የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሳምራውው33 » Sun Oct 28, 2012 3:12 pm

ጀንበሬ

ግልብ እራስ መላጣ
የስላሴ ጦጣ
አሽሟጠጡኝ ሰዎች እኔው ጸጉር ባጣ
ተገልቦ የጠፋው ጸጉር ከአናቴ
በኔ ምርጫ አይደለም ከዘር ነው ካባቴ::
ተውኝ አትነካኩኝ መከራ አታብዙብኝ
ጸጉሬ ከኔ ቢርቅ መሳላቂያ አታርጉኝ
ድሮ ወጣት ሳለሁ እድሜ እንዲህ ሳልጠግብ
የጸጉሬ ብዛቱ መች ነበረውስ ልክ
የአንበሳ ጎፈሬ የሚመስለው ጸጉሬ
በዘመናት ብዛት ከኔ ቢርቅ ዛሬ
ትላንትና ዛሬም እኔው ነኝ ጀንበሬ :!: :!:

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
:!: :!:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ኦኑፈያሮ » Tue Oct 30, 2012 9:22 am

እንኖራለን ገና !


የትላንቱ ስህተት ይወገድ ተፍቆ

ዛሬ ሌላ ቀን ነው እንዳይመጣ ዘልቆ

የህመምዎን አይነት በሽታወን ሳያውቁ

መኖር እየቻሉ ስንቶቹ አለቁ

ስንቶቹ ረገፉ እንደ አደይ አበባ

ማነው ያላዘነ ማነው ያላነባ

እስቲ እጆቹን ያውጣ ካለ ያልቀበረ

ወንድም እህት ወዳጅ ዘመድ ያልገበረ

ስኳር የደም ግፊት ኤች አይ ቪ ጨጓራ

በመሳሪያ ታይቶ ሽንት ደም ምርመራ

የበሽታው አይነት ሲታወቅ ውጤቱ

ይዘየዳል መላ ይገኛል ብልሃቱ

እድሉን ተጠቅሞ ማራዘም ነው እድሜ

አያሻም መሼበር እንዳለም ፍጻሜ

ቆሽታችን ስራውን ቢያቆምም በይፋ

ከሰውነታችን ውስጥ ኢንሱሊን ቢጠፋ

አለ መድሃኒቱ እኛ አንቆርጥም ተስፋ

እርግጥ ነው ህመሙ ባይጠፋም ከሥሩ

መድሃኒት እያለ ምንድነው ችግሩ

እግዚያብሄር ይመስገን እንኖራለን ገና

ዘዴው በጃችን ነው አይነሳንም ጤና

ስኳሩ ቢበዛ ቢያንስም ለነገሩ

ያመጋገብ ስራት ከተቆጣጠሩ

ያኪምዎን ምክር ሰምተው በጥሞና

መኖር ይችላሉ ነገንም በጤና

አለቅጥ አጋንኖ ብዙም ማካበድ


ከንፈር መምጠጥ ብቻ ብዙም አይፈይድ

ስኳር በባህሪው አይወድም ስንፍና

ጠንክረን እንስራ እንድናገኝ ጤና

ሥራውን ቢያዛባም ቢለግምም ቆሽት

መናደድ አያሻም ይኑረን ትግስት

ስኳር በውስጣችን አይኖርም ሼምቆ

በኛ ተከልሎ በኛ ተደብቆ

እድሉን ተጠቅሞ ማራዘም ነው እድሜ

አያሻም መሼበር እንዳለም ፍጻሜ

ፈጣሪ ይመስገን እንኖራለን ገና

መፍትሄው በጃችን ነው አይነሳንም ጤና
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

ሰላምታ

Postby ዋኖስ » Tue Oct 30, 2012 11:14 pm

አጀብ!

ጥበብን ከሳይንስ አዋህዶ አቅርቦ

እያዋዙ መምከር ማስተማር ተጠቦ

ድንቅ ችሎታ ነው ጥልቅ አመለካከት

ሥራሕን አይቼ እጅግ በመደሰት

አጀብ! ስል ላክሁልሕ ትንሽዬ መልዕክት

በርታ! ቀጥልበት::


ዳሞት


ከመልካም አክብሮት ጋ!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Nov 25, 2012 2:17 pm

ኧረ ምነው ሼዋ !


ከጥንት ጀምሮ ሲታመስ ሲቦካ

እንግሊዝ አቅራሪ አጥላይ አሜሪካ

ጀርመን አሳላፊ ቻይና አቀባይ ሹካ

እስራኤል ቀጥቅጣ በሰራችው ቢላ

ታረደ ወገኔ በህወሀት ተበላ

እንቅልፍ አያስተኛ አያስበላ እንጀራ

ጉድ ተሰማ ሼዋ ጉድ ተሰማ ደራ

እኒህ የሠው ጉዶች ወጉ ቢጠፋቸው

የጠጡት ደም ስካር እያስቀረሻቸው

ከጭን ሥጋ ቁራጭ ብልት አማራቸው

ከመካከላቸው ተቆጭ የመጥፋቱ

የጥላቸው መጠን ጥልቀቱ ስፋቱ

ለደዌው መመርቀዝ ይህ ነው ምልክቱ

ኧረ ጎበዝ ሰፋ..ሰፋ ይኼ ጉድጓድ የቆፈራችሁት

ታዘቧት ምላሴን ካልደፈናችሁት

እኒህ አራዊቶች እግዜር የከዳቸው

ከዋልድባ ወዲያ ምን ማተብ አላቸው

ጠላት ከሆኑብን ወዳጅ ስንላቸው

ከባዕድ ይልቅስ ዘመድ አርገናቸው

ከሠው ይልቅ ድንጋይ መሆን ካማራቸው

ጩቤ ከሰኩብን እኛ ስናቅፋቸው

እንፈልግ መድሀኒት ነቀርሳዎች ናቸው

ክህደት ዘረኝነት ዘልቆ በደማቸው

መለያው ዘር አጥፊ መለሳዊያን ናቸው

ትእግስት ፍርሃት መስሎ እንዲህ ከታያቸው

ወንድነት ክዷቸው ብልት ካማራቸው

ጭራሽ ሳያጠፉን ፈር እናስይዛቸው

ይግቡ ትምህርትቤት እርሳስ እንስጣቸው

ተመክሮ ላልሰማ ትምህርት ይኸ ነዋ

እስከመቸ ድረስ ምነው ኧረ ሼዋ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Dec 02, 2012 7:38 am

በሰማዕታት ሠፈር ሄጄ ስነጋገር

የሰማሁት ታሪክ ቃሉ ብዙ ነበር

በሰማዕታት መንደር የሚገኙ ሁሉ

እነ ራስ ገበየሁ ጄግኖቹ በሙሉ

አሉላ አባ ነጋ እነ ራስ ጎበና

አባ ነፍሶ ባልቻ ሃብቴ አባ መላ

አዝነው ተክዘዋል ባገራቸው ዜና

አዳና አባ ደፋር ጅማ ሰንበቴና

ተመልሰው መጥተው ቢኖሩ በሃገር

አድነው ለመሞት በተዋጉ ነበር

አገር ላገር ዞርኩኝ ወንድ ልጅ ፍለጋ

ዳግም ቢወለዱ እነ አብዲሳ አጋ

ያ በላይ ዘለቀ ያ ትልቅ አርበኛ

ይህን ጉድ ሳይሰማ በገመድ ላይ ተኛ

አበበ አባ ገስጥ አበበ አረጋይ

አያትህ ጎበና አልነበረም ዎይ

ኢትዮጵያ ተጨንቃ ስታይ ተቸግራ

መች ትተኛ ነበር ታሪክ ሳትሰራ

እናንተ ሰማዕታት በሠማይ ያላችሁ

እርይ ኡኡ ብለን የምጠይቃችሁ

መንፈሳችሁ ወርዶ ያድነን ባካችሁ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Tue Jan 15, 2013 3:26 pm

ለቅሷችሁ ለምኔ !

በጭንቅ በመከራ ሳትቆሙ ከጎኔ

በሞት ስለያችሁ ለቅሷችሁ ለምኔ

ታምሜ ስማቅቅ ተኝቼ ባልጋ ላይ

ወገን ሳይደርስልኝ በከንቱ ስሰቃይ

ምሕረት ያውርድልህ ሳትሉኝ ጨክናችሁ

ሞቴን ስትሰሙ ተሰባሰባችሁ

እርሱኝ አትምጡብኝ እኔም አላያችሁ

ተስካሬን አታውጡ ጥቁርም አትልበሱ

ንፍሮም አይቀቀል ድግስ አትደግሱ

ለናንተ ካልሆነ ለኔ ምን ሊጠቅመኝ

መቃብር የገባሁ የማላይ በድን ነኝ

በሕይዎት እያለሁ ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ

ሲርበኝ ሲጠማኝ በሽታ ሲያጠቃኝ

ወገንን ፍለጋ አይኔ ሲንከራተት

ያላገኘሁትን እያለሁ በሕይዎት

እርሱኝ አታስታውሱኝ አትተራመሱ

በድኔ ሰላም ያግኝ አጉል አታልቅሱ

በቁሜ ሳትረዱኝ በሕይዎት እያለሁ

ያንገት በላይ ለቅሶን እኔ መች ተመኘሁ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

ሕምምም

Postby ዋኖስ » Wed Jan 16, 2013 12:18 am

ሕምምምም....እንኳን በድን ሆነሕ እስትንፋስሕ ቆማ፣

መሞትሕን አዉቀዉት አስነግረዉ ስማ፣
(ስማ፡በለው)

ከሌለሕ የለሕም በዚሕ ዘመንማ።

እንደ ንፁህ ሠማይ ኪስሕ ሲጠራ አይተዉ፣

ቅድሚያ አንተ ይሉኃል ፦ ቀድሞ ስምህን ትተው።

ከሌለህ…፤

በዕለት ተዕለት ኑሮህ ስትገባ፣ ስትወጣ፣

ድንገት ከአየኃቸው በሾዴ ቆረጣ፣

ዓይናቸዉ እሳት ነዉ ከእቶን ፡ፍም የነጣ፣

ጭራሽ ማያስጠጋ ሁለት አፎት ያለዉ የጩቤ ጋሬጣ።

ከሌለህ… ።፤

ገደ ፡ቢስ ለእነሱ መልከ ጥፉ አንተ ነህ፣

በዚች ሰፊ ምድር በከንቱ የምትኖር መድረሻ የሌለህ።

ከሌለህ…፤

ንግግርህ ጭቃ፣ እሳቦትህ ከንቱ፣ ሚዛን የማይደፋ፣

አንተ ነህ ለእነሱ ምግባረ ፡ብልሹ፣አመዳም ከርፋፋ።

ከሌለህ…፤

በጨዋታ መኃል ምሳሌዉ አንተ ነህ፣

ጥርስን ለማስገለጥ በልብስ በቁመናህ።

ሲፈልጉ ክርፍፍ፣ ሲያሻቸው መናጢ፣

አልያም ዝጋታም፣ ጋግርታም ነዉ ሙጢ፣

እያሉ እያወጉ ስም እያወጡለህ፣

አንተ ነህ ለእነሱ አምላክ ያላደለህ፣

በእነሱ ቤት አንተ የለህም ከሌለህ።

ስለዚሕ፤

አታብዛ ትካዜ፣አትከፋ ብዙ፤

ቀባሪዉ ቀን እንጅ አይደለም ሰፊው ሕዝብ ያገርሕ የወንዙ።ዳሞት ከዳሞት

[/i]
ኦኑፈያሮ wrote:ለቅሷችሁ ለምኔ !

በጭንቅ በመከራ ሳትቆሙ ከጎኔ

በሞት ስለያችሁ ለቅሷችሁ ለምኔ

ታምሜ ስማቅቅ ተኝቼ ባልጋ ላይ

ወገን ሳይደርስልኝ በከንቱ ስሰቃይ

ምሕረት ያውርድልህ ሳትሉኝ ጨክናችሁ

ሞቴን ስትሰሙ ተሰባሰባችሁ

እርሱኝ አትምጡብኝ እኔም አላያችሁ

ተስካሬን አታውጡ ጥቁርም አትልበሱ

ንፍሮም አይቀቀል ድግስ አትደግሱ

ለናንተ ካልሆነ ለኔ ምን ሊጠቅመኝ

መቃብር የገባሁ የማላይ በድን ነኝ

በሕይዎት እያለሁ ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ

ሲርበኝ ሲጠማኝ በሽታ ሲያጠቃኝ

ወገንን ፍለጋ አይኔ ሲንከራተት

ያላገኘሁትን እያለሁ በሕይዎት

እርሱኝ አታስታውሱኝ አትተራመሱ

በድኔ ሰላም ያግኝ አጉል አታልቅሱ

በቁሜ ሳትረዱኝ በሕይዎት እያለሁ

ያንገት በላይ ለቅሶን እኔ መች ተመኘሁ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ኦኑፈያሮ » Wed Mar 13, 2013 7:20 am

ተጠየቅ ልጠየቅ !


ባገር በሃይማኖት በሚስት የለም ዋዛ

ባሞሌ አይለወጥ ባራጣ አይገዛ

ብሎ የዘመተው ባድዋ በማይጨው

ላገር ለነጻነት ሕይዎቱን የሰዋው

ለኛ ሲል የሞተው

ድንበር ያስከበረ ባጥንቱ ቸንክሮ

ባንድነት ያሰረ በጅማቱ አክርሮ

ቆዳው ተፈቅፍቆ ብራና ተሌጦ

ታሪኩ የተጣፈ በደም ተበጥብጦ

ሠንደቅ የሰቀለው ባጥንቱ ሰክቶ

በሥጋው በደሙ በቃል ኪዳን ጸንቶ

ለሠጠን አደራ ለቃል ኪዳናችን

ዛሬ ቢጠይቀን ምንድነው መልሳችን ?

ባሞሌ ለሸጥነው ለነጻነታችን

ለተቸበቸበው ለባድ መሬታችን

ለተሸራረፈው ያገር ድንበራችን

ለተሸረሼረው ጽኑው ዕምነታችን

ለኛ ሲል የሞተው ባድዋ በማይጨው

ዛሬ ቢጠይቀን ምን ይሆን መልሳችን

ለቃል ኪዳናችን መፍረስ ወይ መጠበቅ

መልሳችን ምንድን ነው ተጠየቅ ልጠየቅ

ሲጠየቅ ታሪኩን ቢያንስ አደራውን

በደም የተጣፈ ያባት ኑዛዜውን

ምንድነው መልሳችን ለሰጡን አደራ ማረጋገጫችን

ለኛነት መግለጫ የኛነት ቃላችን

ለቃልኪዳናችን መፍረስ ወይ መጠበቅ

መልሳችን ምንድን ነው ተጠየቅ ልጠየቅ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun May 19, 2013 7:25 am

አዶላ ተናገር !


ተናገር መጋዶ ተናገር ሻኪሶ

ወርቅ ወዴት ተጓዘ ላንተ አፈሩ ደርሶ

ተናገር ሃዲማ ደግሞም ኡላ ኡሎ

እነማን ዘረፉት የወርቁን አለሎ

የወርቁን ቡችላ የለገዳንቢውን

ደብዛውን ንገሩን የደረሰበትን

መሬቱ ተምሶ ወርቁ እየታፈሰ

አዶላ ተናገር ወርቁ የት ደረሰ

እነማን ዘረፉት ማንስ ከበረበት

እነማን ተዝናኑ ማንስ ጨፈረበት

ደሃው በደከመ ደኃ በሞተበት

ጦሙን እንደዋለ አፈር ተንዶበት

አካፋን ዶማ ይዘው ሳይቆፍሩ

ጨለማ መግፈፊያ ሻማ ሳያበሩ

ጠብ ሳይል ላባቸው ባቋራጭ ከበሩ

ያገር አንጡራ ሃብት እየመዘበሩ

በገዛ መሬቱ በተወለደበት

እትብቱ ተቆርጦ በተቀበረበት

ለወርቁ ባለቤት ምንም ሳይሰሩለት

ጉሮሮውን ኣንቀው ካፉ በመቀማት

ኀብታም መዘበረ ሌላው ከበረበት

ተናገር መጋዶ ተናገር ሻኪሶ

ወርቅ ወዴት ተጓዘ ላንተ አፈሩ ደርሶ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby የጃማ ጦስኝ » Tue May 21, 2013 1:47 pm

http://youtu.be/WTMZyphw4YM
ሰላም ለዚህ ቤት እስኪ እኔም አንድ ልበል
በትንሳኤው ሰሞን ከምስጋና የበለጠ ምን አለ !
ሊንኳን ተትጭናችሁ ስሙልኝ ይቺን ምስጋና
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

አመሰግናለሁ

Postby ዋኖስ » Tue May 21, 2013 10:54 pm

እናመሰግናለን! ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው:: ስራዎቻችሁ ቆንጆዎች ናቸው::

አክባሪያችሁ ዳሞት ከዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ዋኖስ » Sat May 25, 2013 1:25 pm

እንቁላልና ቃልእንቁላልና ቃል አንድ ነዉ እጣቸዉ፣

ለትጉሕ ጥንቁቅ ሰዉ፣

እንቁላልም ዶሮ፣

ቃልም መታመኛ፤ መሠረት፤ ጽናት ነዉ፤ ግምብ ነዉ ለኑሮ።

ከጣት ያመለጠ የእንቁላል ሕይወቱ፣

የተሸረፈ ቃል የሳተ አንደበቱ፣

ሁለቱም ያዉ ናቸዉ፤

የዶሮዋም ሕይወት አከተመ በቃ፤ ከጣት እንደወጣ፣

ቃሉም ቃል አይሆንም፤ ሳንካ ነዉ ለትዳር፤ ሽንቁር ነዉ ጋሬጣ።


ዳሞት ከዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

አቤት

Postby ዋኖስ » Sat Feb 22, 2014 2:54 am

እናመሰግናለን! ዋርካን ስላጸዳችሁት::

ዳሞት ከዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Re: የዳሞት ግጥሞች

Postby tutu » Mon Aug 13, 2018 12:20 am

ዳሞት እነዚሕን የመሰሉ ግጥሞች ጥለሕ ወዴት ጠፋሕ
tutu
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Tue Jun 08, 2004 5:54 pm
Location: ethiopia

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests