ምርኮኛ - በፓስወርድ መነጽር ስር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby password » Sun Feb 27, 2011 5:40 pm

ምርኮኛን ተነባቢ ያደረግው የጭውውት ስልት እንመልከት፣ ከገጽ 177

"ፍርዬ በሃሳብሽም ቢሆን ጥለሽኝ እንድትሄጅ አልፈቅድም" አለ አንተነህ በሃሳብ መመሰጥዋን ተመልክቶ።

"የትም አልሄድኩ፣ ምንስ መሄጃ አለኝ ብለህ ነው?" አለችው በአንተነህም ገጽታ ላይ ርቆ የመሄድ መንፈስ እያየች ነው። ፊቱ እንደመገርጣት ብሎአል፣ ድክም ያለውም ይመስላል።

"ሳይድንልህ ነው የተነሳኸው፣ አይደል?"

"ምን መዳን አለ ፍርዬ ..." አንጠልጥሎ ተወው። በውስጡ አንዳች ነገር እየተመላለሰ መሆኑ ይታወቃል...

ይህ ጭውውትንና ገለጣን ምጥን ባለ መልኩ አዋህዶ የማቅረብ ስልት ድርሰቱ ፈጠራ መሆኑ እስረስቶ አንባቢ እውነተኛ ሰዎች በውን የሚነጋገሩ እንዲመስለው የሚያደርግ ነው። ረጅም ገለጣና ረጅም የአንድ ሰው ንግግር ምርኮኛ ላይ አላየሁም። ተናጋሪው የሚታወቅበት ሁኔታ ባለበት ትይንት ውስጥ ጭውውቱን ብቻ እንዳለ፣ እገሌ አለ ወይም እገሊት መለሰች የሚል ተጉዋዥ ሳያስክትል መቀመጡ ራሱ ንባብ ሳይደናቀፍ እንዲፈስ ረድቶአል። እንደ ዘመናዊ ልቦለድ አጻጻፍ ምርኮኛ የጭውውቱና የገለጻው ብዛት የተመጣጠነ ነው ማለት ይቻላል።

ማጠቃለያ
ምርኮኛ ግሩም መጽሃፍ ነው። ቀደም ብዬ እንዳልኩት መጽሃፉ የሃገርንና የህዝብን እጣ ፈንታ የቀየሩ ከፍተኛ የፖሊሲ አዋጆችን፣ የግድያና የሽብር መግለጫዎችንና ወሳኝ ታሪካዊ ክንዋኔዎችን ጊዜና ቦታ በማጣቀስ ቢያካትት ኖሮ እጅግ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ስራ በሆነ ነበር። የትረካው ዘመን መርዘም የገጸባህሪያቱን፣ በተለይም የፍሬህይወት ልጆች እድሜ ያምታታበት ሁኔታ ታዝቤኣለሁ። እንዲህ ዓይነቱን ህፀፅ እንዳይከሰት ካሌንደር ላይ የተመሰረተ የትረካ ጊዜ መስመር ማውጣት ያስፈልጋል። አልያም የትም ቦታ ለዘመን ማመሳከሪያ ሊሆን የሚችል ዓመተ ምህረት ያለመጠቀሱ ይበጃል።

በተረፈ እንደ በርድና ስሊፕለስ መጽሃፉ ያላችሁ ከመደርደሪያ አውጡት፣ የሌላችሁ ደግሞ ፈልጋችሁ አንብቡት። ባለፈው ፖስት ታሪክን ከታሪካዊ ልቦለድ መማር ይቻላል እንዳልኩት፣ ይህን የቅርብ ጊዜ ታሪካችንን ማወቅ የአሁኑንና መጪውን እንድናስብበት በእጅጉ ይጠቅመናል። ያነበባችሁ ደግሞ የተሰማችሁንና ስለታሪኩም ሆነ ስለ ትረካው ያላችሁን ሃሳብ ብታካፍሉን መልካም ነው። ቆንጅትም ስላስነበብሽን መጽሃፍ ከልብ እያመሰገንኩሽ፣ ቀጣዩን መጽሃፍሽን ከአሁኑ እየጠበቅሁ መሆኔን እንድታውቂ እፈልጋለሁና በርቺ። አስተያዬቴን አስመልክተሽ የምትዪው ካለም ወደ ሁዋላ እንደማትዪ አምናለሁ።

ይህን ያህል ካልኩ ዘንዳ ምርኮኛን ያነበበ ማንም ሰው ሊያነሳቸው የሚችሉ፣ መወያያ የሚሆኑ ጥቂት ጥያቄዎች ልጠቁም፣

/ፍሬህይወትና የትግል ጉዋድዎችዋ እንዲያ ወላጅና ቤተሰብ ትተው የትግሉ ነው ህይወቴ እንዲሉ ያደረጋቸው አላማ ምንድን ነው?

/አላማቸው እውን ሊሆን እንደሚችል በምን ተማመኑ?

/አላማቸው ላይ ለመድረስ የተከተሉት የትግል ስልት ሌላ አማራጭ አልነበረውም?

/ከነበረስ ያ አማራጭ ምንድን ነው?

/በህቡእ የሚንቀሳቀስ ድርጀት በጎና ጎጂ ጎኑ ምን ምንድነው? በማን እንደሚዘወርስ በምን ይታወቃል?

/አላማውንስ በፕሮግራሙ እንደሰፈነው ለመተግበሩ ተከታዮቹ ምን ዋስተና አላቸው?

/የኢህአፓ ትጥቃዊ ጥንካሬ የወታደራዊ አስተዳደር ደርግን በሀይል ለመጋፈጥ ብቃቱ ምን ያህል ነበር?

/ብቃት ካልነበረውስ ለምን በሃይል መጋፈጥ አስፈለገ?

/እንደ ቃለ አብና ሜሮን የመሳሰሉ ታዳጊዎች ለትግል የመሰለፉቸው ጉዳይ እንዴት ይታያል?

/እነፍሬህይወት ያልተጠበቁ ጥቃቶችን ለመቁዋቁዋም ምን ያህል ዝግጁነት ነበራቸው? ፓርቲያቸውስ?

/እነ ፍሬህይወት የማፈግፈጊያ፣ የመደበቂያና የመሸሺያ ስፍራዎች በብቃት ስለመዘጋጀታቸው ለምን አልጠየቁም?

/ወጣቱ ከምርኮኛ ምን ይማራል?

/በነፍሬህይወት ጊዜ የደረሰው ጥፋት እንዳይደገም ምን ማድረግ አለበት?

ምርኮኛን ካነበብን እነዚህ ጥያቄዎች በአእምሮአችን ውስጥ መላወሳቸው አይቀርም። ደራሲ ቆንጅት ይህን መጽሃፍ የጻፈችው ወጣቱ ያለፈ ታሪክን እንዲያውቅና ከዚያ ታሪክ ተምሮ እጅግ ከፍተኛ መስዋእትነት ያስከፈለንን የፖለቲካ ችግር አፈታት በጥንቃቄ እንዲመረምር መሆኑን አልጠራጠርም። በመካያው ግን እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በውስጣችን መጫርዋ አልቀረም። ጥያቂዎቹ መልስ ሳይሆን ውይይት የሚያስናሱ ናቸው። ያለፈውን ቁስል መነካካት ህመማችንን የሚቀሰቅስ ቢሆንም ያን የጨለማ ዘመን ታሪክ እውስጣችን ተሸክመን ከሚያጎብጠን በድፍረት አውጥተነው ብንወያይበት ለተጎዳው ትንሽ ፈውስ... ለመጪው ትውልዱም መድህን ይሆነዋል። ይህ ሲሆን ያ ክቡር መስዋእትነት ቢያንስ ለሌላው መድህን ስለሆነ ከንቱ አልነበረም ብለን እንጽናናለን። ስለዚህ አንባቢያን በዋርካ ላይ ሆነ በሌላ መድርክ እነዚህ ጥቃቄዎች እንዲወያዩባቸው ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ከታላቅ አክብሮት ጋር።

ፓስ ....
Last edited by password on Sun Feb 27, 2011 5:56 pm, edited 1 time in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby እባካችሁን » Tue Mar 22, 2011 12:18 am

password wrote:
ሰላም እባካችሁን

የመዓዛን BENEATH THE LION'S GAZE አግኝቼ እያነበብኩት ነው። አንዳልከ(ሺ)ው የዚያን ዘመን ታሪክ መሰረት ያደረገ ነው። መጽሀፉ አለም አቀፍ አድናቆት ሲያገኝ በኛ በባለጉዳዮቹ አካባቢ ሲወራለት አልሰማሁም። አሁንም አንቺ ባትነግሪን ኖሮ ሳናውቀው ብዙ እንቆይ ነበር።

ሰላም ፓስ ዎርድ በቅድሚያ ጾታየ ወንድ ስልሆነ አንተ ልትለኝ ትችላለህ::
ምርኮኛን ካገር ቤት አስመጥቸ አንብቤ ትላንት ጨርስኩ። በእኔ አስተያየት እንደ መጀመሪያ መጽሀፍ ምርኮኛ እጅግ በጣም የተዋጣለትና ብዙም እንከን ያላገኘሁበት መጽሀፍ ነው። እድገት በህብረት ዘምቻለሁ ከዚያም በኍላ በተከተሉት ክስተቶች ውስጥም አልፈአለሁና መጽሀፉ በበኩሌ ያለፈውን ህይወቴን እንደገና እንድቃኝ አድርጎኛል። አብዛኛውም የኔቢጤ አንባቢ ተመሳሳይ አስተያየት ይኖረዋል ብዬ እገምታለሁ።
ያን ያህል ተጋድሎና ታሪክ በ491 ገጾች ላንባቢ በሚዳ መልኩ ፣የነበሩት እውነታዎች ሳይጋነኑና ሳይዘነጉም፣ ከሽኖ ማቅረብ ታላቅ ጥንቃቄና ብዙም ጥረትን ይጠይቃል። እኔ ደራሲ አይደለሁም ሆኖም ታሪካዊ ልብ ወለዱ በቀጥታ ይመለከተኛል:: በተለይ በዚያን ወቅት የነበረው ወጣት በኢህአፓ ሰር ተደራጅቶ ያደርግ የነበረውን ተጋድሎና የከፈለውን መስዋእትነት ከነሁለንተናዊ መልኩ በዝርዝር የተገለጸበት ነው። እስካሁን ባነበብኳቸው ተመሳሳይ መጽሀፍት ውስጥ ወጣቱ ስለተጫወተው ሚና እንዲህ ተተንትኖ የተገለጸበት አንድም አላገኘሁም።
ከእድገት በህብረት ዘምቻ በዓል እለት አንስቶ እስካሁን ያለውን በዚህ መልክ ለመግለጽ የዚያ ዘመን ተጋሪ መሆንን ብቻ ሳይሆን የግድ በወላፈኑ ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። የጠቀሰቻቸውም ዋቢ መጽሀፍት የሉምና ከአእምሮ ቆፍሮ እንዲህ ያለን ታሪክ ላንባቢ ማቅረብ የሚያስደንቅ ነው። በመጽሀፉ ውስጥ አንድም ወቅቱን ያልጠበቀ ጽሁፍ አላየሁበትም የቦታዎችና የአካባቢ መጠሪያዎች በዚያን ወቅት እንደሚጠሩት ሲሆን የወጣቱ መቃጠሪያ ቦታዎችም (በተለይ እንደ ፍላሚንጎ ያሉት) በትክክል በጽሀፉ ውስጥ እንደተጠቀሱት ነበር የሚያገለግሉት:: ሌላው ቀርቶ አዲስ አበባ በኢህአፓ መፈክሮች ለማጥለቅለቅ ሥራ የሚጀመርበት ሰአት ሳይቀር ትክክል ነበር። ሁሌም ከለሊቱ 10 ሰአት ተኩል አካባቢ... ምን ያልተወሳ አለ...አደፍርስ.. ያካባቢ ጋዜጣ።
በሌላ በኩል ካዲስ አበባ ውጭ ደራሲዋ አዋሳንና ዱብቲን ስትገልጽ እዚያ እንደነበረች አድርጌ ገምቻለሁ :: ለምሳሌ ፍቃደና ፍሬ መጀመሪያ የኖሩበት የዋቤ ሸበሌ ቁ.2 ወይም በጥንት ስሙ ኦሲስ ሆቴልና አንተነህ አዲስ አበባ ለቆ ዱብቲ ሲደርስ ስለገጠመው የአልቤርጎ ሁኒታ ያደረገችው አገላለጽዋ ቦታዎች ለሚያውቅ አንባቢ የታሪኩን ልብ ወለድነት እንዲረሳ ያደርገዋል::
በመጨረሻም አዲስ አበባ የውይይት ታክሲ የጄመረበትን ወቅት በትክክል አላስታውስም ሆኖም ፍጅቱ ሰከን ካለ በኋላ ይመስለኛል። ሆኖም በገጽ 296 ላይ እመቤት ተልዕኮዋን አገባዳ ማድረግ ስላለባት ወንድሟ የነገራት መልዕክት “ ....እቃውን ከሰጠሸው በኋላ በመጣሽበት መንገድ አትመለሽም ወደፊት ስትሄጂ ታክሲ መሳፈሪያ ታገኛለሽ የምታውቂውን ቦታ የሚጠራ ታክሲ ተሳፍረሽ ወደቤትሽ ተመለሽ”" የሚለው ብቻ ነው ትንሽ ግራ ያለኝ። ምክንያቱም በዚያን ጊዜ የነበሩት ታክሲዎች የጣሊያን ፊያት 124/5 እና ሴቸንቶዎች ታክሲዎች ሲሆኑ ታክሲ ነጂዎችም ወያላ አልነበራቸውም እዚህ ጋ የሚረዳኝ ካለ አመሰግናለሁ።
አንድ አስተያየት ለመጨመር ታሪኩ በእድገት በህብረት መጀመሩ መልካም ነው ሆኖም ከዘመቻው በዓል ቀደም ሲል ወጣቱ በየትምህርት ቤቱ እየታዘዘ ስላደረገው የአዲስ አበባ የጽዳት ዘመቻ፣እስታድዮም ሄዶ ስለወሰደው ክትባት: እንዲሁም ራሱን በዓሉን ጃንሜዳ ምን ይመስል እንደነበር መግለጹ የሚገባ ይመሰለኛል። ከዚህ በተጨማሪ በወቅቱ መዝመት ያልቻሉት የመንግስት ሰራተኞች እንኳን የመንፈስ ቅናት ያደረባቸው ወቅት ሆኖ ሳለ፣ ፍሬ ህይወት ግን ዘመቻውን እንደማትደግፍ ሆና በገጽ 28 ላይ መገለጿ ብዙም አልተዋጠልኝም።
በመጨረሻም ቆንጅት ወደፊትም ብዙ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ። ላሁኑ እጅሽ ይባረክ ብያለሁ።
ሌላው የመአዛን መጽሀፍ ከዚህ ጋር ማወዳደር አይቻልም ምክንያቱም መአዛ ያነበበችውንና የሰማችውን መሰረት በማድረግ ያዘጋጀችው የፈጠራ ስራ አድርጌ ነው የገመትኩት፡፡ ለማንኛውም በሱም ላይ እስኪ የምትሰጠውን አስተያየት አሰነብበን።

ሰላም
እባካችሁን
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 77
Joined: Wed Sep 17, 2008 10:02 pm

Postby tianes » Wed Sep 05, 2012 2:01 pm

ለእድገት በህብረት እንዝመት
ወንድ... ሴት ሳንል ባንድነት

እባክ...

የ 1967 እድገት በህብረት ዘመቻና የዘማቾችን ገድል የሚዳስስ ልቦለድ መጻህፍት ከ http://babile.webs.com/ebooksinpdf.htm በነጻ መጫን ትችላለህ....
አሳታሚው ለህዝብ] ለቆታል.... ሌሎችም መጻህፍት አሉ... ሳይቱን ሄደህ ጎብኝ
tianes
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 542
Joined: Mon Aug 20, 2007 10:54 pm

Re:

Postby password » Thu Jan 23, 2020 10:37 am

እባካችሁን wrote:
password wrote:
ሰላም እባካችሁን

የመዓዛን BENEATH THE LION'S GAZE አግኝቼ እያነበብኩት ነው። አንዳልከ(ሺ)ው የዚያን ዘመን ታሪክ መሰረት ያደረገ ነው። መጽሀፉ አለም አቀፍ አድናቆት ሲያገኝ በኛ በባለጉዳዮቹ አካባቢ ሲወራለት አልሰማሁም። አሁንም አንቺ ባትነግሪን ኖሮ ሳናውቀው ብዙ እንቆይ ነበር።

ሰላም ፓስ ዎርድ በቅድሚያ ጾታየ ወንድ ስልሆነ አንተ ልትለኝ ትችላለህ::
ምርኮኛን ካገር ቤት አስመጥቸ አንብቤ ትላንት ጨርስኩ። በእኔ አስተያየት እንደ መጀመሪያ መጽሀፍ ምርኮኛ እጅግ በጣም የተዋጣለትና ብዙም እንከን ያላገኘሁበት መጽሀፍ ነው። እድገት በህብረት ዘምቻለሁ ከዚያም በኍላ በተከተሉት ክስተቶች ውስጥም አልፈአለሁና መጽሀፉ በበኩሌ ያለፈውን ህይወቴን እንደገና እንድቃኝ አድርጎኛል። አብዛኛውም የኔቢጤ አንባቢ ተመሳሳይ አስተያየት ይኖረዋል ብዬ እገምታለሁ።
ያን ያህል ተጋድሎና ታሪክ በ491 ገጾች ላንባቢ በሚዳ መልኩ ፣የነበሩት እውነታዎች ሳይጋነኑና ሳይዘነጉም፣ ከሽኖ ማቅረብ ታላቅ ጥንቃቄና ብዙም ጥረትን ይጠይቃል። እኔ ደራሲ አይደለሁም ሆኖም ታሪካዊ ልብ ወለዱ በቀጥታ ይመለከተኛል:: በተለይ በዚያን ወቅት የነበረው ወጣት በኢህአፓ ሰር ተደራጅቶ ያደርግ የነበረውን ተጋድሎና የከፈለውን መስዋእትነት ከነሁለንተናዊ መልኩ በዝርዝር የተገለጸበት ነው። እስካሁን ባነበብኳቸው ተመሳሳይ መጽሀፍት ውስጥ ወጣቱ ስለተጫወተው ሚና እንዲህ ተተንትኖ የተገለጸበት አንድም አላገኘሁም።
ከእድገት በህብረት ዘምቻ በዓል እለት አንስቶ እስካሁን ያለውን በዚህ መልክ ለመግለጽ የዚያ ዘመን ተጋሪ መሆንን ብቻ ሳይሆን የግድ በወላፈኑ ውስጥ ማለፍን ይጠይቃል። የጠቀሰቻቸውም ዋቢ መጽሀፍት የሉምና ከአእምሮ ቆፍሮ እንዲህ ያለን ታሪክ ላንባቢ ማቅረብ የሚያስደንቅ ነው። በመጽሀፉ ውስጥ አንድም ወቅቱን ያልጠበቀ ጽሁፍ አላየሁበትም የቦታዎችና የአካባቢ መጠሪያዎች በዚያን ወቅት እንደሚጠሩት ሲሆን የወጣቱ መቃጠሪያ ቦታዎችም (በተለይ እንደ ፍላሚንጎ ያሉት) በትክክል በጽሀፉ ውስጥ እንደተጠቀሱት ነበር የሚያገለግሉት:: ሌላው ቀርቶ አዲስ አበባ በኢህአፓ መፈክሮች ለማጥለቅለቅ ሥራ የሚጀመርበት ሰአት ሳይቀር ትክክል ነበር። ሁሌም ከለሊቱ 10 ሰአት ተኩል አካባቢ... ምን ያልተወሳ አለ...አደፍርስ.. ያካባቢ ጋዜጣ።
በሌላ በኩል ካዲስ አበባ ውጭ ደራሲዋ አዋሳንና ዱብቲን ስትገልጽ እዚያ እንደነበረች አድርጌ ገምቻለሁ :: ለምሳሌ ፍቃደና ፍሬ መጀመሪያ የኖሩበት የዋቤ ሸበሌ ቁ.2 ወይም በጥንት ስሙ ኦሲስ ሆቴልና አንተነህ አዲስ አበባ ለቆ ዱብቲ ሲደርስ ስለገጠመው የአልቤርጎ ሁኒታ ያደረገችው አገላለጽዋ ቦታዎች ለሚያውቅ አንባቢ የታሪኩን ልብ ወለድነት እንዲረሳ ያደርገዋል::
በመጨረሻም አዲስ አበባ የውይይት ታክሲ የጄመረበትን ወቅት በትክክል አላስታውስም ሆኖም ፍጅቱ ሰከን ካለ በኋላ ይመስለኛል። ሆኖም በገጽ 296 ላይ እመቤት ተልዕኮዋን አገባዳ ማድረግ ስላለባት ወንድሟ የነገራት መልዕክት “ ....እቃውን ከሰጠሸው በኋላ በመጣሽበት መንገድ አትመለሽም ወደፊት ስትሄጂ ታክሲ መሳፈሪያ ታገኛለሽ የምታውቂውን ቦታ የሚጠራ ታክሲ ተሳፍረሽ ወደቤትሽ ተመለሽ”" የሚለው ብቻ ነው ትንሽ ግራ ያለኝ። ምክንያቱም በዚያን ጊዜ የነበሩት ታክሲዎች የጣሊያን ፊያት 124/5 እና ሴቸንቶዎች ታክሲዎች ሲሆኑ ታክሲ ነጂዎችም ወያላ አልነበራቸውም እዚህ ጋ የሚረዳኝ ካለ አመሰግናለሁ።
አንድ አስተያየት ለመጨመር ታሪኩ በእድገት በህብረት መጀመሩ መልካም ነው ሆኖም ከዘመቻው በዓል ቀደም ሲል ወጣቱ በየትምህርት ቤቱ እየታዘዘ ስላደረገው የአዲስ አበባ የጽዳት ዘመቻ፣እስታድዮም ሄዶ ስለወሰደው ክትባት: እንዲሁም ራሱን በዓሉን ጃንሜዳ ምን ይመስል እንደነበር መግለጹ የሚገባ ይመሰለኛል። ከዚህ በተጨማሪ በወቅቱ መዝመት ያልቻሉት የመንግስት ሰራተኞች እንኳን የመንፈስ ቅናት ያደረባቸው ወቅት ሆኖ ሳለ፣ ፍሬ ህይወት ግን ዘመቻውን እንደማትደግፍ ሆና በገጽ 28 ላይ መገለጿ ብዙም አልተዋጠልኝም።
በመጨረሻም ቆንጅት ወደፊትም ብዙ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ። ላሁኑ እጅሽ ይባረክ ብያለሁ።
ሌላው የመአዛን መጽሀፍ ከዚህ ጋር ማወዳደር አይቻልም ምክንያቱም መአዛ ያነበበችውንና የሰማችውን መሰረት በማድረግ ያዘጋጀችው የፈጠራ ስራ አድርጌ ነው የገመትኩት፡፡ ለማንኛውም በሱም ላይ እስኪ የምትሰጠውን አስተያየት አሰነብበን።

ሰላም
ለአዲሱ የዋርካ ደንበኛ።
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 330
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests