የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች:- ሙላቱ አስታጥቄ እና ....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች:- ሙላቱ አስታጥቄ እና ....

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Nov 20, 2009 9:23 am

ሰላም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን :-

የ"BBC" ሰዎች በአብዛኛው ጥሩውን በጥቂቱም መጥፎውን ቀላቅለው በዶክሜንታሪ ፊልም መልክ አቅርበውልናል :: ሙላቱ አስታጥቄ : ቴዎድሮስ ታደሰ : ዳዊት ይፍሩ (ኦርጋን) : ጆቫኒ ሪኮ (ሮሃ ባንድ) : ጌታቸው ካሣ : አለማየሁ እሸቴ : ንዋይ ደበበ : በዛውርቅ አስፋው : ባህሩ ቀኜ : አበበች ደራራ : ነጻነት መለሰ : አስቴር አወቀ .... የሃምሣ አለቃ ውቤሻው ስለሺ : የአብዮት : የፉከራ የቀረ ዘፈን ያለ አይመስልም :: በሰባት ክፍሎች የተከፋፈለውን ዶኩሜንታሪ በ"YouTube" ታገኙታላችሁ ::

ተድላ

ምንጮች :-

ክፍል 1

ክፍል 2

ክፍል 3

ክፍል 4

ክፍል 5

ክፍል 6

ክፍል 7
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Sat Nov 17, 2012 2:03 am, edited 6 times in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

አዝማሪ ...

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Nov 21, 2009 3:18 am

ሰላም ለሁሉም :-

የአዝማሪ ሥር እንዴት እያደገ መጣ ?

ምንጭ:- አዝማሪና ይርጋ ዱባለ - ክፍል 1

አዝማሪና ይርጋ ዱባለ - ክፍል 2


ይርጋ ዱባለ ዘመን የማይሽረው አዝማሪ ነው :: አሁን የትርፍ ጊዜ ጋዜጠኛ የሆነው አበበ በለውም በተለያዩ ጊዜዎች በመድረክ ተወዛዋዥ ሆኖ ይታያል ::

ይርጋ ዱባለ "በአዝማሪነቴ እኮራበታለሁ ::" ይላል :: እንዲህ ነው በሙያ መኩራት ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ትርንጎ* » Sat Nov 21, 2009 7:05 am

ተድላዬ ለዶክመንተሪው እጅ ነስቻለሁ...ሁህ በትዝታ ያነጉዳል:: ልመለስና ልጨርሰው እስቲ...ላነጋው ነው: :D
በነገራችን ላይ "አዝማሪ" የሚለው ቃል ከስድብነት ወጥቶ እንዲህ በመልካም ሲጠቀሙበት ማየቱ ትልቅ ለውጥ ነው::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Nov 21, 2009 7:17 am

---
Last edited by ተድላ ሀይሉ on Sat Nov 21, 2009 7:23 am, edited 1 time in total.
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Nov 21, 2009 7:21 am

ትርንጎ* wrote:ተድላዬ ለዶክመንተሪው እጅ ነስቻለሁ...ሁህ በትዝታ ያነጉዳል:: ልመለስና ልጨርሰው እስቲ...ላነጋው ነው: :D

ትርንጎ ያላቸውን ያቃመሱንን እናመስግን እንጂ እኔማ ምን አደረግሁ ብለሽ ነው :: የ'BBC' ሰዎች ከቀበሩበት አውጥተው አቀረቡት : "Baye Speedy - filfilu" ለ'YouTube' አበቁት :: በቃ ታሪኩ ይህ ነው :: ከ"ሕዝብ ለሕዝብ የኪነት ቡድን" ዝግጅት ወዲህ እንዲህ ብዙ የኪነ-ጥበብ ሰዎች በአንድ ዝግጅት ቀርበው ሣይ የመጀመሪያዬ ሥለሆነ ነው እዚህ መድረክ ላይ የለጠፍኩት ::

በነገራችን ላይ "አዝማሪ" የሚለው ቃል ከስድብነት ወጥቶ እንዲህ በመልካም ሲጠቀሙበት ማየቱ ትልቅ ለውጥ ነው::

አዋቂ ምንጊዜም በራሱ ይተማመናል :: ይርጋ ዱባለ በራሱ የሚተማመን ሰው ስለሆነ በሙያው መጠሪያ አያፍርበትም ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ትርንጎ* » Sat Nov 21, 2009 7:23 am

ታዲያ አንተ ባታመጣው ከየት እናገኘው ነበር...እሺ ለነሱም ካንተ ቀጥሎ እጅ ነስቻለሁ :D

ትክክል...በያዙት መርካትና መኩራት ትልቅ ስጦታ ነው:: እንደው ዘፈናቸውን በደስታ እየኮመኮምን ዞረን እጃቸውን የምንነክሰው እኛ ነን መሰል..."አዎን አዝማሪ ነኝ" ሲሉ ደረታቸውን ነፍተው መስማቱ ትልቅ ለውጥ ነው...ደስ ይላል::
ትርንጎ*
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 716
Joined: Mon Oct 06, 2008 7:43 am

Postby እዮባ » Sun Nov 22, 2009 2:08 am

የድሮ ሙዚቃ ለምትወዱ እስኪ ስንቶቻቹ ይሄንን ዘፈን ታስታውሱታላቹ? ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ይታወቅ ነበር
"" ቦና ሴራ........... ቦና ሴራ ሲኞሪና........ ሲኞሪና ቻው ቻው""
http://www.youtube.com/watch?v=JazOa2c6XrE
A+T ርኛ

MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC.
እዮባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 906
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:30 am
Location: In the state of peace

Postby ከስደተኛው » Sun Nov 22, 2009 2:08 pm

ሰላም እዩባ
ስለሙዚቃህ ግብዣ አመሰግናለሁ!... ብዙ ጊዜ ዋርካ ላይ የምትለቀልቃቸውን ጽሁፎች ስመለከት ""ይሄ ሰውዬ ከጫካ የመጣ ወያኔ ይሆናል""ብዬ አስብ ነበር:: ከዚህ የሙዚቃ ግብዣህ በሗላ ግን ""ከቀንድ የሾለ የእግር ጥፍሩ ባደረገው ኮንጎ ጫማ ቀዳዳ እየሾለከ የሚያስቸግረው ጥፍራም; .... ይህንንም ያነገበው ክላሽ ላይ በተሰካው ሳንጃ በ1983 ሸገር ላይ ሲሞርድ ያየሁት የዘመኑ ሰው ይሆናል ብዬ ገመትኩ:: ምናልባት ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ!!
ከስደተኛው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 316
Joined: Mon Sep 25, 2006 11:12 pm
Location: zxcvb

Postby እዮባ » Sun Nov 22, 2009 8:25 pm

ከስደተኛው wrote:ሰላም እዩባ
ስለሙዚቃህ ግብዣ አመሰግናለሁ!... ብዙ ጊዜ ዋርካ ላይ የምትለቀልቃቸውን ጽሁፎች ስመለከት ""ይሄ ሰውዬ ከጫካ የመጣ ወያኔ ይሆናል""ብዬ አስብ ነበር:: ከዚህ የሙዚቃ ግብዣህ በሗላ ግን ""ከቀንድ የሾለ የእግር ጥፍሩ ባደረገው ኮንጎ ጫማ ቀዳዳ እየሾለከ የሚያስቸግረው ጥፍራም; .... ይህንንም ያነገበው ክላሽ ላይ በተሰካው ሳንጃ በ1983 ሸገር ላይ ሲሞርድ ያየሁት የዘመኑ ሰው ይሆናል ብዬ ገመትኩ:: ምናልባት ከተሳሳትኩ ለመታረም ዝግጁ ነኝ!!

ስደተኛው.....
የሙዚቃ ግብዣዬ ለመልካም ነበር::
ለማንኛውም እዚህ የሰው ርዕስ አላዛባም
ሌላ ቦታ እንገናኛለን::
A+T ርኛ

MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC.
እዮባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 906
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:30 am
Location: In the state of peace

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Nov 24, 2009 12:10 am

ሰላም ለሁሉም ኢትዮጵያውያን :-

ዛሬ ይዤ የቀረብኩላችሁ ሂሩት በቀለን ነው :: ሂሩት በቀለ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃ ጓድ ሥር የሙዚቃ ሥራዎቿን ለሕዝብ ስታቆይ የኖረች ማራኪ ድምጽ ያላት ድምጻዊት ናት :: ከ1983 ዓ.ም. በኋላ ከሙዚቃው ዓለም ርቃለች : ሥራዎቿ ለእኛ ለአድማጮቿ ማስታዎሻዎቿ ናቸው ::

እንደ ገበቴ ውሃ .... መኖሪያ ሣታጣ :- በ1976 ዓ.ም.

ሂሩት በቀለ እና መሥፍን ኃይሌ ... መጀመሪያ በ1955 ዓ.ም. ? የተዘፈነ በ1980 ዓ.ም. ለፖሊስ ሠራዊት የሙዚቃ ጓድ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዮ የቀረበ ::

ሕይወት እንደ ሸክላ 1973 ዓ.ም. ?


ከእነዚህ ሙዚቃዎቿ በጣም የምወድላት "ሕይወት እንደ ሸክላ" የሚለውን ነው ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ስጥ እንግዲህ » Tue Nov 24, 2009 5:02 am

እኔም ሂሩት በቀለ ከማደንቃቸው የቀድሞ ዘፋኞች አንድዋ ናት:: ጥሩ ለዛ ያላት ድምጻዊ ናት:: ታድያ ከብዙነሽ በቀለ አላስበልጣትም:: ሁለቱም በአንድ አካባቢ ነው ሙዚቃ የጀመሩት ከታሪካቸው እንደምረዳው:: ብዙነሽ ወደ 1952 አ.ም. አካባቢ በክቡር ዘበኛ ጀመረች እስከ እለተ ሞትዋ ድረስ ማለት 1982 አካባቢ እዚያው ክቡር ዘበኛ ከእነጥላሁን ጋር ነበርች:: ከጥላሁን ጋር አንድ ሁለት አብረው የተጫወቱዋቸው ዘፈኖች አሉ:: በተለይ በደርግ ዘመን "ነይ እንወረድ ሸገር" የሚለው ዘፈናቸው ግሩም ነው:: እንዳገኝሁት አመጣላችሁዋለሁ:: የሚቀድመኝም ካለ ጥሩ ነው:: ለአሁኑ ይቺን ድንቅዬ ጀባ ልበል:
http://www.youtube.com/watch?v=Ep9-R2hA ... re=related
ስጥ እንግዲህ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1002
Joined: Fri Sep 29, 2006 1:30 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Nov 24, 2009 6:57 am

ስጥ እንግዲህ :-

እናመሠግናለን :: ብዙዬማ እንዴት ትረሣለች :: እንዲያውም እንደ ሥሟ በዛ ያሉ ሙዚቃዎቿን መራርጬ ብቅ እላለሁ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: አዝማሪ ...

Postby ጌዴዎን » Tue Nov 24, 2009 5:25 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ለሁሉም :-

የአዝማሪ ሥር እንዴት እያደገ መጣ ?


ምንጭ:- አዝማሪና ይርጋ ዱባለ - ክፍል 1

አዝማሪና ይርጋ ዱባለ - ክፍል 2


ይርጋ ዱባለ ዘመን የማይሽረው አዝማሪ ነው :: አሁን የትርፍ ጊዜ ጋዜጠኛ የሆነው አበበ በለውም በተለያዩ ጊዜዎች በመድረክ ተወዛዋዥ ሆኖ ይታያል ::

ይርጋ ዱባለ "በአዝማሪነቴ እኮራበታለሁ ::" ይላል :: እንዲህ ነው በሙያ መኩራት ::

ተድላ

ጋዜጠኛው ግን ደከማ ቢጤ ነው :: ሰድቦ ለሰዳቢ የሚሰጥና ባህልን የሚያንቍሽሽ አይነት ሆኖ ነው የታየኝ :: ጎንደር ውስጥ የሚንጸባረቅ በጣም የቆየ.... ጎጅና ኋላቀር የሆነ ባህል አለና እሱን ነው የሚያንጸባርቀው :: በጎንደር ባህል የኪነት ሰዎችን አዝማሪ..... የእደ ጥበብና የእጅ ስራ ባለሙያዎችን ቀጥቃጭ ...ጠይብ እያሉ ማቃለልና ማግለል የተለመደ ባህል ነው :: ሰዎችን በገዛ አገራቸው ባይታወር ለማድረግ....... በራሳቸው እምነት አጥተውና ተሸማቀው እንዲኖሩ ለማድረግ ታስቦ የቀረበ ፕሮግራም እንጂ ሌላ አይደለም :: ታዋቂና ተወዳጅ የኪነት ሰዎችን አዝማሪ የሚል ስም መስጠት በእውነት አስቀያሚ ነገር ነው ::
ጌዴዎን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 134
Joined: Sun Sep 26, 2004 10:42 pm
Location: united states

Re: አዝማሪ ...

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Nov 24, 2009 9:16 pm

ጌዴዎን wrote: ... ጋዜጠኛው ግን ደከማ ቢጤ ነው :: ሰድቦ ለሰዳቢ የሚሰጥና ባህልን የሚያንቍሽሽ አይነት ሆኖ ነው የታየኝ :: ጎንደር ውስጥ የሚንጸባረቅ በጣም የቆየ.... ጎጅና ኋላቀር የሆነ ባህል አለና እሱን ነው የሚያንጸባርቀው :: በጎንደር ባህል የኪነት ሰዎችን አዝማሪ..... የእደ ጥበብና የእጅ ስራ ባለሙያዎችን ቀጥቃጭ ...ጠይብ እያሉ ማቃለልና ማግለል የተለመደ ባህል ነው :: ሰዎችን በገዛ አገራቸው ባይታወር ለማድረግ....... በራሳቸው እምነት አጥተውና ተሸማቀው እንዲኖሩ ለማድረግ ታስቦ የቀረበ ፕሮግራም እንጂ ሌላ አይደለም :: ታዋቂና ተወዳጅ የኪነት ሰዎችን አዝማሪ የሚል ስም መስጠት በእውነት አስቀያሚ ነገር ነው ::

እንግዲህ ሥያሜ ስድብ የሚሆነው ማኅበረሰቡ በወቅቱ ከሚሠጠው ትርጓሜ አንጻር እንጂ ያ መጠሪያ ሥም ሲፈጠር ጀምሮ ሥድብ ስለሆነ አይደለም :: አሁን አዝማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ አዝማሪ አንባልም "አርቲስት" በሚለው የእንግሊዘኛ ቃል (ምንጩ አርስ - "ars" ከሚለው የላቲን ቃል ትርጓሜውም ችሎታ : ውበት : የመጣ ነው :: ) ይቀየርልን ቢሉ ዞሮ ዞሮ ያም ቃል በማኅበረሰቡ አስተያዬት ከሥድብ ያልተለየ አገላለጽ ካለው መጠሪያ ሥምን መቀየር በራሱ ምንም ፋይዳ አይኖረውም :: ስለዚህ የሚሻለው መንገድ ሙያን በሙያነቱ አክብሮ መቀበል ነው ::

ሥያሜ ከሆነ እንግሊዞች እና ጀርመኖች በአብዛኛው ያላቸው የተፀውዖ (የግል መጠሪያ) ሥማቸው የሙያ ሥም ነው :: ለምሣሌ እንግሊዞች -ስሚዝ : ብላክ ስሚዝ : ኮብለር : ቡቸር : ወዘተርፈ የሚሉ መጠሪያ ሥሞች አሏቸው :: አንተ ባቀረብከው መንገድ ብቻ ከታየ እነዚህ ሰዎች መጠሪያ ሥሞቻቸው ሣይቀሩ ሥድቦች ይሆናሉ :: በዚህ ምክንያት ነው ይርጋ ዱባለ "አዝማሪ ነኝ::" ብሎ ራሱን ሲያስተዋውቅ በራስ መተማመኑ እና በሙያው መኩራቱ ያስደሰተኝ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: አዝማሪ ...

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Nov 24, 2009 9:26 pm

---
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests