የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 24, 2012 9:15 pm

ክቡራን wrote:ቆመህ ታያለህ ከማለት ይልቅ ...ቆመህ ታያታለህ ..ብትለው ዜማውን ሞር ይጠብቅልሀል:: ማሰሪያውን ያጠብቅልሀል::
ክቡራን ነን ከቅኔ መንደር:: :D


መሀይም መሳቂያ ነህ ለምን መሰለህ ሰውን የሚያርመው የተሻለ እውቀት ያለው ነው :: ይልቅስ ዋርካ ፖለቲካ ሂድ እነ ሪቾ እየሳቁብህ ነው እዚህ ግጥም ብቻ የሚጻፍበት ቤት ነው :: ቅሉ ቂሎ የኔ ግጥም አይደለም ስለዚህ አልነካውም ደግሞ መነካት አይፈልግም :: በተጨማሪ ደግሞ ተሳስቸ ፈረድኩብህ በቆልት የሚለው የረቀቀ ግጥም ሀሳቡ አልገባህም ምክንያቱም ፋራ ጥፍራም ነህ እንዳልገባህ በምላሽህ አውቄአለሁ ስለዚህ ደግመህ ደጋግመህ አንብብ ወይም እንግሊዝኛ የሚያርሙልህን ጠይቅ እና እንዴት ውብ ግጥም እንደሆነች ታውቃለህ ፋራ እንደወረደ ነህ :lol: :lol: :lol: :lol:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

መልካም

Postby ዋኖስ » Wed Oct 24, 2012 10:09 pm

እንዴት ዋላችሁ ግራ ቀኝ ወዳጆቼ! እንዴት ሰነበታችሁ!

ምን መጣ? ለምን ዉይይታችሁን በእንዲሕ ቋጫችሁት? ይገርማል! በሉ ተስማሙ! እንዲሕ አይነቱን እሰጣ ገባ ከእናንተ ከታላላቅ ወንድሞቼ አልጠብቅምና ደግማችሁ እንደማትመላለሱ ተስፋ አደርጋለሁ::

ቤቷንም በአግባቡ ብንጠቀምባት መልካም ነው::

ከመልካም አክብሮት ጋር!

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 10:12 pm

የክብርነታችን መሲና ሆይ !! አሁንም አልተግባባንም እኔ አወራሀለሁ አንተ የተደፈርክ መስሎህ ወደ ዘለፋ ትንደረደራለህ: የኔ አላማ ገጣሚ እንድትሆን ና ሰው የደረሰበት ደረጃ እንድትደርስ ነው:: :D በውነቱ እኔ ሌላ አላማ የለኝም:: እኔ ግጥም መግጠም ለጊዜው ፍላጎት የለኝም ብፈለግ ኖሮ ግን እንዲህ እያልኩ ነበር የምጽፈው ..
የምኞት ቁጣ ቃል እስትንፋስ ....
የባሩድ ጨሀት እሪታ መውደስ ..
የሳጥናኤል ለቅሶ ኤሎሄ ዳያቢሎስ
በሳምራዊ አካል ሲመተር ሲቀደስ.....( ቄስ)
ኦላላ..ላላላ..ላላላላ ..
ገኅነም ሲጠራ ገኅነም ሲበላ
የሳምራዊን አጽም የሳምራዊን ገላ!! !!
ኢሮዖዖዖዖ..አውውውው!! ዑዑዑዑ.. :D ( የሲቃ ጩሀት )
እያልኩ እጽፍ ነበረ::
በነገራችን ላይ አንተን መሰል ጽሀፊዎች እንዲህ አይነት ጝጥም አትገጥሙም አይገባቸውም:: ይሄ እኛ ሀይ ዳይሜኒሽን ግጥም እንለዋለን:: አንዳንዶች የጸጋዬ ቤት ይሉታል:: እዚህ አገጣጠም ላይ እንድትደርስ ነው የኔ ጥረት :: እና ዘለፋውን ካልሲህ ውስጥ አድርግና ለመማርና ለማደግ ጥረት አድርግ:: እኔ እስካሁን ያለገባኝ ነገር ክብርነታችን እንዴት አድርጎ ክምትጠበቅበት ራንች ሪሊዝ ሰጥቶ እኛ ( ሰዎች) ጋ እንድትቀላቀል ማድረጉ ብቻ ነው የገረመኝ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: መልካም

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 24, 2012 10:26 pm

ዋኖስ wrote:እንዴት ዋላችሁ ግራ ቀኝ ወዳጆቼ! እንዴት ሰነበታችሁ!

ምን መጣ? ለምን ዉይይታችሁን በእንዲሕ ቋጫችሁት? ይገርማል! በሉ ተስማሙ! እንዲሕ አይነቱን እሰጣ ገባ ከእናንተ ከታላላቅ ወንድሞቼ አልጠብቅምና ደግማችሁ እንደማትመላለሱ ተስፋ አደርጋለሁ::

ቤቷንም በአግባቡ ብንጠቀምባት መልካም ነው::

ከመልካም አክብሮት ጋር!

ዳሞት


ሰላም ወንድሜ ዳሞት እስከአሁን መጥፋትህ ገርሞኛል :: ለምን አንተ ፍርድ እንዳልሰጠህ ገርሞኛል እስቲ ስለ በቆልት አንድ በል :: ስለግጥሙ ምን ተረዳህ ? አክባሪህ
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 10:39 pm

ዝታታም ! የዲያቢሎስ ቁራጭ!! ምን አይነት አስተያየት ነው ወንድም ዳሞት እንዲሰጥህ የምትፈልገው..? :D እኔ እኮ ተናጌአለሁ:: ግጥምህ እንኴን ላንባቢው አንተ ለጻፍከውም አይገባም:: እንደ ዳሞት የመሰለ ጸሀፊ ይህን ግጥም የበሰለ ነው እንከን የለውም ካለ ችግር አለ :: ይሄን እንደማይልህ እርግጠኛ ነኝ:: ይልቁኑ ሙያዊ ምክሩን ስማ:: ምን አይነቱ ነው እባካቹ ጅግራ!! :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 24, 2012 11:02 pm

ክቡራን wrote:ዝታታም ! የዲያቢሎስ ቁራጭ!! ምን አይነት አስተያየት ነው ወንድም ዳሞት እንዲሰጥህ የምትፈልገው..? :D እኔ እኮ ተናጌአለሁ:: ግጥምህ እንኴን ላንባቢው አንተ ለጻፍከውም አይገባም:: እንደ ዳሞት የመሰለ ጸሀፊ ይህን ግጥም የበሰለ ነው እንከን የለውም ካለ ችግር አለ :: ይሄን እንደማይልህ እርግጠኛ ነኝ:: ይልቁኑ ሙያዊ ምክሩን ስማ:: ምን አይነቱ ነው እባካቹ ጅግራ!! :D


ለምን ቀድመህ ትቀዝናለህ ከሱ እንስማው በጣም እርግጠኛ ነኝ አልገባህም ምክንያቱም መልስህ ይናገራል::
ግጥምህ ደግሞ old style ነው ባንተ ትንሽ አስተሳሰብ ሳጥናኤል, ገሀነብ , እሪታ, መወደስ ,ኤሎሄ ወዘተ ወዘተ ቃላትን እልፍ አእላፋት ግዜ በየ ግጥሞች ላይ ተብለዋል እነሱን ለቀናት ስታገጣጥም ክርመህ ግጥም ጻፍኩ ትላለህ እስቲ ድገም እንይህ ? :lol: :lol: :lol: ይልቅስ ቤቱን በስነስራት እንጠቀም ብሏል ባለቤቱ ስለዚህ ግጥም ካለህ ጻፍ ያለዚያ ለሚጽፉት ልቀቅ አንተ አጋንንት :twisted: :twisted: :twisted:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 11:20 pm

እግዚአብሄር ምስክሬ ነው ይሄን ግጥም የጻፍኩት ላንተ መመለስ ስለነበረብኝ በ15 -20 ሚኒት ኢንተርቫል ነው የጻፍኩት!! እንዴት ሆኜ ነው ከቀናት በፊት ካንተ ጋር ጉዳይ አለኝ ብዬ ግጥም የማዘጋጀው?? ለካ አራት እግራ ብቻ አይደለህም...ለካ ሪታርድድም ነህ:: ጌኛ!! :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሳምራውው33 » Wed Oct 24, 2012 11:30 pm

ክቡራን wrote:እግዚአብሄር ምስክሬ ነው ይሄን ግጥም የጻፍኩት ላንተ መመለስ ስለነበረብኝ በ15 -20 ሚኒት ኢንተርቫል ነው የጻፍኩት!! እንዴት ሆኜ ነው ከቀናት በፊት ካንተ ጋር ጉዳይ አለኝ ብዬ ግጥም የማዘጋጀው?? ለካ አራት እግራ ብቻ አይደለህም...ለካ ሪታርድድም ነህ:: ጌኛ!! :D


ወሬ ትተህ ድገም በአራት ነጥብ ያለቀ :: የጻፍከው አላለቀም ደግሞ full of old vocabulary.
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ክቡራን » Wed Oct 24, 2012 11:55 pm

መጨረስ የለብኝም እኮ! እኔ ለምሳሌ ያህል እንዲህ አይነት አጻጻፍም አለ ብዬ እኮ ላመላክትህ ነው.. ምን ይመስላል እባካቹ.. ሰንበቴ ፊት!!
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8261
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሳምራውው33 » Thu Oct 25, 2012 12:24 pm

ብርቅርቅ

ምን ጥቅም ይሰጣል ወርቅ ቢያብረቀርቅ
ምን ጥቅም ይሰጣል አልማዝ ቢያንጸባርቅ ?
አእምሮ ውስጥ ገብቶ ህሊናን አያድስ
እረፍትን ሰላምን ከቶ አያላብስ
ማስተዋል ጥበብን ፈጣሪ ላደለው
የሚያብረቀርቀው ለሱ ትርጉም የለው ::
ደክመውበት ይሁን እንዲሁም በእጣ
ከምረው ቆልለው ገንዘቡን ከጓዳ
ባላቸው ገንዘብ ያለምንም እዳ
እነሱ ያጥልቁት አልማዙን በተርታ
ይግባ በጣታቸው ባስሩም ለይታ
ይሄ ሁሉ ነገር ለነሱ ቋንቋ ነው
ደረጃን ማሳያ እኔ የበላይ ነኝ መባባያቸው ነው
ላዛ ላስተዋይ ፈጣሪ ላደለው
ከሚገባ በላይ ገንዘብ ላልቆለለው
አልማዝ ቢያንጸባርቅ ወርቅ ቢያብረቀርቅ
......................ለሱ ትርጉም የለው ::
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ሳምራውው33 » Fri Oct 26, 2012 2:29 pm

የአርባ አመቱ ድንግል


የሴት ዳሌና ባት ቀልቡን ቢነሳውም
ተክለ ሰውነቷ እረፍት ቢያስጣውም
ቀርቦ አነጋግሮ አንሶላ መጋፈፍ ለሱ አላለውም
በወሲብ ረመጥ ፍም ውስጡ እየጋየ
አፍሮ ተሽኮርምሞ ስቃይ ፍዳ እያየ
መፈጠሯን ረስቶ ሄዋን ለቅድመ አያቱ
ዘሯም ተበራክቶ ሞልቶ በየቤቱ
ሳይቀምሳት አለፈ ተለየ በሞት::
የህይወት ታሪኩ ሲነበብ ቀብሩ ላይ
በድንገት ቢጠቀስ ድንግል ሰው መሆኑ
ለቀስተኛው ማዘን መቆዘሙን ትቶ
አፉን በነጠላ እፍን አድርጎ ይዞ
ይሳሳቅ ጀመረ እርስ በርስ ተያይቶ
አርባ አመት ሆኖታል ሲሞት ይሄ ሰው
ከህይወት ታሪኩ እንደተሰማው
መነኩሴ አይደለም ገዳም አያውቀው
መናኝም አይደለም ሰው እስከሚያውቀው
እንደው አስገረመኝ የዚ ሰው እጣው ::
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

ጤናን ማስከበሩ

Postby ዋኖስ » Sat Oct 27, 2012 1:44 pm

ከላይ ለቀረበዉ ግጥም የግል አስተያየት መሆኑ ነው::
ረዥም ዘመንን በማስቆጠር እድሜ፣

ቀዳሚ ሰዉ የለም በሰዉ ልጆች ታሪክ ልንገርሕ ወንድሜ።

ግና፣

በአጭር አስቀረኸው ምነው በአርባ ዓመቱ፣

የዚያን ሟች ዘመናት ምድር በመግባቱ።

ንጹሕ ሆኖ ኖሮ ንጽሕ ሆኖ ቢሞት፣

አልቃሽ ተሰብስቦ፤ ደረት እንደመድቃት፣

ጉንጭን እንደመንጨት፣

አፈር ሳይመለስ እንዲያ የሳቁበት፣

ከቶ ለምን ይሆን የተሳለቁበት።

እርግጥ ነው፣

ቋሚ ሰው ክፉ ነው።

ዳግም ላይመለስ፣

በሕይወት እንዳለው ድንበር ላይጋፋ፣ የሰው ቤት ላያፈርስ፣

ከነአካቴው ሄዶ፣ንብረቱን ትቶልን ባዶ ሆኖ ቤቱ፣

መቃብር አፋፍ ላይ ከዘለዓለም ቤቱ፣

ተሰባስበን ቆመን፤መገልፈጥ፣ መሳቁ፣

አስገራሚ ነዉር፤ወገን የማይረሳዉ፣ የማይሽረዉ እርቁ።

አንተ እንዳነሳኸው ተክለ ቁመናዋ፣

ያነጋገር ለዛ፣ የድምጽ ቃናዋ፣

መስጦት ይሆናል ሽንጥና ዳሌዋ።

ግን ዳሩ፣

ቁልፉ፣ ቁምነገሩ፣

ያላሰመርሕበት የቀረዉ ምስጢሩ፣

ከዘመኑ ደዌ፣ ራስን መጠበቅ፣ ጤናን ማስከበሩ።

ከመልካም አክብሮት ጋ!

ዳሞት

በዘመናችን እንደነማቱሳላ ያለ ፍጡር አይልተገኘምና!!!

ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ሳምራውው33 » Sat Oct 27, 2012 6:56 pm

ኧረ እንዴት ሆኖ ነው ንጹ የሆነው
ድንግል ሆኖ መሞት ላያስቀድሰው
ፈጣሪን አያውቅም ስሙን አይጠራውም
ለነብሱም አይደለም ድንግል የሆነው
አይኑን ባይኑ ማየት በሚገባው እድሜ
ድንግል ሆኖ መሞት አያስቅም እንዴ ?
ቀባሪው መሳቁ ከፍቶ አይደል ጨክኖ
እንደው ቢገርማቸው የሰውየው ኑሮ
አንድ ምክንያት አለ ለድንግልናው
በአርባ አመት እድሜው በጉልምስናው
ልቡ የሚርድ የሄዋን ዘር እንስትን በጣም ፈሪ ነው ::

አክባሪ ወንድምህ :!: :!:

ስለበቆልት ደግሞ ከዚ በላይ መጥለቅ አልቻልኩም ብጠልቅ ዘንቢሉ ውስጥ ስላሉት ጣባዎች : ማንኪያዎች ማውራት ሊሆንብኝ ነው :lol: :lol: በቆልት የሚሽጥ ሰው ደግሞ ከዚ በላይ እንዴት በአማርኛ ይራቀቃል :lol: :lol: :lol:
መልካም ጊዜ :!:
Last edited by ሳምራውው33 on Sat Oct 27, 2012 11:04 pm, edited 1 time in total.
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ዋኖስ » Sat Oct 27, 2012 7:32 pm

አንዳንዴ ጊዜ ሲበረክት! ጥሩ ነው::

አሄሄ ይበሉ ይተዉት ስለንጽሕና፣

አንከራከርም፤ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያዉቀዉ በጠና።

እርስዎም አላዩ፤ እኔም የለኝ ሥልጣን፣

ስለድንግልናዉ፣ በአራት ነጥብ ልዝጋዉ፤አያስሄድም ይብቃን።

ዳሩ ግን፤ እንዲያዉ ለጨዋታ ነገሩ እንዲሰፋ፣

ስለ ባሕላችን፤ ስለሃገር ጉዳይ፤ ይጻፉ በይፋ።

መቃብር አፋፋ ላይ ተሰልፈን እንዲያ፣

አንዷ ጉንጯን ስትነጭ፣ ሌላዋ ስትነርት የደረት "ፓፓያ"፣

አንዱ ጥርሱን ሲፍቅ፤ ሌላው ፖለቲካ፣

በምናብ ዓለሙ ሲዳሥስ ሲዘግብ፤ ሲመጥን፣ ሲለካ፣

የሟች አሟሟቱ ደንታ የሌላቸው፣

የዓዞ እንባ ተካፋይ፤ሺሕ ሕዝቦች ናቸው።


ዳሞት

መልካም ቀዳሚት ሰንበት!


ሳምራውው33 wrote:ኧረ እንዴት ሆኖ ነው ንጹ የሆነው
ድንግል ሆኖ መሞት ላያስቀድሰው
ፈጣሪን አያውቅም ስሙን አይጠራውም
ለነብሱም አይደለም ድንግል የሆነው
አይኑን ባይኑ ማየት በሚገባው እድሜ
ድንግል ሆኖ መሞት አያስቅም እንዴ ?
ቀባሪው መሳቁ ከፍቶ አይደል ጨክኖ
እንደው ቢገርማቸው የሰውየው ኑሮ
አንድ ምክንያት አለ ለድንግልናው
በአርባ አመት እድሜው በጉልምስናው
ልቡ የሚረዳ የሄዋን ዘር እንስትን በጣም ፈሪ ነው ::

አክባሪ ወንድምህ :!: :!:

ስለበቆልት ደግሞ ከዚ በላይ መጥለቅ አልቻልኩም ብጠልቅ ዘንቢሉ ውስጥ ስላሉት ጣባዎች : ማንኪያዎች ማውራት ሊሆንብኝ ነው :lol: :lol: በቆልት የሚሽጥ ሰው ደግሞ ከዚ በላይ እንዴት በአማርኛ ይራቀቃል :lol: :lol: :lol:
መልካም ጊዜ :!:
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ሳምራውው33 » Sat Oct 27, 2012 8:18 pm

The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests