የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች:- ሙላቱ አስታጥቄ እና ....

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ተድላ ሀይሉ » Fri Sep 16, 2011 3:30 am

ኡ ኡ ኡ ኡ አስናቀች ወርቁ አረፈች :: እኔን አፈር ይብላኝ የእንጉርጉሮዋ ንግሥት :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry:

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ጌታ » Fri Sep 16, 2011 1:12 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ኡ ኡ ኡ ኡ አስናቀች ወርቁ አረፈች :: እኔን አፈር ይብላኝ የእንጉርጉሮዋ ንግሥት :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry: :cry:

ተድላ

ኡ...በጣም አሳዛኝ ዜና! እግዜር ነብሷን በገነት ያኑር ለቤተሰቦቿም ሆነ ላፍቃሪዎቿ መጽናናትን ይስጥ:: :cry: :cry:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Sep 25, 2011 4:41 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ:-

በእኒህ የቆዬ ስለአገር ፍቅር በተዜሙ ዜማዎች ዘና በሉ ::

አለማየሁ ፋንታ :- ተው ተው

ይርጋ ዱባለ :- ጀግና በለው በለው

ሒሩት በቀለ :- ኢትዮጵያ ሀገሬ : መመኪያዬ ነሽ ክብሬ ::

ካሣ ተሠማ :- ፋኖ ፋኖ

እሣቱ ተሠማ :- ግሩም ናት ድንቅ ናት ለምለሟ ሀገሬ

???ለማ ገብረሕይወት ??? :- ኧረ ጎራው

መልካሙ ተበጀ :- በባህሌ እኮራለሁ በኢትዮጵያዊነቴ

ምንጮች:-

ክፍል 1:-Best Selection of Classic Ethiopian Oldies Songs - Part 1

ክፍል 2:- Best Selection of Classic Ethiopian Oldies Songs - Part 2

ክፍል 3:- Best Selection of Classic Ethiopian Oldies Songs - Part 3

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Sep 26, 2011 2:44 am

Monica**** wrote:ስላም ተድላ ሀይሉ
በጣም ቆንጆ ቆንጆ የጥንት ዘፋኞችን እየፈለግክ ያስማህን በጣም አመስግናለሁ!!!
ምነው ታዲያ የሙሉቀን እስካሁን አልቀረበም? :lol: :lol:
ሙሉቀንን ስለምወደው ነው እንደዛ ያልኩት!!
ቆንጂትዬ ሻሎም ብያለሁ መርአዊ ዩሀንስ እልም ያለ ቆንጆ አይደል እንዴ ከነዲምፕሉ?? :lol: ይሄኔ አርጅቶ ወዳድቆ ይሆናል....አይ ውበት ባያረጅ ጥሩ ነበር :lol: :lol:
ተድላ ሀይሉ በል ያገር ልጅ እንግዲህ የኮርት ኢንጃክሽን ኦርደርም ብታወጣ ከዚች ቤት አልቀራትም :lol: :lol:

ሰላም ሞኒክ:-

ባለሽበት አገር እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሠሽ :: እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገረሽ ::

በሙሉቀን የሚጨክን ልብ ካለሽ እንግዲህ ምን ይደረጋል :: እኒህን የሙሉቀን መለሰን ዜማዎች ዩ-ቲዩብ ላይ የለጠፉልንን ቸር ሰዎች እያመሠገንሁ ተጋበዢ ብያለሁ ::

ምንጭ:-
1 ..... ሙሉቀን መለሰ : ውቢት ::

2 ..... ሙሉቀን መለሰ : እንዴት ነው ገዳዎ ::

3 ..... ሙሉቀን መለሰ : ተነሽ ከልቤ ላይ ::

4 ..... ሙሉቀን መለሰ : ሄደች አሉ ::

5 ..... ሙሉቀን መለሰ : ውሃ ወላዋይ ::

6 ..... ሙሉቀን መለሰ : ሰውነቷ ::

7 ..... ሙሉቀን መለሰ : ወድጄሽ ነበረ ::

8 ..... ሙሉቀን መለሰ : አካል ገላ የእኛ ::

9 ..... ሙሉቀን መለሰ : ናኑ ናኑ ነይ ::

10 ..... ሙሉቀን መለሰ : ኧረ ወተቴ ማሬ ::

አክባሪሽ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Nov 23, 2011 6:16 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በክራር ግርፍ አጃቢነት በእንጉርጉሮ ዘዬ በተቃኙ ዜማዎቿ ነፍሣችንን ገዝታ የምትኖረው ሟቿ አስናቀች ወርቁ ካረፈች ሁለት ወራት አለፏት :: ለማስታወሻ ይሆን ዘንድ ስለሕይወት ጉዞዋ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘኋቸውን ዘገባዎች ለቃቅሜ አቅርቤያለሁ :: አሁንም የአስናቀችን ነፍስ እግዚአብሔር ይማራት ::

ምንጮች:-
1 ..... Artist Asnakech Worku interviews by Benjamin Watkins.

2 ..... Asnakech Worku her last days Ethiopian Amharic dvd Quality.

3 ..... Asnakech Worku (1926 - 2004 E.C): Queen of KIrar

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዳኘዉ » Thu Dec 01, 2011 1:56 pm

ጌታ wrote:
ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ከ1976 ዓ.ም. ጀምሮ በዜማ ሥራዎቿ ተወዳጅ ሆና የዘለቀችው ሐመልማል አባተ 'ማን አሣየብኝ' እያለች ድምጿን ታንቆረቁራለች :: ይህንን ዜማ በየትኛው ባንድ አጃቢነት : መቼ እና የትኛው መድረክ ላይ እንደተጫዎተችው ያወቀ ሰው ሽልማት ይኖረዋል ::

ሐመልማል አባተ :- ማን አሣየብኝ ::

ተድላ

ጊዜው ቢዘገይም የሽልማት ነገር ስለማያስችለኝ ልሞክራት::

1. አጃቢው ባንድ ሮሃ ሲሆን
2. ጊዜው 1977/78 አካባቢ
3. መድረኩ ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለሰፈራ ፕሮግራም ወደ መተከል አካባቢ የዘመቱበት ይመስለኛል::

ልክ ከሆንኩ ባደባባይ የገባኸውን ሽልማት ከች አድርግ!

በመጀመሪያ ወንድማችን ተድላ ይህንን ዐምድ በመክፈቱ እያመሰገንኩ ዘግይቼ ስለሆነ ያየሁት ብዙ ነገሮች አምልጠዉኛል ብዬ እገምታለሁ:: ወደ ኋላ ተመልሼ ነገር ከማቆረፍድ ላሁኑ መታወቅ አለበት ብዬ የማምነዉን አንድ ታሪካዊ ነጥብ ለማሳወቅ ያህል ነው ያሁኑ አቀራርቤ::
ለዚህ መነሻ የሆነኝ ጌታ የሰጠዉ መልስ ነው:: በትክክል መልሶታል:: የቀረ ነገር ቢኖር የዜማው ደራሲ አበበ መለሰ, የግጥሙ ደራሲ ይልማ ገ/አብ መሆናቸው ብቻ ነው:: ስለጊዜዉ በጣም እርግጠኛ ባልሆንም 1977 ይመስለኛል:: አሁን ወደ ታሪካዊ ነጥቡ እንመለስ:-

ሮሀ ባንድ ለምን ወደ መተከል እና ጋምቤላ ዘመቻ ጣቢያዎች ሄደ(ዘመተ)?
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለሰፈራ ፕሮግራም አገልግሎት ወደ ጋምቤላ እና መተከል አካባቢ ዘምተዉ እንደነበረ ይታወሳል:: በወቅቱ የመንግሥት ባለስልጣኖች ተማሪውን ይጎበኙ ነበር::
በአንድ አጋጣሚ ግን ተማሪዉን የጎበኙት ጓድ ለገሰ አስፋዉ ነበሩ:: በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ ችግሮችን ለመፍታት ነበረ የስብሰባው ዓላማ:: ከመንግስት ተወካዮቹ ሁሉም ይደረጋል...ይሟላል...የሚል ማባበያ ይነገር ነበር::
ሆኖም በአካባቢዉ ከፍተኛ የሆነ የዉኃ እጥረት የነበረ በመሆኑ ተማሪዉ ችግር ነበረበት ::
ተማሪው በከፍተኛ ድምጽ 'ይሄ ሁሉ ቀርቶ እኛ የምንፈልገው ዉኃ ነው' እያለ ይጮህ ነበር::
በጋራ ድምጽ...ዉኃ...ዉኃ...ዉኃ...የሚል ድምጽ በረከተ...ለመስማት እስኪያታክት ድረስ!
ድምጹን በትክክል መለየት ያቃታቸው ጓድ ለገሰ አጠገባቸው ያለዉን ሰው 'ምንድነው የሚሉት?' ብለው ይጠይቃሉ:: ሰዉየዉም..."እኔ እንጃ...ሮሀ ነው የሚሉት መሰለኝ...ሮሀ ባንድ' ብሎ ይመልሳል::
ጓድ ለገሰም ወደ ተማሪው ዞረዉ...በከፍተኛ ድምጽ...'ሮሀ ባንድ ነው የምትሉት....?' ይላሉ::
ተማሪዉም በተቀላቀለ ስሜት....አዎ ይላል:: '...ታዲያ ምን ችግር አለው...በአስቸኳይ እንዲመጣ ይደረጋል...' ብለው ይሄዳሉ::
ግማሹ ሮሀ...ግማሹ ውኃ...ሮሀ...ውኃ...ሮሀ...ውኃ በማለት አስተጋባ::
ሮሀ ባንድ በወቅቱ በነበረው የበላይነትና ተወዳጅነት ያልተደሰተ አልነበረም:: ሆኖም እንዲህ በቀላሉ ወደ ዘመቻ ጣቢያዎች ይመጣሉ ብሎ የገመተ አልነበረም::
በዚህ መሰረት ሮሀ ባንድ አስፈላጊው መሰናዶ ተደርጎ, ሳዉንድ ሲስተም ሎው-ቤድ መኪና ላይ ተገጥሞ ሮሀ ባንድ በ5 ቀናት ዉስጥ ወደ ዘመቻ ጣቢያዎቹ ተንቀሳቅሶ ሾው ለመስራት በቃ::
አይገርምም?! ልብ-ወለድ የሚመስል እዉነተኛ ታሪክ ነው:: ምናልባት ላልሰማችሁ እና ታሪኩን ለማታዉቁ ለማካፈል ያህል ነው::
ይሄ ጉዳይ በወቅቱ በዘመቻ ላይ በነበሩ እንዲሁም በብዙ ሙዚቀኞችና ከሙዚቃ ጋር በተገናኘ ሥራ ላይ በተሰማሩ የሚታወቅ ነው::

መልካም ቀን

*
ዳኘዉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Wed Jan 21, 2009 1:18 pm

Postby MeronZG » Thu Dec 01, 2011 10:02 pm

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በክራር ግርፍ አጃቢነት በእንጉርጉሮ ዘዬ በተቃኙ ዜማዎቿ ነፍሣችንን ገዝታ የምትኖረው ሟቿ አስናቀች ወርቁ ካረፈች ሁለት ወራት አለፏት :: ለማስታወሻ ይሆን ዘንድ ስለሕይወት ጉዞዋ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘኋቸውን ዘገባዎች ለቃቅሜ አቅርቤያለሁ :: አሁንም የአስናቀችን ነፍስ እግዚአብሔር ይማራት ::

ምንጮች:-
1 ..... Artist Asnakech Worku interviews by Benjamin Watkins.

2 ..... Asnakech Worku her last days Ethiopian Amharic dvd Quality.

3 ..... Asnakech Worku (1926 - 2004 E.C): Queen of KIrar

ተድላhttp://www.hubesha.com/audio.php?arid=19&abid=33
Ethiopian Music (7000+) http://www.hubesha.com/audio.php
MeronZG
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Sat Nov 12, 2011 11:26 pm
Location: Seattle

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Dec 01, 2011 11:53 pm

ዳኘዉ wrote:
ጌታ wrote:
ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ከ1976 ዓ.ም. ጀምሮ በዜማ ሥራዎቿ ተወዳጅ ሆና የዘለቀችው ሐመልማል አባተ 'ማን አሣየብኝ' እያለች ድምጿን ታንቆረቁራለች :: ይህንን ዜማ በየትኛው ባንድ አጃቢነት : መቼ እና የትኛው መድረክ ላይ እንደተጫዎተችው ያወቀ ሰው ሽልማት ይኖረዋል ::

ሐመልማል አባተ :- ማን አሣየብኝ ::

ተድላ

ጊዜው ቢዘገይም የሽልማት ነገር ስለማያስችለኝ ልሞክራት::

1. አጃቢው ባንድ ሮሃ ሲሆን
2. ጊዜው 1977/78 አካባቢ
3. መድረኩ ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለሰፈራ ፕሮግራም ወደ መተከል አካባቢ የዘመቱበት ይመስለኛል::

ልክ ከሆንኩ ባደባባይ የገባኸውን ሽልማት ከች አድርግ!

በመጀመሪያ ወንድማችን ተድላ ይህንን ዐምድ በመክፈቱ እያመሰገንኩ ዘግይቼ ስለሆነ ያየሁት ብዙ ነገሮች አምልጠዉኛል ብዬ እገምታለሁ:: ወደ ኋላ ተመልሼ ነገር ከማቆረፍድ ላሁኑ መታወቅ አለበት ብዬ የማምነዉን አንድ ታሪካዊ ነጥብ ለማሳወቅ ያህል ነው ያሁኑ አቀራርቤ::
ለዚህ መነሻ የሆነኝ ጌታ የሰጠዉ መልስ ነው:: በትክክል መልሶታል:: የቀረ ነገር ቢኖር የዜማው ደራሲ አበበ መለሰ, የግጥሙ ደራሲ ይልማ ገ/አብ መሆናቸው ብቻ ነው:: ስለጊዜዉ በጣም እርግጠኛ ባልሆንም 1977 ይመስለኛል:: አሁን ወደ ታሪካዊ ነጥቡ እንመለስ:-

ሮሀ ባንድ ለምን ወደ መተከል እና ጋምቤላ ዘመቻ ጣቢያዎች ሄደ(ዘመተ)?
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለሰፈራ ፕሮግራም አገልግሎት ወደ ጋምቤላ እና መተከል አካባቢ ዘምተዉ እንደነበረ ይታወሳል:: በወቅቱ የመንግሥት ባለስልጣኖች ተማሪውን ይጎበኙ ነበር::
በአንድ አጋጣሚ ግን ተማሪዉን የጎበኙት ጓድ ለገሰ አስፋዉ ነበሩ:: በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ ችግሮችን ለመፍታት ነበረ የስብሰባው ዓላማ:: ከመንግስት ተወካዮቹ ሁሉም ይደረጋል...ይሟላል...የሚል ማባበያ ይነገር ነበር::
ሆኖም በአካባቢዉ ከፍተኛ የሆነ የዉኃ እጥረት የነበረ በመሆኑ ተማሪዉ ችግር ነበረበት ::
ተማሪው በከፍተኛ ድምጽ 'ይሄ ሁሉ ቀርቶ እኛ የምንፈልገው ዉኃ ነው' እያለ ይጮህ ነበር::
በጋራ ድምጽ...ዉኃ...ዉኃ...ዉኃ...የሚል ድምጽ በረከተ...ለመስማት እስኪያታክት ድረስ!
ድምጹን በትክክል መለየት ያቃታቸው ጓድ ለገሰ አጠገባቸው ያለዉን ሰው 'ምንድነው የሚሉት?' ብለው ይጠይቃሉ:: ሰዉየዉም..."እኔ እንጃ...ሮሀ ነው የሚሉት መሰለኝ...ሮሀ ባንድ' ብሎ ይመልሳል::
ጓድ ለገሰም ወደ ተማሪው ዞረዉ...በከፍተኛ ድምጽ...'ሮሀ ባንድ ነው የምትሉት....?' ይላሉ::
ተማሪዉም በተቀላቀለ ስሜት....አዎ ይላል:: '...ታዲያ ምን ችግር አለው...በአስቸኳይ እንዲመጣ ይደረጋል...' ብለው ይሄዳሉ::
ግማሹ ሮሀ...ግማሹ ውኃ...ሮሀ...ውኃ...ሮሀ...ውኃ በማለት አስተጋባ::
ሮሀ ባንድ በወቅቱ በነበረው የበላይነትና ተወዳጅነት ያልተደሰተ አልነበረም:: ሆኖም እንዲህ በቀላሉ ወደ ዘመቻ ጣቢያዎች ይመጣሉ ብሎ የገመተ አልነበረም::
በዚህ መሰረት ሮሀ ባንድ አስፈላጊው መሰናዶ ተደርጎ, ሳዉንድ ሲስተም ሎው-ቤድ መኪና ላይ ተገጥሞ ሮሀ ባንድ በ5 ቀናት ዉስጥ ወደ ዘመቻ ጣቢያዎቹ ተንቀሳቅሶ ሾው ለመስራት በቃ::
አይገርምም?! ልብ-ወለድ የሚመስል እዉነተኛ ታሪክ ነው:: ምናልባት ላልሰማችሁ እና ታሪኩን ለማታዉቁ ለማካፈል ያህል ነው::
ይሄ ጉዳይ በወቅቱ በዘመቻ ላይ በነበሩ እንዲሁም በብዙ ሙዚቀኞችና ከሙዚቃ ጋር በተገናኘ ሥራ ላይ በተሰማሩ የሚታወቅ ነው::

መልካም ቀን

*

ሰላም ዳኘው :-

ድርጊቶችን አንድ በአንድ አስታውሠህ ትክክለኛ ታሪኩን ስላካፈልኸን አመሠግንሃለሁ :: ይልመድብህ :!:

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Dec 03, 2011 5:08 am

ሰላም ውድ ወገኖቼ:-

እስኪ በሜሪ አርምዴ በክራር የታጀቡ ዜማዎች ተዝናኑ ::

ምንጭ:- ሜሪ አርምዴ : ኦሆሆ ..ይ
ኦሆሆ ይ...

ምን ወዳጅ ባበዛ በ'lover' ብሠክር :
ምን ወዳጅ ባበዛ በእጮኛ ብሠክር :
አንተን አልረሣህም ሥላሤ ይመሥክር ::

ሜሪ አርምዴ : አባይ ሲሞላ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Dec 03, 2011 7:29 am

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ:-

የእውቁ ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ሊቅ የፕሮፌሠር አሸናፊ ከበደ የሕይወት ጉዞ ምን እንደሚመሥል ከእኒህ ባለ-አራት ገቢር ዝግጅቶች ተከታተሉት ::

ክፍል 1 ..... Dr. Ashenafi Kebede - Ethiopian conductor & ethnomusicologist : Part 1/4

ክፍል 2 ..... Dr. Ashenafi Kebede - Ethiopian conductor & ethnomusicologist : Part 2/4

ክፍል 3 ..... Dr. Ashenafi Kebede - Ethiopian conductor & ethnomusicologist : Part 3/4

ክፍል 4 ..... Dr. Ashenafi Kebede - Ethiopian conductor & ethnomusicologist : Part 4/4

ኢትዮጵያ ጠቃሚ ዜጎቿን በግፈኛ ገዢዎች ምክንያት እንዴት እንዳባከነቻቸው እንደ እኔ እየታዘባችሁ በቁጭት ተብሰልሰሉ ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby Ahmed-1 » Sat Dec 03, 2011 9:08 am

አዳራሹ ቤቴ ቺምቺቱ ከሴ
እኔስ የሚገርመኝ እያደርኩ ማነሴ

..ያውና እዛ ማዶ በግ ያግዳል ሰዉ
ካላየ ካልሰማ ባላህያ ነው.....(ቂቂቂ)

http://youtube.com/watch?v=QEWtC-Wzd_8&feature=related
Ahmed-1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 174
Joined: Mon Mar 19, 2007 3:17 pm

Postby ዳኘዉ » Wed Dec 07, 2011 3:42 pm

ስጥ እንግዲህ wrote:ተሾመ ምትኩ ዘፈን የጀመረ ኮከበ ጽባህ ተማሪ ሆኖ ነው:: በዚያን ጊዜ ኮከበ ጽባህ በአንድ ስዊድናዊ አሰልጣኝነት የተመሰረተ የሙዚቃ ባንድ ነበር:: ከትምህርት ቤቶች ሁሉ የታወቀ ባንድ ነበር:: እነ ቴዎድሮስ ምትኩ በሳክሰፎን (የተሾመ ወንድም)), ታምራት ፈረንጅ በትራምፔት ተስፋዬ (ሆዶ) በድራም የዚያው የኮከበ ጽባህ ኦርኬስትራ አባሎች ነበሩ:: እነኝህ በሙሉ ስዊድናዊው ወደ ሀገሩ ሲመለስ ትምህርት ቤቱን ለቀው ናይት ክለብ ተቀጥረው መስራት ጀመሩ:: በተለይ ይታውቁ የነበረው ሶል ኤኮስ ናይት ክለብ ባንድ ነበር:: እነ ጋራው ስር ያለሺው , የውሀ ላይ ኩበትን የተጫወተ እዚያው ሶል ኤኮስ እያሉ ነበር:: አሁን ከሁለቱ ወንድማማቾች በስተቀር የዚያ ባንድ ተጫዋቾች በሙሉ በህይወት የሉም::
http://www.youtube.com/watch?v=MJCtdXdm ... re=related

ወዳጄ ስጥ እንግዲህ:- ሠላምታዬ ይድረስህ::
ስላካፈልከን የታሪክ ማስታወሻ ዘግይቼም ቢሆን ላመሰግንህ እወዳለሁ::
ከጻፍከው ዉስጥ italicize ያደረኩት ሶል ኤኮስ ባንድን የሚመለከት ከሆነ ማስተካከያ ቢጤ ለማከል ያህል ነው::

በሶል ኤኮስ ባንድ ዉስጥ ይጫወቱ ከነበሩት ዉስጥ አሁንም በሕይወት ያሉ አሉ::

ግርማ በየነ:- የባንዱ የጀርባ አጥንት የነበረ ሰው እዚሁ አሜሪካ ኑሮዉን መስርቶ በሕይወት አለ:: ግርማ በቤዝ ላየን አጻጻፍ ከፍተኛ ተስጥኦ የነበረው ሰው ነው:: ከሙዚቃ ከተለየ የሰነበተ ቢሆንም በቅርቡ እንደተረዳሁት ከነኃይሉ መርጊያ, ጌታቸዉ ካሳና ከመሳሰሉት ጋር ሆነው እንደገና ባንድ ለመመስረት ዕቅድ አለዉ:: ግርማ "ሴት አላምንም" እና "ፍቅር እንደ ክራር" በሚለው ዜማዉ ይታወቃል::

ፈቃደ አምደመስቀል:- እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሮሀ ባንድ ሳክስፎኒስት የነበረው የ ሶል ኤኮስ ባንድ አባል ነበር:: አሁንም በሕይወት አለ:: በአዲስ አበባ ጥሩ ኑሮ መስርቶ የነበረ ቢሆንም ባሁኑ መንግስት ወደ ኤርትራ "እንደተጠረዘ" ሰምቻለሁ::

አሉላ የሐንስ:- "ስንታየሁ" በሚለው ዜማው የሚታወቀዉ ጊታሪስት አሁንም አለ:: ሌሎችም....

እና እነዚህን ነጥቦች ለማስታወስ ያህል ነው::

መልካም ቀን::

*
ዳኘዉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Wed Jan 21, 2009 1:18 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Dec 08, 2011 3:12 am

ሰላም ዳኘው :-

ጥሩ ይዘኻል :: ግርማ በየነ ከተጫወታቸው ዜማዎች መካከል የተወሠኑት በፈረንሣዩ የሙዚቃ አሣታሚ 'Éthiopiques' ቅፅ መውጣታቸውን አስታውሣለሁ :: ካነሣኸው ላይቀር ከግርማ በየነ ዜማዎች ኢንተርኔት ላይ ላይ ያገኘኋቸውን ላካፍላችሁ ::

ምንጮች :
1 ..... ግርማ በየነ : እንከን የሌለብሽ ::

2 ..... ግርማ በየነ : ይበቃኛል ::

3 ..... ግርማ በየነ :
እኔ ነኝ ባይ ማነሽ
ሴት አላምንም
ይበቃኛል
እንከን የሌለብሽ :: Éthiopiques, Vol. 8: Swinging Addis (1969-1974).

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ዳኘዉ » Thu Dec 08, 2011 11:09 am

ሠላም ተድላ:-
የግርማ በየነን ሙዚቃዎች ስለጋበዝከን አመሰግናለሁ::

እኔም የአሉላ ዮሐንስን (የሶል ኤኮስ ባንድ አባል የነበረ) ሥራዎች ፈልጌ ለማቅረብ ሞክሬ ያገኘሁት የሚከተለዉን ነው::
አሉላ በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸብርቆ ስለ ኢትዮጵያ ሲያዜም ይታያል::
http://www.ethiotube.net/video/2844/Mus ... a-Yohannes

መልካም ቀን *
ዳኘዉ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Wed Jan 21, 2009 1:18 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Dec 18, 2011 2:22 am

ዳኘዉ wrote:ሠላም ተድላ:-
የግርማ በየነን ሙዚቃዎች ስለጋበዝከን አመሰግናለሁ::

እኔም የአሉላ ዮሐንስን (የሶል ኤኮስ ባንድ አባል የነበረ) ሥራዎች ፈልጌ ለማቅረብ ሞክሬ ያገኘሁት የሚከተለዉን ነው::
አሉላ በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸብርቆ ስለ ኢትዮጵያ ሲያዜም ይታያል::
http://www.ethiotube.net/video/2844/Mus ... a-Yohannes

መልካም ቀን *

ሰላም ዳኘው :-

አሉላ ዮሐንስን ደምና ነፍስ ካላቸው ኢትዮጵያውያን ድምፃውያን መካከል እመድበዋለሁ :: የሚያሣዝነው በአሁኑ ዘመን የተነሡት ድምፃውያን ሥራዎች ምንም ስለ ለአገር የማያነሡ ወይም ወያኔን የሚያሞካሹ ሆነውብኝ እምብዛም አላዳምጣቸውም ::

እስኪ ከቆዩ ድምፃውያን መካከል የተስፋዬ ገብሬን ዜማዎች ልጋብዛችሁ ::

ምንጮች:-

1 ...... ተስፋዬ ገብሬ (በጣሊያንኛ) ::

2 ..... ተስፋዬ ገብሬ : አዲስ አበባ ::
አዲስ አበባ ውብ ከተማ :
እህል አየሩ የሚስማማ :

3 ..... ተስፋዬ ገብሬ : ስፖርት::

4 ..... ተስፋዬ ገብሬ : ሰላም ለኢትዮጵያ ::

ቀደም ብዬ የለጠፍሁት ....
5 ..... ተስፋዬ ገብሬ : Ethiopian Animation - Ethiopia The Beautiful.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests