የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሳምራውው33 » Mon Oct 15, 2012 5:42 pm

እውቀትህን አትገድብ

አስተውል አንተ ሰው ኑሮህን አስተውል
መውጣት መግባትህን ጉዞህን አስተውል
ጠይቅ ተመራመር ከየት እንደመጣህ
ጠይቅ አእምሮህን ወዴት እንደምትሄድ
.....................................ህይወትህ ሲያበቃ
ተመልከት ሙታንን ዛሬ በህይወት የሉም
ነገር ግን እንዳንተ ትላንት በህይወት ሳሉ
መብላት መጠጣትን እንዲሁም መጫወት
.........................................ሁሉም ይወዳሉ
ስለዚህ ጠይቀህ ህይወትህን ተረዳ
ከሙታኖች ጎራ መሄድህን አትርሳ
ስራ በጎ ምግባር በህይወት እያለህ
ለህያዋን የሚቀር አንተ አፈር ሳለህ
በፊት በህይወት ያሉት አንተ ሳትፈጠር
አበርክተው ሰጥተው ያገኙዋትን ነገር
ሆኗል መጠቀሚያ አንተ ስትፈጠር
እውቀትና ጥበብ ፈጣሪ ካደለህ
ለመስጠት አትሳሳ ያንን ለከጀለ ::
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

ሰላምታ

Postby ዋኖስ » Tue Oct 16, 2012 12:17 am

ሰላምታዬ ይድረስህ

ለግብዣዎ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነዉ::

በወዳጅነትዎ አብረን እንቆይ!

"እውቀትና ጥበብ ፈጣሪ ካደለህ"

እውቀትም፣ ጥበብም ሁሉም የአምላክ ጸጋ፣

እንደሆኑ አዉቃለሁ ማይገዛቸዉ እንቁ፣ ማይሽራቸው ዋጋ።

ዘመናትም አልፈው፣ ዘመናት ሲመጡ፣

እሳቦቶች ሁሉም በአዲስ ቢለወጡ፣

የእርሱ ግን የእርሱ ነው፤ የጸና ነው ቃሉ፣

የጥበብ በረከት፣ የእዉቀት አድማስ ጠሉ፣

በአንድ ላይ ሊኖሩ፤ ብሎም ላይጣሉ፣

ቃል ኪዳኑን ሰጥቷል፤ በሶሎሞን ልጁ፣

እንግዲሕ ይድረስሕ አምላካዊ ጸጋዉ ከማሳሳዉ እጁ።

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ሳምራውው33 » Tue Oct 16, 2012 8:35 am

ክቡር ዳሞት የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩልህ ይሄን ቤት እስከዛሬ ባይገርምህ አይቼው አላውቅም :: ቶሎ ገረፍ ገርፍ አድርጌ ሳየው ድንቅ የግጥም ሰው መሆንህን አይቼአለሁ :: ግጥምህ ለብዙሀኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚደርስበትን ዘዴ ብትፈልግ ደስ ይለኛል :: በርታ በርታ :!: :!:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ሳምራውው33 » Tue Oct 16, 2012 6:40 pm

'ይቻላል ! '

መፈክሩን አየሁ 'ይቻላልን' ፈተሽኩ
አወጣሁ አወርድኩ በውስጤ መረመርኩ
ታዲያ ባይገርማችሁ በኢምንቷ እውቀቴ
'ይቻላል' ላይቻል ድቅን አለ ፊቴ
እርቁም አልተጓዝኩ ምስክር ፍለጋ
ፎቶውን አየሁት በሩጫ ሲላጋ
ይቻልማ ቢሆን ቋሚ ቢሆን ደንቡ
ከሗላ አተርትረው ሯጮቹ ባልገቡ
እና እንዴት ይቻላል ? 'ይቻላል' አይቻል
ብዬ አሰላስዬ ነገሩን ልቆርጥ ስል
የቋንቋው አካሄድ ደግሞ ከነከነኝ
'ይቻላል' መቻሉ የሚቻል መሰለኝ ::
ከሗላ መሮጡ ይቻላል ቢሆንስ
ከዛም አንጻር አየሁ - እንደዚያ ቢባልስ !?
በዚህ ልቋጨው ስል ደግሞ አገረሸብኝ
'ይቻላል' አይቻል የሚል አዋለለኝ ::
ግን ብዙም አልዋዠቅሁ ቶሎ አቋም ወሰድኩኝ
ምን አከራከረኝ ምን ከሙግት ዶለኝ ?
ያው ለባለቤቱ ! 'ይቻላልን' ተውኩኝ
እኔ ግን 'ይቻላል ' አልኩኝ - 'አይቻልም !'
እንጂማ ! ይቻልማ ቢሆን ማን ይሻል መመራት
................................................ማን ይሻል መቀደም ?


ከሰናፊጭ ቅጽ አንድ መጽሀፍ የተወስደ ::
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

አስበበታለሁ

Postby ዋኖስ » Tue Oct 16, 2012 11:00 pm

አመሰግናለሁ!

እስኪ አስብበታለሁ::

ዳሞት

ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 17, 2012 7:25 pm

ጥሩ ግጥም

የግጥም ውበቱ አርማው ምልክቱ
የቤት አመታቱ የቃላት ጥብቀቱ
እጥር ምጥን ብሎ ልብ ላይ መቅረቱ
አንባቢን አፍዝዞ መስጦ መውሰዱ
በጣም ሳይንዛዛ ኢላማ ሳይስት
አንብቡኝ እያለ አጓጓቶ የሚይዝ
ሀሳቡ የሚያስደስት መልእክቱ የሚያረካ
ባላላቀ የሚያሰኝ ነብስን የሚነካ
እንዲህ ያለ ግጥም የግጥሞች ምሳሌ
በብዛት አይፈልቅም እንደው ባልባሌ ::
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ሳምራውው33 » Fri Oct 19, 2012 8:51 pm

ሌባውን ያዙልኝ !

ሌባውን ያዙልኝ - ሌባውን ያዙልኝ
.....................የሚል ድምጽ ተሰማ
ሌባውን ከደህና እንዴት ይለይና ?
የሰዉ ግርግር በጣም ተበራክቶ
ህግ ስርአቱ ምስቅልቅሉ ወጥቶ
የገበያው ስፍራ ግጥም ብሎ ሞልቶ
ሰውን ከሰው መለየት እጅጉን አዳግቶ
እንዴት ይታወቃል ሌባው ተለይቶ ?
የዘመኑ ሌቦች በጣም የረቀቁ
ከለላ ሽፋንን አቤት መልበስ ሲያውቁ!
የቁጥርን ብዛት መጠቀሙ ሳያንስ
ሱፉን ግጥም አርጎ አጠገቦ ቆሞ
ይሰርቀኛል ብለው እንዴትስ አስበው ?
እርሶ የሚጠብቁት ይሰርቀኛል ብለው
ክርትት ግርጥት ያለን ምስኪን ደሀውን ነው
ተንቀሳቃሽ ሆኖ ህዝብ ባልቆመበት
እንደወንዝ መፍሰሱን ባላቋረጠበት
ሌባውን ለይቶ ማውጣት ጣጣ አለበት ::
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ሳምራውው33 » Mon Oct 22, 2012 9:17 pm

በቆልት

የተናቀ ስራ የረባ ትርፍ የለው
ዘፍዝፎ ባቄላን ከውሀ ማውጣት ነው
ውሀ ውስጥ ተከቶ ያደረ ባቄላ
ለስላሳ ይሆናል ለጥርስ የሚደላ
ኑሮዬን ማሸነፍ ግራ ቢገባኝ
የገቢ ማስገኛ መንገድ ቢጠፋኝ
በቆልትን ቸርችሬ መኖር ጀመርኩኝ
ሳልስት እንደሞላው ሲበቅል ባቄላው
ውሀውን አፍስሼ በቆልቱን ለይቼ
እወሽቀዋለሁ ዘንቢሌን ከፍቼ
ቅመም ማጣፈጫ ሰልቅጦ መዋጫ
ቀምሜ ሰናፊጭ ወስፋትን መክፈቻ
በቆልት ስል እውላለሁ መንደር አስሳለሁ ::
ገቢዬ የማይረባ ሆኖ ሚያንሰኝ
ሳንቲም ለቃቅሜ መኖር ሳይገርመኝ
ኧረ ለምንድን ነው በቆልት የሚሉኝ
እኔን ከባቄላ ምን አገናኘኝ ?
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 5:20 am

የክብርነታችን ሰንጋ በሬ ሆይ:: ይሄ የጻፍከው ነገር ቤት መታ እንጂ ግጥም አይደለም:: ውበት የለውም ምጡቅ አይደለም ጥልቀት የለውም:: :: ስለ በቆልት ሻጩ ይሁን ውሀ ውስጥ ተነክራ ወደ በቆልትነት ስለምትለወጠው ባቄላ ለማን እንደገጠመክ እንኴን አንባቢ አንተም አታውቅወም:: እንደ በቆልት ሻጭ ሆነህ ቀረብክና ራስህ ደሞ በቆልቷን ሆንክ እኮ!! ሰው አያነበኝም ነው?? እነ እንቶኔ ስለገጠሙ እኔም ልግጠም ነው..? ወይስ ምንድነው?? ደግሞ ወስፋት አይከፈትም:: ሙሬ ወይ ሆድ ወይ የምግብ ፍላጎት ይከፈታል ስላንግና የጽሁፍ ቃላትን እያደንክ ጻፍ:: ስድ:: ሙከራህ መልካም ነው:: ግን በጀመርከው ጨርስ:: አንተ እኮ በዜማ ጀመረህ በቀረርቶ አሳረገው ;; ምን አይነቱ ነው እባካቹ ? ጌኛ:: :D ናና ደሞ ኬምስትሪ ላስተምርህ በለኝ...አይ ዊል ሀቭ አ ኮሽን ፎር ዩ ሳም ደይ.. እንዳትጠመለመል ግን ጥምልምል!! :D

የክብርነታችን ሰንጋ በሬ እንደገጠመው እጠቅሳለሁ wrote:በቆልት

የተናቀ ስራ የረባ ትርፍ የለው
ዘፍዝፎ ባቄላን ከውሀ ማውጣት ነው
ውሀ ውስጥ ተከቶ ያደረ ባቄላ
ለስላሳ ይሆናል ለጥርስ የሚደላ
ኑሮዬን ማሸነፍ ግራ ቢገባኝ
የገቢ ማስገኛ መንገድ ቢጠፋኝ
በቆልትን ቸርችሬ መኖር ጀመርኩኝ
ሳልስት እንደሞላው ሲበቅል ባቄላው
ውሀውን አፍስሼ በቆልቱን ለይቼ
እወሽቀዋለሁ ዘንቢሌን ከፍቼ
ቅመም ማጣፈጫ ሰልቅጦ መዋጫ
ቀምሜ ሰናፊጭ ወስፋትን መክፈቻ
በቆልት ስል እውላለሁ መንደር አስሳለሁ ::
ገቢዬ የማይረባ ሆኖ ሚያንሰኝ
ሳንቲም ለቃቅሜ መኖር ሳይገርመኝ
ኧረ ለምንድን ነው በቆልት የሚሉኝ
እኔን ከባቄላ ምን አገናኘኝ ?
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 24, 2012 2:16 pm

ክቡራን wrote:የክብርነታችን ሰንጋ በሬ ሆይ:: ይሄ የጻፍከው ነገር ቤት መታ እንጂ ግጥም አይደለም:: ውበት የለውም ምጡቅ አይደለም ጥልቀት የለውም:: :: ስለ በቆልት ሻጩ ይሁን ውሀ ውስጥ ተነክራ ወደ በቆልትነት ስለምትለወጠው ባቄላ ለማን እንደገጠመክ እንኴን አንባቢ አንተም አታውቅወም:: እንደ በቆልት ሻጭ ሆነህ ቀረብክና ራስህ ደሞ በቆልቷን ሆንክ እኮ!! ሰው አያነበኝም ነው?? እነ እንቶኔ ስለገጠሙ እኔም ልግጠም ነው..? ወይስ ምንድነው?? ደግሞ ወስፋት አይከፈትም:: ሙሬ ወይ ሆድ ወይ የምግብ ፍላጎት ይከፈታል ስላንግና የጽሁፍ ቃላትን እያደንክ ጻፍ:: ስድ:: ሙከራህ መልካም ነው:: ግን በጀመርከው ጨርስ:: አንተ እኮ በዜማ ጀመረህ በቀረርቶ አሳረገው ;; ምን አይነቱ ነው እባካቹ ? ጌኛ:: :D ናና ደሞ ኬምስትሪ ላስተምርህ በለኝ...አይ ዊል ሀቭ አ ኮሽን ፎር ዩ ሳም ደይ.. እንዳትጠመለመል ግን ጥምልምል!! :D

የክብርነታችን ሰንጋ በሬ እንደገጠመው እጠቅሳለሁ wrote:በቆልት

የተናቀ ስራ የረባ ትርፍ የለው
ዘፍዝፎ ባቄላን ከውሀ ማውጣት ነው
ውሀ ውስጥ ተከቶ ያደረ ባቄላ
ለስላሳ ይሆናል ለጥርስ የሚደላ
ኑሮዬን ማሸነፍ ግራ ቢገባኝ
የገቢ ማስገኛ መንገድ ቢጠፋኝ
በቆልትን ቸርችሬ መኖር ጀመርኩኝ
ሳልስት እንደሞላው ሲበቅል ባቄላው
ውሀውን አፍስሼ በቆልቱን ለይቼ
እወሽቀዋለሁ ዘንቢሌን ከፍቼ
ቅመም ማጣፈጫ ሰልቅጦ መዋጫ
ቀምሜ ሰናፊጭ ወስፋትን መክፈቻ
በቆልት ስል እውላለሁ መንደር አስሳለሁ ::
ገቢዬ የማይረባ ሆኖ ሚያንሰኝ
ሳንቲም ለቃቅሜ መኖር ሳይገርመኝ
ኧረ ለምንድን ነው በቆልት የሚሉኝ
እኔን ከባቄላ ምን አገናኘኝ ?ስለ ግጥም መጻፍ ውሻው ሊነግረኝ
እንከን ሰበብ ቢጤ ሲፈልግብኝ
ግጥምን በግጥም ጽፎ ሳይገጥመኝ
ስድ ሆኖ መጣብኝ ሰዎች እዬልኝ
ፍርፋሪ ሰቶ ወያኔ አስሮታል
የማመዛዘኑን ጥበብ ወስዶበታል
የራሱ ፈጠራ ምንም ነገር የለው
እቺን ጠቅ እያለ ሰውን ማሰልቸት ነው ::
ውሻ የውሻ ልጅ ጥንብ ነህ አህያ
አይመጥንም ላንተ መሆን ጋዜጠኛ
ጋዜጠኛ ሰራው የቅድሚያ ተልኮው
እውነትን አውርቶ ለእውነት መሞት ነው ::


ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ
:!: :!: :!: :!:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 2:42 pm

ከለታቱ ባንድ ቀን ባንዲት ከተማ..
የገጠር አህያ መኅል መንግድ ቆማ.. ( ሳምራውን ልብ.ይሏል)
መኪና መጣን ድምጹን ሳትሰማ.. ( እኔን ያጤኗል)
ጨፍልቆ አሳረፋት ውሀ ሳትል ደክማ!!

ከታላቁ የግጥም ባለህብት ከከበደ ሚካኤል የጨለፍኩት ነው:: የኔ ስራ እንዳይመስልህ:: 8) አንተን እያሰቡ የጻፉት ይመስለኛል:: ግጥም ባንተ እጅ መጫወቻ መሆኗን ሳያዩ ሄዱ:: እግዚአብሄር አባታችንን ይባርክ:: አንተ ግን አምቧችር:: ሰዎች ይራመዳሉ እንስሶች ያምቧችራሉ..ትንሽ ቌንቌ ለማስተማር ያህል ነው:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 24, 2012 6:27 pm

ቅሎ የኔ ቂሎ አድምቄ እንዲሁም አስምሬልሀለሁኝ ከገባህ ግጥምህን አሳይ ባዶነትህን አስጥተህ ከምታሳይ :: ኢትዮጵያን የሚያኮሩ ገጣሚዎች ያሉብት ቤት ነው ቅልነትህን ይታዘቡታል ::

ስለ ግጥም መጻፍ ውሻው ሊነግረኝ
እንከን ሰበብ ቢጤ ሲፈልግብኝ
ግጥምን በግጥም ጽፎ ሳይገጥመኝ
ስድ ሆኖ መጣብኝ ሰዎች እዬልኝ
ፍርፋሪ ሰቶ ወያኔ አስሮታል
የማመዛዘኑን ጥበብ ወስዶበታል
የራሱ ፈጠራ ምንም ነገር የለው
እቺን ጠቅ እያለ ሰውን ማሰልቸት ነው ::
ውሻ የውሻ ልጅ ጥንብ ነህ አህያ
አይመጥንም ላንተ መሆን ጋዜጠኛ
ጋዜጠኛ ሰራው የቅድሚያ ተልኮው
እውነትን አውርቶ ለእውነት መሞት ነው ::


ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ
:!: :!: :!: :!:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 6:53 pm

የክብርነታችን አጋዘን ሆይ!! ቤት የመታ ሁሉ እኮ ግጥም አይደለም:: ግጥም ለመባልም አይመትንም::; ካጣጣልህ እንዳየሁት አንተ ጀማሪ ገጣሚ ነህ:: ሳነብህ በበቆልቲ ጀምረህ በራስህ ጨርስከው:: ያን አይቼ አጀማመርህና አጨርራስህ ትክክል አይደለም አልኩ:: ያን ፈትሽ:: ሀሳቤን በስድ ንባብ ማድረሴ ይመጥንሀል እንጂ አይጎዳህም:: በግጥም የምምለስልህ ገጣሚ ብትሆን ነበር:: በርታ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 24, 2012 7:16 pm

Removed :roll: :roll: :roll:
Last edited by ሳምራውው33 on Thu Oct 25, 2012 12:36 pm, edited 1 time in total.
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 8:29 pm

ቆመህ ታያለህ ከማለት ይልቅ ...ቆመህ ታያታለህ ..ብትለው ዜማውን ሞር ይጠብቅልሀል:: ማሰሪያውን ያጠብቅልሀል::
ክቡራን ነን ከቅኔ መንደር:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest