የስርርር መጣጥፎች....>>.....!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሞዴስ » Wed Jun 16, 2010 8:44 pm

ስርርር wrote:የማይገድል እዳዬ

ስቀመጥ እረመጥ... ስቆም የእግር እሳት
ስሄድ ሸክም ሆኖ .... ስተኛም ትኩሳት

ነፍሴ እየቃተተች.....ሌት ቀን ያለፋታ
በደምስሬ ጡዘት... በሲቃ ጨቅይታ


እያንሰፈሰፈ ..... አቅሌን አሳጥቶ
ሁሌ የሚያስጨንቀኝ....በሀሳቤ ሞልቶ

ናፍቆት ኖሯል ለካስ.... ክፉ በሽታዬ
የማይድን የማይሽር.... የማይገድል እዳዬ

መታሰቢያነቷ... በናፍቆትዋ ለተንገበገብኩላት የትውልድ መንደሬ... ለእማማ ኢትዮጵያ ለአባባ ኢትዮጵያ..... ትሁንልኝ

የሎሬት ጸጋየ ድርሰት ነው......በስው ድርሰት እውቅና ትፈልጋለህ ትንሽ አታፍርም....
LIFE I WILL CONTINUE !!!
ሞዴስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Sat Jun 12, 2010 6:34 pm

Postby ስርርር » Mon Jun 21, 2010 7:16 pm

ማለዳ ማለዳ!

አዝማሪው ይህንን መሰንቆ ያለዘፋኝ ይገዘግዘዋል:: ሪትም የለው.... ዘፋኝ የለው.... ብቻ ዝም ብሎ ይገዘግዘዋል:: ዚዚዚዚዚዝ! ያደርገዋል!>>. ጠጪውን ሁሉ ቀና ብዬ ሳይ በዜማው የተደሰቱ ይመስል አብረው ይወዛወዛሉ!. እኔ ግን ራስምታት ሆኖብኛል:: ጢዝዝዝዝዝዝዝዝዝ ሲልማ በቃ የጢንዚዛ ድምፅ ነው የሚመስለው::

ወይ ጣጣ! ይሄ ሱስ እንደው የማያደርገኝ ነገር የለም! ሶስት ብርሌ ጠጅ ጠጥቼ አራተኛውን ግማሽ ላይ አድርሻለሁ:: ኡሁሁሁ... ራሴን ሶስት አራት ሆነው ተባብረው በመዶሻ የሚቀጠቅጡኝ ያህል ህመሙ እረፍት ነስቶኛል:: በዚያ ላይ ደግሞ ይሄ የማይደክም ማሲንቆኛ... ይገዘግዛል ያለዕረፍት!.... እኔን እረፍት ነሳኝ እንጂ ጠጪው ሁሉማ እየተዝናና ጥሩ ሪትም እንዳለው ሙዚቃ አብሮ የወዛወዛል:: ለሱሴ ስል እዚህ ደባሪ ጠጅ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ አራተኛውን ብርሌ ጠጅ ፉት.... እያልኩ ነው::

በመሃል አንዲት የሚያምር ድምፅ ያላት የቀይ ዳማ በሃገር ባህል ልብስ ተሽቆጥቁጣ...አጠገቤ ቁጭ አለች:: እንደገናም ብድግ ብላ በጀርባዬ ዞረችና ፀጉሬንና አንገቴን እያሻሽች "ቦይኖሢያስ ሲኞር!" አለችኝ:: እንደምን አደርክ ጌታዬ! እንደማለት ነው በስፓኒሽ:: ግራ ግብት አለኝና እንዴ ስፓኒሹን ከየት ለመደችው የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ:: እንደዚህ ያለች ደመግቡ በዚያ ላይ ስፓኒሽ የምትችል... እንዴት የጠጅ ቤት ኮማሪ ሆነች?

ማሲንቆኛው... አሁንም ቀጥሏል:: ማሲንቆኛው ሰውየም ከኔ ጋር እልህ የተጋባ ይመስል ሚጥሚጣ በሚመስሉ አይኖቹ በሩቁ እያየኝ ፈገግ ይላል:: ፈገግ ሲል ከዚያ ከጥቁር ፊቱ ውስጥ በቀይ ድዶቹ ላይ ላመል የተደረደሩት ሹል ጥርሶቹ ያስፈራሉ:: ሳጥናዔልን በአካል ያየሁት ያህል እየተሰማኝ አማተብኩና ጠጄን ፉት አልኩ! >>>>>>

አጠገቤ የተቀመጠችውን ቆንጆ መልሼ ሳስተውላት "ምነው የኔ ቆንጆ! የደበረህ ትመስላለህ" የሚል ቃና ያለው አስተያየት አየችኝ:: ዝም ብየ እሷን ማስተዋል ያዝኩኝ:: ራስምታቴ ቢተወኝ ብየ ቁንጅናዋን ማድነቅ ጀመርኩኝ::

ማሲንቆው እረፍት እንደነሳኝ ያወቀችው ይቺ ቆንጆ ሴት ትንሽ ቆየት ብላ ወደ ማሲንቆኛው ጆሮ ጠጋ ብላ! የሆነ ነገር ሹክ አለችው:: ከዚያም ስፒከሩን ይዛ ወደመድረክ ብቅ አለች:: አሁን መሲንቆው ሪትም ያዘ>>>>
"ማለዳ ማለዳ ሸጋ ሰው ማለዳ! እህም ማለዳ!" አያለች ልዩ ቅላፄ ባለው ድምፀ-ቃና አዜመች:: ሙዚቃዋ ልቤ ድራስ ዘልቆ በልቤ ላይ ተፃፈ!....መንፈሴም ተነቃቃ.... ራስ ምታቴ ግን ጨመረ:: እንደምንም ብየ ተነሳሁና ወደዳንስ መድረኩ ሄድኩ>>>...

በዳንስ መንፈስ ውስጥ ሆኜ...እጀን ሳወራጭ ማብሪያ ማጥፊያውን ቀጭ አደረኩት:: ትንሽዋ ክፍሌ የብርሀን ጎርፍ ሞላት:: ራስ ምታቴ በእጥፍ ጨምሮ ቀሰፈኝ:: አሁሁሁሁ>>>. አልኩና አልጋዬ ላይ ቁጭ ብየ ራሴን በሁለት እጄ ግጥም አድርጌ ያዝኩ:: ሩም ሜቴ (የክፍል ተጋሪዬ) አሁንም ያንኮራፋል:: የህልሜ ማሲንቆ! የቅዠቴ ሙዚቃ>>>> የእውኔ ራስ ምታት!

"ቦይኖስያስ ሲኞር" አለችኝ የሞባይል ስልኬ>>> ለሶስተኛ ግዜ ልትቀሰቅሰኝ:: ግዋዴ! የማለዳ ወፌ! ቀስቃሼ!>>> ቀጠል አድርጋም "ማለዳ ማለዳ" የሚለውን የራሔል ዮሀንስ ዘፈን ማሰማት ቀጠለች:: ስልኬ!

ቶሎ ቶሎ ልብሴን ለባብሼ ወደስራዬ አቀናሁ:: መቼ ይሆን ትኝት ብዬ የማረፍደው? መቼ ይሆን ፍርፍር በቅቤ ከትኩስ ቡና ጋር >>>>> ኡሁሁሁ! ይህንንን ሳስብ ራስምታቴ>>>

ልክ ከጥዋቱ 5:30 ሲል ከባህሩ ዳርቻ ደረስኩ::
"d'd you clock in?" አለችኝ በወፍራም ጃኬት የጠረዘችው አለቃዬ....ሱፐርቫይዘሬ! የሀይስኩል ሽፍታዋ ጥቁር!
"yes" አልኩ በኩሩ ቅላፄ::
"k...let's go go go!, what are you waitin fo? አለችኝ
በአሳ የተሞሉ ሳጥኖችን ባልበላ አንጀቴ እየተሸከምኩ ወደፍሪዘር/በረዶ ቤት/ ማስገባቴን ተያያዝኩት:: ብርዱን እንደሆን ለምጀዋለሁ:: አንደበቴ ዝም ቢልም ልቤና አዕምሮዬ "ማለዳ ማለዳ!" እያሉ እየተቀባበሉ አዜሙ!
ፍርፍር እያማረው ሆዴ ቆረር ብሎ ጮኸ!
"ማለዳ ማለዳ!" አለ አንደበቴ.... የሆዴን ጩኸት ለመሸፈን
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Thu Jun 24, 2010 10:02 pm

እስኪ ምረጥ አሉኝ

ከወለላይቱ-- ከእናት ከእማምዬ
ከአባባ ኩራቴ ጌጤ መድመቂዬ

ከግማሽ አካሌ.... ከሚስቴ ከደሜ
ከሴት ልጅ ከወንዱ... ከእህት ከወንድሜ
ከዚያችኛይቱ ሴት... ከሚሏት ውሽሜ

እስኪ እንይህ አሉኝ.....ማንን ትመርጣለህ ...
ህይወትህን ልትሰጥ..... ለማን ትፈቅዳለህ::

እናትም እምዬ ...በፍቅር አኗሪ
አባትም አባባ ... ህይወት አስተማሪ
ፍቅራቸው በልቤ ዘላልም አዳሪ

ሚስቴም ባለቤቴ .... ፍላጭ የጎኔ አጥንት
ክፉዋ ይራቀኝ .... ያርገኝ ከስዋ በፊት

ክንዴ አካላቴ ... ወንድሜም ጋሻዬ
ኩራቴ ስስቴ .... እህቴም አበባዬ

ጧሪ ቀባሪዬ ... ወንድ ልጅ መክበርያ
ሤት ልጄም ናፍቆቴ .... የአይኖቼ ማረፊያ ....

በህገ -እግዚአብሔር .. ፍፁም ነኝ ባልልም
በውሽማ ሰበብ .... አላመነዝርም

ታድያ ለዚህ ሁሉ ...ህይወቴን እንድሰጥ
ፈቃዱ ከሆነ ... እግዚአብሔር ሊደሰት

ታድያማ ምናለ ...ሞትላቸዋለሁ
ሰለእግዚአብሄር ፍቅር ... በፍቅር እሰዋለሁ

ከወንድም ከህት ... ከአባት ከእናት ሐገር
ከሁሉም ይበልጣል .. ፍቅረ -እግዚአብሔር
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Fri Jul 02, 2010 7:41 pm

ባይነጋስ ምናለ!
እንደ አባይ በረሃ....ንዳድ እንደፈጀው
እንደ ጣና ውሃ... ዧ ብሎ እንደተኛው

እንደ ገዳም ደብር..ልብ ከቆዘመ
በፍርሃት ጣር.....ሌቱ ከረዘመ
....... to read more click here
http://www.ethiopianreporter.com/index. ... Itemid=576
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Tue Jul 06, 2010 5:24 pm

በሐገራችን አቆጣጠር ከሰኔ 25 እስከ መስከረም 26 ድረስ ወርሃ ክረምት ይባላል:: የክረምት ወቅት እንደማለት ነው::

ሰኔ 25
ቀና ብየ ሳየው ..... ሰማይ ደፈረሰ
ጎንበስ ብየ ባየው .... ምድር ረሰረሰ

ክረምቱ ከተመ.... በምድረ ኢትዮጵያ
ለሶስት ወር ቆይታ...ለምርት ለገበያ

በጋውን ሸኝቶ ..... ክረምቱ ተተካ
በሰኔ 25 ..... ነጎድግዋድ ተንካካ

ምርትን እንሻለን... ገበሬ በርታልን
በክረምቱ ዝናብ..... ማሳህ ይጥገብልን
ባንተ ምርት በአይነቱ.....ወገን ይርካልን
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Thu Jul 15, 2010 5:51 pm

ሮድዮ!
ሮድዮ..የፅናት አርማ!.....እያለች በልቧ ደጋገመችው:: እንደውዳሴ ማርያም!.. ሮድዮ ባል, ሀገር, እናት አባት አይሆን! መለሰ ህሊናዋ!.... ይሆናል እንጂ! ለምን አይሆንም! ልቧ ተከራከረ.........
አዜብ የሚሊተሪ ሚስት በመሆኗ ስትናገርም ሆነ ስትስቅ ትዕዛዝ የምታዝዝ ነው የምትመስለው:: ባሏ ሳጂን ሰለሞን ሲሆን በሳንዲያጎ የአሜሪካን ኔቪ ካምፕ ውስጥ ከነቤተሰቦቹ (አንድ ልጁንና ባለቤቱ-አዜብን) የሚያኖረው ዝንጥ ያለ ቤት መንግስት ሰጥቶታል:: የኔቪ ወታደር ሚስት መሆን አንዳንዴም በአካል አንዳንዴም በሀሳብ እሱ በሄደበት ሁሉ መሄድ ማለት ነው:: ይህኛውን ቤት ከአገኘ በህዋላ ግን ግዳጅ ለመፈፀም ከሀገር ሀገር ራሱ ይሄዳል እንጂ .... ተመልሶ የሚያርፈው ግን እዚሁ ነው::

የወታደር ሚስቶች አንድ ማህበር አላቸው:: አዜብ የዚህ ማህበር የገንዘብ ያዥ ናት:: በዚህ ላይ "ናቫል ፕሬስ" የተሰኘ የሬድዮ ጣቢያ ውስጥም ብቸኛዋ የሴት ጋዜጠኛ ሆና ትሰራለች::

አዜብ ሳምንቱ ድብር እንዳላት አለፈ:: የድብርቷ መንስዔም የባሏ የ6-ወር የኢራቅ ጉዞ ነው:: ኔቪ ፒር ሰገነቱ ላይ ሆና የልጇን እጅ በግራ እጇ እንቅ አድርጋ ይዛ በቀኟ እጇ እስኪገነጠል ድረስ ነበር ቻዎ ያወዛወዘችው:: መርከቡ ካይኗ እስኪሰወር ድረስ እዚያው ቆማ ... በስተመጨረሻ.... "የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅህ ፍቅሬ" የሚለውን ቃል ስትተነፍስ.... ልጇም እንባውን አቅርሮ...
"mam..is dad coming soon? when is he coming back.. I already miss him"... እያለ በጥያቄ አጣደፋት:: "እንግሊዝኛ ከኔ ጋር ማውራት አይፈቀድም" እያለች እያባበለች ተመለሱ::

ቀኑ ሐሙስ ነው:: ሐምሌ 15/2010. ጠዋት ተነስታ የልጇን ምሳ ካሰረች በህዋላ ትምህርት ቁርስ በሉ:: ከዚያም ለሰመር/ለበጋው/ የሚመች አጭር ቀሚስ ስትለብስ... ሆዷ ፍጥጥ ብሎ ወጣ:: የሶስት ወር እርግዝና!.... ሆዷን እየደባበሰች "ትንሿ አሰገደች!" አለች በለሆሳስ:: እናቷን አስመስላ ለመውለድ እየተመኘች:: የእናቷን ናፍቆት በልጇ ልትወጣ::

"Goooooooood morning! this is the voice of MP (militar press), am Azeb, your host today. we will have current news every 30 minutes. Sizzling summer time is arround. the temp. today is a lil over 100. We accept your calls and 'll play songs of your choises for your loved ones, our men and women in the service. To start with ... Bob says In the summer time......... here we go.....in the summertime" ... Bob Dylan" አለችና ስፒከሩን አስቀምጣ.... ሌሎች ፋይሎችን ማገላበጥ ያዘች:: ሙዚቃው በየቤቱ በሬድዮው ተንቆረቆረ...

ሮድዮ.....የMP ስቱድዮ መጠሪያ ነው...የሀገርዋን የባልዋን የናትዋን...የዚህን ሁሉ ናፍቆትና ሀሳብ የምታስታግስበት:: ሮድዮ....የፅናት አርማ!.... በሀሳብ የምትቆዝምበት... የሀገሯን ሙዚቃዎች የምታሰማበት ባህሏን የምታስተምርበት... ሴትነቷን የምታከብርበት........ ሮድዮ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ዝንቱ » Thu Jul 15, 2010 7:36 pm

multiple personalities አሉህ እንጂ ጥሩ ትፅፍ ነበር:: በተለይ "ማለዳ ማለዳ" የሚለውን ፅሁፍ ሳነብ በ ኩርፊያ /snoring/ ምክንያት እንዲህ እንዳንተ የተቸገሩና እንቅልፍ ያጡ ሰዎችን አስታወስከኝ:: ስኖሪንግ ትልቅ በሽታ ነው:: በዚህ ምክንያት ስንቱ ትዳሩን እንዳጣ በት ይቁጠረው:: በርግጥ መድሀኒት አለው ሲባል ሰምቻለሁ:: እስኪ የሚያውቁ ሰዎች ካሉ ይረዱን ዘንድ ሌላ ትሬድ እከፍታለሁ:: እንግዲህማ ዋርካ ከዘለኩ በህዋላ ሙሉ በሙሉ ንክር ነው እንጂ! እስተመቼ ተመልካች እሆናለሁ::

ሮዲዮም የሚነበብ ፅሁፍ ነው:: በርታ:: ግን have self-respect. If you respect yourself, then everyone is going to look up to you.
አድናቂህ
ዝንቱ
I am black, yet beautiful!
ዝንቱ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 24
Joined: Thu Jul 15, 2010 6:56 pm
Location: MARS

Postby ስርርር » Wed Jul 21, 2010 7:06 pm

ዝንቱ ውዕቱ አሃውየ ዘአፈቅር!" የማፈቅረው ወንድሜ ይህ ነው::

ዝንቱ እንዴት ነህ? በጣም ይቅርታ እየጠየቅሁኝ (በጣም በወፍራሙ) አንተና እንሰት አንድ ሰው ትመስሉኛላችሁ:: አደራ ደግሞ እንዳትቀየምብኝ::

ፅሁፌን ስላነበብክልኝ በጣም አመሰግናለሁ:: ማሌዥያዊያን ምን ይላሉ መሰለህ...."ዳላም ሀቲ አደ ቺንታ" ይላሉ:: በልብ ያለ ፍቅር ሁልግዜም ህያው ነው እንደማለት!... ይቺን ዶናት ፍለጋ የማንሄድበት የለም መቼም! የነጋዴ ነገር::

ስለ snoring ጥሩ ትምህርታዊ የሆነ ፅሁፍ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ::
አመሰግናልሁ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Fri Jul 30, 2010 5:26 pm

:lol: መጣሁ ቆይ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Fri Jul 30, 2010 10:11 pm

ፈ--ን--ዳ--ሳ
ከእንቅልፌ ምን እንዳባነነኝ አላውቅም:: ብንን አልኩ! ሰዓቴን ሳይ ከሌሊቱ 2 AM ይላል በፈረንጂኛው:: እርቃኔን መተኛት ስለምወድ መለመላዬን ነኝ:: ቶሎ ብዬ ከአንሶላው ውስጥ ወጣሁና ወገቡ ላይ ሸብ የሚደረገውን ቢጃማዬን አጥልቄ ከመኝታ ክፍሌ ወጣሁ::

በወጥቤቱ አልፌ ወደመፀዳጃ ክፍል ሄድኩና የውጉን አድርሼ ስመለስ...እግረ-መንገዴን ያኛውን ክፍል አይኔ አማተረ:: ለምን አላያትም በሚል እሳቤ ወደበሩ ሄድኩና ቀስ........ብዬ ከፈትኩት::

የራስጌ መብራቷ አልጠፋም:: በስሱ የከፈተችው የሞዛርት የሙዚቃ ቃናም እየደጋገመ ይጫወታል:: ፀደይ ጧ ብላ ተኝታለች:: ሳያት ውስጤ ተላወሰ! የኔ ብቻ! አልኩኝ:: ነፍሴ ነፍሷን ፍለጋ ሩጫዋን ያዘች:: ልቤ አታሞዋን ደለቀች:: ድንቅ የአምላኬ ስጦታ... የክረምቱን ጨለማ ያለፍኩባት... ይንጋት ውበት ፀደይ::

የክፍሉ መሐል ላይ ቆሜ አስተዋልኳ:: የተስተካከለ አፍንጫ, ትልልቅነታቸውን ተከድነውም ቢሆን የሚያሳብቁ አይኖች, በትራሷ ላይ ዝብርቅርቅ ብሎ የተበታተነው ዞማ ፀጉሯ, እፎይይይይይይይይይይ! እንደው ውበቷን አድንቄ መጨረስ አልቻልኩትም::

ከእንቅልፏ እንዳትነቃብኝ ስፈራ ስቸር በድመት እርምጃ አይነት ሹክክ ብዬ ወደአልጋዋ ቀረብኩና ከቻፉ ላይ ቁጭ አልኩኝ:: ሰላማዊ እስትንፋሷ በአፍንጫዋ ቀዳዳ በወጣ ቁጥር በከፊል የተጋለጠው ደረቷ ከፍ....ዝቅ...... ሲል ማየት አስደሰተኝ:: ዝቅ ብዬም ሳያት ብርድልብሷ በሙሉ ተጠቅልሎ መሬት ወርዶ ያልደረጀው ጭኗ ተጋልጦ... አየሁ::

ሳላስበው "ወይኔ ልጄ!" አልኩኝ:: እሷ እቴ እንኳን ልትነቃ........ፍንድስ ብላለች:: የኔ ፈንዳሳ!.....

ልብሶችዋን አስተካክዬ አልብሻት ሙዚቃዋን አጥፍቼላት ዘወር ብዬ ወደክፍሌ ሄድኩኝ:: አዎን እዛ....ትኩስ እቅፍ ይጠብቀኛል:: ንፁህ ፍቅር, ያልተበረዘ ስብዕና, የማያልቅ ደግነት........:: ውዷ ባለቤቴ ትጠብቀኛለች::

ገና በሩን ስከፍተው.......ውዴ እጆችዋ ተዘርግተዋል:: እኔ ግን ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ:: ....."am ready my dear. አንተን የመሰለ ደቦል ነው የምወልድልህ:: ና!" የሚል ድምፅ ..........
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Mon Aug 02, 2010 11:24 pm

የረጋ ደም
ዝግጅቷን ስትጨርስ ፈገግ አለች:: እቅዷ "ፕላን ሀ" እና "ፕላን ለ" አለው:: ሰማያዊ ቀለም የቀባችውን መኪናዋን እያሽከረከረች ወደዳገትማው የእንጦጦ ተራራ አመራች::

የአቶ ግርማይን ግቢ መግቢያ የኒያሳያትን ቦታ በደንብ አጥንታዋለች:: መኪናዋን በባህር ዛፎች መሀል አቁማ ከህዋላ ትራንክ ውስጥ ከአያቷ የወረሰችውን ጓንዴ አወጣችና አራት ጥይት አጎረሰችው:: በሰሞኑ ስልጠናዋ መሰረት እንክዋን በቀለን የሚያክል ጠረንገሎ ወፍም አትስትም:: የጓንዴውን አፍ ድምፅ ማፈኛ መሳሪያ ገጠመችለትና ለመተኮስ በሚያመቻት ፖሲሽን ተስተካክላ በደረቷ ተኛች:: ከዚያም ትንሽ ፎከስ አስተካክላ የግቢው በር ላይ አነጣጠረች::

ደቂቃዎች ተቆጠሩ:: ሰዓቱ እየመሸ ነው:: ከቀኑ 10 እዚህ ይደርሳል የተባለው በቀለ ይህው 12 ሊሆን ነው:: የውሃ ሽታ ሆነባት:: ምናልባት የከበባትን ፍርሀት ለማስወገድ ብላ የያዘችውን ጠፍጣፋ የውስኪ ሻት ብልቃጥ ከጂንስ ኪሷ ውስጥ አውጥታ ጎርጎጭ አደረገችና...ስሙን ቄስ ይጥራውና ...ዛሬ አበቃለት አለች::

ውስጧ ለበቀል ተጣደፈ:: እስካሁን ታስታውሰዋለች:: በጠራራ ቀን በግድ ቤቷ ገብቶ ያደረጋትን... ከሰው ሁሉ አቆራርጦ ለዚህ ያበቃትን::
ቃላቶቹ ሁሉ እስካሁን ትዝ ይሏታል:: ..... ልጇን ከትምህርት ቤት ወስዳ ገና ቤት መድረሳቸው ነበር:: በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የታወቀው በቀለ ግርማይ!....የግንብ አጥሯን ዘልሎ....ነበር....
.... "የኛ ቆንጆ!" ያላት ያላት ሽጉጥ ደግኖ
"ማነህ አንተ ምን ትሰራለህ ቤቴ..." በፍርሀት ድምፅ
እሱ ደግሞ እየተጀነነ "አንቺን ፈልጌ ነው የመጣሁት::...."
"ኡ ኡ ልል ነው::"
"እንዳትሞክሪው::" ሽጉጡን ይበልጥ እያስጠጋ....
"ይልቅ ተባበሪና ፍቅር እንስራ...እምቢ ካልሽ በግድም አይቀርልሽ...."
"አውሬ ነህ! ቱፍ!" ፊቱ ላይ ተፋችበት
እንዳታስጠጋው ባየ ግዜ...ሰናይትን አፈፍ አደረጋት....አንድዬ ልጇን አንድ ፍሬዋን!
"እንደውም አንቺን አልፈልግሽም"" አለና የሰናይትን ቀሚስ ገልቦ ሰውነቷን በአንድጁ እየነካካ በምላሱ አንገቷን መላስ ጀመረ.......
"ማሚ....ዋይይይይይይይ" ማሚ!" ጮኸች ሰናይት::
"ስለእናትህ ስለ እህትህ....ልጄን ተዋት....ገና 14 አመቷ ነው::"
"የሴትና የ...ትንሽ የለውም" አለ እየገለፈጠ::
"በቃ እኔኑ አድርገኝ:: እንደውም የፈለከውን አይነት ሰጥሃለሁ"....

እህ! ህ! ህ! ህ! ገለፈጠ::

ሮጣ ሄዳ የሱሪውን ዚፕ ፈታችና ብልቱን በአፍዋ ከተተችው:: በቅርቡ የሸናው ሽንቱ ጨው ጨው ሲላት ቶሎ ብላ ከአፏ አወጣችው:: የንዴቱን በሽጉጡ ሰደፍ አገጭዋን መታት:: ተዝለፍልፋ ወደቀች:: በሰመመን አለም ነጎደች::
ስትነቃ ሰኒን አጠገቧ አጠገቧ አየቻት::- ጭንና ጭኗን አጣብቃ ኩርምት ብላ::

ዛሬ ከሁለት አመት እስራት በህዋላ ሊፈታ ነው:: ወይኔ ልጅት! አለች እየፎከረች:: ይፍትህ ያለህ! አለች ደገመችና:: በልጇ ፊት ደፍሯት...ልጇንም ደፍሮ....2 ዓመት ብቻ??????

በደሟ ውስጥ በቀል ተሯሯጠ:: አቅርቦ ማሳያ መሳሪያዋን በአይኖችዋ ሰክታ ተመለከተች:: ምንም የለም::

ብዙም ሳይቆይ አንዲት ላዳ ታክሲ አቶ ግርማይ በር ላይ ቆመች:: አቶ ግርማይ ባጋጣሚ ውጭ ነበሩ::

ትንፋሿን ሰብሰብ አድርጋ አነጣጠረች:: ከታክሲ ውስጥ ፂሙን ያሳደገ ጎልመስ ያለ ወጠምሻ ወረደና ወደ አቶ ግርማይ አመራ::
"አሁን ነው እንጂ ጀግንነትሽ! ፍትህ ቀርባለች!..." አላት አዕምሮዋ
ፍትህ ቀርባለችና ተደሰቱ....
ፍትህ ቀርባለችና የበቀል ሸክማችሁን አውርዱ....

ልቧ ድም ድም ድም! ሲል ለራሷ ይሰማታል:: አካባቢዋን አንድ ግዜ ቃኘችና እንደገና አነጣጠረች:: እጇ ተንቀጠቀጠባት:: በማነጣጠርያው ውስጥ የ + ምልክቱ ጢማሙ ሰውዬ ላይ አርፏል::

"ማሚ....ዋይይይይይ" የልጇ ድምፅ ጮኸባት:: ተኮሰች:: ደማም ተኮሰች:: ሶስተኛም አራተኛም.....እዛው ለጥ ብላ አመሸች::..........

ስትረጋጋ ወደቤቷ አመራች:: ትልቅ ሸክም ከላይዋ ላይ እንዳወረዱላት አህያ መሰፈጠዝ...ማናፋት አማራት:: ደስ አያላት መኪናዋን ነድታ ወደቤቷ ሄደች::


መኪናዋን አጠበች:: ለማንኛውም ብላ የቀየረችውን የታርጋ ቁጥሯን ኮድ 2 8586777 መልሳ ወደነበረበት ኮድ 2 3536111 ቀየረች:: ለብሳ የነበረውን ሁሉ ቀያየረችና በተረጋጋ መንፈስ ቴሌቪዥኗን ከፈተች::

"...አባትና ልጅ የሞቱት በሶስት ጥይት ሲሆን ከየት እንደተተኮሰ ማን እንደተኮሰው.....አይታወቅም:: ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ ነው:: ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜና በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ታስሮ የነበረው የሟች የአቶ ግርማይ ልጅ አቶ በቀለ ግርማይ በወህኒ ቤቶች አስተዳደር ችግር ምክንያት ለ 1 ወር ተጨማሪ መፈታት እንዳልቻለ.........
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ስርርር » Thu Aug 05, 2010 5:41 pm

ዋይ ዋይ!

ከሻርፕ ሜሞሪያል ሆስፒታል ቁልቁል የባልቦዋን ፍሪ ዌይ ተጠቅሜ ወደቤቴ እያመራሁ ነው:: ከአንድ አሳቻ ቦታ ላይ ከፍሪዌይ ወጥቼ የአዳምስ አቬኑን ጎዳና ስይዝ....የትራፊክ መብራቱ ቀጥ አደረገኝ:: ይህ መብራት ደግሞ ከያዘ ቶሎ አይለቅም:: እዛው በቆምኩበት....በሰመመን ወደፍቅሬ ነጎድኩ:: ወደሀገር ቤት:: ገና በቤት ኪራይ እያለሁ....የአሁኗ የናፍቆት ሚስቴ የአከራዬን ልጅ...........የመጀመሪያውን ቀን የፍቅር ግብግብ....ድንግልናዋን የውሰድኩበትን ቀን. በሰመመን አሰብኩት.........

ምራቋን ጎርጎጭ አድርጋ ስትውጥ ጆሮዬ ውስጥ ጥልቅ አለ
ድምፅዋ ቅላጥፄውን ሳተ.....ተቆራረጠ

"ም..ን አ..ልከኝ" ሁለት እጇን በእግሮቿ መሀል አድርጋ እያሻሸች
ቀይ ፊቷ ቲማቲም መስሏል.....ፀዳሏ ያማልላል
"እ...ምንም" አልኩ እኔም
አጠገቧ ቁጭ ብየ የቀኝ እግሬ ባት የግራ ዳሌዋን ነክተዋል:: ስፈራ ስቸር....እጄን እያንፏቀቅሁ ወደመቀመጫዋ አስጠጋሁት::
ልቦቻችን ደብል የሆን "ድም ድም" ሲያሰሙ, ከሩቅ የፋየር ወርክ የሚሰማ ይመስላል::

ዝምታው ነገሰ:: በዝምታዎቻችን መሀል ሙቀታችን ጣራ ነካ

እኔም ጎርጎጭ አድርጌ ምራቄን ስውጥ ድምፁ ዝምታውን አደፈረሰው:: ድንገት ዞር አለች ወደኔ....
አይኖችዋ...."በላ ምን ትጠብቃለህ" ያሉኝ መሰለኝ::
ልቤ ደግሞ...."ካልቆረጡ ቁርጥ አይበሉም...በለው እባክህ......." አለኝ
.................
ከንፈሮቻችን ተገናኙ::
እየተሳሳምን.......ደቂቃዎችን አሳለፍን:: በመሀል...ሲያለቅስ ቆይቶ እልሁን እንዳልጨረስ ልጅ ስርቅ...ሲላት እሰማለሁ:: ልብሶቻችን መቼ እንደወለቁ አላውቅም::
አፈፍ አድርጌ ትንሿ ታጣፊ አልጋዬ ላይ ወረወርኳትና እኔም ሹል አድርጌ ተከተልኳት:: እኔን እንክዋን በወጉ የማትችለኝ አልጋዬ በላይዋ ላይ ሁለታችንን ይዛ በጣር ዋይ ዋይ ዋይ አለች:: .... ከሰመመን ስነቃ ዋይዋይ የሚለው የፖሊስ መኪና ኖሯል::

...."pull over!" አለኝ መኪናው ውስጥ ያለው ፖሊስ በምልክትም ጭምር እያሳየኝ:: .........
Last edited by ስርርር on Tue Nov 02, 2010 4:06 am, edited 1 time in total.
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ዝንቱ » Thu Aug 05, 2010 5:50 pm

ገና ስምህን ሳይ ነበር የሆነ ነገር እንደምትፅፍ በመተማመን የገባሁት:: መቼም እንደነዋናው እና እንደነትርንጎ ጣቶጭ ይለምልሙ ለመባል ባትደርስም, ሳላምሰግን አላልፍም:: ጥሩ ፅሁፍ ነው:: ባይሆን ደገም ደገም አድርግና ፃፍ ካዛ ጣቶጭ ይለምልሙ ቃላቶች ይርቡልህ ብዬ እመርቅሀለሁ::
ዝንቱ ነኝ::
I am black, yet beautiful!
ዝንቱ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 24
Joined: Thu Jul 15, 2010 6:56 pm
Location: MARS

Postby ትርዛ » Wed Aug 11, 2010 12:09 am

:lol: :lol: የት ነው ለመሆኑ ስርርዬ! :lol: :lol: ይሄ ሸርፕ ምሞሪያል ያልከው? በኢንተርኔት ፈልጌ አጣሁት:: :lol: :lol: :lol: ትንሽ ግን መመሳሰል አይባችህዋለው አንተና ትርንጎዬ ላይ:: :lol: :lol: :lol: :lol: ሷም የልጆቿን ስም ፈንዳሳ --ፍንድስድስ ምናምን ነው የምትላቸው:: ሚገርም ነው:: አንድ ሰው እንዳሎናች ትርንግ ነግራኛለች:: :lol: :lol: :lol: :lol: ግን አንተ ኮፒ አድርገህ መሆን አለበት ከሷ:: ለማንኛውም ፈንዳሳ ጥሩ ፅሁፍ ነው:: :lol: :lol: :lol:
ትርዛ (as tringo would call me የልቤ ፌሽታ) :lol: :lol:
ትርዛ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 78
Joined: Fri Apr 09, 2010 10:10 pm

Postby ስርርር » Wed Oct 20, 2010 4:18 am

"እሺ...! እንዴት ነህ?" አለች የደረቴን ፀጉር በአገጯ እያሻሸች:: ለመጠየቅ ያህል እንጂ አብረን ውለን አድረን እንደገና ውለናል:: የቀኝ እጄ ጣቶች እረፍት አልባ ሆነው አንዴ ፀጉሯን, አንዴ ግንባርዋን አንዴ ጆሮዋን, አንዴ የሚያሳሱ ከንፈሮችዋን እየደባበሱ ከወዲያ ወዲህ ይሯሯጣሉ:: ከዳሌዋ በላይ ግማሽ አካልዋ ተጋልጧል:: እሷ እቴ ምን አለባት....ደረቴ እኔን አልጋ አድርጋ ሙሉ በሙሉ ተዘርፍጣብኛለች... አይ ወበት!.......

"ምናባ ዝም ትላለህ...መልስልኝ እንጂ አለችኝ አንድ እጅዋን ወደ እግሮቼ መሀል አንድ እጅዋን ደግሞ ወደብብቻዬ መሀል እየላከች....ልትኮረኩረኝ! ልታስቀኝ....
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests