የስርርር መጣጥፎች....>>.....!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ቤዛ » Thu May 27, 2010 10:31 pm

ኤልሳ* wrote:
ቤዛ wrote:ስላም ስርርር በምትጽፋቸው ጽሁፎች ልትመሰገን ይገባሀል:: ምክንያቱም የሚነበብ ጽሁፍ ነውና:: አንዳንዶቹ አዋቂዎች ነን ባዬች አለማወቃቸውን ፍጹም አያውቁትም ሲነገራቸውም የስድብ ናዳ ነው ሰው ላይ የሚያወርዱት:: ያንተ ጽሁፍ መነበቡን ስላወቁ ከኛ በላይ ማን አለ ብለው ለትችት ሳይጠሩ ለስድብ ይመጣሉ እና አንተም ቦታ አትስጣቸው እነሱ 10 ገጽ ቢጽፉም ሁሉም የስድብ በመሆኑ የሚያነበውም የለም:: ስድብ በደማቸው ስለተዋሀደ መተው ነው ምን ይደረጋል? "ባለጌን ካሳደገ ያነቀው ጸደቀ"" ይባል የለ::

I agree with you!!

ኤልሲ አመሰግናለሁ እንግዲህ እኔ ስላነበብኩት እንጂ ስላላነበብኩት ማውራት አልችልም ስለ ዋኖስ ስለ ቤቲ ስለ ትርንጎ ብጠየቅ ዋው ብዬ እናገራለሁ እንዲሁም ሌላ ሌላ ግሩም ጽሀፊዎች አንዳንዶቹ ደሞ ብዙውን የሚጽፉት እናትክን አባትክን ስለሆነ አንብቤውም አላውቅም:: ለማንኛውም አምሰግናለሁ::
ቤዛ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 87
Joined: Wed Nov 12, 2003 5:39 pm

Postby ስርርር » Fri May 28, 2010 12:00 am

ወጣቷ ዓቃቤ-ህግ

ሴቶች ... አብሮ አደጌ አይበልሽ ከፋ....እያሉ በዘፈን ያለአባት ያደገችበትን ትልቁን ግቢ አድምቀውታል:: የሰርግ ዘፈኖች እዚህም እዚያም በእስክስታ ድምቅ ብለው ግቢውን የጥምቀት በዓል የሚከበርበት አስመስለውታል

የዚያን ግዜ....ከ3 ዓመት በፊት...
ፍርድ ቤቱ ጢም ብሎ ሞልቷል:: በዳኝነት ወንበር ላይ የተቀመጡት ከበድ ከበድ ያሉ አዛውንቶች ወጣቷን አቃቤ ህግ ወደታች እያዩዋት ነበር:: በተለይማ የመሐሉ..."በቃ አለቀ... የህንን ሁሉ ግዜ ያጠፋነው በከንቱ ነበር...." በሚል የንቀት አስተያየት ነበር የሚያዩዋት:: ለአቃቢ ህግ አስቴር ይህ የሞት ሞት ሽንፈት ነበር::

"ክብርት አቃቢ ህግ!" ፍርድ ከማሰማታችን በፊት የምትጠይቂው አለ?... አሉ የመሐል ዳኛው!

"እእእ..." አለችና ጉሮሮዋን ሳለችና
"አቃቢ ህግ...ምርመራውን አጠናቆ... የህግ ምስክሮችን አቅርቦ ... ጨርሷል""... "እንደሚታወቀው... ተከሳሹ ሟች አቶ ሳሙዔልን ከመግደሉ በፊት... ባለቤታቸውን ደፍሮ የ16 አመት ልጃገረድ ልጃቸውን በሳቸው ፊት በጭካኔ ደፍሯል:: ይህም አልበቃ ብሎት አቶ ሳሙዔልን በጭካኔ በጥይት ደብድቦ የገደላቸው ለመሆኑ ማስረጃዎች አረጋግጠዋል:: ለዚህም ጥፋቱ...ከፍተኛውን የወንጀል ቅጣት (የሞት ቅጣት) እንዲቀጣ ክቡር ፍ/ቤቱን በአክብሮት እጠይቃለሁ::" ... አለች:: ይተከሳሽ ጠበቃም በበኩሉ በነፃ እንዲለቀቅ አስተYአየት ሰጥቶ ጨረሰና ፍርድ ከእረፍት መልስ እንዲሆን ተወስኖ ለ15 ድቂቃ ያህል እንዲሁ ሆነ::

የመሐል ዳኛው ሽበት የወረሰው ጢማቸውን በቀኝ እጃቸው ዳሰስ ዳሰስ እያደረጉ..... ፍርዱን ማንበብ ጀመሩ:: ፍርዱ ተነቦ ሲያልቅ... አዳራሹ ውስጥ የነበረው ህዝብ "ይህ እንዴት ይሆናል በሚል... አወካ!.... 8 አመት የታሰረው በሪሁን ይህው እንደ ቅጣት ተቆጥሮለት በነፃ እንዲለቀቅ የሚል ነበር ውሳኔው! "
....በግቢው ውስጥ የሰርጉ ዘፈን እንደቀጠለ ነው:: አብሮ አደግ የወንድ ግዋደኞችዋ...እንዲህ ሲሉ ብርቀት ይሰማታል::

መላዬ መላዬ.... አለው መላ መላ....

"ሆይ መላ ነሽ አሉ.... (2)
እጅግ ተገረመ አንቺን ያየሽ ሁሉ

አማረብሽ አሁን እቴ አውቅሽበት
መረጥሽ የወንዳጥር ይህው ለባልነት....(2)

እስክስታው ድርቷል ጭፈራው ሞቅ ብሏል::

በጫጉላ ቤቷ ሆና ታለቅሳለች:: እውነትም ይህ ሲዳሩ ማልቀስ ወግ ይሆን እንዴ! ሚዜዎችዋ ቢያባብሏት ቢሏት እምቢኝ አለች:: የዛሬ 8-አመት በቤታቸው እዚሁ ክፍል ውስጥ የሆነውን እያሰበች ብዙ አለቀሰች.... እናቷ ወይዘሮ ምንትዋብ ወዲህም ከ አንድያ ልጃቸው ጋር እያለቀሱ, ወዲህም ሲያባብሏት, ወዲህም ልብሷን ሲያስተካክሉ.....አብረዋት ታከቱ:: አስቴር አቃቢህግዋ!

እንደምንም ብሎ ግዜው ሄደ:: ማታ ከውድ ባሏ ከወንዳጥር ጋር ብቻቸውን ሆነው... በሰርግ ግርግር የጋለ ስሜታቸውን በወሲብ ለማብረድ ትግል ጀምረዋል:: ሲጨርሱ.... ቁጡው ወንዳጥር ካአልጋው ተስፈንጥሮ ወርዶ....
"የታለ?" አላት
"ምኑ?'...
"ወርቅሽ"
"የምን ወርቅ"... :wink: :roll: :roll: እኔ ስለምን እንደምታወራ አክገባኝም:: ስለድንግልናየ ከሆነ ድንግል ነኝ ብየህ አላውቅም::
"አይደለሁምም ብለሽኝ አታውቂም....ለመሆኑ እንዴት?" ንዴቱ እየባሰ መጣ.....
"እንዴት ምን? እንዴት ተወሰደ?.....ማስረዳት ቀጠለች:: እንዴት እንደተደፈረች...አባትዋ እንዴት በግፍ እንደተገደሉ... ይህንን ሰው (ደፋሪዋን) ለመበቀል... ያላደረገችው ነገር እንደሌለ... የህግ ባለሙያ ሆናም እጇ ሲገባላት ጉቦኛ ዳኞች እንዴት እንዳታለሏት ...

እያለቀሰች, እያሳዘነች በንፁህ ስብዕና እና በፍፁም ትህትና አስረዳችው::

ስትጨርስ የውስጡን ሁሉ ያጥብ ይመስል አብሯት አለቀሰ:: ከበብዙ ደቂቃዎች በህዋላ.....
"አጎቴ ነበር..." አለ እየቃተተ.....
"ማን"
"ደፋሪሽ... የዛሬ ሶስት አመት በሳምባ ነቀርሳ ሞተ... "
"እንዴት ሊሆን ይችላል..." እያለች ራሷን ሰበሰበች::
"ውዴ አሁን ሁሉም ሆንዋል"... ቃል ለሰማይ ለምድር ይህ ነገር ከኔና ካንቺ አይወጣም አለና እጁን ጠረጴዛ ላይ ባገኘው የፖስታ መቅደጃ ቢላዋ ቆረጠ:: ነጩን የደም ሻሽና አንሶላውን ሁሉ በደሙ ቀባባ.....

ራስዋን አሽሽታ የነበረችው እንቡጥ ፅጌረዳ ሙሉ በሙሉ ያለስስት ራስዋን ልትሰጠው.....ተጋለጠች....

"እስቲ አምጣው የደሙን ሸማ!"....ዘፈኑ ቀለጠ ...ብራምባር ሰበረልህ.....
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ትርዛ » Fri May 28, 2010 6:04 pm

ይቺ ናት ፅሁፍ ማለት:: መጨረሻው ያምራል የታሪኩ:: :o :o አንተ ደግሞ ፖልቲካ አያምርብህም የኒ ጌታ:: በርታ እሺ! :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ስርርር wrote:ወጣቷ ዓቃቤ-ህግ

ትርዛ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 78
Joined: Fri Apr 09, 2010 10:10 pm

Postby ስርርር » Tue Jun 01, 2010 11:05 pm

አማሰግናለሁ ትርዛ... መጣሁ በሌላ ፅሁፍ very soon
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby saron*** » Thu Jun 03, 2010 8:19 am

ሰላም ስርርርርርርርርርርርር

የያነበብን ነው ተሎ ተሎ ጻፍልን

የሔርነና ምብር አየምበርክኸናን እያልክ ቀጥል :lol: ትግጥማ ዲኻ :?:

አክባሪህ ሳሮን
saron***
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 168
Joined: Thu Apr 29, 2010 7:50 am

Postby ስርርር » Thu Jun 03, 2010 8:12 pm

የሐሚልቶን መንገድ

ከማንጠግቦሽ ጋር ልጃችንን ልንጠይቅ ዎሃዮ....የሚባል ሐገር ነበርን:: እምዬ አዲሳባ ተደረስን ይህው 3 ወር ሆነን:: አቤት አቤት የማንጠግቦሽ ደስታ መቼም አይጣል ነበር:: ገና አየር ማረፍያ ስንደርስ መሬት መሳም ነው የቀራት የነበረው::.... ኡይይይ! እሱስ እውነቷን ነው:: እኔንም እንዳው የ1 ኣመት ቆይታዬ 10 አመት የቆየሁ ያህል ነበር የሚሰማኝ::....ሸክም ነው መቼም ተላየ የወረደ::

ሳልሳዊት (ፅግሽ) ... 3ኛ ልጄ ናት:: የዚያን ግዜ ዲቢ ወጥቶላት ነበር ወደዚ ወዳማሪካን የሄደችው:: አሁን ግን ያው ዎሃዮ የሚባል ሐገር ነው ያለችው:: የአማሪካን ጎረቤት ይመስለኛል...... እንደውም ዎሃዮም በወባማ ሳይሆን አይቀርም የምትተዳደር:: በቻ ሐገሩ በወጣትነቱ ለሚሄድ ሰው ጥሩ ነው::

አንድ ግዜ ምን ሆን መሰላችሁ...እንደው ቤት ተምንውል ብዬ ፅግሽ ስራ ስትሄድ...ማንጠግቦሽን እዚያ የድንች ጥብስ ያለበት ልክ እኔን የሚመስል ፎቶ ያለው ሽማግሌ ቤት እንሂድ አልክዋት.... "ኬፍሲ ማለትሁ ነው መሸሻ..." አለችኛ... እሷ እቴ... ከኔ በጣም ትሻላለች:: እንግሊዝኛውን አቀላጥፋ ትናገራለች:: ወይኔ መሸሻ... አንድም ቃል ሳላውቅ መምጣቴ ይቆጨኛል...ለነገሩ ምን ሊረባኝ....

ተዚያም ነጠላዋን ደርባ እኔም ከዘራየን ይዠ ተያይዘን ወጣን.... ሐሚልቶን ሮድ የሚባለውን ይዛችሁ ዳር ዳሩን ዎክ አድርጉ ያለችኝን እያስታወስኩ... ጉዞ በግራችን ጥግ ጥጉን ስንግዋዝ ስንግዋዝ..., ኧረ በፈጠረን.... ይህ ሐሚልቶን ማለቅያ የለውም ግማሽ ቀን እንዲሁ ፈጀንና... በስተመጨረሻ የሽማግሌውን ምስል አይተን ገባን::
ሱዳ እንፈልጋለን ብለን ሱዳ አዘዝን:: ሱዳ ማለት ለስላሳ ማለት ነው:: የድንች ጥብሱን ግን እንዴት እንዘዝ....

ፅግሽ. ስታዝ የሰማችውን ቶሎ ቶሎ ቀልጠፍ ብላ ማንጠግቦዬ.... ዋን ነበር ሴክስ ዋን ነበር ኤ አለች:: ስንት እንደከፈልን አላውቅም ግን ብዙ ገንዘብ ነው ያስከፈሏት:: ከዚያማ አጣጥመን በላንና... ተነስተን ወደቤት....

ውሏችንን ለ ፅግሽ እየተሽቀዳደመች ነገረቻት....! ፅግሽ ታድያ በመገረምም በመናደድም... "አሳማ እኮ ነው የበላችሁት!".... ስትለኝ...ሌሊቱን ሙሉ የበላሁት ሲያስመልሰኝ አደረ

ዎሀዮ ብመለስ የማደርገው ነገር ...ያንን የኮሎምቦስ ዎሐዮን የሐሚልቶን መንገድ እስተመጨረሻው ድረስ በእግሬ መዝለቅ..... በቃ ከዚያ ስሜን በርኮርድ መስቀመጥ!

ፅግሽ...ብታገባ ደስ ይለኝ ነበር:: አንድ መሸጦ ባርያ ጥቁር ሰውየ እኛን ልታስተዋውቀው አምጥታ ነበር:: ግን ምኗ እንደሆነ አልነገረችኝም:: እኔ ግን እሱን ጠርጥሬያለሁ:: ኧረ እንደውም አንድ ቀን በቴሌቭዥን እንደምናየው... መኪና ውስጥ ሲስማት አይቻለሁ:: እንደው እሱ አይሁን እንጂ ብታገባ ደስ ይለኝ ነበር:: ወልጄ ወልጄ ለመሸጦ ባርያ.... ሆሆይ....ባህል የማያውቅ የሆነ ጥርብ!
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Tue Jun 08, 2010 12:18 am

ጉድግዋዱ የማይሞላው

ለቀጭኑ ጠባብ... ለወፍራሙ የሰፋ
ያገኘውን ሁሉ ... አላምጦ የሚያስተፋ

ለምለም ሳሩን ለብሶ...የተሰረጎደው
የሚያባብል መስህብ ... በውስጡ የያዘው

ጉድግዋዱ የማይሞላው ዛሬም ፈልጎሀል
በል ግባና ታኘክ... ፍርጃ ፈርዶብሀል
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Thu Jun 10, 2010 7:56 pm

ይህንን ግጥም የዳሞት ግጥሞች በሚል ቤት ውስጥ ታነቡታላችሁ:: ግን ባለልጅ መሆን ምንያህል ንፍስን እንደሚያስደስት በወንድሜ ስላየሁ እዚህም አምጥቼ ባለ ልጆችን ላስደስት በሚል እሳቤ ነው...

ባባዬ ስትለኝ

የአጥንቴ ፍላጭ ... ቡጫቂ የስጋዬ
መስታወት አለሜ .... ራሴን ማያዬ

ልጄ እምቦቀቅላው ....የአብራኬ ክፋይ
ሳቅ ተጫወትልኝ ..... ነፍሴ ደስታህን ትይ

ባባዬ ስትለኝ .... ነፍሴ ተደሰተች
ህይወቴም በደስታ ... ስላንተ ዘመረች

ስብራቴን ጠገንህ ... ... ሙሉ አደረግህኝ
ስለህይወት ትርጉም ... በእርግጥ አስተማርከኝ

ዶቃው ለአንገትህ ... ብር አልቦውም ለእግርህ
ልጄ እንቦቀቅላው ... ኧረ እንዴት ላስጊጥህ ?

ሁሌ የምሳሳልህ .... ወርቄ ነህ ገንዘቤ ...
የህይወቴ አክሊል .... ደስታ ነህ ለልቤ

ከአንድነት ኑሮ .... ሁለት ያደረግኸኝ
የአምላኬ ችሮታ ....ምንግዜም ኑርልኝ
ልጄ ወዳጄ አንተን ... ክፉ አይንካብኝ

ከስርርር !
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby my ፍቅር » Fri Jun 11, 2010 3:33 am

ወይ ስርር ልብ የሚነካ ግጥም የልጅን ፍቅር ወልዶ ያየው ነው የሚያቀው.ትልቅ ሆኖ ለ ልጂ ባነበለት ደስ ባለኝ
አሪፍ ስራ ነው
lehulum gize alew
my ፍቅር
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 67
Joined: Fri Feb 19, 2010 10:51 pm

Postby ስርርር » Tue Jun 15, 2010 12:15 am

8) thank you ma love (myፍቅር)
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Tue Jun 15, 2010 7:27 pm

(ባህር ዳር ሆስፒታል)... በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

ዋለልኝ የ40 ዓመት ጎልማሳና የ6 ልጆች አባት ነው:: መራዊ ከተማ ውስጥ ትንሽየ ሱቅ ቢኖረውም እሱ ግን ከአገው ገበሬዎች ጋር ድንች ማምረት ስለሚያስደስተው, ከከተማዋ ወጣ ብሎ ጎጆ ቀልሶ በዚያ ነው የሚኖረው:: ባለው ጥሪት ምክንያት ባካባቢው ህዝብ ዘንዳ ጥሩ ተደማጭነት አለው:: መራዊ ከባህር ዳር 16 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽየ ከተማ ብትሆንም የምሽት ድምቀቷ ከባህርዳር አይተናነስም:: እያንዳንዷ መጠጥ ቤት በብልጭልጭ መብራቶች ደምቃ ሀላፊ አግዳሚውን ሁሉ ኑ ግቡ እያለች የምትጋብዝ ትመስላለች:: በዚያ ላይ ያስተናጋጆቹ ውበት ወንዱን ሁሉ ያማልላል::

ዛሬ ግን መራዊ ዋለልኝን የምታስታምም ይመስል ጭልምልም ብላለች:: መብራት ተረኛ ነች እና ያው ጠፍቷል:: ዋለልኝ ቀኑን ሙሉ በቁርጠት በሽታ ሲሰቃይ ውሎ... አመሻሹ ላይ ሲደክም ወርቄ (የልጆቹ እናት)
"አየ ዋሌ እያየሁህማ አትሞትብኝም..." ብላ በቃሬዛ አሸክማ ወደመራዊ የወሰደችው::

"ዶፍተር... ባልተቤቴ ምን እንደሆነብኝ አላቅም... አለች እየፈራች" በከተማዋ ውስጥ ያለው ብቸኛ ጤና ጣቢያ ውስጥ ተረኛ ሆኖ ያደረውን ጤና ረዳት እየተማጠች::

"ለዛሬ መብራትም ጠፍቷል.... ማስታገሻ እሰጥልሻለሁ.... ግን እንደኒ እንደኒ ባህርዳር ብትወስዱት ይሻላል ባይ ነኝ" አለ ተረኛው ጤና ረዳት::

የተሰጠው 'ማስታገሻ' በርግጥ አሻለው:: ምናልባትም ስነልቦና ይሆናል ግን ተሻለው:: ጠዋት ተነስተው የመጀመርያዋን ሚኒባስ ይዘው ወደ ባህርዳር አቀኑ::

ባህር-ዳር ሆስፒታል:: ወጣቱ ዶክተር በደንብ አድርጎ መረመረው::-ዋለልኝን:: በሽታው ምን ሊሆን እንደሚችል ቢገምትም የላቦራቶሪ ምርመራ ለማድረግ ሽንትና ሰገራ እንዲሰጥ ማድረግ ፈለገ:: በዚሁ መሰረት ወደ ላቦራቶሪ ሄዱ.... ወርቄ ባሏን ደግፋ ከሱ ጋር ደከመች::

መንጫቃዋ የላቦራቶሪ ሰራተኛ.... ትንሽየ ብልቃጥና እንደ እንጨት ያልች ችልፋ ሰጥታቸው...
"በሉ ሰገራውን አታብዙ... ሽንቱን ደግሞ በዚች ቢልቃጥ ..." ብላ በቁጣ መንፈስ አስተናገደቻቸው::

"ወይ ጣጣ... አለመያዝ ብቻ.... ሆሆይ የማንም አፍ መጥረጊያ ልሁን? ወይኔ ዋለ!" እያለ እየተቆጨ በሚስቱ ድጋፍ ወደ መፀዳጃ ቤት አመሩ:: ...

"ወርቄ..... እምቢ አልኝ ምን ይሻለኛል?"
"ምኑ አካሌ"
"ሽንቴም እዳሪዬም..."...
"አይ እንደምንም በርታ እንጂ አካሌ!'

ውጤቱም ተሰርቶ ዶክተሩ ጋር እስኪቀርብ ድረስ መነጋገርያ ሆነ!... እንዴት ሊሆን ይችላል?
ወጣቱ ዶክተር....ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ እነዋለልኝን ያስጠራል....

"አቶ ዋለልኝ.... ውጤቱ እንደሚያሳየው ከሆነ......ውጤቱ የሶስት ወር እርጉዝ ነዎት ይላል:: ምንድነው ነገሩ.... እስኪ ያስረዱኝ... እኔን ግራ ገብቶኛል?" አለ ወጣቱ ዶክተር

ዋለልኝ ከተቀመጠበት ወንበር እመር ብሎ ተነሳ!... "እንዴ? እኔ... እርጉዝ.... በፍፁም"
ለመሆኑ ወንድ ነው ሴት ያረገዝኩት?

አይ አቶ ዋለልኝ እሱን አሁን መግለፅ አልችልም... እስኪ ተረጋግተው ያስረዱኝ..."

አይይይይ ተዋረድክውዋ ወርቄ..... አንቺ ነሽ ጉድ ያረግሽኝ... ይሄውልህ ዶክተር! ያኔ ስንፈጥም... ተላይ ታልሆንኩ ብላ ድርቅ ስትል እሺ አልክዋት:: ከዚያ ወዲህ ሁልግዜ ተላይ ነው ፊጥ የምትል.... ይህው....የሶስትወር አርድጋኝ ቁጭ!

ነገሩ ቢያስቀውም ቻል አድርጎ... ሌላ ጥያቄ ጠየቀ ዶ/ር...

አሁን ወርቄ መናገር ጀመረች...
. "ዋለዬ ሽንት እምቢ ሲለው ውይ... ታድያ ምናለ! የኔን እንስጥ! ያው አንዳካል አንዳምሳልም አይደለን?" ብዬ... የኔን ሽንት ነበር የሰጠሁት!
ወጣቱ ዶክተር....እምባው እስኪፈስ ድረስ በሳቅ ተንከተከተ...
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

ቅቅቅቅ

Postby ዋኖስ » Tue Jun 15, 2010 7:36 pm

ቅቅቅቅቅቅ! ስም አጥፊ! "የቅርቃኛ-ገበሬ" ቢያገኝሕ! ዋ! ቅቅቅ
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ኤልሳ* » Tue Jun 15, 2010 8:22 pm

ስርርር wrote:[b]
"ወርቄ..... እምቢ አልኝ ምን ይሻለኛል?"
"ምኑ አካሌ"
"ሽንቴም እዳሪዬም..."...
"አይ እንደምንም በርታ እንጂ አካሌ!

:lol: :lol: ገና ይሄን ሳነብ ውጤቱ ምን እንደሆነ ጠርጥሬ ነበር....
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

Postby ሞዴስ » Wed Jun 16, 2010 12:25 am

ስርርር wrote:(ባህር ዳር ሆስፒታል)... በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ

ዋለልኝ የ40 ዓመት ጎልማሳና የ6 ልጆች አባት ነው:: መራዊ ከተማ ውስጥ ትንሽየ ሱቅ ቢኖረውም እሱ ግን ከአገው ገበሬዎች ጋር ድንች ማምረት ስለሚያስደስተው, ከከተማዋ ወጣ ብሎ ጎጆ ቀልሶ በዚያ ነው የሚኖረው:: ባለው ጥሪት ምክንያት ባካባቢው ህዝብ ዘንዳ ጥሩ ተደማጭነት አለው:: መራዊ ከባህር ዳር 16 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽየ ከተማ ብትሆንም የምሽት ድምቀቷ ከባህርዳር አይተናነስም:: እያንዳንዷ መጠጥ ቤት በብልጭልጭ መብራቶች ደምቃ ሀላፊ አግዳሚውን ሁሉ ኑ ግቡ እያለች የምትጋብዝ ትመስላለች:: በዚያ ላይ ያስተናጋጆቹ ውበት ወንዱን ሁሉ ያማልላል::

ዛሬ ግን መራዊ ዋለልኝን የምታስታምም ይመስል ጭልምልም ብላለች:: መብራት ተረኛ ነች እና ያው ጠፍቷል:: ዋለልኝ ቀኑን ሙሉ በቁርጠት በሽታ ሲሰቃይ ውሎ... አመሻሹ ላይ ሲደክም ወርቄ (የልጆቹ እናት)
"አየ ዋሌ እያየሁህማ አትሞትብኝም..." ብላ በቃሬዛ አሸክማ ወደመራዊ የወሰደችው::

"ዶፍተር... ባልተቤቴ ምን እንደሆነብኝ አላቅም... አለች እየፈራች" በከተማዋ ውስጥ ያለው ብቸኛ ጤና ጣቢያ ውስጥ ተረኛ ሆኖ ያደረውን ጤና ረዳት እየተማጠች::

"ለዛሬ መብራትም ጠፍቷል.... ማስታገሻ እሰጥልሻለሁ.... ግን እንደኒ እንደኒ ባህርዳር ብትወስዱት ይሻላል ባይ ነኝ" አለ ተረኛው ጤና ረዳት::

የተሰጠው 'ማስታገሻ' በርግጥ አሻለው:: ምናልባትም ስነልቦና ይሆናል ግን ተሻለው:: ጠዋት ተነስተው የመጀመርያዋን ሚኒባስ ይዘው ወደ ባህርዳር አቀኑ::

ባህር-ዳር ሆስፒታል:: ወጣቱ ዶክተር በደንብ አድርጎ መረመረው::-ዋለልኝን:: በሽታው ምን ሊሆን እንደሚችል ቢገምትም የላቦራቶሪ ምርመራ ለማድረግ ሽንትና ሰገራ እንዲሰጥ ማድረግ ፈለገ:: በዚሁ መሰረት ወደ ላቦራቶሪ ሄዱ.... ወርቄ ባሏን ደግፋ ከሱ ጋር ደከመች::

መንጫቃዋ የላቦራቶሪ ሰራተኛ.... ትንሽየ ብልቃጥና እንደ እንጨት ያልች ችልፋ ሰጥታቸው...
"በሉ ሰገራውን አታብዙ... ሽንቱን ደግሞ በዚች ቢልቃጥ ..." ብላ በቁጣ መንፈስ አስተናገደቻቸው::

"ወይ ጣጣ... አለመያዝ ብቻ.... ሆሆይ የማንም አፍ መጥረጊያ ልሁን? ወይኔ ዋለ!" እያለ እየተቆጨ በሚስቱ ድጋፍ ወደ መፀዳጃ ቤት አመሩ:: ...

"ወርቄ..... እምቢ አልኝ ምን ይሻለኛል?"
"ምኑ አካሌ"
"ሽንቴም እዳሪዬም..."...
"አይ እንደምንም በርታ እንጂ አካሌ!'

ውጤቱም ተሰርቶ ዶክተሩ ጋር እስኪቀርብ ድረስ መነጋገርያ ሆነ!... እንዴት ሊሆን ይችላል?
ወጣቱ ዶክተር....ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ እነዋለልኝን ያስጠራል....

"አቶ ዋለልኝ.... ውጤቱ እንደሚያሳየው ከሆነ......ውጤቱ የሶስት ወር እርጉዝ ነዎት ይላል:: ምንድነው ነገሩ.... እስኪ ያስረዱኝ... እኔን ግራ ገብቶኛል?" አለ ወጣቱ ዶክተር

ዋለልኝ ከተቀመጠበት ወንበር እመር ብሎ ተነሳ!... "እንዴ? እኔ... እርጉዝ.... በፍፁም"
ለመሆኑ ወንድ ነው ሴት ያረገዝኩት?

አይ አቶ ዋለልኝ እሱን አሁን መግለፅ አልችልም... እስኪ ተረጋግተው ያስረዱኝ..."

አይይይይ ተዋረድክውዋ ወርቄ..... አንቺ ነሽ ጉድ ያረግሽኝ... ይሄውልህ ዶክተር! ያኔ ስንፈጥም... ተላይ ታልሆንኩ ብላ ድርቅ ስትል እሺ አልክዋት:: ከዚያ ወዲህ ሁልግዜ ተላይ ነው ፊጥ የምትል.... ይህው....የሶስትወር አርድጋኝ ቁጭ!

ነገሩ ቢያስቀውም ቻል አድርጎ... ሌላ ጥያቄ ጠየቀ ዶ/ር...

አሁን ወርቄ መናገር ጀመረች...
. "ዋለዬ ሽንት እምቢ ሲለው ውይ... ታድያ ምናለ! የኔን እንስጥ! ያው አንዳካል አንዳምሳልም አይደለን?" ብዬ... የኔን ሽንት ነበር የሰጠሁት!
ወጣቱ ዶክተር....እምባው እስኪፈስ ድረስ በሳቅ ተንከተከተ...

የት ነበር ያነበብኩት..ባልሳሳት ከአዲስ አድማስ የተቀነባበረ ነው መስለኝ...
LIFE I WILL CONTINUE !!!
ሞዴስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Sat Jun 12, 2010 6:34 pm

Postby ስርርር » Wed Jun 16, 2010 6:42 pm

የማይገድል እዳዬ

ስቀመጥ እረመጥ... ስቆም የእግር እሳት
ስሄድ ሸክም ሆኖ .... ስተኛም ትኩሳት

ነፍሴ እየቃተተች.....ሌት ቀን ያለፋታ
በደምስሬ ጡዘት... በሲቃ ጨቅይታ

እያንሰፈሰፈ ..... አቅሌን አሳጥቶ
ሁሌ የሚያስጨንቀኝ....በሀሳቤ ሞልቶ

ናፍቆት ኖሯል ለካስ.... ክፉ በሽታዬ
የማይድን የማይሽር.... የማይገድል እዳዬ

መታሰቢያነቷ... በናፍቆትዋ ለተንገበገብኩላት የትውልድ መንደሬ... ለእማማ ኢትዮጵያ ለአባባ ኢትዮጵያ..... ትሁንልኝ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests