገር

በቅን አሳቢነት ካለ እሚቆም ላገር

ከተገኘ አሳቢ በንጹህ ልቦና

ላገር ወገን ዜጋ እድገት ብልጽግና

መለየት የማይችል መች ጠፍቶ በውነት

መሆን ያለበትን መሆን ከሌለበት

ጥፋቱ ልማቱን ልቦናችን ሲያውቀው

ላገር ሟች መሆኑን ሁሌም እያየነው

በሠላም ለመኖር እንዴት እንንፈገው


ኧረ የሠው ያለህ ይህን ምን እንበለው ?
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Wed Feb 09, 2011 7:42 am

የማይነጋ ሌሊት !


የማይነጋ ሌሊት ጽልመቱ የፋፋ

ዕድሜው የረዘመ ጊዜው የከረፋ

ጥቂቱን አስቆ ብዙውን ያስቆዘመ

እሚገርም ምሽት ጓዙን አንጠልጥሎ

ለካ እሱ ባዶ ነው የተረፈው መስሎ

መከረኛ ሌሊት ከዕንቅልፍ ያራራቀ

በጥም አንገብግቦ ባምሮት ያወደቀ

ጉልበት አሽመድምዶ ቅስም ያደቀቀ

የወሬ መጋዘን የተስፋ ጎተራ

ሌቱ እማያልቅበት ቢወራ ቢወራ

የምሽት ሽንቅላት ታጥቦ የማይጠራ

አይጥሉት ሥጋ ነው አይጥሉት አሞራ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Feb 13, 2011 7:29 am

ጎበዝ አስከ መቼ


የዝምታ ባሕል ሰፍኖ በውስጣችን

ለኛ ለወጣቶች በዕድገት ባህላችን

አስኪ አናስተውለው ካለፈው ስራችን

ያለመወያየት ለኛ ስለሆነ ዋና ጠላታችን

ዝምታ አይበጀውም አሉባልታን መቸ

ባንድ ላይ እንምከር ፍርሃት አስከመቸ

ዘር ቀለምን ሳይለይ ሁሉም ባንድነት

ሳናየው ቆይተን ይህ ሰደድ እሳት

ዶክተርም ምሁራን ሳያስቡበት

ቫይረስ ታጥቆ መጣ ቀጠፈ ሕይዎት

ቆረጠ ቀጠፈ አደረገ መና

እኛም ለመለወጥ ስንል ደፋ ቀና

ጎድቶ ዘረፍን ሃገር ተረካቢውም ወደቀ ጎዳና

ቆንጆ በቤት ዋለ ጎበዝ ከቤት ሆነ

ምርታችን ቀንሶ ልመናም ሰፈነ

ሰውነቱ ደክሞ ጎበዝ ሲንገላታ

ማወቅ ነው ማስተዋል አይሁን በዝምታ

የባለፈው ይብቃ ዳግም እንበርታ

ዳግም የለም ብለን ጉዳት በስተሗላ

መታለል ይቅርብን ከንግዲህ ላይሞላ

መጠንቀቅ ቀድሞ ነው ከመጪው መከራ

ያለዚያ በድፍረት ካልን ደፈር ኮራ

ኤድስ አይኖርም እያልን ከሰአት በሗላ

ያጭድ ይከምራል ሊነዳው በጂምላ

ወጣቱ ባይንህ አይተህ ለሕሊና ከቆምክ

ሁሌም ጥንቁቅ ሆነህ ሌላውን በመስበክ

ስማኝ አንተ ወጣት የሃገሬ ጀግና

ስሚኝ አንች እህቴ የሕይዎቴ ዋስትና

የሃገር ዋልታ መሰረት ናችሑና

ለልማት ተነሱ ላገር ብልጽግና

የዘመኑ ችግር የዕድገቱ እንቅፋት

ሆኗልና ዔድሱ የሰደድ እሳት

ክንድህ ይተባበር ቶሎ ለማጥፋት

ቃል ብቻ አይበቃውም አሉባልታ መቸ

እንወያይ እንጅ ጎበዝ እስከመቸ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Tue Feb 15, 2011 7:23 am

እኔና ሕሊናየ !


ጸጥ ባለው ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ

መጣ አቶ ህሊና ድምጽ ሳያሰማ

ተነስ እንወያይ ብሎ እየተጣራ

ስበእናህን አየሁ ሁሉንም ገምግሜ

ሥራህንም ታዘብኩ ብዙ ደጋግሜ

በሄድክበት ቦታ ምን እንደምትሰራ

ሰርክ ነው የማይህ መብራት እየበራ

እንዳካላህ ቆዳ ከላይህ የማልወርድ

እስከ ዕለተ ሞትህ ካንተ እማልላቀቅ

የውስጥ ዳኛ የስብዕና አውራ

እኔ ነኝ ሕሊና ኗሪ ካንተ ጋራ

ድምጹን ከፍ አድርጎ ጮኾ ቢናገረኝ

እባክህን ተወኝ ብዙ አትጨቅጭቀኝ

በችጋር በሀዘን በስቃይ ተመትቸ

ህሊና ህሊና እያልኩ ልኑር እስከ መቸ ?

ጓደኛ ሲሰርቅ ማንንም ሳይፈራ

በስልጣን ማጭበርበር ሕይዎቱን ሲመራ

ባለታሪክ ነኝ ባይ የሃኬት ሓውልት ሲገነባ

ውጭ ሆኖ ለመቅበር ሠው ሁሉ ሲያደባ

በምልዐት ሠፍሮ ሃሰት መንደር ላይ

ተሸክሞ ነግሶ ቆሞ ባደባባይ

ታጋይ ነኝ ባዮችም ለወገኔ እያሉ

አርነት ለማውጣት በነፍጥ ሲታገሉ

ሲወድቁ ሲነሱ ሲሞቱ ሲገድሉ

ስልጣኑን ሲይዙ ደግሞ ተደላድለው

ጨቍኝ ይሆናሉ ከቀድሞቹ ብሰው

አንዳንዶቹም ደግሞ በውነት እየማሉ

ሸፋጮች ሆነው ተውኔት ይሰራሉ

በሃይማኖት ካባ ደግሞ አንዳንዶቹ

መጻፍ እየቃጣው ፍጹም ሳይሰለቹ

በሥመ እግዚያብሄር ወጥመድ እያበጁ

ሴራ እያሴሩ በፈርጅ በፈርጁ

የሠይጣን ሃዋሪያ ሆነው እየባጁ

ግፍ ይቆልላሉ ገድለው እየፈጁ

እባክህ ሕሊና በቃ አትጨቅጭቀኝ

እንደ ማንኛውም መስሎ ነዋሪ ሰው ነኝ

ብየ ብናገረው ሕሊናን በቁጣ

እሱም በበኩሉ በንዴት ተንጣጣ

ስማኝ የኔ አካል እስቲ ይታወስህ

ቀድሞ እንዴት ነበርክ ኑሮና ሕይዎትህ

ሕሊና ቢሶችን ስታወግዝ ባደባባይ

ንጹህ ሠው ነበርክ በግልጽ የምትታይ

ታከብረኝ ነበረ በቅን ልቦና

ባለትህትና ነበርክ ምክሬን ትሰማና

አሱንስ ደልቶሃል ሥጋህም አጌጠ

አይምሮህ ግን ከስቶ ውስጡ ተሟጠጠ

ብመክርህ ብዘክርህ እያልከኝ አልሰማ

በጣም አዝን ጄመር ልቤ እየደማ

እያለ ተናግሮኝ ባዘኔታ ሕሊና

መልስ ይጠብቅ ጀመር ሆኖ በጥሞና

ታዲያ እኔ ምን ላድርግ ሁሉ እየተሯሯጠ

አንዱ አንዱን ለመጥለፍ ፍጹም ካደፈጠ

ሕሊናውን ረግጦ ባህሉን ደፍጥጦ

ሆዱን አምላክ አድርጎ ከሁሉ አስበልጦ

ልጆቹ አጊጠው ለብሰው ሲያማምሩ

በተሰረቀ ሃብት በምቾት ሲኖሩ

በዚህ ምግባራቸው ደግሞ ሲከበሩ

ባንጻሩ ደግሞ ለሕሊና የሚኖር ለውነት የገበረ

በሕዝብ የከበረ ሃቅን ያፈቀረ

ስቃዩ በዝቶበት ከስቶ እየጠቆረ

ተከፍቶ ይኖራል አንጄቱ እያረረ

ብዬ ብናገረው ሕሊና ተገርሞ

አንዴ ብቻ አድምጠኝ አለኝ በአድምሞ

ለራስ ብቻ አይደለም ሚኖር አንድ ሠው

በጥልቅ ቢመረምር ላገር ጭምር ነው

ማንኛውም ዘር ምድር ላይ ቢበዛ

እንዳፈጣጠሩ ፍሬ እንደሚያፈራ

እኩይም በእኩይ ሠናይም በሰናይ

የተዘራ ነገር ይታጨድ የለም ዎይ ?

እንደዚህ ሁሉ ሕሊና በስም ስራ

ጣፋጩን አድርጎ ጎምዛዛ መራራ

ነገርን አድርጎ እንቧይ ካብ ድርደራ

ትውልድን ያጠፋል ለባለ ወር ተራ

ስለዚህ የኔ አካል ታረቅ ከኔ ጋራ

ቆሻሻና ጉድፍ ካንተ ታጥቦ ይጥራ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sat Feb 19, 2011 3:13 pm

መሬት አትቆጭ !


መሬት አትቆጭ ቀስ ብየ እረግጣለሁ

ነገ ካንች በታች መሆኔን አውቃለሁ

አቀበት ቁልቁለት ደፋ ቀና ብየ ኑሮን ለማሳካት

ድንገት ብጫንሽም አይምሰልሽ ክፋት

ዛሬን ፍቀጂልኝ ካሰብኩበት ልድረስ

የሕይዎት ግዳጄን ጉዞየን ልጨርስ

በጄርባሽ ታዝየ የኖርኩት ኑሮየን

ባንች አይን ስተመን ባንች እጅ ሲመዘን

ወርድና እርዝመቱ ወይ ስፋት ጥልቀቱ

ጥቅምና ጉዳቱ ድፍርስ አተላነት ወይንም ጥራቱ

ድቅድቅ ጨለማነት ወይ ጮርቶ መንጋቱ

እስቲ ምን ይመስላል አጫውችኝ ላንዳፍታ

ላልጨረስኩት ጅምር ለቀሪው ጉዞየ መላን እንድመታ

ያን ዕለት ስመጣ ቤትሽ በድንገት

አጫውትሻለሁ ስላለፍኩት ሕይዎት

ሕመም በሽታየ ቅሬታ ጭንቀቴን

ጥማት እርካታየን ሃዘን ደስታየን

ጨዋታን ቀልዴን ቅኝትና ሕልሜን

አልሳካ ብሎ የቀረ ምኞቴኝ

በጅምር የቀረ ያንጠለጠልኩትን

ያምላክ ፈቃድ ሆኖ ያከናወንኩትን

አንዱንም ሳላስቀር ትንሹን ትልቁን

እጀርባሽ ላይ ሆኘ ያውጠነጠንኩትን

አጫውተሻለሁ ያለፈው ዕድሜየ ሁሉንም ዘርዝሬ

ጉዞየን ጨርሸ ክንዴን ስንተራስ ሲታክተው እግሬ

እስከዛው ታገሽኝ ቀስ ብየ እረግጣለሁ

ነገ ካንች በታች መሆኔን አውቃለሁ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Tue Feb 22, 2011 7:13 am

ላንች ብዬ ሁሉን ትቼ !


ተነድፌ ባንች ፍቅር ባንች መውደድ

ባንች ቆፈን ባንች ንዳድ

ባንች እረሃብ ባንች ጥማት

ባንች አምልኮ ባንች እምነት

ሆኘ ልኑር ያንች አገልጋይ

ያንች ሎሌ ያንች ክፋይ

ይኸው አለሁ ሁሉን ትቸ

ላንች ፍቅር ተገዝቸ

እሕሕ እያልኩ እያለቀስኩ ዕለት ተለት

ላንች ኖሬ ላንች ልሙት

ሁሉን ትቸ አፈቀርኩሽ

እንዳንድዬ አመለክኩሽ

ቀልቤን ወስደሽ እኔነቴን አዘንግተሽ

ባንች እየማልኩ

ላንች እየኖርኩ

እኔነቴን እረስቸው

ሁሉን ንቄ ሁሉን ትቸው

እንደታቦት አንችን ስሜ

በናላዬ ተሸክሜ

እኖራለሁ ሁሉን ትቸ

ላንች ፍቅር ተገዝቸ

ባንች ልድን ላንች ሞቸ

ባንች ምናብ እያሰላሁ

ባንች ራዕይ አልማለሁ

ባንች ልሳን እያወጋሁ

በንባዎችሽ እያጠቀስኩ እጽፋለሁ

እጽፋለሁ እጽፋለሁ እጽፋለሁ

ለፍቃድሽ ለትዛዝሽ እገዛለሁ

አንች በኔ እኔ ባንች እኖራለሁ

ዳግም እኖራለሁ እኖራለሁ እኖራለሁ

እንደገናም እጽፋለሁ እጽፋለሁ እጽፋለሁ

እናም ወደድኩሽ ብዕሬ

ላንች ልሙት ባንች ኖሬ

ብዕሬ !!
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sat Mar 05, 2011 6:53 am

እኔ አንችን ላልረሳ !ክረምቱ ሲቆጣ ሲያለቅስ መሬቱ

የእንጦጦ ተራራ ሲለዋወጥ ፊቱ

በሀምሌ ነጎድጓድ ሲተነተን ዜና

የሰማይ በረዶ ሲሰፈር በቁና

አክሮባት ሲሰራ ሲገለበጥ ጉሙ

ዛፉ ሲገረሰስ ሲወድቅ በቁሙ

ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ጠፈር ሲሰነጠቅ

ሲቀደድ በቁሙ መቀስ ሆኖ መብረቅ

የየረር ተራራ በሁኔታው ሲስቅ

አረንጓዴ ለብሶ ወጨጫ ተራራ

አንገቱን ቀና አርጎ ወደላይ ሲጣራ

የማይቆረጠው ጎፈሬው ሲያስፈራ

አዋሽ አውሬ ሆኖ ሥጋውን ሲያጣጥም

የነ ሉሲን አጥንት ይዞ ሲቆረጥም

ከወለጋ ትግራይ ከትግራይ ቦረና

ከአፋር እስከ ከፋ ከጉዴ እስከ ጣና

ከመተማ ላስታ ከራስዳሼን ጉና

ከሁሉም ቦታ ላይ ለመድረስ በደህና

በመላ ሀገሪቱ ስልክ አስደወለና

ያየር መጓጓዣ ትኬት ቆረጠና

ይኸው ገሰገሰ ተጓዘ ዳመና

እርሻውን ሊጎበኝ በየሁሉ ቦታ

ሥራ ሊቆጣጠር እቃውን በሙሉ አዘጋጅቶ ማታ

ያውና ዳመናው ሄደ በሱሉልታ

አባይ ልማደኛው ጫን አለ ፈረሱን

ትከሻው ላይ አርጎ አፈርና ልብሱን

እያረጋገጠ ግብጽ ጋር መድረሱን

ይኼ ሁሉ ሲሆን እኔ አንችን ላልረሣ

ዝናብ እንዳይመታሽ ሰራሁልሽ ገሣ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Mar 06, 2011 3:26 pm

እሚ !!!!ትዝታም እኮ ስንቅ ነው

ፍቅርሽን ችለን ባንዘልቀው

የውለታሽን ልክ መጠኑን

ቸርነትሽን አስታውሰን

ብድሩን አሁን ባንከፍልው

ትዝታም እኮ ስንቅ ነው

የዘመን ዱካ ያለበት ልባቸው የዘገበው

ባንች ነው እና የቆምነው

መነጋገሩስ አይከፋም እስቲ ላንድ አፍታ እናውራው

የጉያሽ ሙቀት የእቅፍሽ

የእናትነቱ ሚስጥርሽ

ልቤን ፈንቅሎ የገባው እንዴት ቢሆን ነው እባክሽ

እንድፈነድቅ ያረገኝ ብርዱን ከውስጡ አውጥቶ

ክፋትን ከልቤ ነቅሎ ፍቅርን በቦታው ተክቶ

እንዴት ቢሆን ነው እባክሽ ሙቀት የሆነኝ ሙቀትሽ

ፍቅር የሰጠኝ እቅፍሽ ሀሴት ያገኘው ከክንድሽ

እንዴት ቢሆን ነው እባክሽ

ደረትሽ ለኔ መስክ ሆኖ ሕይዎት በውስጡ ያቀፈ

ካጋቱት ከጡቶችሽ ላይ አይኔ በጉጉት ያረፈ

ወተትሽ ሕይዎት የሆነኝ

ያለሱ ያጣሁትን እስትንፋስ የሰጠኝ

እኮ ምንድነው ሚስጥሩ ለኔ ትሩፋት ለኔ በውስጡ ማኖሩ

ምን ያህል ቢሆን ነው ፍቅሩ የኔነትሽ ሚስጥሩ

እስቲ እናውጋው ግድየለም

ሕይዎት ላንዳፍታ ካልቃኟት ውበት ለዛውም አይጥምም

ትዝታ ስንቋ ካልሆነ ተስፋ በውስጧ አይኖርም

እሚ እናውጋው አይከፋም

ችግሬን በኔ ሳላውቀው አዘኔን በውል ሳልፈታው

ሳይገባኝ ጭራሽ ማልቀሴ

እንባን ካይኖቼ ማፍሰሴ

ላንች ግን የሚገለጸው

እንዴት ቢሆን ነው እንዴት ነው

የሆዴን የምታገኝው

ዜማ ቅኝቱን ከልብሽ አውጥተሽ እያዜምሽልኝ

በክራር እያዜምሽልኝ በዋሽንት የምትጠልፊኝ

በሽሩሩ ቃል በዜማ ዝም ረጭ የምታደርጊኝ

እንዴት ቢሆን ነው ንገሪኝ እኔው ለራሴ ጠፍቼ አንች የምታገኝኝ

እናት እባክሽ ንገሪኝ ይህንን ሚስጥር አጫውችኝ

ህመሜ አንችን ማመሙ ስቃዬ ስቃይሽ ሆኖ ጉንጮችሽን በንባ ማቅለሙ

ስሜትሽ ስሜቴን ቃኝቶ ሲከፋሽ አይቶ መክሰሙ

ህልሜን በህልምሽ ማለሙ ደስታየን ልብሽ ማዜሙ

እንዴት ቢሆን ነው እንዴት የመውደድሽ ልክ መጠኑ

የፍቅርሽ ጥልቀት ስፋቱ እንዴት ቢሆን ነው ወሰኑ

እግሮቸ በወገብሽ ላይ ደረቴን ባንች ላይ ጥዬ

ባንቀልባሽ እቅፍ ታዝየ በጄርባሽ ተንጠላጥዬ

አይኔ በኩራት ሲያበራ ፍጥረትን ቁልቁል እያየ

መከታ ጋሻ ሆነሽኝ እንደ ጋላቢ ሲዳዳኝ

ስቃይሽ ለኔ ሳይገባኝ ታዝሎ መቆየት ሲያቀብጠኝ

አንች ግን ፍጹም አይከፋሽ እንደ ጋላቢ ሲቃጣኝ

እስቲ ምንድን ነው ነገሩ በጀርባሽ የትም ታቅፎ የመደሰት ሚስጥሩ

ምን ያህል ቢሆን ነው ፍቅሩ::


በወጣትነት ዕድሜው ከዚህ ዐለም በሞት የተለየው ገጣሚ እና ጋዜጠኛ መስፍን አሸብር::
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ምረቱ » Fri Mar 11, 2011 5:49 am

ግሩም ግጥም!

thanks for sharing!


ኦኑፈያሮ wrote:እሚ !!!!ትዝታም እኮ ስንቅ ነው

ፍቅርሽን ችለን ባንዘልቀው

የውለታሽን ልክ መጠኑን

ቸርነትሽን አስታውሰን

ብድሩን አሁን ባንከፍልው

ትዝታም እኮ ስንቅ ነው

የዘመን ዱካ ያለበት ልባቸው የዘገበው

ባንች ነው እና የቆምነው

መነጋገሩስ አይከፋም እስቲ ላንድ አፍታ እናውራው

የጉያሽ ሙቀት የእቅፍሽ

የእናትነቱ ሚስጥርሽ

ልቤን ፈንቅሎ የገባው እንዴት ቢሆን ነው እባክሽ

እንድፈነድቅ ያረገኝ ብርዱን ከውስጡ አውጥቶ

ክፋትን ከልቤ ነቅሎ ፍቅርን በቦታው ተክቶ

እንዴት ቢሆን ነው እባክሽ ሙቀት የሆነኝ ሙቀትሽ

ፍቅር የሰጠኝ እቅፍሽ ሀሴት ያገኘው ከክንድሽ

እንዴት ቢሆን ነው እባክሽ

ደረትሽ ለኔ መስክ ሆኖ ሕይዎት በውስጡ ያቀፈ

ካጋቱት ከጡቶችሽ ላይ አይኔ በጉጉት ያረፈ

ወተትሽ ሕይዎት የሆነኝ

ያለሱ ያጣሁትን እስትንፋስ የሰጠኝ

እኮ ምንድነው ሚስጥሩ ለኔ ትሩፋት ለኔ በውስጡ ማኖሩ

ምን ያህል ቢሆን ነው ፍቅሩ የኔነትሽ ሚስጥሩ

እስቲ እናውጋው ግድየለም

ሕይዎት ላንዳፍታ ካልቃኟት ውበት ለዛውም አይጥምም

ትዝታ ስንቋ ካልሆነ ተስፋ በውስጧ አይኖርም

እሚ እናውጋው አይከፋም

ችግሬን በኔ ሳላውቀው አዘኔን በውል ሳልፈታው

ሳይገባኝ ጭራሽ ማልቀሴ

እንባን ካይኖቼ ማፍሰሴ

ላንች ግን የሚገለጸው

እንዴት ቢሆን ነው እንዴት ነው

የሆዴን የምታገኝው

ዜማ ቅኝቱን ከልብሽ አውጥተሽ እያዜምሽልኝ

በክራር እያዜምሽልኝ በዋሽንት የምትጠልፊኝ

በሽሩሩ ቃል በዜማ ዝም ረጭ የምታደርጊኝ

እንዴት ቢሆን ነው ንገሪኝ እኔው ለራሴ ጠፍቼ አንች የምታገኝኝ

እናት እባክሽ ንገሪኝ ይህንን ሚስጥር አጫውችኝ

ህመሜ አንችን ማመሙ ስቃዬ ስቃይሽ ሆኖ ጉንጮችሽን በንባ ማቅለሙ

ስሜትሽ ስሜቴን ቃኝቶ ሲከፋሽ አይቶ መክሰሙ

ህልሜን በህልምሽ ማለሙ ደስታየን ልብሽ ማዜሙ

እንዴት ቢሆን ነው እንዴት የመውደድሽ ልክ መጠኑ

የፍቅርሽ ጥልቀት ስፋቱ እንዴት ቢሆን ነው ወሰኑ

እግሮቸ በወገብሽ ላይ ደረቴን ባንች ላይ ጥዬ

ባንቀልባሽ እቅፍ ታዝየ በጄርባሽ ተንጠላጥዬ

አይኔ በኩራት ሲያበራ ፍጥረትን ቁልቁል እያየ

መከታ ጋሻ ሆነሽኝ እንደ ጋላቢ ሲዳዳኝ

ስቃይሽ ለኔ ሳይገባኝ ታዝሎ መቆየት ሲያቀብጠኝ

አንች ግን ፍጹም አይከፋሽ እንደ ጋላቢ ሲቃጣኝ

እስቲ ምንድን ነው ነገሩ በጀርባሽ የትም ታቅፎ የመደሰት ሚስጥሩ

ምን ያህል ቢሆን ነው ፍቅሩ::


በወጣትነት ዕድሜው ከዚህ ዐለም በሞት የተለየው ገጣሚ እና ጋዜጠኛ መስፍን አሸብር::
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
www.borkena.blogspot.com
facebook page: https://www.facebook.com/pages/Borkena/ ... 356?ref=hl
ምረቱ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Sun Jan 14, 2007 5:52 am

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Mar 13, 2011 7:53 am

ተቃርኗዊ ግምደት !


ያዳም ዘር ልዩነት በማህበራዊነት

አንድ የመሆን ቅኝት ታፍኖ ታጅሎ ሲያጭር ወገናዊነት

አብሮ መፈጠሩ ባዳ የሚሉት ስሜት

ይገርማል በውነት የሰውነት ኡደት ተቃርኗዊ ግምደት

ላንድነት ልዩነት ነጻነት ባርነት

ሙትና ነጻነት ለሰላም ጦርነት

ሕይዎትን ለማትረፍ ሕይዎትን መሰዋት

ያንዲት ስንዴ መሞት ስንዴዎችን ማፍራት

ፍቅርን አልሞ ሆዱ እንዳይጎዳ ለፍቅር መጣላት

እርስ በርስ መናጨት አንዱ አንዱን መጉዳት

ሆኖም ባንድ በኩል በዳይ ነኝ ባይ ጠፍቶ

በዳይ በሌለበት ተበዳይ በርክቶ

አንድም ሳይቀር ሁሉም ተበዳይ ነኝ ካለ

ሠው በራሱ እንጅ በማን ተበደለ

እንዳይነጣጠል ፍቅርን ማጣት ጠልቶ

አብሮ መኖር ያለርካታ ሲያውቀው ሳያመልጠው በላብ ማደር ፈርቶ

በእጸ በለስ ብዛት ሜዳ አልታይ ብሎ ተሸፍኖ ጠፍቶ

ሠው እሆን እያለ ሠውነቱን ጠልቶ

እንደዚህ ባንዳ ላይ ሕሊናውን ስቶ

መናቆር መናጨት ሁሉ ነገር ሞልቶ

እራስን ለማክበር ሌላውን ማደህየት

በራስ ላይ የበላይ ሆኖ ለመገኝ አንድ ላይ መጋጨት

ለፍጹም አንድነት ዘልአለማዊነት

በሱነቱ ልቆ ጸንቶ በፍቅር ላይ

የሠው ልጅ እይታው ያንድነቱን ጉዳይ

ማየት እስከሚችል ጉዟችን ነውና በኔነት ጎዳና

የኛን ጉዳይ ጭራሽ አላወቅምንና

በዚያው እየዳከርን ላይታየን ደህና

አፍርሶ መገንባት እየሰሩ ማጥፋት

እራስን ለማግኘት ልዩነት ባንድነት

ባላቸው ዝምድና በኔነት ጎዳና

ነፍስ በራስ እጦት በፍለጋ ባዝና

አንዳች ሳይለወጥ ሂደቱ ይቀጥላል

አንደኛው ተሰብሮ አንዱ እየተቃና

ተቃርኗዊ ግምደት የሠው ሕይዎት ቃና
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Mar 13, 2011 8:08 am

ብዙ ያተረፈ ሸጦ እየለወጠ

ገበያ ያዛባ እየሸመጠጠ

ሲሸጥ ያልከሰረ አውቆ ያደፈጠ

ጣቱ ይወገዳል እየተጋጠ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Mar 13, 2011 10:58 am

ብዙ ያተረፈ ሸጦ እየለወጠ

ገበያ ያዛባ እየሸመጠጠ

ሲሸጥ ያልከሰረ አውቆ ያደፈጠ

ጣቱ ይወገዳል እየተጋጠጠ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Wed Mar 23, 2011 10:36 am

ምንጩ ሲደርቅ !


የማይደርቀው ምንጭ ደረቀ

የሳቅ ትዕይንቱም አለቀ

በቃ ሁሉም አኩርፏል

ከንግዲህ በምን ይሳቃል

አዎ! የማይደርቀው ምንጭ ደርቋል

ሠው ያለ ሣቅ ከኖረ

ሣቅ ሞቶ ከተቀበረ

ታዲያ ምነው የሳቅ ምንጮች

ለምን ሆኑብን ጨካኞች

ከኛ ደስታ እንደተጣሉ

ቀስ ሳይሉ እንደቸኮሉ

እልም ጭልጥ አሉብን

እኛን ያለሳቅ ትተውን

ለሐዘን ድባብ ዳርገውን

በቃ ራቁ ላይመለሱ

የሚናፍቃቸውን እንዳስለቀሱ

ተስፉ እንግዳዘርና አለቤ ተካ

ከሳቁ ምንጫቸው ምንም ሳይተካ

ድንጋይ ተጫናቸው አከተሙ በቃ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

ምስቅልቅል አለ

Postby tekure » Sat Mar 26, 2011 5:31 pm

ይህ ጽሁፍ የገባች ሁ ካላችሁ እባካችሁ አስረዱኝ!
አመሰግናለሁ
ኦኑፈያሮ wrote:ተቃርኗዊ ግምደት !


ያዳም ዘር ልዩነት በማህበራዊነት

አንድ የመሆን ቅኝት ታፍኖ ታጅሎ ሲያጭር ወገናዊነት

አብሮ መፈጠሩ ባዳ የሚሉት ስሜት

ይገርማል በውነት የሰውነት ኡደት ተቃርኗዊ ግምደት

ላንድነት ልዩነት ነጻነት ባርነት

ሙትና ነጻነት ለሰላም ጦርነት

ሕይዎትን ለማትረፍ ሕይዎትን መሰዋት

ያንዲት ስንዴ መሞት ስንዴዎችን ማፍራት

ፍቅርን አልሞ ሆዱ እንዳይጎዳ ለፍቅር መጣላት

እርስ በርስ መናጨት አንዱ አንዱን መጉዳት

ሆኖም ባንድ በኩል በዳይ ነኝ ባይ ጠፍቶ

በዳይ በሌለበት ተበዳይ በርክቶ

አንድም ሳይቀር ሁሉም ተበዳይ ነኝ ካለ

ሠው በራሱ እንጅ በማን ተበደለ

እንዳይነጣጠል ፍቅርን ማጣት ጠልቶ

አብሮ መኖር ያለርካታ ሲያውቀው ሳያመልጠው በላብ ማደር ፈርቶ

በእጸ በለስ ብዛት ሜዳ አልታይ ብሎ ተሸፍኖ ጠፍቶ

ሠው እሆን እያለ ሠውነቱን ጠልቶ

እንደዚህ ባንዳ ላይ ሕሊናውን ስቶ

መናቆር መናጨት ሁሉ ነገር ሞልቶ

እራስን ለማክበር ሌላውን ማደህየት

በራስ ላይ የበላይ ሆኖ ለመገኝ አንድ ላይ መጋጨት

ለፍጹም አንድነት ዘልአለማዊነት

በሱነቱ ልቆ ጸንቶ በፍቅር ላይ

የሠው ልጅ እይታው ያንድነቱን ጉዳይ

ማየት እስከሚችል ጉዟችን ነውና በኔነት ጎዳና

የኛን ጉዳይ ጭራሽ አላወቅምንና

በዚያው እየዳከርን ላይታየን ደህና

አፍርሶ መገንባት እየሰሩ ማጥፋት

እራስን ለማግኘት ልዩነት ባንድነት

ባላቸው ዝምድና በኔነት ጎዳና

ነፍስ በራስ እጦት በፍለጋ ባዝና

አንዳች ሳይለወጥ ሂደቱ ይቀጥላል

አንደኛው ተሰብሮ አንዱ እየተቃና

ተቃርኗዊ ግምደት የሠው ሕይዎት ቃና
tekure
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 34
Joined: Mon Dec 12, 2005 3:20 pm
Location: Jerusalem

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests